ኢትዮ - ኮን ሬድዮ ፕሮግራም

Description
በግንባታው ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሳምንታዊ የባለሙያዎች ፕሮግራም የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ከአሀዱ ሬድዮ 94.3 ትብብር
ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ2፡30-3፡30 ሰዓት የሚተላለፍ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 1 day ago

Last updated 2 weeks, 3 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

2 месяца назад

**ማስታወቂያ *

🫵 ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት በሙሉ!

🔷 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ ቀደም ብሎ የተገለፀላችሁ መሆኑ ይታወሳል፡፡

🔷ይሁንና የምርጫ አመቻች ኮሚቴ አባላቱ በዚሁ ዕለት ቀደም ብለው በተያዙና  በተለያዩ ፕሮግራሞቻቸው ምክንያት መገኘት የማይችሉ መሆኑን በመረዳታችን ጉባዔውን በአንድ ሣምንት ወደፊት ለመግፋት መገደዳችንን  በታላቅ አክብሮትና ትህትና ጋር ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

- ጉባኤው የሚካሄደው ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

- ቦታው ኢንተር ላግዠሪ (የቀድሞው ኢንተር ኮንቲነታል) ሆቴል

- ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ መሆኑን እናስታውቃለን።

🔷የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዳይሬክተሮች ቦርድ

2 месяца, 1 неделя назад

ኢትዮ ኮን ጥቅምት 25፤ 2017

2 месяца, 1 неделя назад
***👉*** የዛሬ ምሽት ጥቅምት 25 ቀን …

👉 የዛሬ ምሽት ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ሳምንታዊ ፕሮግራሞቻችን

🗣ወቅታዊ ፕሮግራም

🔵የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አካሂዷል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ ከመሰረተ ልማት፣ ከኮሪደር ልማትና ሌሎች የተያያዙ ጉዳዮች ጋር ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸውን ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ በዛሬ ወቅታዊ ፕሮግራማችን እንመለከተዋለን።

🏗 የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የሚያቀርበው ልዩ ዝግጅት የፕሮግራማችን አንድ  አካል ነው።

✍️📞☎️የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ ከቀጥታ ስርጭት ፕሮግራማችን ጋር ይሁን!

2 месяца, 1 неделя назад

በአዲስ አበባ ከተማ #ለአፓርትመንት_ቤቶች እና #ለጋራ_መኖሪያ_ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካኝ የሽያጭ ዋጋ ተመን በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

በተሻሻለው  የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሰረት ከኮንደሚንየም እና አፓርትመንት ውጪ ለሆኑ ግንባታዎች፦

➡️ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በጭቃ የተሰራ ቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 15,000 ብር፣

➡️ በብሎኬት የተሰራ የቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 20,000 ብር፣

➡️ የህንጻ ወለላቸው ከG+1 እስከ G+5 25,000 ብር እና፣

➡️ G+6 እና በላይ የሆኑ ቤት ወይም ህንጻ ነጠላ ዋጋ በካሬ 30,000 ተደርጓል፡፡

የቦታው መገኛ ዋጋ ('location value') ለከተማው የቦታ ደረጃ የጸደቀው ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን መደረጉም ተገልጿል።

የቤት ስም ንብረት ዝውውር ክፍያ ማለትም አሹራ 4 በመቶ እና የቴምብር ቀረጥ 2 በመቶ ከጠቅላላ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ተሰልቶ ከመጋቢት17 ቀን 2016 ዓ/ም  ጀምሮ እንዲከፈልም ቢሮ አዟል።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር  ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሻሩንም ቢሮ ጠቅሷል።

በፍርድ ቤት እና በባንክ ሃራጅ ሽያጭ የስም ንብረት ዝውውር የሚጠየቅባቸው ይዞታዎችን በተመለከተ ይዞታ አገልግሎትና መብት ፈጠራ ደንብ ላይ በተቀመጠው አግባብ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።

ይህ ማሻሻያ መምሪያ ከመውጣቱ በፊት የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ጠይቀው በሂደት ላይ ሆኖ ክፍያ የፈጸሙ ተጋልጋዮች በቀድሞ አሰራር በከፈሉት ክፍያ መሰረት ይስተናገዳሉ ተብሏል።

ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች የትመና ስራ የሚሰራላቸው ግንባታው በደረሰበት ወይም አሁን ላይ ባለበት ግንባታ ደረጃ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ያሳወቃል።

2 месяца, 1 неделя назад

በተሻሻለው የካሳ አዋጅ ቁጥር 1336/2016 አፈጻጸም እና  አተገባበር አስመልክቶ ውይይት ተደረገ

በተሻሻለው የካሳ አዋጅ ቁጥር 1336/2016
መሰረተ ልማት እና ማህበራዊ አገልግሎት ንብረት የመገመት፣ የመክፈል እና የማስነሳት ስራ ላይ ችግሮች እያጋጠሙ በመሆኑ ይህንን ችግር መፍታት የሚያስችል አሰራር ማዘጋጀት በማስፈለጉ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና በቀጣይ አካሄዶች ላይ የጋራ መግባባት እንዲኖር በማስፈለጉ ነው ወይይት የተካሄደው።   

በውይይት መድረኩ የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣  ከየክልሉ፣ ከተጠሪ ተቋማት እና ከመንግስት የልማት ድርጅቶች የተወጣጡ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ  ክቡር  አቶ የትምጌታ አስራት  መንግስት ለህዝብ ጥቅም ሲባል ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎችን የሚቋቋሙበት የተሻሻለው የካሳ አዋጅ  ረቂቅ ደንቡ ላይ ውይይት በማድረግ   በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር የውይይት መድረክ ማስፈለጉን ገልጸዋል ።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሬትና ካዳስተር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ብዙሃለም አድማሱ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና የልማት ተነሺዎችን መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1336/2016 ሰነድ እና ሀገራዊ የመሰረተ ልማት ቅንጅት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ ተገኝ ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬት ሲለቀቅ ስለሚከፈለው ካሳ እና የልማት ተነሺዎችን መልሶ ለማቋቋም የወጣ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ረቂቅ ማሻሻያ ደንብ በሚል የተዘጋጁ ሰነዶች ቀርበው ሰፊው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የቀረቡት ሰነዶች  መነሻ በማድረግ ከተሳታፊዎች  የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው በክቡር ሚኒስትር ዴኤታው  ምላሽ እና ማብራሪያ
ተሰጥቶባቸዋል ።

(ከመልሚ)

2 месяца, 1 неделя назад

የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላላፊያ መስመር ግንባታን ተከትሎ ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ በሁለቱም አቅጣጫ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆኗል
- የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

በመገናኛ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት የሚያግዝ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላላፊያ መስመር ግንባታ ተጀምሯል::

በመሆኑም በተለይ ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ እና ከቦሌ ወደ መገናኛ አደባባይ በሁለቱም አቅጣጫ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል::

እግረኞች በሙሉጌታ ዘለቀ ህንጻ በኩል ማለፍ ስለማይቻል በቦሌ ክ/ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ባለው የእግረኛ መንገድ እንዲጓዙ እንዲሁም አሽከርካሪዎችም ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ አሳስቧል፡፡

የአካባቢው መንገድ ተጠቃሚዎች ግንባታው በአጭር ጊዜ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለሚያሳዩት ትብብር የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ምስጋና አቅርቧል፡፡

2 месяца, 2 недели назад

**ማስታወቂያ *

🫵 ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት በሙሉ!

🔷 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ ቀደም ብሎ የተገለፀላችሁ መሆኑ ይታወሳል፡፡

🔷ይሁንና የምርጫ አመቻች ኮሚቴ አባላቱ በዚሁ ዕለት ቀደም ብለው በተያዙና  በተለያዩ ፕሮግራሞቻቸው ምክንያት መገኘት የማይችሉ መሆኑን በመረዳታችን ጉባዔውን በአንድ ሣምንት ወደፊት ለመግፋት መገደዳችንን  በታላቅ አክብሮትና ትህትና ጋር ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

- ጉባኤው የሚካሄደው ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

- ቦታው ኢንተር ላግዠሪ (የቀድሞው ኢንተር ኮንቲነታል) ሆቴል

- ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ መሆኑን እናስታውቃለን።

🔷የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዳይሬክተሮች ቦርድ

2 месяца, 2 недели назад

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የጊዜና የዋጋ መገመቻ ማንዋልና ሶፍትዌር ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዷል

የኢት/ኮንስትራክሽን ባለስልጣን  የግንባታ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ እንዲሁም  በተገቢ ዋጋ ተፈጻሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ሀገር አቀፍ አሰራርን ለመዘርጋት አልሞ እየሰራ ይገኛል።

በዚሁ መሰረትም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሲያስጠናው የነበረው የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የጊዜና የዋጋ መገመቻ ማንዋልና ሶፍትዌር ተቋሙ ሲያስጠና ቆይቷል ፡፡ 

በጥናቱ ረቂቅ ሰነድ ላይ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት ጥቅምት 14/2017ዓ.ም ምክክር ተካሂዶበታል።

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የሆኑት ተስፋሁን ንጋቱ እና በጋሻው ወርቁ በቀረበው የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የዋጋና የጊዜ መገመቻ ረቂቅ ሰነድ ላይ መካተት ስላሉባቸው ሳይንሳዊ፣ ቴክኖሎጂያዊ እና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ግብረ መልሶች ቀርበዋል፡፡

አሁን ላይ ያለውን የግንባታ ፕሮጀክቶች የዋጋና የጊዜ ግመታ አሰራር ክፍቶችን በአግባቡ የመለየት፣ የማንዋሉና የሶፍትዌሩ ዝርዝር እና ጥቅል ይዘቶችን ግልፅ የማድረግ እና በአተገባበር ሂደት ላይ የተሳታፊ አካላትን ሃላፊነትና ሚና የማሳየት ጉዳዮች መካተት እንዳለባቸው ተሳታፊዎች ሙያዊ ግብረ መልስ ሰጥተዋል፡፡

እንዲሁም ማንዋሉና ሶፍትዌሩ ከግንባታ መረጃ ማናጅመንት/ BIM / ጋር የሚናበብ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ትኩረት እንዲሰጥ፣ በቀጣይም ወደ ትግበራ ከመገባቱ አስቀድሞ በተመረጡ ፕሮጀክቶች ላይ የማሳያ ትግበራ እንዲካሄድም ግብረ መልስ ተሰጥቷል፡፡

የጥናት ሰነድ አቅራቢዉ ተስፋሁን ንጋቱ በተሰጡ ግብረ መልሶች ላይ ምሁራዊና ሳይንሳዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በቀጣይም የጥናት ረቂቅ ሰነዶቹ በፍጥነት ዳብረው ለትግበራ እንደሚዘጋጁም ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ ረቂቅ ሰነዶቹ ማለፍ የሚገቧቸውን ሂደቶችና ደረጃዎች እንዲያልፉ ጥረት እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡ በዋናነትም ለጥናቱ ግብአት የሚዉሉ የመረጃ አሰባሰብ ላይ ትኩረት እንዲደረግ አስገንዝበዋል፡፡

የጥናት ሰነዶቹ ሲገባደዱ ከትግበራ አስቀድሞ የሙከራ ትግበራ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ደረጃዎችን ያልፋል ያሉት ኢ/ር መስፍን ነገዎ የወደፊት አሰራሩ በቀጣይ ትግበራ እያደረገ እንደሚሄድ ገልፀዋል፡፡ 

(ኢኮባ)

2 месяца, 2 недели назад

*ማስታወቂያ ለማሕበራት

❇️ ከ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በማህበር የተደራጅታችሁና በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ውስጥ በተለያየ የልማት ሥራዎች ላይ ስትሳተፉ የነበራችሁ ማህበራት ስማችሁ በቢሮው ይፋዊ የማሕበራዊ ሚዲያ ገፆች የተለቀቀ ሲሆን በዝርዝር ውስጥ የሌላችሁ ማህበራት 8 ኛ ፎቅ ምህንድስና ግዥ ዳይርክቶሬት ተገኝታችሁ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 2 ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንዲታደርጉ ያሳስባል ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

ጥቅምት 12/1017

2 месяца, 3 недели назад

✳️ ጅቡቲ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ለመገንባት  ከግብፅ ጋር ተስማማች

❇️ ጅቡቲ ከግብፅ ጋር በመሆን 276.5 ኪሎ ዋት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ለመገንባት የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረማቸውን የግብፅ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

❇️ በግብፅ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ይህ የግንባታ ፕሮጀክት በጅቡቲ የፀሀይ ሀይል ለማመንጨት የሚረዳ ሶላር ፓኔሎችን መትከልን እንደሚያካትት ተነግሯል።

❇️ ስምምነቱ የተፈረሙው የግብፅ መንግስት ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ ለጅቡቲ የኢነርጂ ሚኒስቴር ሰራተኞች የተሳካ የስልጠና መርሃ ግብር ከተጠናቀቀ በኋላ መሆኑም ተጠቁሟል።

✳️ ጂቡቲ ከኢትዮዮጵያ የምታገኘው የኤሌክትሪክ ሀይል

❇️ ጂቡቲ በ2011 በተጠናቀቀው የ283 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ትገዛለች። የሀገሪቱ አብዛኛው ፍጆታ የሚሸፈነው ከኢትዮጵያ በሚገዛ ሀይል ነው።

❇️ በ2022 አመት ጂቡቲ ከኢትዮጵያ የገዛቸው የእሌክትሪክ ሀይል ከሀገሪቱ አመታዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ከ60-80% እንደሸፈነ የአፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ ያመለክታል።

❇️ የቅርብ መረጃዎች ከተመለከትን ጂቡቲ በአሁኑ ወቅት 50 በመቶ የሚሆነውን የኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታዋን በከፍተኛ የሀይል ማስተላለፊያ መስመር የምታስገባው ከኢትዮጵያ ነው።

❇️ በመሆኑም ጂቡቲ እራሷን ከሀይል ግዢ ጥገኝነት ለማላቀቅ እንዲሁም የታዳሽ ሀይል ሀሳብን (green energy) በማራመድ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ እየሰራች ነው።

✳️ ጂቡቲ ለዚህ አላማ መሳካት ምን እርምጃ ወሰደች ?

❇️ ጂቡቲ በ2015 የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ለገለልተኛ ኦፕሬተሮች ክፍት በማድረግ የኢነርጂ ሴክተሩን ለግሉ ዘርፍ ከፍታለች።

❇️ በዚህም በሴፕቴምበር 2023 በሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል በግሉ ዘርፍ ኦፕሬተሮች ታግዞ የመጀመሪያው የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ተመርቆ ተከፍቷል።

❇️ ይህ የንፋስ ሀይል ማመንጫ ተራራማ እና በሀገሪቱ በጣም ነፋሻማ የሚባል ቦታ ላይ የተገነባ ሲሆን ጣቢያው አጠቃላይ 60 ሜጋ ዋት አቅም ያላቸው 17 የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች እንዳሉት ተገልጿል።

❇️ ሀገሪቱ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎችን፣ የጂኦተርማል ኃይል እና የባዮማስ ፋብሪካዎችን  ፕሮጀክቶችን በመንደፍም በ2035 ለዜጎቿ 100% ታዳሽ ሃይል በማቅረብ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ለመሆን ግብ አስቀምጣለች።

❇️ ይህ ከግብፅ ጋር የተፈራረመችው የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታም የዚሁ ግብ አካል እንደሆነም ነው የተገለፀው።

(Tikvahe)

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 1 day ago

Last updated 2 weeks, 3 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago