ለምን አልሰለምኩም?

Description
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 year, 2 months ago

እውነት አላህ የቁርኣን ጠባቂ ነው ተብሏልን? The Islamic Dilemma

ሙስሊሞች ከሚያነሱት ሙግቶች አንዱ፣ ቀጥሎ ያለው ነው:

"መፅሐፍ ቅዱስ የተበረዘው ሰዎች ጠባቂዎቹ ስለተባሉ ሲሆን የቁርአን ጠባቂ ግን አላህ ነው ተብሏል።"

የሚጠቅሱትም ሱራ ይሄ ነው: ሱራ 15:9

إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ

እኛ "ቁርኣንን" እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡

ነገር ግን እዚህ ላይ "ቁራኣን" ተብሎ የተተረጎመው - "አል-ዚክራ" የሚል ቃል እንጂ ቁርአን አይደለም

ዚክር- ማለት "reminder- ማስታወሻ፣ admonition- ምክር" ማለት ነው።

ታድያ መፅሐፍ ቅዱስ ዚክር አልተባለምን? መልሱ ተብሏል ነው።

ሱራ 21:48

وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ

ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን (ወዚክራ) በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡

ሱራ 16:43

وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ إِلَّا رِجَالًا نُّوحِي إِلَيْهِمْ ۚ فَاسْأَلُوا أَهْلَ#الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

ከአንተም በፊት ወደእነሱ ወሕይን (ራእይን) የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ #የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡

በዚህ ክፍል ላይ أَهْل الذِّكْرِ (አህላል-ዚክሪ) የሚለውን- የዕውቀትን ባለቤቶች ብለው ተርጉሞውታል። ኢብኑ ከሢር ግን በተፍሲራቸው አህለል ዚክር ማለት "the people of the previous Books" " የቀድሞ መጽሓፍት ባለቤቶች" ማለት እንደሆነ አስቀምጧል ።

ስለዚህ ለሙሴ የወረደውና ከቁርኣን በፊት የወረዱት መፅሓፍት "ዚክር" ከሆኑ፣ ሙግቱ ቀጥሎ ያለው ይሆናል:

1- አላህ ዚክሩን ያወረድነው እኛው ነን፣ እኛው ጠባቂዎቹ ነን ካለ እና ተውራት ዚክር ከሆነ፣ ተውራት ተበርዟል ካልን አላህ ውሸታም መሆኑ ነው። ምክኒያቱም አልጠበቀውማ።

2- አይ፣ ተውራት አልተበረዘም ከተባለም፣ አላህ ውሸታም ይሆናል። ምክኒያቱም ፔንታቱክ የምንላቸው ወይም "ተውራት" ውስጥ እግዚአብሔር ያስተማረው የቁርአን ተቃራኒ ናቸው።

ለምሳሌ: ዘጸአት 4

23 እስራኤል የበኵር ልጄ ነው፤ ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ ትለዋለህ።

እንደ ቁርአን ትምህርት ግን አላህ ባሪያ እንጂ ልጅ የለውም!

3- አይ፣ ኦሪት ከተውራት ይለያል አልተጠበቀም ወይም አሁን ላይ ተውራት ጠፍቷል ከተባለም፣ አላህ መጀመሪያ ያወረደውን ዚክር አሁንም መጠበቅ አልቻለም ማለት ነው።

Hence, Islamic Dilemma! Damned if you do, damned if you don't!?

1 year, 2 months ago

ለወልድ ሕይወት ተሰጥቶታል ማለት ካለመኖር ወደ መኖር ማለት ነውን? And what does the Koine Greek say?

2 years, 8 months ago

Christ died for us!

3 years, 10 months ago

በነገራችን ላይ ዮሐንስ 10:30 ላይ "እኔ እና አብ አንድ ነን" የሚለውን ሙስሊሞች ግሪኩን ሲጠቃቅሱት እያየሁ ነው። heis, hen, mia የሚለውን ትርጉም ሲሰጡት አይቻለው። የአላማ አንድነት፣ የህላዌ አንድነት...ምናምን። እንዲህ አይነት ትርጉም በአጭሩ በዘመናዊው ቋንቋ "ሳክስ" ይባላል።? ከዬትኛውም ተአማኒ ግሪክ ኤግዝጄስስ ሙግትህን ማስደገፍ አትችልም። እነኚህ ቃላቶች ትርጉማቸው "አንድ" ማለት ሲሆን በግሪክ ግራማቲካል ፆታ ብቻ ነው የሚለያቸው። እሱም እንደ adjective ከመጡ ከሚገልፁት ባለቤት ጋር ለመስማማት ነው፣ except in few exceptions። አንዱ እንዲህ አይነት exception ምሳሌ፣ እራሱ ዮሐንስ 10:30 ነው። በዚህ ክፍል ላይ፣ ግሪኩ "ኤጎ ካይ ሆ ፓቴር #ሄን ኤስሜን" ይላል። 'ኤጎ' ማለት እኔ ሲሆን 'ፓቴር' ማለት ደግሞ አብ ማለት ነው። ሁለቱም masculine gender ናቸው። ስለዚህ፣ በኖርማል ግራማቲካል ሕግ ቀጥሎ መምጣት የነበረበት "ሄስ"(masculine) እንጂ "ሄን"(neuter) መሆን አልነበረበትም። ነገር ግን፣ እንደ ታላቁ ስኮላር ሮበርትሰን "Word pictures of the NT" ፣ #ሄን የተጠቀመበት ምክንያት አብ እና ወልድ አንድ አካል አለመሆናቸውን ለማሳየት እና እንዲያውም በEssence አንድ መሆናቸውን ለማሳየት እንደሆነ ፅፏል።
ዮሓኒስ ደግሞ ቴዎሎጂካል መልዕክቱን ለማስረዳት፣ አንዳንዴ የሰዋ ሰው ህጎችን እንደሚጠመዝዝ የታወቀ ነው። ለምሳሌ፣ Dr. T.Cowden Laughling በ1902 የPHD dissertationኑን በራዕይ መፅሃፍ ውስጥ ዮሓኒስ እንዴት አድርጎ ግራመር እንደተጠቀመ የሚያጠና The Solecism of the Apocalypse ብሎ የፃፈውን ደስ የሚል ጥናት ማየት ይቻላል።

@Jesuscrucified
@Jesuscrucified

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana