ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ወደ ቤት ተመለሱ‼****
"ለጥያቄ ይፈለጋሉ "ተብለው ጠዋት ላይ ሲቪል ልብስ በለበሱ የፀጥታ አካላት የተወሰዱት አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ አሁን ከመሸ ወደ ቤታቸው እንደተመለሱ ታውቋል።
EsatMereja?**https://t.me/EsatMerejaa
በኬኒያ ሊመረቁ የነበሩ ለአትሌቶች የተሰሩ ሐውልቶች በህዝብ ተቋውሞ እንዲፈርሱ ተደረገ።
ከሰሞኑ በኬንያ ኤልዶሬት ከተማ አትሌቶችን ለመዘከር የተሰሩት ሐውልቶች ከሕዝብ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።
በከተማዋ የቆሙት የሦስት አትሌት ሐውልቶች በርካቶች ከተሳለቁባቸው እና “አሳፋሪ ቀልድ” ብለው ከገለጿቸው በኋላ የከተማዋ ባለሥልጣናት ሐውልቶቹን ለማንሳት ተገደዋል።
ባለሥልጣናቱ ሐውልቶቹ ማንን እንደሚወክሉ ባይገልጹም በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ግን አንዱ የኪፕዬጎን ሌላው ደግሞ የኪፕቾጌ ሐውልት ሊሆኑ እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
በዛሬው እለት ሊመረቁ የነበሩት ሐውልቶች ከአትሌቶቹ ጋር ጭራሽ የማይቀራረቡ መሆናቸውን ኬንያውያን በተለያዩ ማኅበራዊ ትስስር ገጾች ሲገልጹ ቆይተዋል።
በዚህም የከተማዋ ባለስልጣናት ከነዋሪው የገጠማቸውን ተቃውሞ ተከትሎ ሐውልቶቹን በማንሳት ወዳልታወቀ ቦታ እንደወሰዷቸው አንድ የአካባቢው ነዋሪ ገልፀዋል ።
EsatMereja?**https://t.me/EsatMerejaa
በአሶሳ ከተማ ከሚስቱ ጋር በመሆን ሳይታገቱ ታግተናል በማለት ለቤተሰቦቿ የደወሉ ጥንዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ሳይታገት ታግቻለሁ በማለት በሃሰት ከሚስቱ ጋር በመሆን ለቤተሰቦቿ የደወሉ ጥንዶች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተነግሯል ።
በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የወረዳ ሁለት ፖሊስ የአካባቢ ፖሊስ አስተባባሪ የሆኑት ምክትል ሳጅን አብዱሰላም ያሲን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ተጠርጣሪዎች በከተማ አስተዳደሩ ወረዳ ሁለት ቀበሌ 4 ነዋሪ ሲሆኑ አ/ቶ ዮሐንስ አሰቡ እና ወ/ሮ ብርቱካን ፀጋው የተባሉት የባልና ሚስት መሆናቸውን ተናግረዋል ።
ሆኖም ባልና ሚስት በመመሳጠር ባል ለቤተሰቦቿ በመደወል ታግቻለሁ 17 ሺህ ብር ላኩልኝ ማለቱ ተነግሯል ። ይሁን እንጂ ፖሊስ ከማህበረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ጥንዶቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣረባቸዉ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ድርጊት የሚፈጽሙ አካላት ሲገጥሙት ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባ ምክትል ሳጅን አብዱሰላም ያሲን ጨምረው ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
EsatMereja?**https://t.me/EsatMerejaa
#Tigray
መምህርቷ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።
በትግራይ፣ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳስላሰ ሽረ ከተማ ነሀሴ 7/2016 ዓ.ም ሌሊት ጭካኔ የተሞላበት እጅግ አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል።
አስቃቂ ግድያ የተፈፀመባት መምህርት ብርኽቲ ተስፋማርያም ትባላለች።
የትግራይ መምህራን ማህበር በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ በአባሉ ላይ በተፈፀመው ጭካኔ የተሞላበት ዘግናኝ ግድያ የተሰማው ጥልቅ ሃዘን ገልጿል።
የዚህ እጅግ አሰቃቂ የወንጀል ተግባር ፈፃሚዎች በአስቸኳይ ተጣርተው ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲጣልባቸውም ጠይቋል።
ሟች መምህርት ብርኽቲ ተስፋማርያም ከሑመራ ተፈናቅለው ከባለቤታቸውና 3 ልጆቻቸው በእንዳስላሰ ከተማ ይኖሩ እንደነበር ማህበሩ አመልክቷል።
" የሟች ባለቤት ቤት ውስጥ አለማደሩ ያጠኑና ያረጋገጡ ግፈኞች ነሀሴ 7/2016 ዓ.ም መምህርትዋ ልጆችዋ ፊት አርደው ገድልዋታል " ብሏል የመምህራን ማህበሩ።
" ይህ አስነዋሪ የግፍ ተግባር የትግራይ ህዝብ መልካም እሴት የሚፃረርና የሚያጎድፍ ሰይጣናዊ ተግባር ነው " ያለው መገለጫው " የፍትህ አካላት የአሰቃቂ ተግባሩ ፈፃሚዎች በማጣራት የህግ የበላይነት እንዲያረጋግጡ እንጠይቃለን " ብሏል።
EsatMereja?**https://t.me/EsatMerejaa
ዶ/ር ጋትሏክ ሮን የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ!
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዶ/ር ጋትሏክ ሮንን የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ፡፡የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ የቀረበውን ሹመት ተቀብሎ ዶ/ር ጋትሏክ ሮንን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሹሟል፡፡
EsatMereja?**https://t.me/EsatMerejaa
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana