በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን (ከገድላት አንደበት)

Description
ይኽ ለ3ኛ ጊዜ የተከፈተ አዲስ ቻናል ነው። በየቀኑ ገድለ ቅዱሳንና የተለያዩ አገልግሎቶች በጽሑፍና በድምፅ ይተላለፉበታል።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 6 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 3 weeks, 2 days ago

Last updated 3 weeks, 2 days ago

3 weeks, 3 days ago

ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ፀሐይ ዕድሜያችን ሳትጠልቅ በእምነት እንፈልገው፡፡ አሞጽ4፡፡ የአህያን ጀርባ ያልናቀ ጌታችን ትሑት ሰብእና እና የተሰበረ ልቡና ወዳለው ሰው ዘወትር ይጓዛል፣ የተዋረደውንና የተሰበረውን ልብ አይንቅም፡፡ ኢሳ.66፡2፤ መዝ.50፡17፡፡
ጌታችን በአህያ ውርንጫ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ስለሆነ የክብረ በዓሉ ምስጋና በዋዜማው ይጀመራል፡፡ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ካህናቱ በእምርት ዕለት በዓልነ፣ በታወቀ የበዓላችን ዕለት ከበሮ ምቱ በማለት የዋዜማውን ምስጋና ይጀምራሉ፡፡ የዋዜማው የምስጋና ቀለም እጅግ ሰፊ ስለሆነ በዚህ መዘርዘር አይቻልምና ከዋዜማው ፍጻሜ በኋላ ያለውን ሥርዓት እንመልከት፡-
በሌሊተ የሆሳዕና ማኅሌት ከመቆሙ በፊት በካህኑ ተባርኮ በሰሙነ ሕማማት ሲነበብ ሲተረጎም የሚሰነብተው ግብረ ሕማማት የተባለው መጽሐፍ መነበብ ይጀምራል፡፡ ስቡሕ ወወዱስ ዘሣረር ኩሎ ዓለመ፣ ዓለምን ሁሉ ፈጠረ እግዚአብሔር ፍጹም የተመሰገነ ነው በሚለው የምስጋናዎች ሁል ርእስ የዕለቱ የማኅሌቱ ምስጋና በካህናትና በሊቃውንት ይጀመራል፡፡
ከዐቢይ ጾም መግቢያ ጀምሮ ማዕቀብ ተጥሎባቸው በዝምታ የሰነበቱት ከበሮና ጽናጽል የምስጋናው ባላድርሻዎች ይሆናሉ፡፡ በዚህ የተጀመረው ማኅሌት ሌሊቱን ሙሉ አድሮ መዝሙር በሚባለው . . . ምስጋና በኩል አድርጎ ሥርዓተ መወድስ ተደርጎ ሰላም በተባለ ምስጋና ይጠናቀቃል፡፡
ሥርዓተ ዑደት በሆሳዕና
ሥርዓተ ማኅሌቱ ተፈጽሞ ሥርዓተ ቅዳሴው ከመጀመሩ በፊት እሰካሁን ከነበረው ሥርዓት ለየት ያለ ሆኖ እንመለከታለን፡፡ ይኸውም ሊቃውንቱ የዕለቱን ድጓ እየቃኙ እየመሩና እየተመሩ፣ ዲያቆኑ ከመዝሙር ዳዊት የዕለቱን በዓል የተመለከተ ምስባክ በዜማ እየሳመረ፣ ካህናቱም በዓሉን የተመለከተ ወንጌል በዐራቱም መዓዘን እያነበቡ ቤተ መቅደሱን አንድ ጊዜ ይዞሩታል፡፡
ለምሳሌ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ባለው በር ፊት ለፊት በመቆም መምህሩ አርእዩነ ፍኖቶ ወንሑር ቤቶ፣ ወደቤቱ እንገባ ዘንድ መንገዱን አሳዩን፡፡ የሚለውን ድጓ ይቃኛሉ ካህናቱ እየተከተሉ ያዜማሉ ዲያቆኑ ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘየሐድር ውስተ ጽዮን፣ በጽዮን የሚገለጥ እግዚአብሔርን አመስግኑ እያለ ያዜማል፡፡ ካህኑም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 21፡ 1-13 ያለውን ኀይለ ቃል ያነባል፡፡ በዚህ ዓይነት መልክ በዐራቱም መዓዘነ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ዑደት ይፈጸማል፡፡
ይህን ሥርዓት ሊቃውንቱ ሲተረጉሙት አንደኛ ጌታችን በአህያ ውርንጫ ተጭኖ በሕፃናት አንደበት እየተመሰገነ ኢየሩሳሌም የገባበትን የምስጋና ጉዞ ለማመልክት ሲሆን ሁለተኛ ሕገ ወንጌል በዐራቱም ማዕዘነ ዓለም ለሕዝብና አሕዛብ መዳረሱን ለማመልከትና ሕዝብና አሕዛብ በሕገ ወንጌል አንድ አካል መሆናቸውን በገቢር ለማሳየት መሆኑን ያስተምራሉ፡፡
ሥርዓተ ቅዳሴ ዘሆሳዕና
በዕለተ ሆሳዕና አሁንም የቅዳሴው አገባብ ሥርዓት ከሌሎች ዕለታት ለየት ያለ መሆኑን እንመለከታለን፡፡ ዲያቆናቱ ሕብስቱን በመሶበ ወርቅ ወይኑን በጽዋዕ ይዘው በምዕራብ በር በኩል ይቆማሉ፣ ሠራኢው ዲያቆን በዜማ አሰምቶ እርኅው ኆኅተ መኳንንት፣ አለቆች ደጆችን /በሮችን/ ክፈቱ ይላል፡፡ ካህኑም በመንጦላዕክት ውስጥ ሆኖ መኑ ውእቱ ዝንቱ ንጉሠ ስብሐት ይህ የክብር ንጉሥ ማነውÃÂ ብሎ ይጠይቃል ዲያቆኑም ይህ የኃያላን አምላክ እግዚአብሔር ነው ብሎ ይመልሳል፡፡ ዲያቆኑ ሦስት ጊዜ የክፈቱልኝ ጥያቄያዊ ዜማውን ካዜመ በኋላ ካህኑ ይባዕ ንጉሠ ስብሐት፣ የክብር ንጉሥ ይግባ ብሎ ፈቅዶለት ይገባል፡፡ መዝ. 23፡7
ይህንንም አበው እንደሚከተለው ያመሰጥሩታል፡፡ አንደኛ ቅዱስ ገብርኤልና ወላዲተ አምላክ በምሥጢረ ብስራት ጊዜ የተነጋገሩት እንደሆነና በመጨረሻም ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ፣ እንደቃልህ ይደረግልኝÂ ብላ መቀበሏን ሲያሳይ ሁለተኛው ፈያታይ ዘየማንና መልአከ ኪሩብ በማእከለ ገነት የተነጋገሩትን በድርጊት ለማሳየት መሆኑን ያስተምራሉ፡፡ ዋናው ምስጢር ግን ክርሰቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ሊገባ ሲል ብዙዎቹ እንዲገባ መፍቀዳቸውን ያሳያል፡፡
እንደተለመደው ሥርዓተ ቅዳሴው ከተጠናቀቀ በኋላ እግዚእ ሕያዋን /የሕያዋን ጌታ/ የተሰኘው ጸሎት በካህናት ተደርሶ ለምእመናን ሥርዓተ ፍትሐት ይደረግላቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ሥርዓተ ፍትሐት ስለማይደረግ፡፡ በሰሙነ ሕማማት የማይከናወኑ ምሥጢራት በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
ምእመናንም ተባርኮ የተሰጣቸውን የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ ወደየቤታቸው ያመራሉ፡፡ የዘንባባው ምሥጢር የተጀመረው በታላቁ አባት በአብርሃም ነው፡፡ ኩፋ.13፡21 ይህን የአባታቸውን ሥርዓት አብነት አድርገው እስራኤል የኤርትራን ባሕር ሲሻገሩ፣ ዮዲት ድል ባደረገች ወቅት ዘንባባ እየያዙ እግዚአብሔርን አመስግነውታል፡፡ ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባም ሽማግሌዎችና ሕፃናት የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው እንደተቀበሉት እናነባለን፡፡ ሉቃ.12፡8
ኢትዮጵያውያን ምእመናንም ክርስቶስ የሰላም፣ የነጻነት፣ የድኅነት አምላክ መሆኑን ለመመስከር ዘንባባውን ይዘው ወደቤታቸው ይገባሉ፡፡ ዮሐ.14፡27 በእጃቸውም እንደቀለበት ያስሩታል፡፡
ለታሰሩት መፈታትን ሊሰብክ ሰው የሆነ ጌታችን ከማሰሪያዋ በተፈታች አህያ እንደተቀመጠ ሁሉ ከኃጢአት እስራት በተፈታ ሕይወት ዛሬም ያድራል፤ የኅሊና ሰላምን ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ንስሐ ገብተን ጌታችንን ሆሳዕና በአርያም እያልን ልናመሰግነው ይገባል፡፡

(ምንጭ፡ ሐመር ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ መጋቢት/ሚያዝያ 1996 ዓ.ም፣ ስምዐ ጽድቅ ዘኦረቶዶክስ ተዋሕዶ ጋዜጣ፣ ከመጋቢት 20-24 ቀን 2002 ዓ.ም፤ ልዩ እትም፡፡)

3 weeks, 3 days ago

ከዘጠኙ ዐበይት የጌታችን በዓላት ውስጥ አንዱ ለሆነው ለታላቁ የሆሳዕና በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን!
"ሆሳዕና በአርያም" ማለት በአርያም /በሰማይ/ ያለ መድኃኒት ማለት ነው፡፡ ሆሳዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ሆሻአና" የሚል ሲሆን ትርጉሙም "እባክህ አሁን አድን" ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩከ ነው፡፡ መዝ.117፡25-26፡፡
የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት "ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያም" በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ በዓሉም ሆሳዕና የሚለውን ስያሜ ያገኘው በዕለቱ ከተዘመረው መዝሙር ነው፡፡
በሌላ አነጋገር ይህ ዕለት የጸበርት እሑድ /Palm Sunday/ ይባላል፡፡ ታሪካዊ አመጣጡ የመልካም ምኞትና የድል አድራጊነት መገለጫ ሆኖ ከደገኛው አባታችን ይስሐቅ ልደት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡ ይኸውም ሣራ የወላድነት ዕድሜዋን ጨርሳ ልማደ እንስት ከተቋረጠባት በኋላ ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ይስሐቅን በሰጣት ጊዜ ዘመዶችዋ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ የጎበኟትን አምላክ አመስግነዋል፡፡ እስራኤል ከአስከፊው የግብፃውያን አገዛዝ ተላቀው ባሕረ ኤርትራን በደረቅ ሲሻገሩ የተሰማቸውን እጥፍ ድርብ ደስታ በገለጡ ጊዜ፣ እንዲሁም ዮዲት የተባለች ንግሥተ እስራኤል ሆሎፎርኒስ የተባለ አላዊ ንጉሥን ድል ባደረገች ጊዜ ቤተ እስራኤል እንደ ሰንደቅ ዓለማ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ አደባባይ ወጥተው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በዘመነ ሐዲስም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር ከዲያብሎስ ቁራኝነት ከሲኦል ባርነት ነጻ ለማውጣት ወደ ዙፋን መስቀሉ /ሉቃ.22፤18/ በተጓዘ ጊዜ ሕፃናት እና አእሩግ ነጻ የሚወጡበት ቀን መድረሱን እነርሱ ሳያውቁ እግዚአብሔር ባወቀ ዘንባባ በመያዝ ዘምረዋል፡፡ እስራኤል ዘንባባ በመያዝ እንዳመሰገኑት እኛም አስራኤል ዘነፍስ ዕለቱን ዘንባባ /ጸበርት/ በግንባራችን በማሰር በዓሉን በየዓመቱ እያስታወስን እናከብራለን፡፡ በዚህ ዕለት ዘንባባ እየተባረከ ለሕዝቡ ይታደላል፡፡
ሕፃናትና አእሩግ "ለዳዊት ልጅ መድኃኒት መባል ይገባዋል" እያሉ ዘምረዋል፡፡ ይህ ሁሉ በአንድ ወገን የነበረው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ሲሆን በሌላ በኩል የነበረው አቀባበል ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን ነበር፡፡ ሥርዓተ ኦሪትን፣ ትንቢተ ነቢያትን በሚገባ እንከተላለን ይሉ የነበሩ ጸሐፍት ፈሪሳውያን "መምህር ሆይ! ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው" አሉት፡፡ ጌታችንም መልሶ "እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ" ሲል መልሶላቸዋል፡፡ ቅናት አቅላቸውን ያሳታቸው ፈሪሳውያንም የዋህ የሆነው ሕዝብ ምስጋና ወደ ጥላቻ እንዲለወጥ አድርገዋል፡፡ ከሁሉ የሚያሳዝነው በዕለተ ሆሳዕና እሑድ ዘንባባ ይዘው የዘመሩለትን ጌታ ዓርብ ላይ "ይሰቀል ዘንድ ይገባል" ብለዋል፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ በዚህም በነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ፡፡ "እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፣ በአህያዪቱ ግልገል በውርንጫዪቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡" ዘካ.9፡9፤ ማቴ.21፡4፤ ማር.11፡1-10፤ሉቃ.19፡28-40፤ ዮሐ.12፤15፡፡ ጌታችን በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ የሰላም ንጉሥ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እስራኤል ዘመነ ምሕረት ሲሆንላቸው አባቶቻቸው በአህያ ጀርባ ተቀምጠው ይታዩ ነበር፡፡ ጌታም እውነተኛ የኅሊና ሰላም ይዤላችሁ መጣሁ ሲለን በአህያ ጀርባ ወደ ቤተ መቅደስ ሕይወታችን ተጉዟል፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ" አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17
ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተውአቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡
ለምን ዘንባባ ያዙ ቢባል፤ ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡
የተምር ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፤ ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡
የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፤ ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡
ልብሳቸውንም ማንጠፋቸው፤ እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡
“የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ዘካ.9፡9 የሚለው የዘካርያስ ትንቢት ተፈጸመ፡፡ ሕዝቡም ኢየሱስ በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ ከፊትና በኋላ ያሉት ደግሞ “ሆሳዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” እያሉ በታላቅ ድምፅ ይጮሁ ነበር፡፡ ኢየሱስ በሕዝቡ እልልታና ደስታ ታጅቦ ሲገባ ተጠንቅቀው ይታዘቡትና ይመለከቱት የነበሩ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርቱን ዝም እንዲያሰኛቸው ተናገሩት፡፡ እርሱም ሕዝቡ ዝም ቢል ድንጋዮች እንደሚጮኹ አስታወቃቸው፡፡
በጌታችን በዕለተ ልደቱ "በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል በምድር ሰላም ለሰው ሁሉ ይሁን" /ሉቃ.2፡13/ እያሉ የዘመሩለት የሰላም ባለቤት ነው፡፡ በመዋዕለ ትምህርቱም "ሰላሜን እሰጣችኋለሁ" /ዮሐ.14፡27/ ብሎ እንዳስተማረ ያን ሰላም የሚሰጥበትን ዕለት መቅረቡን ለማመልከት ነው፡፡ በሌላ በኩልም በአህያ ጀርባ መቀመጡ ኅቡዕ ምሥጢር አለው፡፡ በአህያ ጀርባ የተቀመጠ ሰው ሌላውን አሳድዶ አይዝም፣ እርሱም ሮጦ አያመልጥም፡፡ በዚህም ጌታችን በእምነት ለሚፈልጉት የሚገኝ ቅርብ ሲሆን በእምነት ለማይፈልጉት ግን የማይገኝ መሆኑን አስተምሯል፡፡

3 weeks, 4 days ago

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!
ሚያዝያ 19-የፋርሱ ኤጲስቆጶስ አባ ስምዖን ከ150 ሰማዕታት ጋር በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ይኸውም ቅዱስ የአርማንያ ሰው ሲሆኑ የፋርስ ሀገር ኤጲስቆጶስ ሆነው ካገለገሉ በኋላ ከእርሳቸው ጋር ከነበሩ 150 ሰዎች ጋር በሰማዕትነት ያረፉ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ በዘመኑ ባሶር የተባለው ከሃዲ ንጉሥ ለጣዖት ካልሰገዳችሁ በማለት ክርስቲያኖችን እጅግ ያሠቃይ ጀመር፡፡ አባ ስምዖንም ለዚህ ከሃዲ ንጉሥ ስለ ጣዖቱ ከንቱነት ነቀፉት፡፡ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር በመንገር ከዚህ ክፉ ሥራው እንዲመለስ ካለተመለሰም ክርስቲያኖችን ቢያሠቃያቸውም ክርስቶስን በማመን እስከመጨረሻው እንደሚጸኑ በደብዳቤ ገለጹለት፡፡
ንጉሡም የአባ ስምዖንን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ እጅግ ተቆጥቶ አባ ስምዖንን አሥሮ አሥር ቤት ውስጥ ጣላቸው፡፡ ከእርሳቸውም በፊት 150 ክርስቲያኖችን አሥሮ ያሠቃያቸው ነበር፡፡ አባ ስምዖንም በእሥር ቤት የታሰሩትን ክርስቲያኖች እየመከሩና እያጽናኗቸው በመንግሥተ ሰማያት ስለሚጠብቃቸው ክብር እየነገሯቸው ሰማዕትነታቸውን በድል እንዲፈጽሙ መከሯቸው፡፡ ንጉሡም ሰማዕታቱን ብዙ ካሠቃያቸው በኋላ ሚያዝያ 19 ቀን አባ ስምዖንን እና 150ዎቹን ክርስቲያኖች ወደ ፍርድ አደባባይ አውጥቶ ሁሉንም በየተራ አንገታቸውን በሰይፍ አስቆረጠውና የሰማዕትነት ፍጻሜያቸው ሆነ፡፡ ሁሉም የክብርን አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀዳጁ፡፡
የአባ ስምዖንና የ150ዎቹ ሰማዕታት ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

1 month ago

"ለዐቢይ ጾሙ የሚኾኑና በ MP3 የአዘጋጀሁትን የንስሓ የመዝሙራት ስብስብ አጣነው" እያላችሁ በተደጋጋሚ ለጠየቃችሁ እኅት ወንድሞች ኹሉ!
(መዝሙሩን በድጋሚ "share" አድርጌላችኋለሁ። መዝሙራቱ ፍጹም የንስሓ ሲኾኑ ከምድራዊው ዓለም አውጥተው በመንፈስ ቀራኒዮ ወስደው የመድኀኔ ዓለም ክርስቶስን መከራ መስቀል የሚያሳዩን የሚያሳስቡን ስለሆኑ ተጠቀሙባቸው።)

1 month ago

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሚያዝያ 12-ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወደ ነቢዩ ኤርሚያስ የተላከበት ዕለት ነው፡፡ ነቢዩም በጉድጓድ ተጥሎ ሳለ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አውጥቶታል፡፡
+ ከሃዲው መክስምያኖስ ያሠቃየው የኢየሩሳሌሙ ቅዱስ አባ እለእስክንድሮስ ዐረፈ፡፡
+ ጠመው የምትባለው አገር ኤጲስቆጶስ የሆነው የአባ እንጦንስና የአውሳንዮስ መታሰቢያቸው እንዲሁም መጥምቁ ዮሐንስ የተገለጠላቸው ጋይዮስና ኤስድሮስ ዕረፍታቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡
አባ እለእስክንድሮስ ዘሀገረ ቀጰዶቅያ፡- የቀጰዶቅያ አገር ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ሲያገለግል የከበሩ ቦታዎችን ሊሳለም ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣ ነበር፡፡ በኢየሩሳሌምም በርኪሶስ የሚባል 110 ዓመት የሆናቸውና በሹመት የሚያገለግሉ ጻድቅ ነበሩ ነገር ግን ሕዝቡ እምቢ ስላላቸው በሹመት ቆይተው ነበር፡፡ አባ እለእስክንድሮስም በኢየሩሳሌም የከበሩ ቦታዎችን ተሳልሞ ወደ ሀገሩ ሊመለስ ሲል ከሰማይ ‹‹እለእስክንድሮስን ይዛችሁ ሹሙት›› የሚል ቃል ተሰማ፡፡ ሰዎቹም እንደተባሉት ይዘው እርሱን ለመሾም እንግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ሲግሩት እርሱ ግን ‹‹ይህ አይሆንልኝም እኔ የጵዶቅያ ኤጲስ ቆጶስ ነኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ድምጽ ከሰማይ እንደሰሙና እግዚአብሔር እንደዳዘዛቸው ነገሩት፡፡ ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑንንም ካወቀ በኋላ አብረውት ለመጡ ሰዎች ወደ ሀገሩ ደብዳቤ ልኮ ሌላ ኤጲስ ቆጶስ እንዲሾሙ አዘዛቸው፡፡ የኢየሩሳሌሙን አባ በርኪሶስንም እየተራዳቸው 5 ዓመት አብሯቸው አገለገለ፡፡ እርሳቸውም ሲያርፉ ሕዝቡን እንደ ሐዋርያት ሆኖ ጠበቀ፡፡

ከሀዲው መክስምያኖስም በነገሠ ጊዜ አባ እለእስክንድሮስን ይዞ ጽኑ በሆነ ሥቃይ አሠቃያቸው፡፡ እርሳቸውን የሚገድልበትንም ነገር እስኪያስብ ድረስ እስር ቤት ጣላቸው፡፡ በመሀልም ጌታችን ይህን ከሃዲ አጠፋውና ገርዲያኖስ ሲነግሥ ሰላም ሆነ፡፡ ሌላኛው ከሀዲ ዳኬዎስም ሲነግሥ በክርስቲያኖች ላይ ሥቃይን አመጣ፡፡ እርሱም አባ እለእስክንድሮስን በድጋሚ እጅግ አሠቃያቸው፡፡ ስለት ባላቸው በትሮች ሲያስገርፋቸው የጎን አጥንቶቻቸው ተሰብረው ወደ ሆዳቸው ገብተው እጅግ ተሠቃዩ፡፡ ደማቸውም በምድር ላይ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ ጎትተው ወስደው እስር ቤት ጣሏቸው፡፡ ይህም ቅዱስ አባት በዚያው በእስር ቤት ሳሉ ሰማዕትነታቸውን ፈጽመዋል፡፡ ዕፍታቸውም ሚያዝያ 12 ነው፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + + + +
ዳግመኛም በዚኽች ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን እግዚአብሔር ወደ ነቢዩ ኤርሚያስ ላከው፡፡ ነቢዩ ኤርሚያስን ጠባብና ረግረግ ከሆነ እሥር ቤት ንጉሥ ሴዴቅያስ ባሠረው ጊዜ የንጉሡ ባለሟልና የጭፍራ አለቃ የሆነው ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አውጥቶታል፡፡ ያንጊዜም የኢየሩሳሌምን ጥፋት እንዳያይ መራራ ምርኮንም እንዳይቀምስ ነቢዩ ኤርሚያስ መረቀው፡፡ እንደመረቀውም ሆነለትና ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ 66 ዓመት ተኝቶ ኖረ፡፡ ከእርሱም ጋራ ወይንና በለስ ነበረ፣ ነገር ግን አልተለወጠም ነበር፡፡ የእስራኤልም ልጆች ከምርኮ እስኪመለሱ ድረስ የኢየሩሳሌምንም ጥፋት እንዳያይ እግዚአብሔር በመልአኩ በቅዱስ ሚካኤል አማካኝነት ጠብቆታል መግቦታልም፡፡

1 month ago

የሚነበበው መጽሐፈ ስንክሳር)
በእንደዚህ ዐይነት መንገድ ሰማዕትነትን ይቀበሉ ዘንድ ጌታችንን በጸሎት እየጠየቁ በሥጋቸው ብዙ አሰቃቂ መከራዎችን የተቀበሉ ቅዱሳን ሰማዕታት እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ይኽም የሚያሳየን እግዚአብሔር የመረጠው ካልሆነ በቀር የሰማዕትነትን ክብር ማንም ሊያገኘው እንደማይችል ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚቀበለው ንጹሕ የሆነውን መሥዋዕት ስለሆነ ጌታችን ሰማዕታቱን ንጹሕ መሥዋዕት አድርጎ ነው የሚቀበላቸው፡፡
የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ መድኃኔዓለም በቸርነቱ ያስበን! አሜን!!
(ምንጭ፡- ሰማዕትነት በክርስትና መጽሐፍ፣ ስንክሳር ዘወርሃ ሚያዝያ)

1 month, 1 week ago

“እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ” (መዝ 50፡5) ማለቱ ስለዚህ ነው። ቅዱሱም ተወልዶ ጉልበቱ ከጸና በኋላ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ አድጓል።

እረኛና ብላቴና የነበረ ቢሆንም የፍልስጤማውያኑን ኃያል ሰው ጎልያድን በ12 ዓመቱ 5 ጠጠርን ከወንዝ ለቅሞ በወንጭፍ ወርውሮ ገድሏል፡፡ 1ኛ ሳሙ 12፡45-51፡፡ ንጉሥ ሳዖል በጌልቦአ ተራራ በራሱ እጅ ከሞተ በኋላ አስቀድሞ በይሁዳ 7 ዓመት በመላው እስራኤል 33 ዓመት ነግሡዋል፡፡ 2ኛ ሳሙ 2፡4፤ 5፡1-5፡፡ ‹‹እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መርጦአል” (1ኛ ሳሙ 13፡14) ተብሎ በእግዚአብሔር የተመረጠና ነገረ ሥጋዌን፣ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን፣ ዳግም ምጽዓትን፣ ነገረ ማርያምን፣ ክብረ ቅዱሳንን፣ በስፋትና በጥልቀት የተናገረ የብሉይ ኪዳን ‹‹ወንጌላዊ›› የተባለ ቅዱስ ነቢይ ነው። “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ። አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም። ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ…” እያለ የጌታችንን መከራ መስቀል በትንቢት ተናግሯል፡፡ መዝ 21 (22)፡ 16-18፡፡

“አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።”፣ “ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል። አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊት ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ…” እያለ የጌታችንን ዕርገቱንና ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣ መሆኑን በግልጽ ተናግሯል፡፡ መዝ 46(47)፡4-5፣ መዝ 49(50)፡ 1-5፡፡ “የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” እያለ የእመቤታችንን ክብር አይቶ በትንቢት ተናግሯል፡፡ መዝ 44(45)፡9፡፡

ቅዱስ ዳዊት ታላቅና ገናና የከበረ ንጉሥ ከመሆኑ የተነሣ መንግሥቱ የመሢሕ መንግሥት ምሳሌ ሆኗል፤ መሢሑም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት ስም ብዙ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሶ ይገኛል። (ኢሳ 9፡7፣ ኤር 23፡5-6፣ ኤር 33፡14-17፣ ሕዝ 34፡23፣ ሆሴዕ 3፡5) በሐዲስ ኪዳንም ወንጌላዊያኑ ጌታችንን ‹‹የዳዊት ልጅ›› በማለት ነው መጀመሪያ ነገረ ልደቱን ማውሳት የጀመሩት፡፡ ማቴ 1፡1፡፡ ራሱ ጌታችንም ‹‹እኔ የእሴይ ሥርና የዳዊት ዘር ነኝ›› ብሏል፡፡ ራእ 22፡16፡፡
ቅዱስ ዳዊት 7 ሀብታት የተሰጡት ጻድቅ አባት ነው፡፡ እነዚህም የተሰጡት ሀብታት፡- ሀብተ ክህነት፣ ሀብተ መንግሥት፣ ሀብተ መዊዕ (የማሸነፍ ሀብት)፣ ሀብተ ትንቢት፣ ሀብተ ኃይል፣ ሀብተ በገና (ዝማሬ) እና ሀብተ ፈውስ ናቸው። ቅዱስ ዳዊት 24 ሰዓት ሙሉ የእግዚአብሔር ምስጋና እንዳይቋረጥ መዘምራንን መድቦ እንዲያገለግሉ ያደርግ ነበር፡፡ ራሱም 10 አውታር ባለው በገና ሌት ተቀን በፍጹም ተመስጦ ያመሰግን ነበር፡፡ በመዝሙሩም አጋንንትን ያቃጥል ነበር፡፡ መዝሙረ ዳዊት በውስጡ የያዘው ሚሥጢር እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ አባቶቻችን ዛሬም በዱር በጫካ ሆነው መዝሙረ ዳዊትን አብዝተው ይደግማሉ፡፡ እንኳንስ የሰው ልጅ ይቅርና ‹‹መዝሙረ ዳዊትን›› ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም እግዚአብሔርን ለማመስገኛነት ተጠቅመውበታል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እድሜ ዘመኑን እግዚአብሔርን በማገልገልና በመፍራት ኖሮ በታኅሣሥ 23 ቀን በሰላም ዐርፎ በኢየሩሳሌም ተቀብሯል፡፡
ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!

1 month, 1 week ago

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሚያዝያ 6-አባታችን ቅዱስ አዳምና እናታችን ቅድስት ሄዋን ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡
+ በዮረዳኖስ በረሃ ብቻዋን 47 ዓመት ስትጋደል የኖረችው የከበረች ቅድስት ግብፃዊት ማርያም ዕረፍቷ ነው፡፡
+ ጌታችን በከበረች በቅድስት ትንሣኤው ሳምንት ለሐዋርያው ቶማስ ተገለጠለትና የእጆቹንና የእግሮቹን የችንካሮች ምልክት አሳየው፤ በጦር የተወጋ ጎኑን ያስዳሰሰው እንደዛሬዋ ባለችው ጥንተ ዕለት ነው፡፡ ቅዱስ ቶማስም በዚህ ጊዜ ‹‹ጌታዬና ፈጣሪዬ ሆይ ከሞት መነሣትህን አመንኩ›› አለ፡፡
+ ልበ አምላክ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት ልደቱ ነው፡፡
+ ጻድቁ ኖኅ ልደቱ ነው፡፡
ቅድስት ማርያም ግብፃዊት፡- ገና በ12 ዓመቷ ሰይጣን ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ሥጋዋን እስከመስጠት አድርሷት ነበር፡፡ ጌታችን ወደ መቃብሩ የሚሄዱ ሰዎችን ገልጦላት ከእነርሱ ጋር ትሄድ ዘንድ ወደደችና በመርከብ ተሳፈረች፡፡ የመርከብ ዋጋ እንኳን ሳትከፍል ሰውነቷን ሰጠቻቸውና ይህንንም ሥራዋን ኢየሩሳሌም እስክትደርስ አላቆመችም ነበር፡፡ ወደ ጌታችን መቃብር ቤት ልትገባ ስትል ግን መለኮታዊ ኃይል መግባት ከለከላት፡፡ ከሚገቡ ሰዎች ጋር ለመግባት ብዙ ደከመች፡፡ በኋላ ግን ስለ ረከሰ ሥጋዋ አስባ በእመቤታችን ሥዕል ሥር ወድቃ አለቀሰች፡፡ ‹‹ያዘዝሽኝን ሁሉ እፈጽማለሁ ተዋሽን›› አለቻትና መግባት ቻለች፡፡ ወደ ሥዕሏም ተመልሳ አለቀሰች፡፡ ከሥዕሏም ድምፅ ወጣና ‹‹ወደ ዮርዳኖስ በረሃ ሂጂ›› አለቻት፡፡ ዮርዳኖስን ተሸግራ ሄዳ 47 ዓመት በበረሃ ብቻዋን ስትጋደል ኖረች፡፡ ሰይጣንም በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር፡፡ 40 ጾምን ሊፈጽም ቅዱስ ዞሲማስ ወደ በረሃው መጣ፡፡

በዚያ በረሃ ውስጥ የሚጽናናበትን ነገር እንዲሰጠው ወደ ጌታችን ጸለየና ማርያምን ገለጠለት፡፡ ሲጠጋት ሮጣ አመለጠችውና ‹‹ዞሲማስ ሆይ ጨርቅ ጣልልኝ›› ብላ በስሙ ስትጠራው እጅግ ደነገጠ፡፡ ልብሱንም ከሰጣት በኋለ ሰገደላት፡፡ ገድሏንም እንድትነግረው በብዙ ለመናትና ነገረችው፡፡ በዓመቱ ሥጋ ወደሙን አምጥቶ እንዲያቆርባት ጠየቀችው፡፡ በዓመቱ መጥቶ አቆረባት፡፡ አሁንም በዓመቱ ይመጣ ዘንድ ለመነችው፡፡ ድጋሚም ሲመጣ ዐርፋ አንበሳ አስክሬኗን ሲጠብቀው አገኛት፡፡ አንበሳውም መቃብሯን ቆፍሮ አሳየውና ገንዞ ቀበራት፡፡ ገድሏንም ለመነኮሳቱ ሁሉ ነገራቸው፡፡

አባ ዞሲማስም ከደጋግ ክርስቲያን ፍልስጤማውያን ወላጆች የተገኘ ጻድቅ ነበር፡፡ ለመምህርም ሰጥተውት በሚገባ ተምሮ ካደገ በኋላ መነኮሰ፡፡ ሲሠራም ሆነ ሲበላ እንኳን ምስጋናን ከአፉ የማያቋርጥ ደገኛ አባት ከሆነ ከ45 ዓመት በኋላ ቅስና ተቀበለ፡፡ ተጋድሎውንም ጨምሮ 13 ዓመት ከቆየ በኋላ ሰይጣን በልቡ ክፉ ሀብን አሳደረበት፡፡ በልቡም ከበጎ ሥራዎች ሁሉ እኔ ያልሠራሁት ምን ነገር አለ?›› ይል ጀመር፡፡ ጌታችንም ሊተወው አልወደደምና መልአኩን ልኮ ወደ ዮርዳኖስ አቅራቢያ ወዳለው በረሃ እንዲሄድ ነገረው፡፡ በዚያም ሌሎች ደጋግ አባቶችን አገኘና ከእነርሱ ተማረ፡፡ በዚያም ሳለ ወደ በረሃው ገብቶ የሚጽናናበት ነገር ይገልጥለት ዘንድ ወደ ጌታችን በጸለየ ጊዜ ነው ማርያምን ያገኛት፡፡ ዞሲማስ ብሔረ ብፁዓንም ድረስ ሄዶ የቅዱሳንን አኗኗራቸውንና ገድላቸውን አይቶ የጻፈልን ታላቅ አባት ነው፡፡ (ሙሉ ገድሉን በዕረፍቱ ዕለት ሚያዝያ 9 ቀን እናየዋለን) ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!

      • ጻዲቁ ኖኅ፡- እርሱም ከአባታችን አዳም ጀምሮ 10ኛ ትውልድ ነው፡፡ ከታናሽነቱ ጀምሮ ኃጢአት እንደሚበዛና ደጋጎች እንደሚያንሱ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በጥፋት ውኃ እንደሚደመሰስ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያይ ሆነ፡፡ ስለዚህም ፊቱ የተቋጠረ ሆኖ ፈጽሞ ያለቅስ ነበር፡፡

ጻድቁ ኖኅ ኖኅም የአቡዚር ልጅ የሆነች ሐይከል የምትባል ሴት አግብቶ ወደ እርሷ ሦስት ጊዜ ቢገባ ሦስት ልጆችን ሴም ካም ያፌትን ወለዳቸው፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ለኖኅ ከደብር ቅዱስ ዕንጨት ቆርጦ መርከብን እንዲያሠራ ካዘዘው በኋላ አሠራሯን በዝርዝርና በጥልቀት አስረዳው፡፡ የቃየል ልጆችም ኖኅን መርከብ ሲሠራ አይተው ዘበቱበት፡፡ የአዳምንም ሥጋ ወስዶ በውስጡ አኖረ፡፡ ሴም ወርቁን፣ ካም ከርቤውን፣ ያፌት ዕጣኑን ወስደው ወደ መርከብ አስገቡ፡፡ ኖኅም ከልጆቹና 500 ዓመት ድንግልናውን ጠብቆ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ለአባታችን አዳም ሥጋ ሲያገለግል ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ ሚስት እንዲያገባ እግዚአብሔር አዘዘው፡፡ ሥጋ የለበሰ ሁሉ እንደሚደመሰስ ከእርሱ ዘር በቀር የሚተርፍ እንደሌለ ነገረው፡፡ ጻድቁ ከሚስቶቻቸው ጋራ ወደ መርከቡ ገባ፡፡ ንጹሐን የሆኑት እንስሳትና አእዋፋት ሴትና ወንድ ሰባት ሰባት፣ ንጹሐን ካልሆኑት ደግሞ ሁለት ሁለት ሴትና ወንድ አስገባ፡፡ ከዚያም ሰማይ ተከፍቶ የምድርም ምንጮች ሁሉ ተነድለው ራጃጅም ተራራዎችም እስኪሸፈኑ ድረስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ዘነመ፡፡ ውኃውም በላያቸው 15 ክንድ ከፍ አለና ሥጋ የለበሰ ሁሉ ሞተ፡፡

ከ150 ቀንም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን አስቦ ነፋስን በምድር ላይ አመጣና ውኃውን አጎደለ፡፡ ምንጮች ተደፍነው የሰማይ መስኮት ተዘጋ፡፡ መርከቢቱም በ7ኛው በ12ው ቀን አራራት ተራራ ላይ አረፈች፡፡ ከጊዜም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን ከነቤተሰቡ አንድ ላይ ከመርከቡ እንዲወርዱ አዘዘው፡፡ ኖኅም መሠዊያን ሠርቶ ንጹሕ ከሆኑት ሁሉ ወስዶ መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር መልካም መዓዛን አሸተተ፡፡ ዳግመኛም ምድርን በንፍር ውኃ እንዳያጠፋ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ ምድር ፀንታ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ዘር መከር፣ ቅዝቃዜና ሙቀት፣ በጋና ክረምት፣ መዓልትና ሌሊት እንደማይቋረጥ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፡፡ ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉዋት ግዟት አላቸው፡፡
ኖኅም ምድርን ያርሳት ይቆፍርራትም ጀመር፡፡ ወይንም ተክሎ ከእርሶ ፍሬውን አድርሶ ወይን ጠጥቶ በሰከረና ራሱን በሳተ ጊዜ የከነዓን አባት ካም የኖኅን ራቁትነት አይቶ ሳቀ፣ ሄዶም ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ ያፌትና ሴምም ልብስ ወስደው የአባታቸውን ርቃን ሸፈኑ፡፡ ኖኅም ከስካሩ በነቃ ጊዜ ሁሉም ያደረጉትን ዐወቀ፡፡ ‹ከነዓን የተረገመ ይሁን፣ ለወንድሞቹም ተገዥ አገልጋይ ይሁን› ብሎ ከረገመው በኋላ ‹‹የሴም ፈጣሪ እግዚአብሔር ይመስገን፣ እግዚአብሔርም የያፌትን አገር ያስፋ፣ በሴም ቤትም ይደር›› ብሎ መረቃቸው፡፡ አባታችን ኖኅ ‹‹እግዚአብሔር በሴም ቤት ይደር›› ማለቱ የጌታችንን ሰው መሆን በትንቢት መናገሩ ነው፡፡ እርሱም ከጥፋት ውኃ በኋላ 350 ኖረ፡፡ በአጠቃይ ዕድሜው 950 ዓመት በሆነ ጊዜ በሰላም ዐረፈ፡፡
የአባታችን የቅዱስ አባ ኖኅ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ንጉሠ እስራኤል ቅዱስ ዳዊት፡- ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ነሐሴ 13 ቀን ተጸነሰ፣ በሚያዝያ 6 ቀን በይሁዳ በቤተልሔም ሀገር ተወልደ። 1ኛ ሳሙ 16፡10-11፡፡
ዳዊት ማለት ‹‹ኅሩይ›› ማለት ነው። አንድም ‹‹ልበ አምላክ›› ማለት ነው። ሐዋ 13፡22፡፡ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ነው። አባቱ እሴይ እናቱ ሁብሊ ይባላሉ። ሁብሊ መልከ መልካም ሴት ነበረች። ከጎረቤታቸው ያለ ጎልማሳ መልኳን እያየ በሐጸ ዝሙት ተነደፈ። እሴይ የእሷም ፈቃድ እንደሆነ አውቆ መንገድ እሄዳለሁ ብሎ ስንቁን ይዞ ወጣ። የሄደ መስሎ ከዚያው ውሎ ሲመሽ በልብሱ ተሸፋፍኖ ድምጹን ለውጦ ያንን ሰው መስሎ ገብቶ ከእርሷ ጋር አድሮ ጎህ ሳይቀድ ወጥቶ ሄደ። ዳዊት በዚህ ዕለት ተጸንሷል።

1 month, 1 week ago

"ለዐቢይ ጾሙ የሚኾኑና በ MP3 የአዘጋጀሁትን የንስሓ የመዝሙራት ስብስብ አጣነው" እያላችሁ በተደጋጋሚ ለጠየቃችሁ እኅት ወንድሞች ኹሉ!
(መዝሙሩን በድጋሚ "share" አድርጌላችኋለሁ። መዝሙራቱ ፍጹም የንስሓ ሲኾኑ ከምድራዊው ዓለም አውጥተው በመንፈስ ቀራኒዮ ወስደው የመድኀኔ ዓለም ክርስቶስን መከራ መስቀል የሚያሳዩን የሚያሳስቡን ስለሆኑ ተጠቀሙባቸው።)

3 months, 1 week ago

ከረቡዕ ጥር 29 ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 4 ድረስ ለመሸጥ ታስቦ የነበረው "መልክዐ ጉባኤ" መጽሐፍ ዛሬ ሐሙስ ጥር 30 ምሳ ሰዓት ላይ የመጀመሪያው 650 ኮፒ ተሸጦ አልቋል።

2ኛው ዙር የፊታችን ቅዳሜ ሳምንት (የካቲት 9) ይወጣል። ስለዚኽ ተራ ለመያዝ የተመዘገባችሁም ሆነ ገንዘቡን የከፈላችሁ እኅት ወንድሞቼ ከታላቅ ይቅርታ ጋር እስከ የካቲት 9 ድረስ እንድትታገሡኝ በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ!!!

(ለምትልኳቸው ተቀባይ ወዳጅ ዘመዶቻችሁም መረጃውን በማድረስ ተባበሩኝና ቅዴሜ የካቲት 9 ድረስ በተደጋጋሚ እንዳይደውሉ ንገሩልኝ። "ሳናገኘው እንዳንቀር" ብላችሁ በስጋት በተደጋጋሚ የምትደውሉልኝ እኅት ወንድሞቼም እባካችሁ ተረጋጉ! በተቻላችሁ መጠን በተደጋጋሚ መደወላችሁንም ብታቆሙት ለእኔም ዕረፍት ነው፤ አሁን ተሸጦ ያለቀው 650 ፍሬ ብቻ ሲሆን ከ3ሺው ውስጥ ወደፊት ገና ከማተሚያ ቤት የሚወጣ 2,350 መጽሐፍ አለ።)

አምላከ ቅዱሳን ፍጻሜውን ያሳምርልን!

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 6 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 3 weeks, 2 days ago

Last updated 3 weeks, 2 days ago