ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
የላጤወች ህይወት..
👉 «መኖር አይባልም»
የበሆነ አጋጣሚ ከእለታት አንድ ቀን፡
በሳቅ በጨዋታ ለፈገግታ ደምቀን፡
የዱንያን ቆይታ ተራ ተጠያይቀን፡
እድሜየን ጠየቁኝ አልኖርኩም አልኳቸው፡
አልኖርኩም ማለቴ ቃሌ አስገርሟቸው፡
ዞረው ተያዩና፤
ፊታቸው ላይ አየሁ ሲመጣ ሳቃቸው፡
እኔ አልገረመኝም ፤
ማመን ተስኗቸው ቢጮሁ ቢስቁ፡
ለኔ ነው የገባኝ፤
የሀሳቤ ትርጉም ሰም ህብረ-ቃል ወርቁ፡
የላጤነት ህይወት፤
መኖር እንዳልሆኘ ጭራሽ መች አወቁ፡
ዱንያዊ ቁሳቁስ ተሟልቶ ባይጎልም፡
የላጤነት ህይወት መኖር አይባልም፡
©በኑረዲን አል አረብ
አሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ
ዓረብኛ ፅሁፍ የተመዘገባቹ እህት ወንድሞች
በየ ጉሩፑ ስላስገባናቹህ ቴሌግራማቹሁን ቼክ አርጉ!
👉 ተመዝግባቹህ እስካሁን ጉሩፕ ላይ ያልገባቹህ ካላቹህ በውስጥ መስመር አናግሩኝ።
ወንድማቹህ አቡ ዓቲካህ
መውሊድን ከማላከብርበት ምክንያቶች፦
1) ረሱል ﷺ የተወለዱት አመል ፊል በተባለው አመት ነበር ፤ አብረሃ ካዕባን ለማፍረስ የሞከረበት አመት ማለት ነው። እንዲሁም የተወለዱት ሰኞ ቀን እንደሆነና ቀኑን እንደሚፆሙት ነግረውናል፤ ሆኖም የቱኛው ሰኞ እንደሆነ ግን የተገለፀ ነገር የለም። እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚቻለው የተወለዱት በዓመል ፊል ሰኞ ቀን መሆኑን ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ያለው ሁሉ ስምምነት የለበትም።
2) ነብዩ ﷺ በዱንያ ላይ 63 አመታትን ቆይተዋል ፤ በዚህ ረጅም ቆይታቸው በፍፁም አንድም ቀን አመት ጠብቀው ይህ የተወለድኩበት ቀን ነው ብለው አላከበሩም አልተናገሩምም። ሰኞ ቀን መወለዳቸውን ከመግለፅ ውጭ።
3) ከዚህ ውጭ የረሱል ﷺ ባልደረቦች ፤ ታቢኢዮችም ይሁኑ አራቱ አኢማዎች ማለትም ኢማሙ አቡ ሀኒፋ ፣ ኢማሙ ማሊክ ፣ ኢማሙ ሻፊዕይ ኢማሙ አህመድና እንደ እነ ኢማሙ ዙህሪ ሱፍያኑ ሰውሪ ኢማሙል አውዛኢይ እና ሌሎችም ይህንን ቀን ነብዩ የተወለዱበት ቀን ብለው አላከበሩም። ቀን ቆርጦ ማክበሩ መልካም ቢሆን በቀደሙን ነበር።
4) እንዲሁም ረሱል ﷺ ኸይር ነገር የተባለን ነገር ሁሉ እንደጠቆሙንና እንዳመላከቱን መጥፎን ነገር ደግሞ እንደከለከሉንና እንዳስጠነቀቁን ግልፅ አድርገው ነግረውናል። ሆኖም መውሊድን አክብሩልኝ ብለው የተናገሩት ነገር ግን በፍፁም የለም።
5) ረሱል ﷺ ተወለዱበት ተብሎ የሚከበረው ረቢዐል አወል 12 ኡለሞች ዘንድ ያለ ልዩነት አሽረፈል ኸልቅ የሞቱበት ቀን እንደሆነ ተስማምተዋል። የተወለዱበት ቀን መች እንደሆነ እርግጠኛ ሳይሆኑ የሞቱበት ቀን መሆኑን ግን ስምምነት እያለ በምን መልኩ ይህን ቀን አቅል ያለው ሰው በዓል አድርጎ ያከብረዋል።
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ይላሉ፦ 『ረሱል ﷺ የሞቱበት የመሰለ አስከፊና ጨለማ ቀን አልገጠመኝም።』ሚሽካቱል መሳቢህ
6) ነብዪ ﷺ ሰኞ ቀን የተወለዱበት ቀን መሆኑን ሲናገሩ ቀኑን በፆም እንደሚያሳልፉት ተናግረዋል። ቀኑ እንደ ዒድ በአል ተደርጎ ቢቆጠር ኖሮ አይፆሙትም ነበር ምክንያቱም በኢድ ቀን መፆም የተከለከለ ነውና። እርሳቸው የተወለዱበትን ሰኞ ቀን በመፆማቸው ውስጥ ለአዕምሮ ባለቤቶች ጥቆማ አለ። ይህም የተወዱበትን ቀን ኢድ አድርጎ መያዝ አለመቻሉን ነው።
ጌታዬ ሆይ! ያንተንም የመልዕክተኛህንና የናንተን ወዳጆች የሚወድ ልብ ለግሰኝ! አቡ ቁዳማ
▪️ቢድዓ ለሁለት ይከፈላል የሚሉ ሰዎች ማምታቻቸው እና ምላሹ ክፍል 1.
#የመጀመሪያው_ማምታቻ ፡ ተከታዩ ሐዲስ ነው ፦
من سن في اْلسلام، سنة حسنة،فله أجراها وأجر من عمل بها من بعده، من غير "]
[" .. أن ينقص من أجورهم شيء، ومن سن في اْلسلام سنة سيئة
[ በእስልምና ውስጥ መልካም ሱናን መንገድ አድርጎ የጀመረ ፤ ለእርሱየሱ ምንዳ አለው ፤ ከእርሱ በኋላ በእርሱ የሰራበት ምንዳም አለው ከምንዳዎቻቸው አንድም ሳይቀንስ። በእስልምና ውስጥ መጥፎን
መንገድ የጀመረ ለሱ ከእርሱ በኋላ በእርሱ የሰራበት ወንጀል ምንም ሳይቀነስ ከወንጀሎቻቸው አለው። .. ] (ሙስሊም ፥ 1017).
°
?ይህን ሐዲስ [ በእስልምና ውስጥ መልካም ሱናን መንገድ አድርጎ የጀመረ ሰው ] የሚለውን ትርጉም በእስልምና ውስጥ አዲስን ቢድዓ የፈጠረ ሰው በማለት ይተረጉሙት እና መልካም ቢድዓ ከሆነ መፍጠር
ይቻላል ይላሉ ፤ ለዚህ የሚሰጠው መልስ እንደሚከተለው ይሆናል ፡
°
?ይህ ሐዲስ አዲስ ቢድዓን ለመፍጠር ማስረጃ አይሆንም። የማይሆንበትም ምክንያት ሐዲሱ የወረደበትን ሰበብ(ምክንያት) ስንመለከት ግልፅ ይሆንልናል ፤ የወረደበት ምክንያት ከጀሪር ኢብኒዐብዲሏህ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው ፦ ሶሓባዎች ከነብዩ - صلى الله عليه وسلم - ጋር ተቀምጠው እያለ ከሙደር የሆኑ የገጠር ሰዎች ተቸግረው በመጡ ጊዜ ረሱል - صلى الله عليه وسلم - ሲያዩዋቸው በነሱ ሁኔታ በማዘን ፊታቸው ይቀያየር እና ለነዚህ ሰዎች ሰደቃ እንዲሰጡ ሶሓቦቻቸውን ኹጥባበማድረግ ያነሳሱዋቸዋል ፤ በዚህን ጊዜ ከመካከላቸው አንድ ሶሓባ ተነስቶ ወደቤቱ በመሄድ እጁ እስኪከብደው ድረስ በዘንቢል ሙሉ ሰደቃ ይዞ ይመጣል ፤ ይህንንም ያዩ ሶሓቦዎች የሱን አርአያ በመከተል የአቅማቸውን ያክል ሰደቃ እየያዙ መምጣት ጀመሩ ፤ የተሰበሰበውሰደቃም ነብዩ - صلى الله عليه وسلم - ፊት እንደ ተራራ ተቆለለ። የዚህን ጊዜ ነብዩ - صلى الله عليه وسلم - ይህንን የሰደቃ ሱንና ለከፈተው በመጀመሪያው ሰውዬ ተደስተው ፊታቸው በደስታ አበራ እና [ በእስልምና ውስጥ መልካም ሱና መንገድ አድርጎ የጀመረ ሰው ] የሚለውን ሐዲስ ተናገሩ ማለት ነው።
°
?ከላይ እንደምንረዳው ሐዲሱን የተናገሩት በሰደቃ ምክንያት ነው ፤ሰደቃ ደግሞ በቁርአን እና በሐዲስ የተደነገገ መልካም ተግባር እንጂ አዲስ ፈጠራ ወይም ቢድዓ አይደለም። እንደነሱ ትርጉም የምንሄድ ከሆነ እስኪ የትኛው ነው አዲስ ቢድዓ የሆነው? ሰደቃ ቢድዓ ነውን?
°
?ስለዚህ [ መልካም ሱንና የጀመረ ] ሲባል ከዚህ በፊት በሸሪዓ ያልተደነገገ አዲስ ቢድዓን ያመጣ ለማለት ሳይሆን ሰዎች ከሱ የተዘናጉበትን ወይም ችላ ያሉትን በሸሪዓ የተደነገገን ሱና እንደአዲስበመስራት የጀመረ እና በሱም ተነሳስሽነት ሌሎች ሰዎች ተከትለውት ከሰሩ ከነሱ ምንዳ ሳይቀነስ ለርሱም ምንዳ አለው ለማለት ነው። በመሆኑም ይህ ሐዲስ ቢድዓን ለሁለት ለመክፈል ማስረጃ መሆንአይችልም ማለት ነው።
°
?የሐዲሱ ሁለተኛ ክፍል ማለትም [ በእስልምና ውስጥ መጥፎን መንገድ የጀመረ ] የሚለው ደግሞ ትርጉሙ በመሰረቱ የወንጀሉ ክልከላነት በሸሪዓ ውስጥ የተቀመጠ መጥፎ ተግባር ሆኖ ነገር ግን ሰዎች ያንን ወንጀል ከመስራት ሰላም ሆነው(ታቅበው) ባለበት ወቅት ወንጀሉን እንደአዲስ መንገድ አድርጎ የጀመረ ሰው ከሰሪዎቹ ወንጀል ሳይቀነስ ለርሱም ወንጀል አለው ማለት ይሆናል።
✍️ ____
©ዲን መመካከር ነው
____
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ
ሸውካኒ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት)
~
ሙሐመድ ብኑ ዐሊ አሸውካኒ በ1250 ሂ. የሞቱ ታላቅ የመናዊ ዓሊም ናቸው፡፡ በሰፊው የሚታወቁ ስለሆኑ እሳቸውን በማስተዋወቅ ረጅሙን ፅሑፌን ይበልጥ ማስረዘም አልሻም፡፡ ሸውካኒ መውሊድ ላይ እጅግ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡ ዛሬ በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው መውሊድ ተኮር ጥያቄዎች ውስጥ የተወሰኑትን በመምዘዝ በሸውካኒ ንግግር ምላሽ እሰጣለሁ፡፡ ሙሉ ንግግራቸውን መመልከት የፈለገ ሰው “አልፈትሑ ረባኒ ሚን ፈታዋ አልኢማሚ ሸውካኒ” በተሰኘው የፈትዋ መድብላቸው ውስጥ ሁለተኛውን ጥራዝ ከገፅ 1087-1101 ድረስ መመልከት ይችላል፡፡ (ፅሑፉ ስለ ረዘመ ዐረብኛውን ማካተት አልቻልኩም፡፡)
ሸውካኒ፡- “እስካሁን ድረስ ከቁርኣንም፣ ከሱናም፣ ከኢጅማዕም፣ ከቂያስም (ንፅፅራዊ ምልከታም) መሰረት እንዳለው የሚያመላክት መረጃ አላገኘሁለትም፡፡” [ገፅ፡ 2/1087]
ሸውካኒ፡- “እንዲያውም ከዘመናት ሁሉ ምርጡ በሆነው (የሶሐቦች) ዘመንም፣ ከነሱ ቀጥሎ በነበሩትም፣ ቀጥሎ በነበሩትም (ዘመን) እንዳልነበር ሙስሊሞች ወጥ አቋም ይዘዋል (ኢጅማዕ አድርገዋል፡፡)” [ገፅ፡ 2/1087]
ሸውካኒ፡- “ቢድዐ በመሆኑ ላይ ከሙስሊሞች አንድ እንኳን የተቃወመ የለም፡፡” [ገፅ፡ 2/1088] “ይሄ ነገር ቢድዐ በመሆኑ ላይ ከሁሉም ሙስሊሞች ኢጅማዕ እንዳለበት አረጋግጠንልሃል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091]
ሸውካኒ፡- “በምርጡ ነብይ ﷺ የማያሻማ ምስክርነት ቢድዐ ሁሉ ጥመት እንደሆነ ተነግሮ ሳለ የመውሊድን ቢድዐ መሆን ካመነ በኋላ ይፈቀዳል የሚል ሰው የተናገረው ከንፁሁ ሸሪዐ ጋር የሚፃረር ንግግር ነው፡፡ ያለ አንድ ተጨባጭ እውቀታዊ መነሻ ቢድዐን ወደተለያዩ ክፍሎች ለከፈለ ሰው በጭፍን ከመከተል ያለፈ ነገርም የለውም፡፡ የትኛውንም አቋም ይቻላል የሚልን ሰው ይህንን ቢድዐ በተለየ የሚመለከት ማስረጃ ካቀረበ በኋላ እንጂ አንቀበለውም፡፡ … እንጂ ‘እከሌ እንዲህ አለ’፣ ‘እከሌ እንዲህ አይነት ኪታብ አዘጋጅቷል’ የሚል ባዶ ንግግር ፋይዳ የለውም፡፡ ሐቅ ከየትኛውም አካል ይበልጣልና፡፡” [ገፅ፡ 2/1088 - 1089]
“ከነሱ (ከፈቃጆቹ) ውስጥ ቢድዐነቱን አምኖ መጥፎ ነገር ካልተቆራኘው በሚል መስፈርት የፈቀደው አለ፡፡ ምንም ማስረጃ ግን አላመጣም፡፡” [ገፅ፡ 2/1094]
ኢብኑ ሐጀር እንዳደረገው የዓሹራን ፆም ማስረጃ ማድረግ፣ ወይም ሲዩጢ እንዳደረገው ከነብይነት በኋላ ለራሳቸው ዐቂቃ ማውጣታቸውን መመርኮዝ ቢድዐን የማፅናት ፍቅር እንዲህ አይነት ነገር ላይ እንደሚጥል ከሚያሳዩ አስገራሚ ነገሮች ውስጥ ነው፡፡ [ገፅ፡ 1095]
ሸውካኒ፡- “በሰዎች ንግግሮች ላይ የምንመረኮዝ ከሆንና የእንቶ ፈንቶ ጅራቶችን የምንጨብጥ ከሆንን መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ‘ይፈቀዳል’ ባዮቹ ከሙስሊሞች በአቋም ያፈነገጡ ናቸው፡፡ …” [ገፅ፡ 2/1087-1089]
“ሲጨመቅ የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ አንፃር ሲታዩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለዚያውም እነሱም ቢሆኑ ምግብ ለማብላትና ለዚክር ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል፡፡” [ገፅ፡ 1095–1099]
(አስተውሉ! ይህ እንግዲህ በሸውካኒ ዘመን ነው፡፡ የሞቱት በ1250 ሂ. ሲሆን ሁለት መቶ አመት ሊሞላቸው ጥቂት ነው የቀራቸው፡፡ ሱፊያ ደፋር ነውና የዛሬን የመውሊድ ጨፋሪዎች በመመልከት ሸውካኒን “ውሸታም ነው” እንዳይሉ እሰጋለሁ፡፡)
ሸውካኒ፡- “ግና ቢድዐን በማፅናትም ሆነ በማጥፋት ላይ ንጉሳን ተፅእኖ አላቸው፡፡ ይህንን ቢድዐ (በሱኒው ዓለም ውስጥ) የፈጠረው ያ ንጉስ (ሙዞፈር) ሲሆን ኢብኑ ዲሕያ ደግሞ ‘አተንዊር ፊ መውሊዲል በሺር ነዚር’ የተሰኘ ኪታብ በማዘጋጀት አግዞታል፡፡ ሰውየው በዘገባ እውቀት ላይ የጠለቀ ከመሆኑም ጋር በዚህ ኪታቡ ግን ግልፅ ማስረጃ አላቀረበም፡፡ ለዚህ ስራው - ኢብኑ ኸሊካን እንደጠቀሱት - አንድ ሺህ ዲናር በንጉሱ መሸለሙ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ የዱንያ ፍቅር ከዚህም በላይ ያደርሳል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091]
“የቢድዐ ስርጭት ከእሳት ስርጭት የፈጠነ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ መውሊድ፡፡ ምክንያቱም የመሃይማን ነፍሶች ጥግ የደረሰ መናፈቅን ይናፍቁታልና፡፡ በተለይ ደግሞ ከምሁራን፣ ከክቡራንና መሪዎች በርከት ያለ ሰው ከተካፈለበት በኋላ ይሄ ቢድዐ ወሳኝ ከሆኑ ሱናዎች ይመስላቸዋል፡፡ … እንደ መውሊድና አምሳያዎቹ ያሉ ለሐራም ነገሮች የሚያመቻቹ የጥፋት መዳረሻዎች መሃይሞች ፈጥነው እንደሚገቡባቸው አያጠራጥርም፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ በዒልም፣ በክብርና በስልጣን ዝና ያለው ሰው መካፈል ሲታከልበት ሐራም ነገሮችን እንደ ፈጣሪ ትእዛዛት ሲፈፅሙ፣ በድንቁርናና በጥመት ሸለቆች ውስጥ ገብተው ሲዘባርቁ፣ “የተከበሩ እከሌ፣ እከሌ፣ እከሌ፣… ተገኝተዋል” እያሉ ከተቃውሞ ሲያመልጡ የባሰ ይሆናል፡፡
መሃይሙ ህዝብ ይቅርና አንዱ በዒልም ፍለጋ ላይ ገኖ የወጣ ሰው አንዳንድ የኢጅቲሃድ እውቀቶችን ለመማር ከፊቴ ተቀምጦ ነበር፡፡ በዚህ ወር ከተከናወኑ መውሊዶች ውስጥ በአንዱ አዳር ላይ እንደተካፈለ ሲነግረኝ ተቃወምኩት፡፡ አንገሸገሸኝ፡፡ በዚህን ጊዜ ‘ሰዪዲ እከሌ፣ እከሌ፣ እከሌ፣… ተካፍለዋልኮ’ አለኝ፡፡ በነዚህ ታዋቂ ሰዎች ፊት የነበረውን አፈፃፀም ስጠይቀው እንዲህ አለኝ፡-
‘እነዚያ ታዋቂ ሰዎች እየዘፈኑና እያዳመጡ መንዙማውን አንድ ዱርየ አነበበ፡፡ ከዚያም አንዱ ልክ ከእስር የተነሳ ይመስል አፈፍ ብሎ ተነስቶ “መርሐባ ያ ኑረ ዐይኒ፣ መርሐባ” (እንኳን መጣህ ያይኔ ብርሃን እንኳን መጣህ!) ሲል ታዳሚው በመላ ታዋቂዎቹን ጨምሮ ተከትለውት ቆሙ፡፡ እነሱ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ቆሞ ማጓራት ያዘ፡፡ አንዱ ታዳሚ ደክሞት ቢቀመጥ ከታዋቂዎቹ ውስጥ አንዱ ንዴቱ ከፊቱ ላይ እየታየ ‘ተነስ! ጨዋታኮ አይደለም!’ ብሎ ጮኸበት፡፡ ቃል በቃል! የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚያች ሰዓት ከነሱ ዘንድ እንደደረሱ ጭራሽ አይጠራጠሩም፡፡ ከዚያም ተጨባበጡ፡፡ ከመሀይማን ከፊሎቹ በእጆቻቸው ሽቶ በመያዝ በፍጥነት ቀቡ፣ ተቀቡ፡፡ ልክ የሳቸውን ﷺ መገኘት ለመጠቀም፡፡’
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! የዲን ክብር የት ገባ?! ይህም ከጠፋ አይናፋርነት፣ ግብረ ገብነት፣ ህሊና የት ገባ?” [ገፅ፡ 2/1089-91]
መውሊድን የሚያከብሩ ሰዎች “ከኛ በላይ ነብዩን ﷺ የሚወድ ላሳር!” የሚሉ ናቸው፡፡ እውነት ለመናገር የነብዩ ﷺ ዘሮች ሙእሚኖች ከሆኑ ለነብዩ ﷺ ያላቸው ፍቅር ልዩ ነው፡፡ መውሊዱ የፍቅር መገለጫ ቢሆን ኖሮ ከማንም ቀድመው ባከበሩት ነበር፡፡ ግን ከነሱ የተገኘው መውሊድን ማክበር፣ ማስከበር፣ ለሱ ሽንጥን ገትሮ መሟገት ነውን?
ሸውካኒ፡- “ከነብዩ ﷺ ንፁሕ ቤተሰብም ይሁን ከተከታዮቻቸው ይህ ነገር እንደሚፈቀድ የተናገረ አንድም ፊደል አላገኘንም፡፡ እንዲያውም ይህቺ ቢድዐ ከተከሰተች ጀምሮ ወደ ጥፋቶች ከሚያሻግሩ አስቀያሚ መዳረሻዎች አንዷ እንደሆነች ንግግሮቻቸው ከሞላ ጎደል ተስማምተዋል፡፡” [ገፅ፡ 1089]
አሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ
القواعد الأربع ኪታብ
ጨርሰናል በአላህ እገዛ
ቀጣዩ ኪታብ የሚሆነው
كتاب التوحيد ከነ መሳኢሉ
ከነገ እንጀምራለን በአላህ ፍቃድ
በሳምንት 2ቀን
ያሀገሬ ሰው ሲተርት እንድህ ይላል ገንዘብ የሚገኝው በ20 አመት እውቀት የሚመጣው በ40 አመት እና ምን ለማለት አስቤነው ብዙ እህቶች ከስደት በ11 አመታቼው ሀገር ገብተው ድጋሜ ስደት ተሰደዱ አንች ስደተኛዋ እህቴ እወቂበት ማሻአላህ ትሰሪያለሺ ትለፊያለሺ ስራፍተሺ አተውቂም ግን ብር የለም ለምን አላውቅም. ብዙወቹ እህቶች ከኔጀምሮ እየሰራን ብሩ የት እንደሚሄድ አናውቅም እንላለን…
*ያሀገሬ ሰው ሲተርት እንድህ ይላል
ገንዘብ የሚገኝው በ20 አመት
እውቀት የሚመጣው በ40 አመት
እና ምን ለማለት አስቤነው
ብዙ እህቶች ከስደት በ11 አመታቼው
ሀገር ገብተው ድጋሜ ስደት ተሰደዱ
አንች ስደተኛዋ እህቴ እወቂበት ማሻአላህ
ትሰሪያለሺ ትለፊያለሺ ስራፍተሺ
አተውቂም ግን ብር የለም ለምን
አላውቅም. ብዙወቹ እህቶች
ከኔጀምሮ እየሰራን ብሩ የት እንደሚሄድ
አናውቅም እንላለን ግን ስህተት ነው
እናቴ አባቴ እህቴ ወንድሜ አጎቴ
አክስቴ እያልን የምናወጣውን
አስተውላችሁታል እናት አባት አወ ፈርድ
ነው ግን እኮ እራሳችሁን ስችሉነው
ለቤተሰብ የምትተርፉት ወላሂ. ኢትዮጵያ
ገብታችሁ የረዳችሗቼው ሰውች ዞር
ብለው አያዋችሁም እንዳውም የጥላቻ ባህሪ
ነዉ የሚያሳዩት እራስሺን ቻይ
እራስን ካልቻሉ እናት እና አባትም አይወዱ
ሽክም መሸከም ማን ይወዳል
መፍትሄውን ልገርሺ. ከጓዶኞችሺ ጋር
ቁብ ግቢ መጨርሻ. ተቀበይ ከዛ ብሩ
እንደተቀበልሺ ባይሞላም ተበድርሺም
ቢሆን በታ ግዥ ድጋሜ ትገቢያለሺ
ቤትሺን. ከዛ ይቀጥላል. ልብ ካለሺ
አለዛ እየተቀበል. እየመዘዝሺ እንቅጭ ከሆነ
የት እንደሚሄድ አላቅም አትበይ
ምክር ተቀበይ ልብሺ አይሙላ ሰምተሺ
ተግብሪ ካለሺ ሁሉም ወዳጂሺ ነው
የሚመኝሺ ብዙ ነው በጎንሺ ብዙ ሰወች አሉ
ከለለሺ ዘመድ ጥላትሺ ነው.
ከተሞከረሰው ምክር ውሰዱ. እሺ
በሰው ሀገር ልጂ የለኝ እድሜየ ሄደ
ከማለት ውል ስሪ አርብ ሀገር
ካልተጠቀምሺበት እድሜሺን
ጊዜሺን ጤናሺ እሱው ሀገሩ ይጠቀምብሻል
እነዚህን በማሳጣት ስለዚህ ንቂ ንቂ ንቂ
የደት እንድጠቀምብሺ ሳይሆን አንችው ተጠቀሚበት
የኢክሩዩ እናት ነኝ*https://t.me/EmuIkramAselefiyahttps://t.me/EmuIkramAselefiya
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana