AMAN FLY

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 23 hours ago

Last updated 4 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 2 days ago

1 year, 6 months ago

የሃጅና ዑምራ አፈፃፀም በአማርኛ

t.me/alhadith_islamic

1 year, 6 months ago

ለፀሃፊዎች !

ብዙሃኖች የሚረዱት ተራውን የአፃፃፍ አይነት ሲኾን፤ ከዚህ በተቃራኒ ቃላቶችን እየመረጡና ከባባድ ቃላቶችን እየፈለጉ በፅሁፎቻቸው ውስጥ የሚያሰፍሩ በርካቶች ናቸው። እኚህ አንዳንዴም ጥሩ ደራሲያን መኾናቸውን ለማሣየት የሚፈልጉ (ደራሲዎች) ሲኾኑ አንዳንዶቹ ደግሞ (ደራሲ ያልሆኑ) አንባቢዎች ነን ባዮች ናቸው። ምናለ ሁሉንም አማክላችሁ ፍትፅፉ ? ፖለቲከኞቹስ ይሁኑ ፓለቲካ እንኳን ቃል ተመርጦለት በአምስተኛ ክፍል አማርኛም ቢፃፍ ሁሉም ማህበረሰብ አይረዳው። ግን ሃይማኖታዊ የኾኑ ፅሁፎችን ለምን ? እንጠቅማለን ብላችሁ ብዙሃኑ ላይ ብዥታን እየፈጠራችሁ መሆኑን ተረዱ። ዓሊይ (ረ.ዐ) እንዳለው፦ «ሰዎችን በሚገነዘቡት ልክ አውሯቸው» ።

https://t.me/amanfly50

1 year, 6 months ago

ብዙዎቻችን ትኩረት የማንሰጠውና በብዛት ማህበራዊ ድህረገጾች ላይ ከተስፋፉ መጥፎ ተግባሮች መካከል አንዱ የሌሎችን ጠቃሚ አስተምህሮዎች ወደ ራስ አስጠግቶ ለሌሎች ማሰራጨት ነው። ፅሁፎች፣ ምስሎች፣ ቪዲዩች እና ሌሎች የሰዎችን መልእክቶች የግለሰቡን አድራሻና ስም በማጥፋት የራስን ስም ወይም የራስን የሶሻል ሚዲያ ጦማር በማድረግ መለጠፍ ሲኾን ይህ ተግባር በተለይ ጧሊበል ዒልም በኾነ ግለሠብ ላይ ነውር የሆነ እንደ ኢስላምም የተወገዘ ተግባር ነው። የእውቀት ባለቤቶች እውቀትን ወደ ባለቤቱ አለማስጠጋትን አጥብቀው ይከለክሉ ነበር።

ኢማም ኢብኑ ዓብድልበር እንዲህ ይላሉ፦
" ከዒልም በረካ(በረከቶች) መካከል አንድን ነገር ወደ ተናጋሪው(ምንጩ) ማስጠጋት ነው። ይባላል።" [ ጃሚዑ በያኒል ዒልም 2/922]

ኢማም አን ነወዊ እንዲህ ይላሉ፦
 « ከምክሮቼ መካከል፦ የተለዩ (ሃሣብ) ፋኢዳዎችን ወደ ተናጋሪው ማስጠጋት ተገቢ ነው። ይህንን ያደረገ በእውቀቱና በተግባሩ የተባረከ ይኾናል። የሌሎችን ንግግር ወስዶ የእርሱ እንደሆነ አድርጎ ሌሎችን ብዥታ ውስጥ የከተተ፤ በእውቀቱ ከማይጠቀሙት መኾኑ የተገባ ነው። በተግባሩም በረካን አያገኝም። የእውቀት ባለቤቶች የሚጠቅሙ ነጥቦችን ወደ ተናጋሪው ያስጠጉ ነበር።» [ቡስታኑል ዓሪፊን 11/47-48]

https://t.me/amanfly50

1 year, 6 months ago

ባእድ ወንድ (አጅነቢይ) በሌለበት ቦታ ላይ ከነ ኒቃብ መስገድ የተጠላ ነው። ሶላቱ ግን ተቀባይነት አለው።
https://t.me/amanfly50

1 year, 6 months ago

ስድስት አመት ብቻ ?!

ሰዕድ ኢብኑ ሙዓዝ ይባላል። ታላቅ ሶሃቢይ ነው። ኢስላምን የተቀበለው በሰላሳ አመቱ ነው። በሰላሳ ስድስት አመቱ ነው የሞተው። ስድስት አመት ብቻ ነው ኢስላም ውስጥ ያሳለፈው። የአር-ራህማን ዓርሽ በሞቱ ተንቀጥቅጦለታል። ሰባ ሺ መላኢኮች ጀናዛውን ሸኝተውታል። ከቀብሩ ውስጥ የሚስክ ሽቶ መኣዛ ሸቷል።
ረዲየሏሁ አንሁ

https://t.me/amanfly50

1 year, 7 months ago

የአኼራ ወንድማችሁ ነኝ ፦
አይፎን (iphone 14 pro max ) ለፈጅር ሶላት አላርም ምሞላበት እፈልጋለሁ ፤

ቁርአንና ኢስላማዊ አስተምህሮዎችን ማዳምጥበት (Airpods pro) እና ከመስጂድ የቀረበ መኖሪያ ቤት እፈልጋለሁ ። ㋛

የዘመኑ አደብ ያለው ልመና シ

https://t.me/amanfly50

1 year, 7 months ago

ያው አባት ስትሆኑ ታውቁት ይኾናል ስለ አባትነት እና ልጁ ሲወለድ ስለነበረው ገጠመኝ እናወራለን እኛ አባቶች ... እና በጣም ካሣቀኝ የሠማሁት ገጠመኞች ውስጥ ሁለት ጓደኞቼ የነገሩኝ ገጠመኝ ነው ...

አንዱ ፦ እኔ የመጀመሪያ ልጄን ስወልድ  በጣም ደንግጫለሁ አለኝ ። ለምን? ስለው
እኔ የተወለደ ህፃን ልጅ የማቀው ሴቶች አቅፈው ይዘውት መንገድ ላይ ሲሄዱ የማየውን ነው(የአራት የአምስት ወር ልጅ አይቶ እኮ ነው¡)። ያንተ ልጅ ነው ተብዬ ልጄን ሳየው በጣም ትንሽ ከመኾኑ የተነሣ ቀፈፈኝ፤ እኔ ከዚ ቀደም እንደዚህ ገና የተወለደ ልጅ አይቼ አላውቅምና ለሚስቴ “ምንድነው ይሄ” ብያታለሁ አለኝ።

ሌላኛው ደግሞ ፦ እኔ የመጀመሪያ ልጄን ስወልድ በቃ ለማቀውም ፣ለማላውቀውም፤ ለሚመለከተውም፣ ለማይመለከተውም ልጅ ወልድኩ ብዬ ነበር ምናገረው ...
ደስ የሚለው እነሡም ሣያሳፍሩ ነበር እንኳን ደስ አለህ ሚሉኝ አላለም ...

እናንተስ ምን አጋጥሟችሁ ይሆን ?¡

https://t.me/amanfly50

1 year, 7 months ago

ከሶላት በኋላ የምንላቸው ዚክሮች

1- ሶስት ጊዜ ኢስቲጝፋር (አስተጝፊሩሏህ) ካሉ በዃላ እንዲህ ማለት፦ “ አሏሁመ አንተ ሠላም ወሚንከ ሰላም ተባረክተ ያ ዘል ጀላሊ ወል ኢክራም’’ [ሙስሊም]

ትርጉም ፦(አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ፡፡ ሰላምም ካንተ ነው፡፡ የክብርና የሞገስ ባለቤት የሆንከው ጌታ የተባረክ ነህ፡፡)

2- “ ላ ኢላሀ ኢልለልላሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁ-ልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲይር፤ ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ፤ ላ ኢላሀ አልለላሁ ላ ነዕቡዱ ኢልላ ኢይያሁ፤ ለሁ-ንኒዕመቱ ወለሁ-ልፈድሉ፤ ወለሁ-ሥሠናኡ-ልሐሰን፤ ላ ኢላሀ ኢልለልላህ ሙኸሊሲይነ ለሁ-ድዲይነ ወለው ከሪሀ-ልካፊሪዉን፡፡” [ሙስሊም]

ትርጉም ፦ (ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ብቻውን ነው፡፡ ብጤ የለውም፡፡ ንግስናም ለርሱ ነው፡፡ ምስጋናም ለርሱ ነው፡፡ እርሱም በሁለም ነገር ላይ ቻይ ነው፡፡ በርታትም ሆነ ነገሮችን መለወጥ በአላህ ካልሆነ በስተቀር የለም፡፡ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላን አናመልክም፡፡ ጸጋም ለእርሱ ነው፡፡ ችሮታም ለእርሱ ነው፡፡ መልካም ውዳሴም ለእርሱ ነው፡፡ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ከሐዲያን የሚጠሉ ቢሆንም ለእርሱ ቅን ታዛዦች ነን፡፡)

3- “ላ ኢላሀ ኢልለልላሁ ወሕደሁ ላ ሸሪይከ ለሁ ለሁ-ልሙልኩ ወለሁ-ልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲይር፤ አልላሁምመ ላ ማኒዐ ሊማ አዕጠይተ ወላ ሙዕጢየ ሊማ መነዕት ወላ የንፈዑ ዛል ጀድዲ ሚንከ-ልጀድ፡፡” [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]

ትርጉም፦ (ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ብቻውን ነው፡፡ ንግስናም ለእርሱ ነው፡፡ምስጋናም ለእርሱ ነው፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ቻይ ነው- አላህ ሆይ! ለሰጠኸው ከልካይ የለም፡፡ ለከለከልከውም ሰጪ የለም፡ ፡ ካንተ ችሮታ ይበልጥ የሌላ ችሮታ ፈጽሞ አይጠቅምም፡፡)

4- “ሱብሓነ-ልሏህ” (33) ጊዜ፡፡ “አልሐምዱሊልሏህ” (33) ጊዜ፡፡ “አልሏሁ አክበር” (33) ጊዜ፡፡ መቶ መሙያውን “ላ ኢሏሀ አልለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ወሁወ ዓላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር ” አንድ ጊዜ ማለት፡፡[ሙስሊም]

5- “አላልሁምመ አዒንኒ ዐላ ዚክሪከ ወሹክሪከ ወሑስነ ዒባደቲክ፡፡

ትርጉም፦ (አላህ ሆይ! አንተን በማስተወስ፣ አንተን በማመስገን፣ ማመለክህን በማሳመር ላይ እርዳኝ፡፡) [አቡ ዳውድ እና ነሣኢይ]

6- “አልላሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነ-ልቡኽሊ ወአዑዙ ቢከ ሚነ-ልጁብኒ፣ ወአዑዙ ቢከ አን ኡረድደ ኢላ አርዘሊ-ልዑሙሪ ወአዑዙ ቢከ ሚን ፊትነቲድዱንያ ወአዑዙ ቢከ ሚን ዓዛቢ-ልቀብር፡፡” [ቡኻሪይ]

ትርጉም፦ (አላህ ሆይ! ከንፉግነት ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከፈሪነትም ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ ወደእርጅና እድሜ ከመመለስም ባንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከምድራዊው ሕይወት ፈተና ባንተም እጠበቃለሁ፡፡ ከቀብር ቅጣትም ባንተ እጠበቃለሁ፡፡)

7- “ረብቢ ቂኒ ዓዛበክ የውም ተብዓሡ ዒባደክ”[ሙስሊም]

ትርጉም፦ (ጌታዬ ሆይ! ከቅጣትህ ጠብቀኝ ባሮችህን በምተሰበስብበት ቀን )

8- “ቁል ሁወሏሁ አሐድ” “ቁል አዑዙ ቢረብቢ-ልፈለቅ”ን እና “ቁል አዑዙ ቢረብቢ-ንናስ” መቅራት፡፡[አቡዳውድ]
° ከመጝሪብ እና ከሱብሂ ሶላት በኋላ ሶስት ጊዜ ይደጋገማሉ።

9- “አየቱ-ልኩርሲይን” መቅራት

10- ከሱብሂ እና ከመግሪብ በኋላ አስር ጊዜ ይህን ማለት “ ላ ኢላሀ ኢልለልላሁ ወሕደሁ ላ ሸሪይከ ለሁ ለሁ-ልሙልኩ ወለሁ-ልሐምዱ ዩህይ ወዩሚት ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር።”[ቲርሚዚይ]

ትርጉም፦(ከአሏህ በስተቀር (በእውነትም የሚመለክ) ሌላ አምላክ የለም። ብቻውን ነው። ብጤ የለውም። ንግስናም ለእርሱ ነው። ምስጋናም ለርሱ ነው። ህያው ያደርጋል። ሙትም ያደረጋል። እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው።)

√ ከሶላት በኋላ ዚክር ስናደርግ ሌሎች ተፈጻሚ መሆን ያለባቸው ነገሮች

- ዚክሮችን በእጅ ማድረግና በቀኝ እጅ ማድረግ።

-እኚህን ዚክሮች ስናደርግ ቦታ ሳንቀይር ሶላት በሰገድንበት ቦታ ላይ ሊኾን ይገባል።

√ ከሶላት በኋላ የሚባሉት ዚክሮች ያላቸው ትሩፋት

- ግዴታዊ ከኾኑ ሶላቶች ኋላ ያሉት ዚክሮች በተገቢው መልኩ ማስገኘት እና በዚህ ተግባር ላይ ዘውታሪ መሆን በቀላሉ 55 የሚሆኑ ሱንናዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንዲገኝ ይረዳዋል።

- እኚህን ዚክሮች በማድረግ ዘውታሪ የኾነ ሶዶቃህ እንዳደረገ ይቆጠርለታል። መልእክተኛው እንዲህ ብለዋል፦ “ እያንዳንዱ ተስቢሕ (ሱብሐነልሏህ) ሰደቃህ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተሕሚድ (አልሐምዱሊሏህ) ሰደቃህ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተህሊል (ላኢላሀ ኢልለሏህ) ሰደቃህ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተክቢር (አሏሁ አክበር) ሰደቃህ ነው፡፡”[ሙስሊም]

- በእኚህ ተስቢሆች ላይ ዘውታሪ የኾነ በየቀኑ ጀነት ውስጥ 500 ዛፎች ይተከሉለታል። መልእክተኛውﷺ ከእለታት አንድ ቀን አቡሑረይራ ዛፎችን እየተከለ ባለበት መንገድ አለፉና እንዲህ አሉት ፦ “ አንተ አቡ ሑረይራ ሆይ! ላንተ ከዚህ የተሻለ መትከልን ላመላክትህን? እርሱም አዎን!  አለ። ነብዩምﷺ ሱብሐነልሏህ፣ አልሐምዱሊሏህ፣ አሏሁ አክበር በል። በየአንዳንዱ ተስቢሕ ጀነት ውስጥ አንድ ዛፍ ይተከልልሃል አሉት።” [ኢብን ማጃህ]

- በእርሱና በጀነት መካከል ሞት እንጂ ምንም የለም ተብሏል “አየተል ኩርሲይ”ን ከሶላት በዃላ ለቀራ ።

- ወንጀሉ የባህር አረፋ እንኳ ቢኾን ከላይ የተጠቀሱ ተስቢሆች(ዚክሮች)ን ያለ ወንጀሉ ይማርለታል ተብሏል።[ሶሂህ ሙስሊም]

- በእኚህ ዚክሮች ላይ ዘውታሪ የሆነ ከአኼራም ኾነ ከዱንያ ክስረት የተጠበቀ ነው።

- በፈርዱ ሶላት ላይ የተገኘውን ጉድለትና ክፍተት አሟይ ናቸው።

https://t.me/amanfly50

1 year, 7 months ago

ኢብኑል ጀውዚይ እንዲህ ይላል፦
“ እወቅ ! ልብ እንደ አጥር ነው። ሸይጣኖች ደግሞ የጠባቂውን ዝንጉነት በመሻት በዚህ አጥር ዙሪያ ከመዞር አይወገዱም። ጠላት አይሰላችምና ጠባቂው ለአፍታ እንኳ ከጥበቃው መሰላቸት አይገባውም ።” [ተልቢስ ኢብሊስ 23]

https://t.me/amanfly50

1 year, 7 months ago

በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ያለው መቀመጥ (አል ጁሉስ በይነ ሰጅደተይን) ይባላል። ሶላት ውስጥ ያለው ብይን አብዝሃኛዎቹ የፊቅህ ሊቃውንት ከጡመዕኒና(እርጋታ) ጋር ሩክን(ምሶሶ) ነው ብለዋል። ይህንን የጁምሁሮች አቋም ኢማም አቡሃኒፋ ተፃርረዋል። መቀመጡ እና ጡመዕኒና (እርጋታ)ግድ አይደለም ፤ አንገቱን ከሱጁድ ትንሽ ቀና ብሎ መልሶ ሱጁድ ማድረግ ይበቃለታል  ብለዋል። በሌላ የአቡ ሃኒፋ ንግግራቸው ላይ…

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 23 hours ago

Last updated 4 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 2 days ago