ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago
ሰበር ዜና
የ802ኛ ኮር 58ኛ ክፍለጦር ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በመቶዎች የሞቱበትና የቆሰሉበት ታላቅ ድል ተሰራ::
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ራያ ቆቦ ዞብል እና ራማ ድንጋይ ቀበሌ እና አዲስ ቅኝ አሳምነው ክፍለጦርና ሃውጃኖ ክፍለጦር ከባድ ትንቅንቅ ላይ ናቸው::
ከትናትና ጥር 20/2017 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ እስከ ዛሬ ጥር 21/2017 ዓ.ም ምሽት ድረስ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ በዞብል በኩልና በድንጋይ ቀበሌ በኩል በሁለት አቅጣጫ ወደ ራማ በብረት ለበስ በአራት ዙ23 እንዲሁም በሞርተርና መድፍ በመካናይዝድ ታግዞ የወጣ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በአሳምነው ክፍለጦር እና በሃውጃኖ ክፍለጦር ከባድ የፀረ ማጥቃት ዉጊያ ተሸንፎ አዲስ ቅኝ እና ጎለሻን አድርጎ ገሚሱ ወደ ራያ አላማጣ ዋጃ ከተማ እና ገሚሱ ወደ ራያ ቆቦ ጮቢ በር ፈርጥጧል::
የምስራቅ አማራ ኮር1 አሳምነው ክፍለጦር እና ሃውጃኖ ክፍለጦር በጋራ በሰሩት በዚህ ተጋድሎ የ58ኛ ክፍለጦር ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በመቶዎች የሞቱበትና የቆሰሉበት ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: የቀድሞው 8ኛ ዕዝ የአሁኑ ሰሜን ምስራቅ ዕዝ 48ኛ 49ኛ እና 58ኛ ክፍለጦሮች እንዲሁም ከምስራቅ ዕዝ 12ኛ ክፍለጦርን ጨምሮ ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ ሆነው ተበታትነው ያለቁበት ሁኔታ ነው ያለው::
በዚህ እልክ አስጨራሽ የሞት የሽረት ተጋድሎ በጀግኖቹ ተጋድሎ ያለዉን ሁሉ ተጠቅሞ ሽንፈት የገጠመው ጠላት እንደተለመደው ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ የከባድ መሳሪያ ድብደባ እየፈፀመ ዉሏል:: ድንጋይ ቀበሌ አዲስ ቅኝ እና ኮባ ቀበሌዎች በከባድ መሳሪያ በሰው ህይወት በእንስሳቶችና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም ከራያ ቆቦ ሮቢት በምዕራብ በኩል ባሉ የገጠር ቀበሌዎች ንፁሃንን ኢላማ ያደረገው የከባድ መሳሪያ ድብደባ ሲፈፀም ዉሏል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ)
ጥር 21/2017 ዓ.ም
-----------------🔹🔹🔹-----------------
▪️YouTube= https://youtube.com/@ghiondaily?si=0OarH2pZE6jgN6Ebw
ሰበር ዜና ከወሎ
ኤቢሲ ቲቪ ፡-20/2017 ዓ/ም
የአማራ ፋኖ በወሎ ተጠናክሮ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ወልድያ ዙሪያ ከባድ ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::
የሰሜን ወሎ ዞን ዋና መቀመጫ ወልድያ ከተማና በዙሪያው በርካታ ተጋድሎዎችን እያደረገና በርካታ ድሎችን እየተጎናፀፈ የሰነበተው በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ ከትናትና ህዳር 19/2017 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ እስከ ዛሬ ንጋት ለ24 ሰዓት ቀንና ሌሊት ያለማቋረጥ በተደረገው ተጋድሎ 49ኛና 52ኛ ክፍለጦር የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ የጠላት ሃይል በርካታ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ይዞታወቹን ለጀግኖቹ አስረክቦ እንደተለመደው ፈርጥጧል::
በተጋድሎው አሳምነው ክፍለጦር አራት ሻለቆችና ሃውጃኖ ክፍለጦር ሁለት ሻለቆች የዞብል አምባ ክፍለጦር ሁለት ሻለቆችን ተጠባባቂና ደጀን አድርገው የተፋለሙ ሲሆን በጠላት በኩል ሁለት ክፍለጦር አሰልፎ በርካታ ተጋድሎዎች ተደርገዋል::
በፍልሚያዉም የጠላት ሃይል ከፋኖ መካናይዝድ በኩል የሚወነጨፍበትን ሞርተር መቋቋም ያቃተው ሲሆን ወልድያ ስታዲዮምና ማር ማቀነባበሪያው ላይ ያለ ጠላትም የሞርተር ጥቃት ተፈፅሞበት በርካታ ሙትና ቁስለኛ ሆኗል::
ተጋድሎው በበርካታ የወሎ ቤተ-አምሐራ ቀጠናዎች በበርካታ የደፈጣና የመደበኛ ዉጊያ ድሎች ታጅቦ እየተደረገ ያለ ሲሆን በቅርቡም የወረዳና የዞን ከተሞችን መቆጣጠርን ያለመ ተጋድሎ የሚደረግ ይሆናል:: በእስካሁኑ ተጋድሎዎችም ከራያ አላማጣ ዋጃ እስከ ወልድያና ደሴ የፌደራል መንገድ እየተባለ የሚጠራዉን መስመር ጨምሮ በርካታ የቀጠናው አካባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር ያሉና የህዝብ አስተዳደርም የተዘረጋበት ሁኔታ እንዳለ የሚታወቅ ነው::
-------------???-------------
▪️YouTube= https://youtube.com/@ghiondaily?si=0OarH2pZE6jgN6Eb
ትናንት በኦሮምያ ክልል በጅማ መስመር፣ ከአዲስ አበባ 70 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኝ ቆቦ ቀበሌ፣ 6 አዝመራ ለመሰብሰብ ወደ አካባቢው ያቀኑ የአማራ ተወላጅ የቀን ሰራተኞች፣ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የ4ቱ ሰዎች አንገት ተቆርጦ አውራ መንገድ ላይ መጣሉን፣ ሁለቱ ሰዎች ግን በጥይት እንደተገደሉና መንገድ ተዘግቶ እንደነበርም ምንጮች ገልፀዋል።
-------------???-------------
▪️YouTube= https://youtube.com/@ghiondaily?si=0OarH2pZE6jgN6Eb
የOMN ሚዲያ የዘር ጭፍጨፋ ጥሪ!
በብዛት አማራ የሚኖርበት በኦሮሞ ክልል ዞኖች ውስጥ ያሉ ቀበሌዎችን ለይቶ ህዝብን እንደ ፋኖ በመቁጠር እነዚህን አካባቢዎች በወረራ ይዘውታል ብሎ ዘገባ ሰርቷል።
በዚህ ዘገባ ላይ በኦሮሞኛ የተነገረውን ቃል በቃል ተተርጉሟል።
በኦሮሞ ክልል ቀጣይ በአካባቢ የሚኖረውን አማራ ለመጨፍጨፍ የልየታ ስራ አንዱ አካል ነው።
ዜናው ሲጀምር "የወረራው ዋና አላማ በኢትዮጵያዊነት ስም የኦሮሞ ህዝብ እና የማንነነቱ መገለጫዎችን በማጥፋት፣ ታላቋን ኦሮሚያ አፍርሶ፣ ታላቋን አማራ መገንባት ነው" ብሎ ይጀምራል፤
ቀጥሎም "ይህም በጉልበት እና በነፍጥ እያደረጉ ነው። የአማራው ኃይል ወይም ፋኖ በወረራ የያዟቸውን ቀበሌዎችን እዘረዝራለሁ" በሚል ይጀምራል።
ምስራቅ ወለጋ ዞን የተወረረው በሚል የተጠቀሱ አካባቢዎች:- ደግዳአያና፣ ክረሙ፣ ልሞ፣ ጉቶ ጉዳ፣ ገንደጉተ ወረዳዎች
ከክረሙ ወረዳ ውስጥ ዋቲን፣ መረገጭረና፤ ጫፌ ሶራና፤ ጫፌ አናን ቀበሌዎች እና በተጨማሪ 13 ቀበሌዎች በዚሁ ሃይል ተይዘዋል ይላል። ቀጣዩ ደግሞ ሆራጉዱሩ ወለጋ ሲሆን፦ ጃርቴጃረገማ፤ አሙሩ ፤ አቤዶጎሮ የተወረሩ ወረዳዎች ናቸው ይላል።
ከአሙሩ ወረዳ ውስጥ ቾኮር ፤ ኩርቾቾ ጭረት፤ ሉማ፤ ሱሞዳሙ፤ ሀራርሳሞ፤ ሀራርጃር እና የሀሮ ከተማን ጨምሮ 16 ቀበሌዎች በዚሁ ሃይል ተወሯል። በምስረቅ ወለጋ እና ሆራጉዱሩ ዞኖች ውስጥ ካሉት ቀበሌዎች ውስጥ 44 ቀበሌዎች ከኦሮሚያ ክልል መንግስት እጅ በመውጣት በፋኖ ሃይሎች ተይዟል።
ከምስረቅ ሸዋ ዞን የፈንተሌ ወረዳ እና ቦሰት ወረዳ በዚሁ በወራር ሃይል ተወሯል ፤ ከፈንተሌ ወረዳ ውስጥ እዶጎዶ ፤ እዶቀሎ፤ ቦርቦር መልከጭሎ እረንቡቴ ፤ አሮአረም ፤ ኡለገ፤ ጥንጅ፤ ቆኜ ፤ ምንጭ ፤ ዶዶትጉዶ ሀሮሬሳቀለ፤ ሀሮሬሳበለ፤ ፉኛንዋጋዮ፤ ፋኛንቦሬሳ እና ቆርኬ ቀበሌዎች ሲሆኑ ከቦሰት ወረዳ ኮይሾ፤ ምንዳ፤ ገረዳቀ፤ አንዶዴ፤ ገርባአድ፤ ሴራኤ፤ ቦርትቻ፤ መቅላ፤ ሴራቡብሳ ቀርሳ አባቡኔ ፤ ዱብደ ደሌቻ ጨዠ፤ ጫላላቀ፤ ፎሶን እና ቂሌአረባ ቀበሌዎች በዚሁ ወራሪ ተወሯል።
ከሰሜን ሸዋ ወረዳዎች የቅባብት ወረዳ እና የደራ ወረዳዎች በዚህ ወራሪ ተይዟል። ከደራ ወረዳ ውስጥ ዴኙማቤሶ፤ ጅሩዳዳ፤ ቱት ኦልጎና ጫፌ፤ ሰረንቁላ ፤ ሳለይሽ፤ መከፍተማናዮ፤ ወሬማናዮ ፤ በዬት ፤ ማናለጎ፤ ገብሮ፤ በሬሳ፤ ሆነቦናያ ቀበሌዎች በዚህ ሃይል ተወሯል።
በሚል በOMN ሚዲያ ግልጽ የዘር ጭፍጨፋ አዋጅ ታውጇል።
ይሄን ግልጽ ወረራና አዋጅ ለአካባቢው ነዋሪዎች ለዓለም አቀፉ ነዋሪዎች መረጃው እንዲደርስ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
ሙልጌታ አንበርብር!
-------------???-------------
▪️YouTube= https://youtube.com/@ghiondaily?si=0OarH2pZE6jgN6Eb
√#የ3ኛ(የጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር ዛሬም እንደተለመደው የአብይን ጭፍራ ሰራዊት በከበባ ሲያጭድ ሲወቃው ውሏል።ዛሬ ሞት የጠራው የብርሃኑ ጁላ ጦር ከተለያዩ ቦታዎች አሰባስቦ ወደ አይደፈሬዎች መንደር ፋግታ ከተማ ቢመጣም #ዋዝ ላይ ሲለበለብ ውሏል።
በውጊያው
#፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ (ያፋግታ ለኮማ ወረዳ
#ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ብርጌድ(ዳንግላና አካባቢው)
#ዘንገና ብርጌድ(ቲሊሊና አካባቢው) በጥምረት የአብይን ገዳይ ቡድን እያጨዱ ሲከምሩት ውለዋል።
ከ120 በላይ ጠላት ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።ጠላትን መልሰው በመጣበት እግሩ ሰደውታል።የፋኖን በትር ያልቻለው የጠላት ኃይል 3 ንጹሃንን ጤፍ እየወቁ በነበረበት ሰዓት በግፍ ረሽኗል።
√#የ2ኛ(ተፈራ ዳምጤ)ክፍለ ጦር አካል የሆነው የጎንጅ ቆለላው #ንስር ብርጌድ 3ኛ ሻለቃ ከጎንጅ ከተማ ወጥቶ ወደ ዴጋንሳ ቀበሌ ሲንቀሳቀስ የነበረን ጠላት በደፈጣ ልኩን አግኝቶ የአንድን የፋኖ አመራር ቤት አቃጥሎ ተመልሷል።
√#የ5ኛ(የራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም) ክፍለ ጦር አካል የሆነው ሁሌም ባለድሉ #አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ቢተው(ማንኩሳ) ሻለቃ ማንኩሳ ከተማ ላይ የነበረን ጠላት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ከሞት የተረፈው ጠላት እግሬ አውጭኝ ብሎ በመፈርጠጡ ማንኩሳ ከተማን ከጠላት ነፃ ማድረግ ተችሏል።
በሌላ ግንባር ይሄው አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ፍኖተ ዳሞት ሻለቃ ከብርሸለቆ፣ከፍኖ ተሰላምና ከማንኩሳ አወጣቶ አሰሳ ላይ የነበረን የጠላት ኃይል #ክሊኒክ(ርግብ) ላይ ጠላትን ረፍርፈው ሙትና ቁስለኛውን አሸክመው መልሰው ሰደውታል።
ሰሞኑን ወደ የቦቅላ ንዑስ ወረዳ በ4 አቅጣጫ ሂዶ የነበረው ጠላት በጀግኖቹ የ7ኛ ክፍለ ጦር አናብስቶች ተመቶ ሲመለስ የቦቅላ ከተማ ላይ ካሉ ባንኮች ለጥበቃነት ሲያገለግል የነበረን የጦር መሳሪያ ዘርፎ ወጥቷል።
ከፀደይ ባንክ 3 የጦር መሳሪያ
አቡና ባንክ 2 የጦር መሳሪያ
ከንግድ ባንክ 2 የጦር መሳሪያ እንዲሁም ከየቦቅላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 1 የጥበቃ መሳሪያ በድምሩ 8 የተቋማትን መጠበቂያ መሳሪያ ወስደዋል።
ይሄን መሳሪያ ከወሰዱ በኃላ ከፋኖ የማረኩት ለማስመሰል እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
--------------???-------------
▪️YouTube= https://youtube.com/@ghiondaily?si=0OarH2pZE6jgN6Eb
ደብረማርቆስ
የብልፅግና ጉድ
የኔዉብ አደራዉ ትባላለች ደብረማርቆስ መስከረም ሆቴል እስተናጋጅ ነች ነገርግን ብልጽግና ሃምሳ አለቃ ማረግ ተሸክማ የመከላከያ አባል ሆና ከች ብላለች።
የፈረሰው ብልጽግና ተፈጥሯዊ ስሪት አማራን ከነ ምልክቱ ከምድረ ገጽ ማጥፋት ነው።ይህን ተፈጥሮ ይዞ ወደ ስልጣን የወጣን ደማዊ ጠላት አትግደለኝ በማለት ሞትህን አትገታውም፣እታፈናቅለኝ በማለት ስደትህን አታቆመውም፣ መንፈሳዊና ቁሳዊ ሀብቴን አታውድም በማለት ምልክትህን አትታደገውም!!!አንተን ከነ ምልክትህ ማጥፋት ስልጣን ላይ የወጣበት ተቀዳሚ አላማው ነው!!!ሁሉ ነገር የሚቆመው በመሰልጥን፣ በመደራጀት፣ በመታጠቅና ገጥመህ በማጥፋት ብቻ ነው!!!ከንግስና ማማው ተፈጥፍጦ ወደ ሽፍትነት የወረደው ደማዊ ጠላት ሀይል በዲማ ያደረሰው ውድመት ከዚ ተፈጥሮው የሚቀዳ ነው።የወደመው ሙዚየም የሁለት ነገሮች ውጤት ሲሆን
1ኛ መለኮታዊ ግኝት
2ኛ የአማራው የአዕምሮ ውጤት የእጅ ስራው ሆኖ የአማራን ከትላንት እስከ ዛሬ አዕምሯዊ ምጥቀትና መለኮታዊ ቁርኝት የሚገልጽ ሙዚየም ነበር።ደማዊ ጠላቶቻችን ያልተረዱት ነገር መለኮታዊ ውጤቱ የሚጠፋው በራሱ በሰጭው ክርስቶስ ሲሆን የአማራው የአዕምሮ ውጤቶች የሚጠፉትም አማራነት ጨርሶ ሲጠፋ ብቻ ነው!!!እኛ ደግሞ ትውልዱን የበለጠ ከራሱ ጋር፣ከነባር እውቀትና ማስተዋሉ ጋር እያስታረቅነው ነው!!!ፋሲልን ወደ ከገነቡ፣ላሊበላን ወደ አነጹ አባቶቹ ጥበብና ማስተዋል እየመለስነው ነው!!! ከአባቶቹ ጥበብ ላይ የራሱን እሴት እየጨመረ ዘመኑን እየዋጀ የሚሄድ የራሱን አዲስ ስነ ልቦናዊ ውቅር ይዞ የተነሳ ትውልድ እየፈጠርን፣ለዓለም አዲስ የአኗኗር ፍልስፍና ይዞ የሚገለጥ ማህበረሰብ እየገነባን መሆናችን አልተረዱም!!!እና ይህ ትውልድ ከነጻነቱ ማግስት ሙዚየሙን በራሱ መልክ መልሶ ይገነበዋል!!!
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!!
እሸቱ ጌትነት በላይ
የአማራ ፋኖ በጎጃም የአደረጃጀት መምሪያ ሀላፊ።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago