ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
*🔥የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር የሁለት ቀን የድል ውሎዎች‼️*
~~///~~~~~
አሽከርነት የባህሪው የሆነው የብአዴን ውላጅ የሆነው የትናንቱ አዴፓ የዛሬው የብልፅግና አሽከር በመላው የአማራ ነባር እርስቶች ሊያደርግ የፈለገው የደም ግብር ሰላማዊ ሰልፍ በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው ከተሞች ሁሉ እንዳልተሳከለት እና ፋኖም በተለያዩ ቦታዎች አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ላይ ነው።
በትናንትናው እለት በደብረ ማርቆስ ከተማ አደርገዋለሁ ያለውን ሰልፍ በሴፍቲኔት የሚተዳደሩ ስልሳ የሚደርሱ እናቶችን ወደ አደባባይ ቢያስወጣም እናቶች እንዲህ ሲሉ ድምጣቸውን ለአገዛዙ ገልጠዋል።
እኛ በድህነታችን ላይ እናንተ ተጨምራችሁ ተወልደን ባደግንበት ሀገር ውሃ ሽጠን፣የቀን ስራ ሰርተን የእለት ኑሯችንን መኖር አላስችል አላችሁን፣እናንተ ግን በአስር አይነት አጃቢ እየታጀባችሁ ለዚህ ምስኪን ህዝብ ጠብ ያለ ነገር አላደረጋችሁለትም።ሲጀመር አንፈልጋችሁም ውጡልን ፋኖዎች ልጆቻችን ናቸው፣ቢመራቸውና ተወልደው ባደጉበት ሀገር ባይተዋር ቢሆኑ ነው ወደ ጫካ የወጡት በማለት መንግሰት ነኝ ባዩን የወንበዴ ቡድን አዋርደው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።
የመንግስት አካላትም በማስፈራሪያ እና በዛቻ በተለያዩ ደብዳቤዎች ብሎም ነፍጥ በታጠቁ ኃይሎች በየቤቱ እየተዘዋወሩ ሰልፍ እንድትወጡ ብለው ቢያስገድዱም አንድም የመንግስት ሰራተኛ ወደ አደባባይ እንዳልወጣ ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በሌላ ዜና በትናንትናው እለት በደብረ ኤልያስ ከተማ ወሽቆ ከሚገኘው የጠላት ኃይል ብዛት ያለው የመከላከያ ኃይል ከእነ ሙሉ ትጥቁ ፋኖን ሲቀላቀል፤ከፊሎቹ ደግሞ የሞርታር መሳሪያን አባላሽተው መውጊያውን በመንቀል ሶስት ሆነው ወደ ፋኖ ተቀላቅለዋል።አሁን ላይ የጠላት ኃይል እየተሸበረና በአድማ ብተና እና በመከላከያ መካከል ከፍተኛ ልዩነት ተፈጥሮ ይገኛል።
በተለይም ደግሞ በደብረ ኤልያስ ከተማ ከሚንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ የኮለኔሉ አጃቢ ክአነ እስናይፐሩ ከከዳ በኃላ ጠላት የገዛ ጥላውን ማመን እንዳቃተው ነው ከውስጥ ያገኘነው መረጃ የሚጠቁመው።
በዛሬው እለት ደግሞ በጅጋ፣በደንበጫ፣በእምቡሊ ብሎም በሌሎች ከተሞች አደርገዋለሁ ብሎ ያሰበው ሰልፍ በጀግኖች ፋኖዎች እንዲከሽፍ ሆኗል።
በተለይ በየጨረቃ ከባቢ ዛሬ በኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ጠላት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል።
እንግዲህ ሸክም ልማዱ የሆነው የኢህዴን ብአዴን አዴፓ ውላጅ የሆነው የብልፅግናው አሽከር ቡድን ዛሬም በወንድሞቻችን ደም ላይ የመጨረሻ የሆነው የህዝብ መድረክ በደም ቀለም የተዋበውን ካራባቱን ለብሶ የውሸት ፕሮፖጋንዳውን ሊነዛ ቢሞክርም አረንዛው ጎጄ ልቡን አላወቁትም መሠል እርቃናቸውን አስቀርቷቸዋል።
የመጨረሻው መጨረሻ የብልፅግና ሰልፍ ሰላማዊ ያለው ሰልፍ ተገልብጦ ወደ መፈክራዊ ሰልፍ የተቀየረበት ቀን ነበር።
መንግስት አሁን ላይ እጁም እግሩም ተቆርጦ ምላሱ ብቻ በቲቪ መስኮት ብቻ ነበር የሚሰማው። ይህን በሰራው ዶክመንታሪ ቪዲዮ ራሱ ተዋርዶበት ተቀባይነቱን አጥቶበታል።
መውጫ፦የተከበርከው የአማራ ፋኖ ሆይ ላለፉት አስራ ስምንት ወራት የሰራሐው ስራ አብቦ ሊያፈራና ከፍሬው የአማራ ህዝብ ብሎም የኢትዮጵያ ህዝብ ሊመገብ ትንሽ ቀን ነው የቀረውና አንድነትህን አፍጥነህ በአንድ ትንፋሽ ቁምና የአባቶችህን ቤተመንገስት በመገማሸር ተቀብለህ የህዝብህን እንባ በጋራ ታብስ ዘንድ አበክረን እንጠይቃለን።
ድላችን በክንዳችን
አንድ አማራ ፣ድል አለማራ ፋኖ ፣አዲስ አብዮት
አዲስ ድል ፣አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በክንዳችን እና በአንደበታችን እንፈጥራለን።
©የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ መ/ር ታደገ ይሁኔ(ሸርብ)#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️#ምረር_አማራ💪#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
10/04/2017 ዓ.ም**@NISIREamhra
🔥#የጨቅላው አብይ አህመድ የእምቧለሌ ጉዞ..‼️
የጨቅላው አብይ አህመድ የአንካራ ስምምነት በትዳር ላይ ሌላ ትዳር እንደማለት ነው። ለሶማሌላንድ ያሰረውን ቀለበት፣ ለሶማሊያም አጥልቋል። በአጭሩ ጨቅላው ሲኳትን ከርሞ፣ በሶማሌላንድ ላይ ቺት በማድረግ የሽንፈት አልጋ መለመላውን ተጋድሟል። (በእርግጥ ለኢሱም ቀለበት አድርጎ ነበር 😁) የብብት ስር ዲፕሎማሲ መጨረሻው እንዲያ ሆነልህ።
የሆነው ሆኖ የብልጽግናው አገዛዝና ግሪሳዎቹ በቀጣይ ትኩረታቸው ወዴት ይሆናል የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ጥያቄ ነው። ግሪሳዎቹ የአንካራው ስምምነት ከተሰማ ጀምሮ የወደብ አጀንዳውን ከበርበራ ወደብ ወደ አሰብ አምዘግዝገውታል። ይህ አጀንዳ እንዲሁ በቀላሉ የተሳበ አይመስልም፤ ምናልባትም ነገሮችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ "ጨቅላው ለሶማሊያው መሪ ሃሰንሼክ መሃመድ ጋር ያለውን ግንኙነት እያደሰ፣ ስለምን ለኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ግልፅ እንች እንካ ጀመረ?" ለሚለው ጥያቄ ምላሽ መፈለጉ መልካም ነው።
በእኛ አረዳድ ድንቁርና የዘለቀው ጨቅላው አብይ አህመድ ከሶማሊያ ጋር ከሚኖር ጦርነት ይልቅ፣ ከኤርትራ ጋር ያለውን ቢያንስ በሚከተሉት ምክንያቶች ይፈልገዋል፦
1) የምዕራቡ ዓለምና የአረብ ሊግ ሃገራት ከሶማሊያ ይልቅ ከኤርትራ ጋር የሚኖርን ጦርነት ይፈልጋሉ የሚል ዕሳቤ የወረሙማው በረት ውስጥ መኖሩ መንጋውን ኤርትራን ላይ ግርርር ለማለት አደፋፍሯቸዋል።
2) ሌላው ኤርትራን ለመውረር የወረሙማው ምክንያት "በኤርትራ ላይ ቂም የያዙ ህውሓታውያን አብረውኝ ይሰለፋል፤ ይፋለማሉ" የሚለው አስተሳሰብ ነው። ይሆናል አይሆንም የሚለው ሃሳብ አከራካሪ ቢሆንም ነገር ግን ይህ ዕሳቤ የወረሙማው በረት ውስጥ እንደ ግስጥ ብሎ የተቀመጠ ዕሳቤ ነው። የሁኔታው ግምገማ ሲሰሩም እንደ opportunity የታየ ነው።
3) በኤርትራ በኩል የሚደረግ ጦርነት አሁንም ዋና ስጋታቸውን የሰሜኑን ክፍል በድጋሚ ለማድቀቅ የሚያግዛቸው ይሆናል፤ በዚህም ትግራይና አማራ የጦርነት አውድማ ሆነው ይቀጥላሉ ማለት ነው። ነገር ግን በሶማሊያ በኩል የሚጀመር ጦርነት በሶማሌ ክልል ህዝብ እራሱ ቢያንስ በለዘብተኝነት የመታየት እድሉ ሰፊና ኦሮሚያ ክልልንም በቀላሉ ለወረራ የሚያጋልጥ ስለሚሆን ሶማሊያንና በሶማሊያ የጦር ሰፈር የመሰረቱትን ሃገራት ማባበሉ ቀላል ሆኖ ተገኝቷል። ቀለበቱም ከኢሳያስ ወደ ሙሴባሂ ከዛም ወደ ሃሰንሼክ እንዲዞር ምክንያት ሆኗል።
4) ሌላው ለጨቅላው የኤርትራ ጋር ያለን ጦርነት ተመራጭ ያደረገለት ነገር በተራቁጥር ሁለት እንደተመላከተው ከኤርትራ ጋር የሚኖር ጦርነት አዲስ የኃይል አሰላለፍን በመፍጠር በአጋጣሚው አማራና ትግራይም ዳግም ወደ ግጭት ይገባሉ፤ ፋኖን ለማዳከምም ተጨማሪ እድል ያስገኛል" የሚል አረዳድ መኖሩ "አሰብ አሰብ" የሚለውን ከበሮ ድለቃ ዳግም ለመጀመር ምክንያት ይሆናል። ከዚህም ባሻገር የምዕራቡ ዓለም ለኤርትራ መንግሥት ካለው ጥላቻ ጋር ተያይዞ ፋኖንም ለማዳከም የሚያግዝ የጦር መሳሪያና የዲፕሎማሲ ድጋፍ አገኝበታለሁ የሚል ድለቃ ከዛ ማዶ ያለ ይመስላል።
ለማንኛውም እኛ እንደሁ ጨቅላው አብይ አህመድ ሲፈልግ ለመሃመድ አብዱላሂ ሲፈልግ ደግሞ ለሃሰንሼክ መንታ መንታ ይውለድላቸው የሚል አቋም ነው ያለን (አሳድጉ ግን እንዳይለን 😁)።
ወይ ፍንክች ያባቱ ልጅ!
©Bw
#ላንጨርስ_አልጀመርንም*‼️#ምረር_አማራ💪#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪*
4/04/2017 ዓ.ም**@NISIREamhra
*🔥"#እሜቴን_ከማዝገም_አዝሎ_መሮጥ_ይሻላል*‼️"
ከምዕራብ ወሎ ወታደራዊ ኮር በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ የተሰጠ አጭር መግለጫ
ወሎ ቤተ - አምሓራ
የአማራን ህዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ከቤት እስከ ሀይማኖት ተቋማት የሚዘረጋ ጥቃት እየተሰነዘረ እልፍ አእላፍ ወገኖቻችን በቀያቸው እና በመስጂድ እንድሁም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ጭምር በግፍ ሲገደሉ አይተናል ሰምተናል:: ይህ ህዝብ መጥፋት አለበት ተብሎ ተፈርዶበት የዘር ፍጅት ስለባ የሆነ ህዝብ ልጆች ነን:: አንዱ አማራን ገለን ቀብረነዋል ሲል ሌለኛው አከርካሪውን ሰብረነዋል በማለት የተዘባበተበት ህዝባችን የጠላቶቹን የጥፋት እና ሴራ መረብ በመበጣጠስ ዛሬ ላይ ደርሷል::
በህዝባችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመቀልበስ የፋኖ ትግል ለአማራ ህልውና የሚል አላማ ሰንቀን ወደ ጫካ ከገባን ሁለተኛ አመታችን እየተቃረበ መሆኑ አይዘነጋም:: ባለፉት ወራት በርካታ ድሎችን ተጎናፅፈን የብልጽግና ስርአትንም አፍረክርከን አብዛኛውን የክልላችንን ክፍል መቆጣጠር ችለናል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ያለፉት ወራት የፈተና እና የትምህርት ወራት እንደነበሩም ግልጽ ነው:: እኛን ሲፈትነን የከረመው ዋነኛው ችግር አንድነት ማጣታችን ነው:: ሌለኛው ችግር ደግሞ የባንዳው መብዛት መሆኑን ሁላችሁም የምታውቁት ነው::
በተለይ የአማራ ፋኖ ወደ አንድ መጥቶ በአንድ የዕዝ ሰንሰለት ውስጥ አለመግባቱና የጎንዮሽ ትግል መጀመሩ ለጠላት መቼም ተፈልጎ የማይገኝ እድል ሆኗል:: ራሳችንን በራሳችን የማጥፋት አዙሪት ውስጥ ልንገባ ምልክቶች ታይተው ነበር። ይህ እጅግ በጣም አሳዛኝ የሆነ አካሄድ መሆኑን እናምናለን።
በጠላት ቤት በጊዜያዊነት ላሉት የውስጥ አርበኞችም ተስፋ አስቆራጭ ክስተት ሆኖ እኛ ላይ ሙሉ እምነት እንዳይኖራቸው አድርጓል:: ስርአቱን ከውስጥ ሆነው እየገዘገዙ ያሉት የውስጥ አርበኞች ተልዕኳቸውን አጠናክረው እንድቀጥሉና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ወደ መዋቅራችን እንድገለበጡ፣ ይህን ትግል እና የፋኖን ድል በጉጉት የሚጠብቀው ህዝባችን ምኞት እንድሳካ፣ የሰማዕታት አላማ ግቡን እንድመታ፣ ህዝባችን ላይ የተጋረጠው የህልውና ስጋት ተወግዶ ለአማራ እና ለመላው ኢትዮጵያዊ ምቹ የሆነ የፓለቲካ እና ፀጥታ እንድሁም ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ከባቢ እንዲፈጠር ለማስቻል የአማራ ፋኖ አንድነት ወሳኝ ነው::
ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጎንደር ወንድሞቻችን የአንድነት ስምምነት ተፈራርመው እንደ ቀጠና የጋራ ቤት ለመስራትና ለአማራ ፋኖ የአንድነት ጉዞ ዝግጅት ለማድረግ የወሰዱት ቴዎድሮሳዊ እርምጃ ያለፉት ወራትን የዘመነ መሳፍንትነት ምዕራፍ የዘጋ በሳል እና አስደሳች ውሳኔ ሆኖ ስላገኘነው የተሰማንን ደስታ እየገለፅን ለአማራ ህዝብ፣ ለጎንደር ነዋሪዎች በልዩ ሁኔታ ደግሞ ለአማራ ፋኖ በጎንደር እና ለአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ሰራዊት እና አመራር በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታችን ይድረስልን እያልን የምዕራብ ወሎ ኮር በበኩሉ የጎንደር ፋኖ አንድ መሆን ለአማራ ፋኖ ወደ አንድ መምጣት ወሳኝ ነው ብሎ እንደሚያምን ለመግለፅ እንወዳለን። ስለሆነም ለአንድነት ጉዟችን መሰረት ለጣላችሁልን ወንድሞቻችን በህዝባችን ስም ምስጋናችን ይድረሳችሁ። በሸዋ በኩል ያለው ጅምር ስራ አልቆ ደስታችን ሙሉ እንደሚሆንም ተስፋ እናደርጋለን።
የወሎ ቀጠናን በተመለከተም በትናንትናው ዕለት የድርጅታችን የአማራ ፋኖ በወሎ አካል የሆነው ላስታ ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ኮር ባወጣው መግለጫ ላይ ለኮሎኔል ፈንታው ሙሀባው ያቀረበው ጥሪ የእኛም ጥሪ ስለሆነ የምዕራብ ወሎ ኮር ከመቼውም ጊዜ በላይ ለወሎ ፋኖ ውህደት እና ለአማራ ፋኖ አንድነት ቀናኢ እሳቤ ያለው በመሆኑ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባው ወደ መጀመሪያ ቤቱ ተመልሶ ከዚህ በፊት በወሎ ፋኖ የውህደት ስምምነት መሰረት የሰጠውን ታላቅ ክብር እና ኃላፊነት እንደገና ተቀብሎ ትግሉን ከጓዶቹ ጋር ሆኖ እንድመራ ስንል በአማራ ህዝብ ስም በአደባባይ ለመጠየቅ እንወዳለን::
ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በወሎ በበኩሉ ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባን አግጀበታለሁ ያለውን ወረቀት በመቅደድ የአንድነት በሩን እንድከፍት እንደ ምዕራብ ወሎ ኮር በይፋ የምንጠይቀው የአሳምነው ፅጌን የኑዛዜ ቃል በማስታወስ ጭምር ነው:: ከአንድነት እንጅ ከተናጠል ጉዞ የሚገኝ ህዝባዊ ትርፍ የለም። ተነጣጥለን ተጉዘን እንኳን ህዝብ እራሳችንንም ልናተርፍ አንችልም።
በመሆኑም ከቤተመንግስት እስከ ጫካ አማራ ተኮር ተልዕኮ አንግቦ ለጥፋት የተሰማራው ጠላት ከየጫካው ተጠራርቶ አዲስ አበባ ላይ እየመከረበት ባለበት በዚህ ወቅት የፋኖ ውስጣዊ አንድነት ለነገ የማይባል በመሆኑ ህዝባችን የተደቀነበት አደጋ እየከፋ መምጣቱን ተገንዝበን በጋር ቆመን ለመመከት መዘጋጀት ስላለብን ሀይልን የማሰባሰብ ወዳጅም የማበራከት ሂደት የመጀመሪያው እርምጅ የሆነውን የፋኖ አንድነት እውን እናደርግ ዘንድ በድጋሜ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የአብይ መንግስት የአማራ ህዝብን እንደ ጠላት ቆጥሮ በሰማይ በድሮን በምድር በወታደር ጉልበት ህጻናትን፣ እናቶችን፣ ባልቴቶች እና ሽማግሌዎችን ጭምር ታርጌት ያደረገ ወንጀል እየፈፀመ ያለው ሊያጠፋን ስላቀደ እንጅ ሲቪሎች ለሰራዊቱ የደህንነት ስጋት ሆነውበት አይደለም። ስለዚህ ጥፋት የታወጀበት ህዝብ ልጆች መሆናችንን አውቀን በፍጥነት ወደ አንድ ድርጅት ጥላ ስር ተሰባስበን ለህልውናችም በጋር እንድንታገል ስንል ደግመን ደጋግመን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በትግሉ ሂደት አንዳንድ እንቅፋት መኖሩ የትግል ባህሪ ስለሆነ "እሜቴን ከማዝገም አዝሎ መሮጥ ይሻላል" የሚለውን የአበው ብሂል መሰረት በማድረግ እንቅፋቱን እያነሳን ሩጫችንን መቀጠል እንዳለብንም እናምናለን። "ከቅርብ ያልመለሰ እረኛ ሲሮጥ ይውላል" እንደሚባለው አሁን አንድ መሆን ካቃተን ብዙ ዋጋ እንደምንከፍል ተገንዝበን ከወዲሁ በፍጥነት የቤት ስራችንን መስራት ይኖርብናል::
በመጨረሻም:- የቴዎድሮስ ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ ሰይድ አለምዬ በትናንናው ዕለት ማለትም ታህሳስ 2 ቀን በተንታ ወረዳ ደበቅ ቀበሌ በነበረው ጦርነት የጥምር ጦሩን የቁም ምሽግ በቦንብ በመስበር 21 ጠላት ደምስሶ አስገራሚ ጀብዱ በመፈፀም በመሰዋቱ የተነሳ ጥልቅ ሀዘን የተሰማን ቢሆንን እንደ ፊታውራሪ ገብርዬ ለህዝብ እና ለታሪክ ታምኖ ያለፈ ጓድ ስለሆነ የኮራችን ሰራዊት የተለየ ኩራት ጭምር ይሰማዋል:: እንደ ፋኖ ሰይድ አለምዬ ያሉ ጀግኖች የተሰውለት አላማ ከዳር የሚደርሰው አንድነት ሲኖረን መሆኑንም እናምናለን። በዚሁ አጋጣሚ ለፋኖ ሰይድ አለምዬ ወዳጅ ዘመድ እና ለተንታ ህዝብ በሙሉ የምዕራብ ወሎ ኮር መጽናናትን ይመኛል።
©የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር ጠቅላይ አዛዥ አርበኛ አደም አሊ#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️#ምረር_አማራ💪#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
3/04/2017 ዓ.ም**@NISIREamhra
*🔥#የደብረኤልያሱ_ትንቅንቅ‼️*
ደብረ ኤልያስ ላይ የነበረው ውጊያ ተፋፍሞ እንደቀጠለ ነው።
የጠላት የእግር እሳት የሆኑት አናብስቱ የቀስተ ደመና ፋኖዎችና ንስር ኮማንዶ ሁለቱ ዛሬም ላይ ማለትም በታህሳስ 03/2017 ዓ.ም ሞቴን ሞት ያርገው ብሎበከተማው ውስጥ መሽጎ የተቀመጠውን ይህን የሞት ሰራዊት ስምን ከግብር አስተካክለው የያዙት ባለሰንደቆቹ የደመና ቀስቶችና በብርሃን ፍጥነት የሚደርሱት ደብረ ኤልያስ ከተማ ውስጥ በመግባት ዙሪያውን በመክበብ እንደ አውድማ ሰብል ሲወቁት ውለዋል።
በአርበኛ ኢያሱ ሞላ የሚመሩት ሰይፈ ነበልባሎቹ የቀስተ ደመና ብርጌድ ፋኖዎች ከሌሊቱ 8:00 አካባቢ የጠላትን መስፋፊያ ምሽግ አስቀድመው በመያዝ ጠላት አስፍቶ እንዳይመሽግ ካደረጉት በኋላ ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ላይ ውጊያ ጀመሩ።
በሌላ በኩል በመቶ አለቃ አዲሱ የሚመራ የንስር ኮማንዶ ከቀስተ ደመና ጋር በመተሳሰር የአበሸብን መውጫ በመያዝ ጦራቸውን ለውጊያ ዝግጁ አድርገው ተቀመጡ።
ለተወሰኑ ቀናትም ቢሆን የጠላት በከተማቸው መፈንጨት የበሰጫቸው እኒህ ፋኖዎች ወደ መናፈሻ የገንዳ ውሃ እንደሚገቡ እየተወረወሩ ወደ ጠላት ምሽግ ይገቡ ጀመር።
ጠላት በቁመቱ ልክ የቆፈረው ጉድጓድ አላዳነውም።ከመሽጉ ድረስ በመግባት በኤፍ ዋን ቦንብና በብሬን ጥይት እያዳፈኑ ጠላትን ከዚያው ከምሽጉ ይቀብሩት ጀመር።
በለው በለው የሚለው የአዋጊዎች ቃል ነበልባሎቹን የቀስተ ደመና ፋኖዎችና ንስሮቹን እንደ ቋያ እሳት ያጋግላቸው ጀመረ።
ውጊያው በፖሊስ ጣቢያ፣በእስላምየና ነብዩ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ተፋፍሞ ቀጥሏል። ጥሩ ባለሙያ እንደያዛቸው ድምጸ መልካም የሙዚቃ መሳሪያዎች ስናይፐሮቻቸውንና ብሬኖቻቸውን የሚያቀነባብሩት አልሞ ተኳሾቹ የጠላትን ስናይፐርና ዲሽቃ ተኳሾችን ከዛፍና ከፎቅ ላይ እያወረዱ ይጥሏቸው ጀመር።
ጠላት ግራ ገብቶታል።የያዘው ዙ-23፣የተሸከመው ሞርተርና ዲሽቃ ሊያድኑት አልቻሉም።ቀስተ ደመናዎቹ እየፎከሩ ይተኩሳሉ።ጥይታቸው ግን መሬት አትወድቅም።ለሆዳሞች የወንበር ደህንነት የጣዖት መስዋዕት የሚሆነውና የሞት መንፈስ የወደቀበት ወራሪ ጦር እግሬ አውጭኙን እየሮጠ ጭንቅላቱን በክላሽ ጥይት እየተቀወረ ይወድቅ ጀመር።
እንደ ተምዘግዛጊ ሚሳኤል ጠፈር ደፈር ሳይከለክላቸው ባሕር ተሻግረው፣ብዙ ኪሎሜትሮችን አቋርጠው፣ዳገቱን ወጥተውና ቁልቁለቱን ወርደው እየተወነጨፉ ጠላትን የሚያስጨንቁት፤አፈሩ ጠርቶት ከደጃቸው ድረስ ሲመጣ ነገሩ ሁሉ ሰርግና ምላሽ የሆነላቸው የእሳት ወላፈኖች ቀስተ ደመናዎቹ ጠላትን እያዘዋወሩ ያሹት ጀመር።
የትግል ክንፏ የማይዝለው የንስር ኮማንዶ በቀኝ ክንፍ ጠላትን ስታራግበው ውላለች።የሁለቱን ጣምራ ክንድ መቋቋም ያቃተው የጠላት ጦርም በአንድ በኩል ለመቁረጥ ቢሞክርም ጀግኖቹ ግን ወይ ፍንክች ብለዋል።
ከሌሊቱ 11:00 የተጀመረው ይህ ውጊያ በአናብስቱ የቀስተ ደመና ብርጌድ ፋኖዎችና በንስሯ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ደሞቆ ውሏል።በዚህም ውጊያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ሠራዊት የሞት ሲሳይ ሆኗል።እጅግ በርካታ ጦርም ቁስለኛ ሆናል።
ጠላት አሁን የረሳውን የደብረ ኤልያስን ማንነት በደንብ እንዲያስታወስ ሆኗል።
ደብረ ኤልያስን ለመውረር የመጣው አብዛኛ ኃይልም በፋኖ ጥይት እየተቆላ እስከ ወዲያኛው ተሸኘ።
ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት እስከ እኩለ ቀን የቆየው ውጊያ ትንሽ ጋብ ካለ በኋላ እንደገና በአዲስ ጀመረ።
ከሰዓት በኋላ የጠላት እግር እሳት የሆነችው የበረኸኛዋ ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ጦሯን ጭና ከተፍ ብላለች።አሁን ጠላት የሞት ድባቡ ተጭኖታል።ጀግኖች ይተኩሳሉ።የዓቢይ ሠራዊት እንደ ጎመን እየተቀረደደ ይወድቃል።
በአሁኑ ሰዓትም ውጊያውን በአየር ኃይል የታገዘ ለማድረግ ማስፈራሪያው በሆነችው ድሮን ከፍተኛ የሆነ አሰሳ በከተማዋ እያደረገ ይገኛል።
ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ነው።
©ፋኖ ኢንጅነር ዘመን ባሳዝነው
የቀስተ ደመና ብርጌድ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ።#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️#ምረር_አማራ💪#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
3/04/2017 ዓ.ም**@NISIREamhra
*🔥#ጀግናው_የአባቱን_የአፄ_ቴዎድሮስ *ታሪክ ደግሟል‼️**
በዛሬው ዕለት የአማራ ፋኖ በጎንደር ጉና ክፍለ ጦር ስማዳ ሀገረቢዘን ብርጌድ አባል የሆነው ከሻለቃ ውባንተ አባተ ጋር ብዙ ዎጋ የከፈለው አናብስት የሻለቃ 4 ( ወርቄ ሙላቴ) ሻለቃ ጓዳችን ፋኖ አስፋው(አስፌ) ሆድ አደር ሚሊሻ እና የኦሮሙማው ሰራዊት ጥምር ጦር ስማዳ ወረዳ ፀዶዬ ቀጠና ልዩ ቦታው ላይ ሽሜ ቀበሌ 16 በሚባል ቦታ ለማፈን የተንቀሳቀሰን ጠላት መንገድ መሪውን ጀሮ ጨምሮ 4 ሚሊሻ ፣ 2 መከላከያ በመግደል ፣በርካቶችን ያቆሰለ ሲሆን ጥይት በማለቁ ቦንብ ተጠቅሞ የመጨረሻዎን ጥይት ጠጥቶ በክብር ለአላማውና ለህዝብ ነፃነት ታምኖ ወደቀ፣ ጓዳችን ታሪክ ሰርቶ አርፏል‼️
ሲሉ የብርጌዱ ቃል አቀባይ ፋኖ ደጉ አውለው ለንስር አማራ የገለፁ ሲሆን አያይዘውም ባለፈው በተዘረፉ ባንኮች ምክንያት ተፈጥረው የነበሩ ችግሮችን ከህዝባችን ጋር በመሆን የፈታናቸውና ሪፎርም በማድረግ ጠንካራ ስራ እየሰራን እና ህዝባችንን ከሌሎች ወንድሞቻችን ጋር በጋራ በመሆን ነፃ ለማውጣት በዝግጁነት እና በጥሩ ቁመና ላይ እንገኛለን በማለት ገልፀዋል‼️
ክብር ለአማራነት በአራቱም አቅጣጫ ለተሰዉ ጓዶቸ ይሁን‼️#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️#ምረር_አማራ💪#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
26/03/2017 ዓ.ም**@NISIREamhra
*🔥#ከቲሊሊምርክታ_ፋግታ‼️#የጎጃም *አገው ምድር ክፍለ ጦር በ24ና 25/2017 ዓ.ም ከቲሊሊ፣ከአዲስ ቅዳምና ከዳንግላ ከተሞች ተሰባስቦ ወደ #ፋግታ ከተማ ለመግባት የተንቀሳቀሰው የአብይ አህመድ የሙታን ስብስብ ዛሬም እንደተለመደው ልማደኛው የጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር ብርጌዶች በጥምረት የመከራ ዶፍ ሲወርድበት ውሏል።በዚህ አውደ ውጊያ :-#ኮሰበርና አካባቢው~ ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ#የፋግታ ለኮማው ~፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ#የቲሊሊው~ዘንገና ብርጌድ#የሰከላው~ ግዮን ብርጌድ እንዲሁም ከ5ኛ ክፍለ ጦር የፍኖተ ሰላምና አካባቢው #አረንዛው ዳሞት ብርጌድ በጥምረት #ምርክታ፣#አሰም፣#ዳንጊያ **ኪዳነ ምህረትና ኮሰቦር ከተማን ያከተተ ውጊያ በማድረግ የአብይን የሙታን ስብስብ በርካታውን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ መልሰው ሰደውታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ #የቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ ቀሪዉ ሻለቃ በቀጥታ ቲሊሊ ከተማ በመግባት እንደ ቀበሮ ጉድጓድ ቆፍሮ የመሸገውን አራዊት ቡድንን አፈር ሲያበሉት አምሽተዋል።
በዚህም ዉጊያ የጠላትን ሀይል እሬሳና ቁስለኛ ማድረግ ሲቻል በወገን በኩል ምንም የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ አጃይብ የሚያስብል ሁኖ በድል ተጠናቋል።
ነገር ግን በዚህ የተጨነቀዉ ጠላት ከ10 ጊዜ በላይ ሞርታር ቲሊሊ ከተማ ላይ በመጣል ብዛት ያላቸዉ ንፁሀንን ጉዳት አድርሷል።
ስለዚህም የመጨረሻው ምጥ ላይ መሆኑ ግልፅ ነዉና ወገን በያለንበት ሁሉ እንበርታ‼
አሸንፈናቸዋል💪💪💪
ሲሉ የዘንገና ብርጌድ ቃል አቀባይ ፋኖ አለበል አወቀ ለንስር አማራ ገልፀዋል‼#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️#ምረር_አማራ💪#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
26/03/2017 ዓ.ም**@NISIREamhra
ጠላትን እረፍርፎ የመጨረሻዎን #ጥይት ለአማራነትና ለክብሩ ሲል #ጠጥቷል በክበር ወደቀ ‼️**
ይህ ከታሪክ ያነበብነው ሳይሆን ጎንደር ምድር ላይ አንድ ጀግና በዛሬዋ ቀን በደሙ የፃፈውን ወድ መስዎትነት ነው መረጃ አጠናክረን እንመለሳለን‼️
ትግሉ ትናትም፣ዛሬም ዎጋ እየተከፈለበት ነውና ትግላችንን ከጩልሌዎች እንጠብቅ‼️#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️#ምረር_አማራ💪#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
26/03/2017 ዓ.ም**@NISIREamhra
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana