ግጥምን በዜማ📚🎻

Description
ሰላም ለእናንተ ይህ የናንተው ቻናል "ግጥምን በዜማ" ነው። በዚህ ቻናል የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን ያገኛሉ።

ለማንኛውም አስተያየት @Firew1221

ግጥም መላክም ይቻላል /
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago

3 months, 2 weeks ago

ፈረስ ሳትፋቀር ለአህያ ታጭታለች
በቅሎም ባባቷ አፍራ እናቴ ትላለች
እርግጫ ንክሻ ትጀማምራለች
ከማን ወርሳ እንጃ አመል ታመጣለች

አለንጋና ጩኸት ሲያፈራርቅባት መግራት ይሉት ጣጣ
አመል ትጠፋለች ሰይጣኗ ተቀምጣ
ከዚህ ሁሉ ጣጣ
ፈረስ አትገደድ አህያም ለአህያ
በግርፍያና ጩኸት አይደምቅም ገበያ።

     ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

5 months, 1 week ago

ሰላም፣ሰው፣ጤና ሁሉም ሞላልኝ። ነገር ግን አንቺ ጎደልሽ። ያንቺ መጉደል እኔን አጎደለኝ። ዱኒያ ብትሞላ እኔ ከጎደልኩኝ ምን ሊረባኝ?...ታስታውሻለሽ ለመጨረሻ ጊዜ ስንገናኝ ህመማችንን በምን እንደብቀው ስልሽ የሰጠሽኝ ምላሽ "አንተ በፅሁፎችህ እኔ በጥርሶቼ" እንደዛ ስትዪኝ አምኜሽ ነበር። ሞከርኩ ሞከርኩ ግን አልሆነልኝም። ህመሜን ለመደበቅ ፅሁፎቼ በቂ አልሆኑም። አንቺስ እንዴት ነው ህመምሽን በጥርሶችሽ መደበቅ ሆኖልሻል? ከሆነልሽ እባክሽ ነይና አስተምሪኝ። ጥርሶቼ እህል ከማላመጥ የዘለለ ፋይዳ የማይሰጡ ከሆኑ ሰነባበቱ። አንድ አፍታ ከባልሽ እቅፍ ተነጠይና ሳቅን ካልሆነም ፈገግታን አስለምደሽኝ ከደረቱ ትሰየሚያለሽ። መቼስ ለኔ ስትይ ቅፅበታዊ ብርድ ቢመታሽ ቅሬታሽ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ሀኑኔ የኔ ህመም የኔ ጤና የኔ መሪር የኔ ጣፋጭ ሀኑኔ የኔ ሳቅ የኔ ሀዘን የኔ ጉድለት የኔ ሙላት እንዴት ውብ አርጎ ፈጠረሽ? እንዴትስ የምታሳሺ ነሽ? እንዴት የማትረሺ ሆንሽ? ሀኑኔ ህይወቴ ሀኑኔ ሞቴ።

    ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

5 months, 4 weeks ago

በራፉ አልተዘጋም ገርበብ ብሎ ነበር። በደከመ ሰውነት ከፍቶት ሲገባ እናቱ ምስር ስትለቅም አገኛት። እግሯ ስር ወደቀ፤እናት አልተደናገጠችም አዘነች እንጂ ነገሩ ገብቷታል። ምስሩን ከጎኗ ካለ ወንበር ላይ አስቀመጠችም። ደገፍ አርጋው አንስታ ጭንቅላቱን ጭኗ ላይ አስቀምጣ ፀጉሩን ትደባብሰው ጀመር ልክ እንደ ልጅነቱ። ....አለቀሰ፤ አላባበለችውም። በማባበል የሚድን ህመም እንዳልሆነ ታውቃለች። ቃል አወጣ። አ...አ...አገባች እኮ። ምንም አልተናገረችውም። ውስጡ ያፈነውን አውጥቶ እንዲቀለው የፈለገች ይመስላል፤ ባይቀለውም። ....ዳርኳት እያየኋት ችቦ አይሞላም ወገቧ ብዬ ብር አምባር ሰበረልሆ ጨፍሬ። አናስገባም ሰርገኛ ሲባል እውነት የማይገባ መስሎኝ አምላክ የውስጤን አይቶ ረዳት እንደላከልኝ ተደሰትኩ፤ ሰርገኞቹ መልአክ ናቸው አልኩኝ። ትንሽ ተጋፉና መሳሳቅ ጀመሩ፤ ሙሽራው የጫጉላው ንጉስ ገባ። እንዴ አምላኬ ሆይ ምነው ተስፋ ሰጥተህ ነሳኸኝ? በወደደ ይቀለዳል? በምን ሀጥያቴ? አምላኬን አማረርኩ። መልአክ የነበሩት በቅጽበት ጋኔል ሆነው ታዩኝ፤ እየተጠቋቆሙ የሳቁብኝ መሰለኝ። ህመሜን ታማው ይሆን ብዬ ተመለከትኳት አይኖቿን ከአይኖቼ ታሸሻቸዋለች፤ ጥርሷን ማሸሽ አልቻለችም ነበር። አየኋቸው ደስተኛ ነበረች አይኖቿን ባላያቸውም። በድንገት እንባ ከአይኖቿ መፍለቅ ጀመረ። ሀዘኔን አዝናለች ይኸው አነባች አልኩኝ ለራሴ፤ በሰዎች መሀል ብቸኛ ሆነናል የሚረዳን አጣን እንጂ። አንድ የማላውቀው ሰው "ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ" ሲል ሰማሁት። እውነት ነው ሲዳሩ እንጂ ሲያገቡ የሚያለቅሱ ማን ናቸው? እንዴትስ ቢሞኙ? ከጭኖቿ ቀና ብሎ እማ...አቤት ልጄ...በቃ አገባች አትደውልልኝም ድምጿን አልሰማውም አትደውልልኝም እንደ ድሮው አባቴ ብላ አጠራኝም እኔም ሀኑኔ እያልኳት ደስታዋን ማየት አልችልም ናፍቀኸኛል አትለኝም....እማ ወሰዷት እኮ። እናቱ ስታዳምጠው ቆይታ ልጄ ልብህን አደንድነው። እነዛ በወደዱት የተወደዱ የሚወዱትን ያገኙ ምነኛ እድለኞች ናቸው።....ልብህን አደንድነው ልጄ። በረጅሙ ተነፈሰች ዝምታ ሰፈነ....።

አፈቀራት ተከልክሎ
ይኸው ዳራት እልል ብሎ
አንቺን ይንሳኝ ምሎ ነበር
ልታገባ ቆሞ ሊቀር።

   ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

6 months ago

በጨዋታቸው መሀል...ሀኑኔ...ወዬ...ብር ባይኖረኝም ታገቢኛለሽ?...ሳቋ ደበዘዘ፤አንገቷን ደፋች። ለጥያቄው ዝምታዋ መልስ ሆነ ግና ዝምታዋ ብዙ ያወራል። ሀሳቡ ተደበላለቀበት፤ ተነስቶ መንገዱን ጀመረ። አልጠራችውም። ቆይ አንዴ ላስረዳህ አላለችውም። የምታስረዳው ነገር እንዳልሆነ ታውቃለችና። ሊወቅሳት አልፈለገም ቤተሰቧ ጋር የምታገኘውን ምቾት እሱ ሊሰጣት አይቻለውምና። ከእናንተ ውስጥ ምቾቱን ለፍቅር ሲል የሰዋ እስቲ ይውቀሳት። ፍቅር የተራበ ሆድን አይሞላም የታረዘ ገላን አያለብስም የተጠማ ጉሮሮን አያርስም። ፍቅር መንፈስ ነው። የማይታይ የማይዳሰስ የማይጨበጥ በምናብ ያለ የሀሴት ምንጭ የመኖር ሚስጥር የተግባቦት ቀመር የመፈላለግ ጥልቀት። እሷ ንግስት ንብ ፈላጊዋ ብዙ በመልክ ብትሻ በስነምግባር ቢያሰኛት ሀብትማ የግሏ እሱ እሱ ግን ተራ ሰራተኛ መኖሩ የማንም ብስራት ያልሆነ ቢሞት ሞቱ የማንም ሀዘን የማይሆን ታዲያ ስለምን እሱ የመጀመሪያ ምርጫዋ ሊሆን ይቻለዋል። በእርግጥ ማንም እንደሱ አይሆንላትም እሱም እንደ ማንም አይሆንላትም። መንገዱን ቀጠለ በጨለማው ሰፈር በጣም በሚያስፈራው። ፀሀይ ከጠለቀች ማንም ዝር ከማይልበት፤ እሱም ከዚ በፊት ያልደፈረው ነገር ግን ዛሬ ምንም ሆነበት። ለካስ የሰው ልጅ ፍረሀት ውስጡ የሚጫረው ተስፋ ሲኖረው ነው፤ የሚወደው ነገር ህይወቱ ውስጥ ሲያገኝ ግና እሱ ያንን ተነጥቋል። ጨለማው ለሱ ምንም ሆኗል። መኖሬ ትርጉም ይሰጣታል ያላት ለፍጡራን ቀሎ ለእሷ የከበደ ማንነቱ ወድሟል። ታዲያ ስለምን መኖሩን ይኑረው? ፍርሀትንስ ይፍራው? ልቡ ለጨለመ የመንገድ ብርሀን ምኑም ነው። የልቤ ብርሀን...እኔነቴን አለመለመችልኝ ያላት...እሷ...ዝም አለች.....

ከበትር የላቀ የማይቀል ከቃል
ለካ ለተረዳው ዝምታም ይሰብራል.... መንገዱን ቋጨው የጨለማውን....ወደ ሌላ ጨለማ....

ቆመሽ እንዳትቀሪ ቆሞ መቅረት ለኔ
ላንቺ ጀምበር ወጥታ ምሽት ይሁን ቀኔ
የሰርግሽ 'ለት ጥሪኝ ተረረም ተረረም
ባላገባሽ እንኳን ላጨብጭብ ግዴለም።

ተፃፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

8 months, 3 weeks ago

....ረሳሁት ያልኩት ነገር በጊዜ ቆይታ እየተመላለሰ ያንገዳግደኛል። በስንት ፍጭት ገነባሁት ያልኩት ማንነቴን እንክትክቱን ያወጣዋል። እራሴን የማዘዉ እኔ ልሁን አልያም ሌላ አንዳች ሀይል አላውቅም። ግራ መጋባት ውስጥ ነኝ ምክንያቱም ነኝ ብዬ የማስበውን አይደለሁምና። እሳቤዬ ሌላ ድርጊቴ ሌላ። አለኝ ብዬ የማስበው ማንነት የለኝም ያለኝን ማንነት አልፈልገውም። ምን እየተካሄደ እንደሆነ መረዳት አልቻልኩም። ማነኝ? ምንድነኝ? አእምሮዬ   ያዘኛል? ወይስ እኔ ነኝ የማዘው? የሱ ነኝ? ወይስ እሱ የኔ ነው? አላውቅም። የማውቀው ነገር ቢኖር ያለፍቃዴ የሚመራኝ ከኔ በተቃራኒ መስመር ላይ ያለ ማንነት እንዳለ ነው። እውነቱን ለመናገር ውስጤ ካሉት ማንነቶች የትኛው እኔ እንደሆንኩ አላውቅም። ብቻ........ሌላውም እንደኔ ግራ ገብቶት ይሆን?........ከሀሳቧ ተመለሰች። ያገባደደችውን ምግብ ጨርሳ አስተናጋጁ ሂሳብ እንዲያመጣላት በእጇ ምልክት ሰጠችው፤ አመጣላትም። አየችው እንደገና ሌላ ሀሳብ....ለኔ ድርጊት ለምን ሌላው ሂሳብ ይሰራልኛል? ያገኘሁት እና የምከፍለው ዋጋ ሚዛናዊ ይሁን አይሁን ከኔ በላይ ማን ሊያውቅ ይቻለዋል?......በሀሳብ ውስጥ ሆና ከቤቷ ደረሰች። ሀሳቧን ባትደርስም.......

     ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

8 months, 3 weeks ago

ልብሷን እየለባበሰች ልሄድ ነው አለችኝ። ዝም አልኩ በብዙ መሄድ ውስጥ መምጣት እንዳለ አልተረዳችም.....አካሌን ብትርቀዉ መንፈሴ እንደሚከተላት ማመን አልፈለገችም.....ጠዋት ነበር ለዛም ይሆናል መሄድ የፈለገችው። ምናልባት እስኪመሽ.....ምናልባት እድሜዋ እስኪገፋ.....ምናልባት ውበቷ እስኪነጥፍ....ምናልባት......ወጣች በሩን ዘጋችው የቤቱን አልነበረም። ሌላ እንዳይገባ...ሲመሽ ጠብቃ ልትመጣ....

ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago