ትዝታዊ?

Description
ስላላቹ አመሰግናለው !!

ለሃሳብና አስተያየታቹ . . . . @tiztawe1_bot ይጠቀሙ
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

4 months, 2 weeks ago

?……………

ዝምታውና ግድየለሽነቱ ነገሩን ምን ያኽል እንደተለማመድነው ያሳየናል………

ኢትዮጵያ ሴት ልጆች ከሚደፈሩባት የዓለም ሃገራት ማሃል አስር ውስጥ አለችበት ……… ስሰማ አልገረመኝም ቅዱስ ሃገር ትባላለች እንጂ እንዳልሆነች ቀድሜ ካወኩ ቆይቻለው ………

የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ስለህጉ መሻሻል ተሰብስበን እያወራን አንዷ ልጅ ህንድ ውስጥ በ 24 ሰዓት ውስጥ ከሰባ በላይ ሴቶች እንደሚደፈሩ እያወራችልን በመሃል ግቢ ውስጥ "ኦ ሃይማኖተኛ እኮ ነው" ሚባለው ልጅ ጣልቃ ይገባና

"ካላቸው የህዝብ ብዛት አንፃር ትንሽ ነው እንደውም " ብሎ ሲናገር ሌሎቹ ሲያማትቡና ሲደናገጡ አይቼ ነበር ፣ እኔ ግን አልገረመኝም

ሲጀምር እዝች ሃገር ላይ ያሉ የእምነት ተቋማት ስለእርስታቸውና ስለወንበራቸው ሲቆሙ በዘመኔ አይቻለው ነገር ግን እንደተቋም የአንዲት ሴት በደል ስለወለደው እንባ ትንፍሽ ሲሉ አልተመለከትኩም ……

' የሃይማኖት ሃገር ናት' ከምትባል ሃገር ውስጥ ብዙ ደፋሪዎችን ከልላና ተንከባክባ አወድሳ እንደምትኖር መስማት ባያስገርምም መታለል ግን ያማል !

ነፍሴን እርር ያረጋት ደሞ የህፃን ሔቨንን በአሰቃቂ ሁኔታ መደፈርና መገደል በአንድ በኩል ለፖለቲካዊ አጀንዳ መጠቀምያ አርገው የሁለት ጎራ የብሔር ፍጅት መፍጠሩን ሳይ፣ በሌላ በኩል ደሞ "አንዲት ዶሮ እንቁላል መውለዷን" እንኳን ሳይቀር ትልቅ ሽፋን የሚሰጡ ሆድ አደር ሚዲያዎች ሳይቀሩ ቀባ ቀባ አርገው ማለፋቸው ስመለከት ፣ በዚህ በኩል ደሞ አንድ አንዱ ለዮቱዮብ መሸቀያ በሌላው ስቃይ ሲቀልድ ሳይ ከአንዲት ሴት ህይወትና ክብር በላይ አንድ የበሰበሰ የሃጥያት ወንበር ዋጋ አለው የሚል መልዕክት አይቻለው ፣ ሃገሪቷ ምትመራው ፣ ስትመራ የነበረው ፣ በቀጣይም ምትመራው በእንደዚህ የወደቀ አስተሳሰብና ቁሽሽና በተሞሉ አመራራሮች ስለሆነ አስር ውስጥ መግባታችን አይግረማቹ !

እኔ ግን አሁንም ለታናናሾቼም ሆነ ፣ለታላላቆቼ ሴቶች ለራሴም ጭምር ይኼን እላለው ፣……………:
:

"የበቃሽና ጠንካራ ሴት ሁኚ በዙርያሽ ያሉትንም ሴቶች ጠብቂ ፣ ሃገር ምትቃናው ባንቺ ነው ፣ የራስሽ ፍርድና አቋም ይኑርሽ ፣ ሃጥያት እራስን መሆን ሳይሆን እራስሽን እንዳትሆኚ የሚጨቁኑ እጆች ላይ ነው ያለውና ያን እጅ ሰብረሽ ቁሚ !……… ምታፈቅሪውን፣ ምታገቢውን ምትመርጪበት ፣ ወንድ ልጅሽን ሴት ልጅሽን ምታሳድጊበት መንገደሽ የበሰለ ይሁን:( ስለደበደበሽ ፣ ስለሰደበሽ ፣ ስለቀና እያፈቀርሽ ሳይሆን መጥፍያ መንገድሽን እየቆፈረልሽ ነው እና ምርጫሽ ጤነኛና ሰላማዊ የፍቅር ምርጫ ይሁን : ስላፈቀርሽው ብቻ አታግቢው የሰውነት ስብዕናው ያልተጓደለና ለሰውነት ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑን አረጋግጪ ፣) ጤነኛ ልጆች በመረጥሽው ጤነኛ ትዳር ላይ ይመሰረታል !  ጤነኛ ቤተሰብ ደሞ ጤነኛ ሃገር ይሰራል !
………… ምን ልልሽ ነው ቁልፉ በእጃችን ነው !

ምን አልባት ያን ፍትሕ አንድ ቀን ታመጪው ይሆናል በራስሽ ታላቅነት ውስጥ ፣ አሁንም ቢሆንም ግን በብዙ ጠላቶች ተከበሽ ቢሆንም ስለራስሽ መጮኽ እዳታቆሚ !! "

ፍትሕ !!!

ፍትሕ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍረው ህይወታቸውን ላጡ ሴቶች ፣ ህፃናት !

ፍትህ ተራቸውን ለሚጠብቁ በፍርሃት ለተደበቁ ሴቶች ፣ ህፃናት !

ፍትሕ ጓዳው የደበቃቸው እንባቸው ደም ሆኖ የስቃይ ድምፅ ለሚያሰሙ ሴቶች !

ፍትሕ !!

4 months, 2 weeks ago

ላምባ ዲና........

አይኖቿ ያበራሉ ብቻ ሳይሆን ያንጸባርቃሉ.... ድንገት ሳያት እንዴት እንደሆነ አላውቅም ተደናበርኩኝ የሆነ የሂወቴ ፍሬን እንደተበጠሰ አይነት ነገር ተንቀዠቀዥኩኝ በደመነፍስ ወደሷ አመራሁኝ ስቀርባት ደሞ ይበልጥ አየኋትኝ ውይ...አይን!...

ለማውራት ድምጼን ስጠራርግ
" ይቅርታ ካላስቸገርኩኝ አስፋልቱን ታሻግረኝ? " አለች ዱላዋን እያስተካከለች
....አይኖቼ አያዩ ብርሃን የላቸው በልጅነቴ ገና አጥቻቸው...
.. የሚለው የቴዲ ዘፈን ወደ አይምሮዬ መጣ. ..ግን...ግን... ከሱ ዘፈን የሷ የአይን ዜማ ይለይ ነበር በምን አይነት ረቂቅ መንገድ ይሆን ከአይኗ የተጻፈው አጃኢብ....

.....በዛች ቅጽበት እሷ ለአለም እኔ ለፍቅር ታወርን.....

/beki-Heron!/

:
:
:#……… ደፍሪን የሚፈለፍል ፣ ህግ ይውደም
………… ጠንካራና ማስተማርያ ቅጣት እንሻለን!!!

ፍትሕ !!

4 months, 3 weeks ago

……………?

አስራአንደኛ ክፍል ጨርሼ ክረምቱን ምን ላረግ እንዳሰብኩኝ አባቴ ሲጠይቀኝ ፣ እየሰሩ ወላጆቻቸውን እያገዙ የሚማሩ ተማሪዎችን ለቀጣይ አመት እንዲሆናቸው ማስጠናት እንደምፈልግ ስነግረው ፣ የሚያቀው የመንግስት ትምህርት ቤት ዳይሪክተር ነበርና ከሱ ጋር እንዳወራ አደረገኝ እሱም ከተወሰኑ ተማሪዎች ጋር የመገናኘት እድል ፈጥሮልኝ ነበር ……ተቀጣጥረን በጋራ የማስጠናቱን ሂደት በጀመርን ወቅት ከአንዴት የአስረኛ ክፍል ተማሪ ሴት ልጅ ጋር ከማስጠናቱ ባሻገር የማውራት እድል ገጥሞኝ ነበር…………

" እናቴ ሴተኛ አዳሪ ናት ፣ አባቴ ሳይሞት በፊት እራሱ ትሰራ ነበር ፣ እራሱም እንድትሰራ ያስገድዳታል ፣ አባቴ ብዙ ጊዜ በግድ ደፍሮኝ ያውቃል ፣ አንዷ ጓደኛዬንም ይዘሻት ካልመጣሽ እያለ ይመታኝ ነበር …………"

ፊቷ ላይ ያለው ህመም አሁን እራሱ ባሰብኩት ቁጥር አዲስ ህመም ይሰማኛል ፣ እናቷን የማግኘትና ከእናቷ ጋር አብረው ሚሰሩ ሴቶችን የማውራት እድሉን አግኝቼ ነበር………

አብዛኛዎቹ ሴቶች በታመመ ቤተሰብ ውስጥ የወጡ ናቸው ………በአባታቸው ፣ በጎረቤታቸው ፣ በአባታቸው ጓደኞች ፣ ሰፈራቸው ባለ ባለሱቅ ፣ እፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ናቸው ………

እንደዛ ጊዜ አቅመ ቢስነት ተሰምቶኝ አያውቅም
………… የሰውን ስቃይ ሰምቶ እንደ አለመድረስ ከባድ ህመም የለም ………

ያልተወሩ ፣ ያልሰማነው ፣ የተደበቁ ብዙ የሴት ልጅ ስቃዬች አሉ ፣ የሰማነው ጥቂት ነው ………ብዙዎቹ ልጅነታቸውን ፣ ደስታቸውን፣ ተስፋቸውን ፣ ህይወታቸውን ፣ ክብራቸውን በጭካኔ ተነጥቀዋል ………… እንደምታስቡት ቀላል አደለም ……… ማንነትን እንደመነጠቅ ከባድ ስቃይ የለም !

እነዚህ አጥቂዎች አይናችን ስር ናቸው ፣ አንዲት ሴት ስትለከፋ ኖርማል ነው ብለን ማለፋችን የብዙ ሴትን ስቃይ ይወልዳል ፣

መድፈር ሚጀምረው ከመልከፍ ነው !

የማያዳግም እርምጃ ያስፈልገናል ፣ ጠንካራ ህግ ፣ ደፋሪን የሚሰቅል !!

ፍትሕ!

4 months, 3 weeks ago

?……………

"አባቢን እና እነ አጎቴን መፍራት አለብኝ?....ግን ልጆች ምን ሲያረጉ ነው ሚደፈሩት....መደፈር ግን ምንድን ነው .....ለማሚ እንዳነግርያት ልትቆጣኝ ትችላለች ግን ስታወሩ ፈርቻለው ማሚ ስልክ ያለችው ልጅ በህልሜ መጣች"

የ10 አመቷ የወንድሜ ልጅ ናት በጭንቀት ያለችኝ…… ምንድን ነው የምላት ?

"አዎ አባትሽን እና አጎትሽን መፍራት አለብሽ"

ልጆቻችን እንዴት ነው ሚያድጉት አንድ ህፃን ጥቃት በደረሰበት ቁጥር ለራሳችን ብለን መጮህ አለብን እኮ አጠገባችን ያሉት ልጆች  በፍርሃት ታመዋል .....ለሔቨን እና ለሌሎቹ ብቻ አይደለም ምንጮኽው አጠገባችን ላሉት  ተራቸውን ለሚጠብቁት ለሴት ልጆቻችን ነው!!

/እሌኒ  እሌኒ /

4 months, 3 weeks ago

?………

. . . ይኼን የምፅፍላቹ በውስጥ እየመጣቹ ወይም ለሌላ ሰው ወይም ለራሳቹ "ሁሉም ወንድ እኮ አንድ አደለም የምትሉ ፣ ስለሴት ስናወራ አንቺማ 'fiminist' ነሽ አጀንዳ አለሽ '666' እያላቹ ለማሸማቀቅና እውነታውን ለመካድ ለምትሞክሩ ይሁንልኝ !……

?………
"ስንት ጥሩ አባቶች ፣ ወንድሞች ፣ ባሎች ፣ ልጆች የሆኑ ወንዶች አሉ ' ብላቹ መከራከርያ ነጥባቹን ትጀምራላቹ ፣ እኔም እላችዋለው ……… ያላቹዋቸው ሰዎች አሉ ግን እነዚህ ሰዎች ለእናንተ ነው ጥሩ የሆኑት እንጂ ሌላዋ ሴት ጋር ያላቸውን ሚና አታውቁም !

……… ሚገርም አባት ነው ያለኝ ከራሴ ጋር ፍቅር እንዲይዘኝ አርጎ ያሳደገኝ ፣ ሳይኖር እንደኖረ እንዳለ የሚሰማኝ አባት ነበር ያለኝ ፣ ፍቅሮቼን ሁሉ ማፈቅረው ……… ይኼ እኔ ሚሰማኝ ነው ስለአባቴ ግን ሌላ ሴት ሚሰማትን አላውቅም ………

የሆነ ጊዜ ላይ አክስቴ " ይኼን የመሰለ አባት ይዘሽ ምንድነው እንደዚህ የወንድ ፍረጃ በጅምላ " አለችኝ ………አባቴ አብሮን ተቀምጦ 'BBC ' ዜና እየተመለከተ ነበር …… ለመመለስ አንዴ እንኳን አላሰብኩም ይኼን አልኳት

"አዎ ጥሩ አባት አለኝ ፣ ግን ለኔ ነው ……… ሌላዋ ሴት ጋር አባቴ ያለውን ሚና አላውቅም ፣ የትኛዋ ሴት በሱ አልቅሳ እንደነበር ማውቀው የለኝም " አክስቴ አማተበች ………እንደ አክስቴ አይነት ሴቶች አይመቹኝም 'አሽቃባጭና ፣ ልወደድ ባይ ነው ሚመስሉኝ '

ከአባቴ ጋር ተያየን ፈገግ አለልኝ 'ልክ ነሽ ' ነበር ፈገግታው ………

"የሴት ጥቃት " መደፈር ብቻ ሚመስላቹ ሰዎ አላቹ ……… እሱ እኮ ካንሰሩ የመጨረሻ ደረጃ ደርሶ መሞት ሲያስከትል ነው ……… ከዛ በፊት ግን ካንሰሩን የሚያመጡና ከመጣም በኃላ የሆነ የአካል ቦታ እንደመቅደድ ነው………
'ሴትን መደብደብ ፣ ለከፋ ፣ እንደማትፈልጋት እያወክ አብረክ ማደር ፣ ሳትፈቅድልክ እጇን እንኳን መንካት ፣ (በአፍክ ፣በአካልክ መተንኮስ ) ፣ ወዘተ ተረፈዎች …………

እናም ወንድሞቻቹ ፣ አባቶቻቹ ፣ ልጆቻቹ ፣ ባሎቻቹ ……… ለእናንተ ጥሩ ናቸው ማለት ለሌላዋም ሴት ጥሩ ናቸው ማለት አደለም ፣ አባቴ ለኔ መልካም ቢሆንም በሆነ ወቅት በሆነው እድሜ ላይ የሆነች ሴትን ለክፎ እንደነበር አላውቅም እሱ ለክፏት የተሸማቀች ሴት ትኖር ይሆናል ፣ ተስፋ ሰቷት ተስፋዋ የደቀቀች ሴት ትኖር ይሆናል ………… አላውቅም እኔ ማውቀው ለኔ ጥሩ አባት መሆኑን ብቻ ነው ይኼ ደሞ "ሁሉም ወንዶች መጥፎ አደሉም "ወደሚል ህሳቤ አይወስደኝም …………

እንደውም ሚመስለኝ ሁሉም የወንዶች ነፍስ ውስጥ የተደበቃ የመጀመርያው ከሰማይ የተባረረው ሰይጣን ያለ ይመስለኛል ለዚህም ነው ፀልዬ የምቀርባቹ ………!!

ሌላው ደሞ መደፈርን አቅላቹ ምታዩ ሰዎች…… ' ያለፍቃዳቹ ወይም ፍላጎት በሌላቹ ሰዎች እጃቹ ተነክቶ ያውቃል ?' እንዴት እንደሚቀፍ ወደላይ ነው ሚለው እንግዲ ደሞ ሌላውን አስቡት ………

አንዲት የተደፈረች ሴት ውጫዊ ስቃይዋ በህክምና እርዳታ ይድናል የጊዜ ጉዳይ ነው እሱንም ስላቹ ስቃዩ ከባድ ነው ብዙ ዓይነት የጤና መታወክ ይፈጠርባታል ፣ ከዛ ሁሉ በላይ ደሞ ውስጣዊ የአእምሮ ጉዷቷ ስቃዩ በቃላት ሚገለፅና ሚወራ አደለም ……… በዚህ ላይ ደሞ ያ ነፍሷን የነጠካት አውሬ ወንድ ንፁ አየር ይተነፍሳል ፣ ቤተሰብ ሊመሰርት ይችላል ፣ ወይ ይኖረው ይሆናል ፣ ህጉ አዝናንቶ ይለቀዋል …ቀላል ቁጥር ውስጥ ይቀልበዋል ብዙ ደፋሪዎችን የፈለፈለ ደደብ ህግ ነው ያለን ……ለነገሩ ህጉ እራሱ በሚሰነፍጡ ወንዶች የተሞላ ነው ………

የዘጠኝ ወር ህፃንን የሚተኛ ስሜት ፣ በኦቲዝም የተያዘች የ12 ዓመት ልጅን ፣ የሰባት አመት ህፃንን የሚተለትል ፣ የሰማንያ አመት አቅመ ደካማ ሴትን የሚያጠቃ ፣ ለአራት ለአምስት ሆኖ አንድ ሴት ላይ የሚጫወት ፣ ወዘተ …… ዘግናኝ ጥቃት ለመቃወም ሲወጣ ከጥቃቱ በላይ ሚያሳስባቹ " እራሳቹን ነፃ ማውጣት ነው ፣ ሁሉም ወንድ አንድ አደለም በማለት " ወይም ነገሩን ለመሸፋፈንና ለማቅለል መሞከር ……… በዚህ ማሽሞንሞን ውስጥ ደሞ አንዳንድ ደጋሽ አሽቃባጭ ሴቶች አላቹ የእውነት እላችዋለው ከእናንተ በላይ የሰይጣን ደቀመዝሙር የለም !

ደሞ " ስለኔ ጥሩነት እናቴንና እህቴን ፣ ሚስቴን ወዘተዎቼን ጠይቂ " ምትሉ ወንዶች አሁንም ደግመዋለው ለእነሱ የዓለም መብራት ትሆናላቹ ሌላዋ የሴት ታሪክ ውስጥ ግን አስፈሪ ጨለማ ከመሆን አያግዳቹም !

ሴት እንድታከብራት ወይም መልካም እንድትሆንላት የምትፈልገው እናትክ ፣ እህትክ ወዘተዎችክ ሴት ስለሆኑ ሳይሆን
……… ከነዛ ቤተሰብክ ውጪ ሰው እንደሆነች አስበክ ነው !……ገባክ ………!
'ስለሴት ሲነሳ እናትህ ፣ እህትክ ………ምናምን ሴት ስለሆነች ተንከባከባት የሚለው ' ዘግናኝ መደበቅያ ቃል ያቅለሸልሸኛል………!

ፍትህ ነፍሷን በቆሻሾች ለተደፈረባት ሴት , ፍትህ ገላዋን ለተጫወቱባት ሴት !

ሞት ለደፋሪዎች !
ስቃይ ለደፋሪዎች !!

ፍትህ !!

4 months, 4 weeks ago

"ወንድ ፣ ወንድ ነው ጊዜና ቦታ ብቻ ነው ሚጠብቀው …… ዘንዶ ሲጠግብ ስለሚጋደም አልፈሽው ትሄጃለሽ ፣ በተራበ ሰዓት ግን ሚመርጠው የለም ……… ስለዚህ ወንድ ወንድ ነው ጊዜና ቦታ ሚጠብቅ "

……… አለችኝ ዛሬ አንድ ነርስ ……………

ምን አልባት ትክክል ትሆናለች …………?

:
:
ሴት ልጅ እንደ ሰው የማትታይበት ዓለም ላይ ነው ያለነው ! እንደ ዓለም ነው ሴት ልጅ የተገፋችው ……… በየጓዳ የተደበቀ ብዙ ሚስጥር አለ ፣ በስልጣን ፣ በገንዘብ ፣ በፍራቻ የተደበቀ !

ፍትህ ለሴት ልጅ ፣ ፍትል ለሴት ህፃናት !

5 months ago

ይድረስ ይገስግሰው እላይ
ከሁሉ በላይ ላለ በሰማይ

የበረሀው ጥዬ፣ የምድረበዳው ጓደዬ፥ እናትም አባትም፣ ወንድምም እህትም፣ እውቀትም ጥበብም ሞገስሞ ድፍረትም ሁሉን ለሆንክልኝ !!

አዎ... በእኔ ዘንድ መቻልህ የማይጠረጠር ነውና፥ ሁሌ ፀሎቴን ሰምተ መለስከው፤...አመታት ያላደከሙህ ወራቶች ያላስረጁህ፣ ሺህ አመትን እንደ አንድ ቀን የምትኖር፣ የሺህ ዘመን ታሪክን በአንድ ቀን የምትከውን፣ ባለሞያው እግዚአብሔር፥... ከተመስገን በቀር ብልህም ብሰጥህም የልቤን የሚያደርስ የለኝም።

....እንደኔ የረዳኸው ማን አለ ? እንደኔስ ያገዝከው ማን አለ ?... በተዘጋው ልቤ ገብተ፥ ሰላም ለእናንተ ይሁን ብለህ፥ ሰላም ስላደረግክኝ ተመስገን !!

... ሊያሳልፈኝ የመጣውን ሁሉ አሳልፈ፤ ያንተ የሆነውን የዛሬውን ቀን "የአንተ ነው" ብለህ ስለሰጠኸኝ፥ እኔም የሰጠኸኝን "ያንተ ነው" ብዬ በምስጋና፣ በክብር መልሼ ለአንተው እንሰጣለሁ።

በደሌን ይቅር እያልክ በብዙ ትእግስትህ የተሸከምከኝ፣ አመሌ ያልከበደህ አንተ ብቻ ነህና፤... ሳጎድል ሞልተ የምትወደኝ፣ ሳጠፋ ትተኸው ያቀፍከኝ አንተ ነህና፣... ተመስገንኝ !!

ቃልህን በመስማት ውስጥ ባአለ ተስፋ አረጋጋኸኝ፣ ቃልህንም አሰምተህ ጥልቅ ሀዘኔን አፅናናኸኝ...
ተመስገንኝ !!

በመዳሰስህ ቁስሌን ፈወስከው፣ በይቅርታህም ብዛት የህይወት ጠባሳዬን ነጣጥለህ ሻርከው፣ ትላንትን እያስረሳህ ወደ ነገው አስገሰገስከኝ... ተመስገንልኝ !!! 
.
.
በቃ...
   ... እንደ ሁሌው ሁሉ ዛሬም፥ ለልጅህ የተከፈተውን በር ስለምትሰጥ... ተመስገን !!

እኔ በአመሌ የዘጋሁትን፣ እኔ ትእግስትን በማጣቴ የዘጋሁትን፣ እኔ ባለመታዘዜ የዘጋሁትን፥ ጠላትም ደግሞ የዘጋብኝን በር፤.. አንተ ድል አድራጊው ንጉስ፣ በሞት ላይ የገነንከው፣ የተዘጋብኝን የሞት እና የሲኦል በር ከፍተህ ታወጣን ዘንድ፥ የሞትን እና የሲኦልን ቁልፍ በእጅህ የያዝከው፤ አንተ ያንን በር ስለምትከፍትልኝ... ተመስገንልኝ !!!

...እንዳንተ ተናግሮ የሚያረጋጋኝ፣ ተናግሮ የሚፈውስኝ፣ ተናግሮ ትንሳኤ እና ህይወትን የሚሰጠኝ ማንም የለምኝም !! ...

አሁንም አሁንም እልላለው
አይወጣልኝም ጨምራለው.. ..በእውነት ተመስገንልኝ !!   
.
.
ታሪኬንና ዘመኔን ሁሉ አንተው ፃፍበት፣ አንተው ድመቅበት፣ አንተው ንገስበት፣ አንተው ተገለጥበት፤ ...ጌታ ሆይ ከአንተ ውጭ ታሪክም የለኝም፣ ክብርም ፣ ዝናም፣ አለኝ የምንለውም ከአንተ ውጪ የለኝም፤... ስጣራው ይደርሳል የምለው፣ በጭንቄ የሚረዳኝ ካንተ ውጪ የለኝም.

...ደግሞ እንኳን አንተ ብቻ ሆንክኝ !!

ሳትታዘብ የተገለጠውን የምትከድን፣ ሳትነቅፍ የጎደለውን የምትሞላ አንተ ብቻ ነህ፥ በእውነት አመሰግንሀለው !!

በመጨረሻም ሁሌ እንዲህ እልሀለው እንዲሁ ነህና ...

አንድ ሆነህ ከሺህ ሰራዊት ትከባለህ፣ አንድ ሆነህ ከሀያላን በላይ ትረታለህ፣አንድ ሆነህ በሰማይ በምድር ካሉ ጠቢባን በላይ ትጠበባለህ፣ አንድ ሆነ እናት፣ አባት፣ እህት፣ ወንድም፣ ዘመድ ወዳጅ ጓደኛ ትሆናለህ፣  አንድ ሆነህ ሁሉን ትሆናለህ ሁሉ በሁሉም ነህ፤

ተመስገን *3 !!

...ግሩም ብእር !!

5 months ago

ውድድሩ አልቆዋል እንደፈጣሪ ፍቃድ እሁድ ተሸላሚውን እናውቃለን??

ግን ግን የእውነቴን ነው ስለላካቹልኝ ሁላቹንም ከልቤ በሃይል አመሰግናለው !!

በማንበብ ድጋፋቹን ስሰጡ ለነበራቹ ፣ ለተከታተላቹ ሁሉ አመሰግናለው !!

?

እና ደሞ ዛሬ አመስግኛቸው አመስግኛቸው ስላለኝ ስለሚገባቹም ላመስግናቹ………

ስላላቹ ደስ ይለኛል ፣ ስለምትከታተሉ ፣ ሃሳባቹን ስለምሰጡኝ ፣ በዝምታም አይታቹ ያላቹ ፣ እንደዚህ ቤት ሰላም የሚሰጠኝ ቦታ የለም ከምሬን ነው ፣ ትቼው ጠፍቼም ስመጣ ኖራቹ ለምጠብቁኝ ሁሉ ፈጣሪ ያክብርልኝ!

የተሻለ ነገር ቢኖረኝና ያን ሁሌ ቤቱ ላይ ባመጣ ደስታዬ ነው ፣ የሞላ ስለሌለኝ እድትሞሉት ነው ፁሑፋቹን ላኩልኝ ምላቹ ፣ ቤታቹ ነው የፈለጋቹትን ተንፍሳቹ ላኩልኝ ለቀዋለው ፣ ደስ እያለኝ !! እየፈገኩ?

እና ብሶት ያስቀባጥራል ስለሚባል ሳልቀበጣጥር ቢበቃኝስ ?ሆሆሆ

እና ሰላም ዋሉ?

5 months ago

?………………

---እራሴን ዋሸሁት አዎ ደግሞ ይመጣል----
በሚል የውሸት ተስፋ እራሴን ሸወድኩት………
አይመጣም የሚል ነገር ለራሴ መስጠት ትልቅ ህመም አለው፡፡ ሁሌም እራሴን አታላለው አዎ ይመጣል ዳግም ፍቅራችንን እንቀጥላለን፡፡ እንዲ ነበር ጓደኛዬን ወደድኩት አዎ ከጓደኛዬ ጋር ፍቅር ያዘኝ  ሃሃሃሃ ጓደኝነትን ትቼ ፍቅሬን አስቀደምኩ፡፡ አዎ ጥቅምት 2/2012 ፍቅሬን ሀ ብዬ የጀመርኩት፡፡   ጣፋጭ የፍቅር ግዜ ነበረን ከምንም እና ከማንም በላይ ፍቅሬን ወደድኩት ከሱ ውጪ ህይወትን ማሰብ ከባድ ህመም ነው ጣፋጩን የፍቅር ህይወት ሳናጣጥመው ከእንቅልፋችን ነቃን……እኔ ስነቃ አለው በቦታዬ ፍቅሬ ውዱ ጓደኛዬ ፍቅሬንም ጓደኛዬንም ከእንቅልፌ ስነቃ አጣሁት……..አጠብቂኝ ኦ ከባድ ቃል ነው አዎ ያማል አንተን እሱን አለመጠበቅ ህመም አለው አዎ ይመጣል እጠብቀዋለው ይሄ ሰላም አለው ከሱ ውጪ ህይወት ከሱ ውጪ እኔን ማሰብ ሃሃሃሃሃሃሃ ድጋሚ እራሴን ዋሸሁት  ይመጣል  አዎ ፍቅሬ ይመጣል………..02/ጥር/-----------ዓ.ም  መርከበኛዬ አዎ  ትመጣለህ እጠብቅሀለው  እንሞላዋለን

/ Tinibit/

7 months, 2 weeks ago

....?
እንዳልጠላሽ ስወድሽ... እንዳትገፊኝ ስትስቢኝ  ያ እንዳይሆን ይሄን አርገን ካንዱ ወገን ተለጥፈን የምኖረው ለምንድነው?

መጠየቅን ጠይቀነው ምላሽ ሰጪ ፈልገናል ላለመቆም ተራምደናል
.
.
ማነው በአለም ፍላጎቱን ሁሉ በማሳካት የደመደመ ? ማንስ ይሆን ከምኞት ኋላ ዳግም በሌላ ምኞት ያልተከበበ..?
ህይወት መንገድ የሚሄዷት ማብቂያ ኬላ ሞት የሚሉት እስኪወስዳት ሞትም ቢሆን ድልድይ ነው ሰፊ ጉዞ ስጋን ትቶ የሚነጉደው ከነብስ ጋር ተያይዞ

/ዮቶር /

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana