ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
መካሪ ሁሉ ጨዋ አይደለም። በምክሩ ውስጥ አብዝቶ ስለፅድቅና የሚነግርህ ሰው ፃድቅ ነኝ እያለም አይደለም። በተሸወደበትና በወደቀበት ነገር ውስጥ የከፈለውን ዋጋ እየነገረህ ሊሆን ይችላል። ነፍሱን ማሰር በተሳነው ጉዳይ ላይ "ይህ ነው ክፈተቴ አንተ ግን በዚህ በኩል ነፍስህን አሸንፋት" ይሆናል የሀሳቡ ውጥን።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
በመጨረሻም ዱንያ ከቤተሰብህ የበለጠ ውድ ነገር ልትሰጥህ አትችልም። ዱንያን በሙሉ ብትዞራት ከነርሱ የበለጠ ዋጋ ያለውን ነገር አታገኝም። ደስታን ከነርሱ ጋርና በነርሱ ውስጥ አብዝተህ ታሸተዋለህ፣ ትኖረዋለህ። ቤተሰብ ከዚያም ቤተሰብ ከዚያም ቤተሰብ።
ከጊዜ ጋር… የእድሜያችንን እኩሌታ ስናልፍ… ወደ አመሻሽ ላይ እንደድሮው ሁሉንም ነገራችንን ለሰው አንናገርም። መጥፎ የሆኑ ስሜቶቻችንን የመደበቅ ትልቅ ችሎታ ከወዴት እንደመጣ ሳናውቀው ይቆጣጠረናል። እንደጉድ እንችላለን። በጣም ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ምንም ያልሆንን ፅኑ መስሎ መታየት እንዴት እንደሆነ እንማራለን። አይገርምም? ወላጆቻችን የራሳቸውን ችግር ሲነግሩን እንኳን በአስተውሎት እናደምጣለን። የኛን ጉዳይ ሳንተነፍስላቸው። እንድናለቅስ የሚያስገድዱን ነገሮች ተፈጥረው እንኳን ፈገግታ ለመላበስ እንውተረተራለን። ፈገግታ የሚያሸነፈው የማይደረመስ የእንባ ግድብ ከየት መጣ? አቤት የአመሻሽ ውበት…
"ዱዓዬ እጣፈንታዬን ለመቀየር በቂ አልነበረም ማለት ነው?" የሚሉ ከርታታ ልቦች አሉ። በህይወት ልዩ መልኮች እንቅፋት የተመቱ ልቦች። በህመም፣ በእዳ፣ በትዳር አለመሳካት፣ በሁኔታዎች መዘበራረቅና ግራመጋባት የሚዋኙ ስሜቶችም እንዲሁ። ምን ያህል ጌትዬን ተለማምጠናል? … ከአለሙ ሁሉ እስኪያስቀድመን፣ ከጠያቂዎች ሁሉ እስኪመርጠን። እርሱ የሚለማመጡትን ይወዳል። የሚወደውን ደግሞ ይመርጣል።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
አቡበከር የቢላልን ያህል ድብደባ አላስተናገደም። ድህነትም እንደአቡዘር አልፈተነችውም። ሰይፎች የኻሊድን ያህል ታዘውት በካሃዲያን አንገት ላይ አላሳረፈም። ግን ከሁሉም የሚበልጥ ሰሓባ ነበር። ለነብዩ ልቡን ሰጥቷል። እንዳሻዎት ያድርጉኝ ብሏል። የልብ ሰው!!
በዙሪያህ ያለውን ሁሉንም ነገር ለመረዳት አትሞክር። አንዳንድ ጉዳዮችን አለመረዳት ነው የሚሻለው። አንዳንዴ ነገሩን በመረዳትህ የሚመጣብህ የልቦና ቀውስና አንደበትህ ላይ የሰዎች ስም መመላለስ ብቻ ነው። … በቃ ምናገባኝ ማለት አስፈላጊ ነው። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ!
ሰዎችም እድል ናቸው። በሆነ አጋጣሚ የምናገኛቸው ወይንም የምናጣቸው። ሁል ጊዜ በነበረበት የምናገኘው አይኖርም። ምናልባት ዛሬ ለኛ የተገባ ሰው… ነገ ላይሆን ይችላል።
ድንገት አልነበረም። የቀደር መስመር ላይ ነው የተገናኛችሁት። በህይወትህ ላይ የሆኑ ትምህርቶችን ሰጥተውህ ያለፉት ሁሉ(ምናልባትም ክፉዎች)፣ ከዋክብቶች ሲሸሹህ ሰማይህን ሊያበሩልህ የመጡት ምርጥ ሰዎችህ ሁሉ… ለነርሱ የተወሰነላቸው የህይወት ዓለም ከተወሰነልህ የህይወት ዓለም ጋር እንዲነካካ ተፅፏል። ሌላ አይደለም።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana