MyDataInfo

Description
your infotainment channel
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 years, 3 months ago

የኖቤል የኬሚስትሪ ዘርፍ ሽልማት ለሶስት ሳይንቲስቶች በጋራ ተበርክቶላቸዋል።

ለሶስቱ ሳይንቲስቶች ሽልማቱ የተበረከተላቸው ዘርፉ ይበልጥ ገቢራዊ ይሆን ዘንድ ለጣሉት መሰረት ነው ተብሏል።

ሽልማቱን አሜሪካውያኑ ሳይንቲስቶች ካሮሊን በርቶዚ እና ባሪ ሻርፕልስ ከዴንማርካዊው ሞርተን ሜልዳል ጋር የተጋሩት መሆኑን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
@MyDataInfo

2 years, 6 months ago

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል ወስነዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጠየና ሳይንስ ኮሌጅ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው÷ ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ እስካሁን የተቋረጡ ትምህርቶችን በማካካስ የሕክምና ትምህርቱን ካቆመበት እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡
የተማሪ ቢንያም ኢሳያስን ትምህርት በተመለከተ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የሕክምና ትምህርት ቤት ለተማሪው የትምህርት ሂደት ይረዳሉ ያሏቸውን አማራጮችን ቢያቀርቡም ÷ ተማሪ ቢንያም ብቸኛ ፍላጎቱ የሕክምና ትምህርትን መማር እንደሆነ ተገልጿል።
በዚሁም መሠረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል ተወስኗል።
እስካሁን የተቋረጡ ትምህርቶችንም በማካካስ ትምህርቱን ካቆመበት እንዲቀጥል ይደረጋል መባሉን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ምንም እንኳን የትምህርት ሂደቱ ከባድ እና ውስብስብ ቢሆንም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የሕክምና ትምህርት ቤቱ የተማሪ ቢንያምን ትምህርት የተሳካ እንዲሆን የሚችሉትን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት ወደ 6624 Ok ብለው ይላኩ
@MyDataInfo

2 years, 6 months ago

በአዲስ አበባ ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውደቅ ተደረገ!!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ያወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ውድቅ አደረገ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን 2014 የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ መደረጉን ተናግረዋል።
ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት ወደ 6624 Ok ብለው
@MyDataInfo

2 years, 6 months ago

በዛሬው ዕለት የአሜሪካ የጦር መርከብ ከቻይና መንግስት ፈቃድ ውጪ በደቡብ ቻይና ባሕር በሚገኙ ደሴቶች አካባቢ መግባቱን የቻይና ጦር አስታወቀ፡፡

የቻይና ጦር የደቡብ ዕዝ ቃል አቀባይ ቲያን ጁንሊ በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ÷ በቀጠናው የታየው የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የቻይናን ሉዓላዊነትና የሠላም ፍላጎት የሚጋፋ ነው ብለዋል፡፡

ቲያን ጁንሊ በቻይና ግዛት ውስጥ የተስተዋለው የአሜሪካ የባሕር ጦር እንቅስቃሴ የደቡብ ቻይናን ባሕር ሠላምና መረጋጋት የሚጎዳ፣ ዓለም አቀፍ ህግጋትን እና የዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶችን ኅግ የጣሰ ነው ሲሉም በመግለጫቸው ተናግረዋል።

“አሜሪካ በደቡብ ቻይና ባሕር አካባቢ የፈጸመችው ጥሰት የደኅንነት ሥጋት ፈጣሪ እና የአካባቢውን ሠላም እና መረጋጋት አጥፊ መሆኗን ያረጋገጠ ተግባር ነውም” ብለዋል - ቃል አቀባዩ፡፡

የቻይና ጦር የሀገሪቷን ሉዓላዊነት፣ ደኅንነት ፣ ሠላም እና መረጋጋትን ለመጠበቅ ሁልጊዜም በተጠንቀቅ እንደሚገኝ ማስታወቁንም ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ወደ 6624 Ok ብለው ይላኩ
MyDataInfo

2 years, 6 months ago

በተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ ላይ ለደረሰዉ መጉላላት ኃላፊነቱን እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል አስታወቀ

በህክምና ትምህርቱን መቀጣል ባይችልም በሶስት የትምህርት ዓይነቶች መማር እንደሚችል ዉሳኔ ተላልፏል

በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 5ኛ ዓመት የሕክምና ተማሪ የሆነው ቢኒያም ኢሳያስ በሕክምና ትምህርት ክፍሉ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየ ቢሆንም ለመመረቅ 2 ዓመት የማይሞላ ጊዜ ሲቀረው ትምህርቱን እንዲቋርጥ መገደዱን ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ መናገሩ ይታወሳል፡፡ይህ የሆነው ባለብኝ የአካል ጉዳት ምክንያት ነዉ የሚለዉ ተማሪ ቢኒያም አትችልም ተብሎ ትምህርቱን እንዲያቋርጥ እና ሌላ ትምህርት እንዲጀምር የሚል ዉሳኔ መተላለፉን አስረድቷል፡፡

ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ ያለበትን የአካል ጉዳት ተማሪዎች እና መምህራን ሊገናኙ በማይችሉበት የኮሮና ወቅት ላይ እና ተማሪ ቢኒያም ያለበት የአካል ጉዳት ሊታወቅ የቻለዉ ከህሙማን ጋር በተግባር በተገናኘበት አጋጣሚ መሆኑን በማንሳት ለተፈጠረዉ መጉላላት ሀላፊነቱን እንደሚወስድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዱአለም ደነቀ መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡

የተለያዩ ድጋፎች ለተማሪዉ እየተደረገለት ውሳኔው ከ7 ወር በፊት የጽሁፍ የተሰጠው ቢሆንም ሊቀበል አልቻለም ብለዋል ። የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሄራዊ ማህበር ደብዳቤ በመላክ ትምህርት ቤቱ ገለልተኛ እንዲሆን ተደርጎ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ውሳኔ ሊተላለፍ ችሏል። ተማሪው የህክምና ትምህርት ቤት ከገባበት ጀምሮ ጉዳዩ እስከተከሰተበት ድረስ ያለውን ሁኔታ የሚያጣራ ኮሚቴ ስራውን እንዲሰራ እንዲሁም በሙያው ላይ ሁለት እጅ እንዴት ያስፈልጋል የሚል ወርክሾፕ መካሄዱን ዶ/ር አንዱአለም ደነቀ ተናግረዋል፡፡

ኮሚቴ ያቀረበዉን ምክረ ሃሳብ መነሻ በማድረግ ውሳኔ መተላለፉንም ገልጸዋል:: ትምህርት ቤቱም እነዚህም ምክረ ሃሳቦች እና አለም አቀፍ የህክምና ስምምነቶችን እንዲሁም በ2018 የወጣውን ካሪኩለም በማጣቀስ ባሳለፈዉ ዉሳኔ ተማሪዉ በነርሲንግ ፣በሚድዋይፍ ፣በዴንታል፣ ሜድስን እና መስል ትምህርቶች ላይ ተቀባይነት የማያገኝ ሲሆን በክሊኒካል ፋርማሲ ፣ በራዲዮሎጂ እንዲሁም በላብራቶሪ መቀጠል እንዲችል ውሳኔ ተላልፏል።

በተጨማሪም ተማሪው እስከዛሬ በተማረው ብቻ ዩንቨርስቲው ባችለር ኦፍ ባዮ ሜድኪል ሳይንስ ዲግሪ ሊሰጠው በዝግጅት ላይ ሲሆን ተማሪ ቢኒያም ከተስማማ በቀጣዩ አመት መስከረም ላይ ማስተርስ ኦፍ ፐብሊክ ህልዝ መማር እንዲችል ይደረጋል ሲሉ ዶ/ር አንዱአለም ተናግረዋል ።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ትምህርት ከፍል በተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ ላይ በደረሰዉ መጉላላት ክስ እመሰርታለዉ ማለቱን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአካልጉዳተኞች ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ አሳልፈው አህመዲን መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡
ለበለጠ መረጃ ወደ 6624Ok ብለው ይላኩ
@MyDataInfo

2 years, 6 months ago

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሀገር አቀፍ የማስተዋወቂያ መድረክ እየተካሄደ ነው
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ያዘጋጀው የተለያዩ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን የማስተዋወቂያ መድረክ በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው።
በስነ-ስርአቱ ላይ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የተለያዩ ሞዴል ተሽከርካሪዎች ለእይታ ቀርበዋል።
ለበለጠ መረጃ ወደ 6624 Ok ብለው ይላኩ
@myDataInfo

2 years, 9 months ago

በአሜሪካ አሪዞና ግዛት የተከሰተው የሰደድ እሳት ከ700 በላይ ቤቶችን አወደመ
በአሜሪካ ሰሜናዊ አሪዞና ገጠራማ አካባቢ በተነሳ ንፋስ የተከሰተው የሰደድ እሳት ከ700 በላይ ቤቶችን ማውደሙ ተገለጸ።
በሰሜናዊ አሪዞና ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፍላግስታፍ ከተማ ወጣ ብሎ የተነሳው ፈጣን ሰደድ እሳት ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን እና ይህን ተከትሎም በአካባቢው የአደጋ ጊዜ መታወጁ ተመላክቷል።
የሰደድ እሳቱ ከ23 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ የሸፈነ ሲሆን ቢያንስ 24 ህንፃዎች ማውደሙ ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ ወደ 6624 Ok ብለው ይላኩ
@MyDataInfo

2 years, 9 months ago

አዋሽ ባንክ በኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ ተብሎ መመረጡን ተገለጸ ግሎባል ፋይናንስ ለ29ኛ ጊዜ በፈረንጆቹ 2021 ዓመታዊ የዓለም እና የየአገራቱን ምርጥ ባንኮች ምርጫ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ከአፍሪካ አህጉር የደቡብ አፍሪካው “የስታንዳርድ ባንክ” አንደኛ ምርጥ ባንክ ተብሎ ሲሰየም÷ከኢትዮጵያ ደግሞ አዋሽ ባንክ ተመርጧል።
ምርጫው የተካሄደው በ150  አገራት  ላይ ባሉ ባንኮች መካከል ሲሆን÷ 36ቱ ባንኮች ከአፍሪካ የተመረጡ መሆኑነሰ ለማወቅ ተችሏል።
ለበለጠ መረጃ ወደ 6624 Ok ብለው ይላኩ
@MyDataInfo

2 years, 9 months ago

በአዲስ አበባ መጪውን የፋሲካና የኢድ አልፈጥር በዓላትን ታሳቢ በማድረግ 1.5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት መቅረቡ ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ አደም ኑሪ ሁለቱን ሀይማኖታዊ በዓላት ታሳቢ በማድረግ አስቀድሞ በመደበኛ ኮታ ከተሰራጩ ምርቶች በተጨማሪ ለበዓሉ 1.5 ሚሊዮን ሊትሪ ዘይት ፣120 ሺህ ኩንታል ስኳርና 25 ሺህ 550 ኩንታል የስንዴ ዱቄት በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንደሚቀርብ ይፋ አድርጓል፡፡

ለበለጠ መረጃ ወደ 6624 ok ብለው ይላኩ @MyDataInfo

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana