ሚኪያስ ፈይሣ

Description
ግጥም
ወግ
ሀሳቦች
ልቦለዶች
🤝 @mika145
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 weeks ago

ቸኮሌት በጣም ትወዳለች። ልክ እንደ ህፃን ልጅ ነው የሚያደርጋት። እሷን ላገኝ ካሰብኩኝ የግድ ቸኮሌት ኪሴ ውስጥ መኖር አለበት። እንደ ድንገት እረስቼ ብሄድ እንኳን የግድ ተመልሼ ሚኒ ማርኬት ፈልጌ እሷ የምትለው አይነት ቸኮሌት ( waffers የሌለው full chocolate ) ገዝቼ መመለስ አለብኝ። ብዙ ጊዜ የማትፈልገው አይነት ቸኮሌት ይዤ ሄጄ የምሯን ተናዳብኛለች።
"ይሄ ሁሉ ለቸኮሌት ነው?" እላታለው።
"ለምንድነው ሁሌ የምነግርህን የማትሰማኝ .. ለምነግርህ ነገር ትኩረት ስለማትሰጥ እንጂ ከባድ ነገር ሆኖ አይደለም" ትለኛለች። ከዛን ከንደገና ልዩነታቸውን ማብራራት ትጀምራለች። የማትጠራው አይነት ስም የለም። ሰው እንዴት ይሄን ያህል ለቸኮሌት ይጨነቃል? ። ያው እንደተለመደው ስታብራራልኝ አይን አይኗን አያታለው። ምንም የሰማሁት ነገር ባይኖርም ዳሩ። ብዙ ጊዜ ወደድኩት ያለቺኝን ቸኮሌት ስም ሸምድጄ ሌላ ጊዜ ልገዛ ስሞክር አላገኘውም። የሆነ ጊዜ እንዳጋጣሚ የገዛውትን ቸኮሌት ደግሞ በጣም ከመውደዷ የተነሳ ልጣጩን ፎቶ አንስታ በየሱፐር ማርኬቱ ስታዞረኝ ከርማለች። ለሌላ ነገር እኮ ደንታ የላትም። በላች አልበላች ጉዳዩዋ አይደለም። እኔ እንደ ጅብ ብቻዬን ሳግበሰብስ ቸኮሌታም እየጎመጠች አይን አይኔን ታየኛለች።
"ምንድነው ቤብ?"
"የቸኮሌት ከለር እኮ ነው ያለህ"
"ቸኮሌት የሚባል ከለር የለም ጥቁር ነኝ"
"ምናልባት ጣዕምህ ይሆናል ቸኮሌት ቸኮሌት የሚለኝ"
"ቸኮሌት በጎረስሽበት አፍሽ ስለምትስሚኝ ነው"
"ጠረንህ ግን እኮ እሱን እሱን ነው የሚለው"
"የገዛሺልኝ ስኘላሽ ነዋ ቤብ"
" ድሮም አንተ ፍቅር አይገባህም .. የውሸት ነዋ ከኔ ጋር የምታስመስለው " እምባዋን አቀረረች። እናቱ ገበያ ስትሄድ እያየ ለማልቀስ እንደፈራ ህፃን ነው አኳኋኗ።
" አይደለም የኔ ጣፋጭ" በአንድ እጄ ሲናደድ የሚቀላ ፊቷን ዳበስ አደረኩት።
" ምንለማግኘት ነው ማስመስለው? .. ብቻ ይሄ የቸኮሌት ፍቅርሽ ከመጠን አለፈብኝ ለዛ ነው"
" ያንተን ስሜት አልባነት በርሱ አታሳብ " ብላ እጄን ከጉንጯ ላይ ገፈተረችው። ግራ ግብት ብላኝ ትኩር ብዬ እያየዋት ነው እጇ ላይ የነበረው ቸኮሌት ማለቁን ያስተዋልኩት። "ok" አልኩና በግራ ኪሴ ይዤው የነበረውን መጠባበቂያ ላወጣ እጄን ላኩት። አልነበረም። ለካ ቅድም ታክሲ ውስጥ ስታለቅስ የነበረችውን ህፃን ልጅ አባብዬበታለው።
እንግዲህ አፏን የማጣብቅበት ቸኮሌት መግዣ ቦታ እስከማገኝ ድረስ እንደፈረደብኝ ንጭንጯን ቁጭ ብዬ ልጠጣ። እድሌ ነው😏

@mikiyas_feyisa

3 weeks, 5 days ago

ሁሉም ውሸት ነው
ተረት ተረት
ልበ ደካሞች ድነው ቢያልፉም
ሀኪማን ሆዬ ቆዳን እንጂ
የተቀደደ ፡ ልብ አይሰፉም!

@mikiyas_feyisa

4 weeks, 1 day ago

ተታግለናል እጣ ፈንታን
አብሮ የመሆን ተስፋ እንዳለው፥
እንዳይቆጭሽ ስንለያይ፡
ሞክረሻል
ሞክሪያለው!።

@mikiyas_feyisa

3 months, 2 weeks ago

አስጠነቆልኩባት

ዱር ገደል ወርጄ
ጠንቋይ ዘንዳ ሄጄ
መስተፋቅር ብቻ
ለሚጠነቁሉ.. ለታወቁ አባት
ጠጉሯን ይዤ ሄጄ.. አስጠነቆልኩባት

የታባቷንና
ለምን እኔ ብቻ ከርሷ መሄድ ማልተው
ለምን እኔ ብቻ ሳያት ምደሰተው
ለምን እኔ ብቻ በፍቅሯ ምቃጠል
ለምን እኔ ብቻ
ጡት እንዳየ ህፃን ላዩዋ ምንጠለጠል
ለምን እኔ ብቻ የ'ርሷም ዕጣ ይድረስ
የካበችው ገላ ከእግሬ ስር ይፍረስ
ለምን እኔ ብቻ
ለእርሷ ምንገበገብ በናፍቆት ምቀጣ
እርሷም በተራዋ ተንቀልቅላ ትምጣ

የታባቷን
በምዕናቤ እየሳልኩ
በፍቅሬ ተቃጥላ
ወደኔ ስትከንፍ ወደኔ ስትበር
እንደ ነብይ ቃል እጠብቃት ጀመር
ብጠብቅ .. ብጠብቅ
ብጠብቅም በጣም
ናፍቆቷ ነው እንጂ አካሏ አልመጣም
ጠንቋዩን አምኜ
ጠብቂያት
ጠብቂያት
በመጠበቅ ብዛት ጉልበቴ ቀለለ
ከመቅረቷ ይልቅ
በጠንቋዩ ስራ ቆሽቴ ድብን አለ

ወደ ጠንቋዩ ቤት
መብረር እየቃጣው እግሬ ተራመደ
እቅጩን ልነግረው
የርሱ ጥንቁልና ቁብ እንዳልፈየደ
ልጣላው ወስኜ
ከቤቱ ደርሼ አንኳኳው የምሬን
አልመልስም ካለ
"መስተፋቅር" ብሎ የበላኝን ብሬን

አልከፈት ብሎኝ
በርግጄ ስገባ ..ትግስቴ ተሟጦ
ጠንቋዩን አስተዋልኩ
ቆርጬ ያመጣሁት ፀጉሯ ላይ አፍጦ

አይ አለመታደል
ይህ ታታሪ ጠንቋይ
ስራን ከምንም ላይ ተነስቶ የፈጠረ
ፀጉሯ ጦስ ሆኖበት
ጥንቁልና ትቶ ከምንም ላይ ቀረ

"ፍቅሯ አደንዝዞት
እሷን አገኝ ብሎ
ጠንቁሎ ጠንቁሎ ..ከመጠንቆል ብዛት
መጠንቆያው ሲኒ..የሲኒ ጨብጥ ያዛት"
አያለ ይታማል

እኔ ግን እኔ ግን
የርሷ አለመምጣት
የብሬ መበላት ..ቅንጣቱን ሳይከፋኝ
እርሱን ማባበሉ ..በጣሙን አለፋኝ

ፍቅሯ ተምታቶበት
ፍቅሯ አጃጅሎት
በእርሷ ዘንዳ ሚኖር ሲሆን ቋሚ በድን
አማራጭ ስላጣን
ሌላ ጠንቋይ ጋራ ለማስጠንቆል ሄድን

------------------
@mikiyas_feyisa
(11-09-2015)
የቆየ ነው ደሞ😁🫡

3 months, 4 weeks ago

እንደ ተበዳይ አታልቅሺ
ለበደል ነበር አመጣጥሽ
ፀባይ አመልሽን ማጣፈጥሽ
እስስት ውስጥሽን መለወጥሽ

እንደ ንፁህ ሰው "እሪ" አትበይ
ባገር በሰፈር አታሳጂኝ
የሳልሽው ብረት በላሽ እንጂ
እቅድሽ ነበር ልትጎጂኝ

የዋህ አልነበርሽም እንዳሰብኩሽ
ጅል አልነበርኩም እንዳሰብሺኝ
አባዝተሽ ከኔ ለመውሰድ ነው
ሽሙንሙን ፍቅር የሰጠሺኝ

ፍቅርሽን ይዤ ዝም ብልሽ
ከእብድ አየሺኝ ከወንበዴ
ክፉ ሰው ሆንኩኝ ልትሄጂ ስል
ቀድሜሽ እኔ በመሄዴ

እሰይ ደግ አረኩ
የኔ አስመሳይ
ብትቀበሪም ፡ አላምንሽም
እምባሽ ላይ ሳቅሽ ይታየኛል
ውሸት አትፈሪም እየማልሽም
ድራማሽ ይብቃ ተነቃቃን
ከበቀል ጠጪ ከእልሁም
መለየት መርሳት እችላለው
እንደ ወንዶችሽ አይደለሁም!

እንዲያ ነው ብለሽ አውጂልኝ
ይሄ ጥቅስ አለ ከኔ ዘንዳ
"ደግ ነው በዳይ የሚያስለቅስ
ብፁዕ ነው ክፉ የሚጎዳ!"

እሰይ ..
እንኳን ጎዳሁሽ
@mikiyas_feyisa
@mikiyas_feyisa

4 months ago

..
ለገላዋ እራፊ ፡ ብጣሽ አልገዛሁም፤
እረዥም ታሪኳን ፡ ቁጭ ብዬ አልሰማሁም
ምኞት ፍላጎቷን ፡ ለይቼ አላወኩም
የእግሯን ወለምታ ፡ አሽቼ አላዳንኩም፤
አሞሌ ጭንቀቷን ፡ በሳቅ አላሟሟው፤
ያመቃትን ስቃይ ፡ ጠጋ ብዬ አልሰማው

ከድርብርብ ውጥረት
አስሮ ከደበቃት፤
ሽሮ ለመላቀቅ ፡ ቀልዴ ለሚበቃት
ማድያት ሽፍታ ፡
ሲያጨላልም መልኳን፤
ተራራ ሆኖብኝ ፥
"ምነው?" ማለት እንኳን
ፈገግታ እድሜዋን ፡ ጊዜ ሲከረክም፤
የትም እንደማትሄድ ፡ የኔን ብቻ ሳክም
ለእንስፍስፍ አንጀቷ ፡ ላይሆን መቀነቻ
ወኔዬም ፣ ጀብዱዬም ፡
"ወዳታለው" ብቻ።

ይቅርታ.. እማ።

@mikiyas_feyisa
@mikiyas_feyisa

6 months, 2 weeks ago

እድሜዬን ሁሉ ተሞኘሁኝ
እንደ ሸዋዬ  እንደ እንግዳ
መልክ ስሰፍር በአይን ስሌት
ቀለም ስመትር የሴት ቆዳ

ይገልጣል እኩይ አይነጥላ
ከወደዱት ጋር ማውጋት መቻል
መልክ ብቻውን ዓለም ቢያክል
"ነፍስ"  ከሌለው ይሰለቻል!

@mikiyas_feyisa

6 months, 2 weeks ago

በዛ በበጋ
በዛ በክረምት
እጮኛ ጠፍቶ  ፍለጋ
መሸበትና ሰው ቤት ገባ
ልጅቷን አያት  ተከናንባ
.....

የሚል ዘፈን አዘፍነው
በጭብጨባ አሳድገው
በጋ ሀሩሩን ተቋቁሜ
ያንን ክረምት ስፈልገው
ስሄድ ስሄድ  ይመሽና
ገርማ ለሊት ሲያስጨንቀኝ
መከናነብ ሚገባት   ልጅ
ተገላልጣ ብትጠብቀኝ
ስላልቻልኩኝ ልክ እንደርሱ
በሌት መጥፋት እሷን ይዞ
ስሉም አይኔ ሲያያት ቢያድር
በገላዋ ቅላት   ፈዞ
ሊነጋ ሲል ብንደርስም
አቅማችን ተበልቶ አልቆ
ሰርክ ሙላት የነበረው
በምትሃት አባይ ደርቆ
ለመሻገር ስንሞክር
ወይ አልገባች ወይ አልገባው
እሺ አሁን ምን አጊኝቼ
እያለቀስኩ የማባባው?

ተሻገርን የአባይን ሙላት
የፍቅር እንባን ሳናለቅሰው
እሺ አሁን አብሮ ሲያየን
ምን ይለናል የሚያቀን ሰው?
.
@mikiyas_feyisa

6 months, 2 weeks ago

ሰው ሆኜ ቀረብኳት፡
በድን ሆና ቀረበቺኝ
ህይወት ፍቅሩን አቀመስኳት፥
የሞት ጣዕሙን አሳየቺኝ
ሰላም አለው አልፈርድባት
ቢያስገመግም የሞት ዜና
ምድሩ ሁሉ ፀጥታ ነው
ውጥረት ሁሉ ,ባዶ ፡ ኦና።

የኔን አለም ገመገምነው
የኔ ለኔ ታየ በልጦ
ለኔ ስትል ከኔ ኖረች
❴ሙትነቷ❵  ተለውጦ።
ልብ ምቷን አዳመጠች
እስትንፋሷን ለካካችው
ካሳደጋት ሰላም በላይ
ትርምሱን ወደደችው።

እኔም ለሷ ፡ ሞትኩኝና
"ምንም" መሆን  ቢማርከኝ፤
ውዝግቡ ትዝ እያለ
አንጀት ልቤን ሲያሳክከኝ፤

(ይኸው አሁን ጊዜ አልፎ)
.
.
ፀጥታውን ስላመደው
እሷም ወረት ሲነካካት፥
በድን መሆን ደስ ሲለኝ
ሰው መሆኗ ሲማርካት

እኔን ገድላ ፡ ብትሰወር
በከፈትኩት የህይወት በር፡
ገባኝ መኖር ሚስጥር -ህጉ
አብሮ መሞት ይሻል ነበር!።

@mikiyas_feyisa

6 months, 3 weeks ago

ወዳጄ ይሁን ጠላት እንጃ
ማመንታት ሆኗል ደመወዜ
ህመሜን ያራቀልኝ እርሱ
አንቺንም የወሰደሽ ጊዜ
አልጠላው ነገር ታሪክ አለኝ
አጥቦ ነው ዳግም ያፀደቀኝ
አልወደው ነገር አሳስቆ
አንቺን ነው ከእጄ የነጠቀኝ

@mikiyas_feyisa

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana