Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

Description
የቀጨኔ መድኀኔ ዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago

1 month ago
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ …
1 month ago

#አቡነ_ገብረ_ናዝራዊ_ዘደብረ_ኀረይክዋ_ዘጥሙጋ)፤ #ጥር_29
ጻድቅሰ በአሚን የሐዩ (ጻድቅ ግን በሃይማኖቱ በሕይወት ይኖራል) /ዕን. 2፥4፤ ሮሜ 1፥17/ ጻድቃን ምንም እንኳን በሥጋ ቢሞቱም የነፍስ ሞት የለባቸውምና ነው፡፡
አቡነ ገብረ ናዝራዊ ዘደብረ ኀረይክዋ(ዘጥሙጋ)፤ አባታቸው ስቡሐ አምላክ እናታቸው ክርስቶስ ክብራ የሚባሉና ከነገሥታት ወገን የነበሩ ናቸው፤ በ14ኛው ክፍለ ዘመን ሰሜን ሸዋ ይፋትና ጥሙጋ ደብረ ሲና ተወለዱ፡፡ ስማቸውን ያወጡላቸው ወላጆቻቸው ናቸው ገብረ ናዝራዊ ማለት በስዕለት ለእግዚአብሔር የተሰጠ ልዩና የተቀደሰ ማለት ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲማሩ አድገው በ15 ዓመታቸው ከአቡነ ዮሐንስ ዘንድ ዲቁናና ተቀበሉ፡፡
ኋላ ሥርዐተ ምንኵስናን ደግሞ ከአቡነ ጎርጎሬዎስ (የደብረ ጽጋጋው የታላቁ አኖሬዎስ ልጅ) ከተቀበሉ በኋላ የተወለዱበትን ደብር ሲያገለግሉና በምደረ ሸዋና አካባቢዋ ሲያስተምሩ ቆዩ፤ ንጉሡ ዐምደ ጽዮን የአባታቸውን ሚስት በማግባታቸው ጻድቁ አቡነ ገብረ ናዝራዊ፣ ጳጳሱ አቡነ ያዕቆብና ሌሎች ካህናት ይህንን ተግባር በመቃወማቸው ለጥቂት ሳምንታት በእስር ቤት ቆዩ፤ ጻድቁ ከእስር እንደተፈቱም በላስታ ላሊበላ ለ12 ዓመታት፣ በሐይቅ እስጢፋኖስ ደግሞ ለጥቂት ወራት ሰንብተው፤ ወደ ትግራይ ተጕዘው ከአባ የዕቆብ ዘንድ የመጻሕፍት ትርጓሜን ሲማሩ ቆዩ፤ ዛሬ በስማቸው ወደ ሚጠራው ታላቁ ገዳም እምባ ላም ደብረ ኀረይክዋ ለምናኔ ከመግባታቸው በፊትም በትግራይ ሃገር እየተዘዋወሩ ሦስት ገዳማትን መሥርተዋል፤ እነርሱም፤
#አጋዝና_ተራራ /#መበቊል_ቋጥኝ/ (ምዕራብ አዲግራት)
#ከቋጥኝ_ድንጋይ_ፈልፍለው_ያነጿት_ቂዓት_ማርያም፤ /ጻድቁ ለ8ዓመት ቆይተውባታል/
#ባለ_2ት_ዐምድና_ባለ_1_በር_አድርገው_ያነጹት_ማይ_ኢየሱስ_/#ቀበሌ_አዘባ_ቤት_ሓባ_ተራራ/
እነዚህን ገዳማት ከሠሩ በኋላ በዘንዶ እንደ አቡነ አገረጋዊ ወደ ደብረ ኀረይክዋ ተራራ ለምናኔ ወጥተዋል፤ ቦታውን ‹‹ደብረ ኀረይክዋ›› ብለው ራሳቸው ሲሆን የሰየሙት፤ ምክንያቱም ቦታው በተራራማና በተፈጥሮ የተዋበ ቦታ በመሆኑ፤ በተፈጥሮ ቅርጽነቱ ባለ ሦስት ማዕዝን ክብና በገመድ የሚወጣ ገዳም ነው፡፡

#ጻድቁ_ከሚታወቁባቸው_ነገሮች_ዋነኞቹም
በተሰጠቻው ሀብተ ፈውስ ብዙ ሕሙማንን ይፈውሱ ነበር፤
ፍጹም ተሐራሚ በመሆናቸው(የበሰለ ነገር ወደ አፋቸው ሳያስገቡ ሃያ አራት ሰዓት በዳዊት መዝሙር ይደሰቱና ላባቸው እስኪንጠፈጠፍም ይሰግዱ ነበር) ደቀ መዛሙርቶቻቸውም ከአንድ ማዕድ ውጪ አይቀምሱም ነበር፤
ይስሐቅ የተባለው ደቀ መዝሙራቸው ሩቅ ሃገር ሄዶ ሲያርፍ ተገልጾላቸው ጸሎት እንዲደረግ ለደቀ መዛሙርቶቻቸው ተናገረዋል፡፡
*ከ44ት በላይ የውኃ ጕድጓዶችን ፈልፍለዋል /ለአብነትም ማይ መስቀል፥ ማይ ዮርዳኖስ፥ ማይ መቅደስ፥ ማይ ጠላዕ፥ ማይ ፀላእ ሰዋ የሚሉት ይገኙበታል/
ሰንብታት እንዲከበሩ /በተለይ አብዛኛው ትቷት የነበረችውን ቀዳሚት ሰንበት እንድትከበር ታግለዋል/ በዚህም ከታላቁ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ቀጥሎም ሰንበትን አክብሮ በማስከበር ጻድቁ ትልቁን ቦታ ይይዛሉ፡፡
በየሃገራቱ እየተዘዋወሩ ወንጌልን የሚሰብኩና ወንጌል የሚያዘውን ያለቻቸውን ነገር ይመጸውቱ ነበር
ለደቀ መዛሙርቶቻቸውም ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲያስተምሩ፤ ሃይማኖታቸው በጸና ዓለት ላይ የተመሠረተ እንዲሆንና ሃይማኖትን ከሚያስቱ ሐሰተኞች እንዲጠበቁና ዓለምና ክብሩ እንዳያታልሏቸው ይመክሯቸው ነበር፡፡
**በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል፡፡

#ላህም_አምባ_ደብረ_ኀረይክዋ
#እንደነ #ደብረ_ዳሞ#ደብር_ማርያም #አቤር #አቡነ_ሰላማ ገዳም በገመድ የሚወጣበት ገዳም ነው፤
#በተራራማና በተፈጥሮ የተዋበና በተፈጥሮ ቅርጽነቱ ባለ ሦስት ማዕዝን ክብ ተራራ ነው፤
#የተራራው ርዝመትም 28ሜትር ነው፡፡
#ገዳሙ ከአዲግራት ደቡብ ምዕራብ በ27ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
#በወቅቱ ከገዳመ ዋሊ (ዋልድባ) ቀጥሎ ጥብቅ ሥርዓት የነበረበት ታላቅ ገዳምም ሆኖ ነበር፡፡
#ጻድቁ በአንዶ አማካይነት ተራራውን ሲወጡ የረገጡበት የእግር ጣታቸው ምልክት ያለበት ዐለት ይገኛል፤
#እናቶች ምጥ ሲይዛቸው፥ ሰዎች ሲታመሙ የሚፈውስ፥ ድርቅና ችግር ሲፈጠር ምሕረት የሚያወርድ፥ የተጣሉ ሰዎች የሚታረቁበት #ነባኢ_መስቀል (አልቃሽ መስቀል) የሚገኝበት ነው፤
#ክረምት ከበጋ የማይደርቁና ፈውስን የሚሰጥ ጠበል ያለበት ቦታ ነው፡፡

ጻድቁ #ጥር_29_ዕረፍታቸው_ሲሆን፤ የከበረ አጽማቸው በገዳመ ደብረ ኀረይክዋ ከአንድ ቋጥኝ በተጠረበ ሦስት መዓዝን ባለው ድንጋይ ታትሞ ይገኛል፡፡

**ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘተሰብሐ ወተወደሰ፤
በአፈ አምላክ አሚነ ወዕበየ ስብሐት ዘለብሰ፡፡
ገብረ ናዝራዊ እትናበብ ማኅሌተከ ሐዲሰ፤
አፉየ ምላእ እግዚኦ ማኅሌታዌ መንፈሰ፤
ወተናብቦትየ ረሲ ንባበ ቅዱሰ፡፡
/#ዋልድባ_ዋሊ/

1 month ago
[#ጥር\_29\_ጻድቁና\_ሰማዕቱ\_አቡነ\_ታዴዎስ\_ዘጽላልሽና\_አቡነ\_ማትያስ\_በውቢት\_ገደል\_](?q=%23%E1%8C%A5%E1%88%AD_29_%E1%8C%BB%E1%8B%B5%E1%89%81%E1%8A%93_%E1%88%B0%E1%88%9B%E1%8B%95%E1%89%B1_%E1%8A%A0%E1%89%A1%E1%8A%90_%E1%89%B3%E1%8B%B4%E1%8B%8E%E1%88%B5_%E1%8B%98%E1%8C%BD%E1%88%8B%E1%88%8D%E1%88%BD%E1%8A%93_%E1%8A%A0%E1%89%A1%E1%8A%90_%E1%88%9B%E1%89%B5%E1%8B%AB%E1%88%B5_%E1%89%A0%E1%8B%8D%E1%89%A2%E1%89%B5_%E1%8C%88%E1%8B%B0%E1%88%8D_)/ጽላልሽ፥ ከሰም ወንዝ ቆላ ውስጥ የሚገኝ/ …

#ጥር_29_ጻድቁና_ሰማዕቱ_አቡነ_ታዴዎስ_ዘጽላልሽና_አቡነ_ማትያስ_በውቢት_ገደል_/ጽላልሽ፥ ከሰም ወንዝ ቆላ ውስጥ የሚገኝ/ #ተወርውረው_ሰማዕትነት_የተቀበሉበት_ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ለብዙ ዓመታት ጠፍ ኹኖ ቆይቶ በ2005ዓ.ም. የመቃኞ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶለታል፡፡
#አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፤ አባታቸው ካህኑ ሮማንዮስ /የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አጎት/ እናታቸው ማርታ ይባላሉ፡፡ የትልድ ቦታቸው ጽላልሽ ዞረሬ ነው፡፡ ሲወለዱ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ የታየ ሲሆን እርሳቸውም በብርሃን ልብስ ተጠቅልለው ታይተዋል፡፡ ትምህርታቸውን ከሊቀ ካህናቱ ለሕይወት ብነ በጽዮን በሚገባ ተምረዋል፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዳሞት ተሻግረው ሞተሎሚን አስተምረው ካሳመኑት በኋላ አቡነ ታዴዮስን ወደ እርሳቸው እንዲመጡ ልከውባቸው ሄደው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እያገለገሉ ዘጠኝ ዓመት ተቀመጡ፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ግን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አባ በጸሎተ ሚካኤል ሲሄዱ አቡነ ታዴዎስም ወደ ጽላልሽ ተመልሰዋል፡፡ ሁለቱም ከ32 ዓመት በኋላ ተመልሰው በጽላልሽ ተገናኘተው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለአቡነ ታዴዎስ ማዕረገ ምንኵስናን ሰጥተዋቸዋል፡፡ ከዚያም አቡነ ታዴዎስም በሥጋ ዕድሜ ታላቅ ቢሆኑም እንደታናሽ ብላቴና አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እያገለገሉ በደብረ ሊባኖስ ተቀምጠዋል፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ታዴዎስን ወደ ጽጋጋ እንዲሄዱ ነገሯቸው ምክንያቱም አቡነ አኖሬዎስ በዚያ ሲያስተምሩ ከሃዲያን ደብድበው አስረዋቸው ነበርና አቡነ ታዴዎስን ሕዝቡን ከኃጢአት ግዞት፥ አኖሬዎስን ከእስራት እንዲያስፈቱ ላኳቸው፡፡
አቡነ ታዴዎስም በነፋስ ሠረገላ ተጭነው መዩጥ ከተባለውና አኖርዮስን ካሰራቸው ንጉሥ ፊት ቢደርሱ ንጉሡ በግንጋጤ መልአክ የመጣበት መስሎት ሲፈራ ከሰው ወገን መሆናቸውን ነግረው ክርስትናን አስተማሩት፡፡ ጋኔን ከእሳት ጥሎት ሲሠቃይ የሚኖርና ሊሞት የደረሰ ልጁን ቢፈውሱለት በትምህርታቸውና በተአምራታቸው አምኖ ሕዝቡ ክርስትናን እንዲቀበል በአዋጅ አስነገረ፡፡ አፍጃል የሚባለው ባለጸጋ ወደ አቡነ ታዴዎስ ቀርቦ ሲማር ‹‹ባለጸጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀላል›› (ማቴ 19፡24፣ ማር 10፡25፣ ሉቃ 18፡25) የሚለውን የወንጌል ቃል ሲሰማ ለአእምሮው ረቆበት ‹‹እስቲ አድርገህ አሳየኝ?›› አላቸው፡፡ አቡነ ታዴዎስም እናቲቱን ግመል ከነጇ ቀጥሎም 28 ግመሎችን በየተራ በመርፌ ቀዳዳ እያሾለኩ አሳይተውታል፡፡ ሕዝቡ ሁሉ በእጅጉ ሲገረምና ‹‹በአምላከ ታዴዎስ ስም አምናለሁ›› ሲል የባለጸጋው ልጅ ሙሳ ግን ‹‹በምትሃት አሳይቶን ነው እንጂ የእውነት አይደለም›› በማለት አባቱንም እንዳያምን ይናገር ጀመር፡፡ ይህንንም ሲናገር በመጀመሪያ ያለፈችው እናቲቱ ግመል ረግጣ ገደለችው፡፡
አቡነ ታዴዎስም ንጉሡን፣ አባቱን አፍጃልንና ሕዝቡን የሞተ እንደሚነሣ ሲያስተምራቸው ‹‹የሞተ ይነሣልን? እስኪ ይህ የሞተው ልጅ ይነሳና ሁሉም አይቶ ይመን›› አሏቸው፡፡ እሳቸውም ‹‹ዛሬ ተቀብሮ ይዋልና ነገ በሦስተኛው ይነሣል›› ብለዋቸው ተቀብሮ ዋለ፡፡ በማግሥቱም አፍጃልን ጠርተው ‹‹‹አልዓዛርን ከሞት ባስነሣው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ልጄ ሆይ ና ውጣ› ብለህ ከልጅህ መቃብር ላይ አኑረው› ብለው ዘንጋቸውን ሰጡት፡፡ ሄዶም እንዳሉት ቢያደርግ ልጁ አፈፍ ብሎ ተነሥቷል፡፡ ይህንን ያዩ የሀገሩ ሰዎች ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል፡፡ እሳቸውም 12 አብያተ ክርስቲያናትን አሳንጸው ሞቶ የተነሳውን ሙሳን ሙሴ ብለው ሰይመው አስተምረው ሊቀ ካህናት አድርገው ሾመውት አቡነ አኖሬዮስን ይዘው ወደ ጽላልሽ ዞረሬ ተመልሰዋል፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በኋላ አባ ያዕቆብ የተባሉ ጳጳስ ከግብፅ መጡ፡፡ የአቡነ ታዴዎስን ዜና ሲሰሙ ተደስተው ከአቡነ ፊልጶስ ጋር ሆነው አስጠርተዋቸው ‹‹የአባታችሁን ዜና ገድል ንገሩኝ›› አላቸው፡፡ አቡነ ታዴዎስም ‹‹ጨዋታ በአስተርጓሚ አይሰምርም›› ብለው ወደ ጌታችን ቢጸልዩ የጳጳሱ ቋንቋ ለታዴዎስ፣ የታዴዎስም ቋንቋ ለጳጳሱ ተገልጦላቸው የመሸ የነጋ ሳይመስላቸው 40 ጾምን ሲጨዋወቱ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ጳጳሱ ከንጉሡ ተማክረው ‹‹ሊቀ ካህናት ዘጽላልሽ›› ብለው ሾመዋቸዋል፡፡
በነግህና በሰርክ ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ፣ ቀን ወንጌልን እየሰበኩ፣ ሌሊት ከባሕር ገብተው ሲጸልዩ እያደሩ በታላቅ ተጋድሎ እየኖሩ ሳለ ከ10 ዓመት በኋላ ሰይጣን በንጉሡ በዓምደ ጽዮን ፍቅረ ዝሙት አሳድሮበት በክፉዎችም ምክር አታሎት የአባቱን ቅምጥ አገባ፡፡ አቡነ ታዴዎስም ይህን ሲሰሙ እንደ ነቢዩ ኤልያስና እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በቀጥታ ሄደው ንጉሡን ገሥጸው አወገዙት፡፡ ገሥጸውና አውግዘው አቡነ ማትያስን አስከትለው ሲመለሱ ቅምጧ የንጉሡ ሚስት በፈረስ ተከትላ ደርሳ የኋሊት አሳስራ ዛሬ ‹‹ማርያም ገዳም›› ከሚባለው ቦታ ፊት ለፊት ካለውና ‹‹ውቢት ገደል›› ከሚባለው ትልቅ ገደል ውስጥ ሁለቱንም ጣለቻቸውና ጥር 29 ቀን በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡
በሰማዕትነት ዐርፈው ደማቸው ከፈሰሰበት ከገደሉ ስር በፈለቀው ጸበላቸው ‹‹ታዴዎስ ወማትያስ›› እያለ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያለ የተጠመቀ ሰው እንደ 40 ቀን ሕፃን እንደሚሆን ጌታችን ቃልኪዳን ገብቶላቷቸዋል፡፡ ይህ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ የተሠራው ቤተ ክርስቲያናቸው በጠላት ወረራ ጊዜ ፈርሶ ቦታው ጠፍ ሆኖ የኖረ ቢሆንም የአካባቢው ሕዝብ ቦታውን ከልሎ በክብር ሲጠብቀው ስለኖረ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ የአቡነ ታዴዎስ ታቦታቸው በ2005 ዓ.ም ከኢቲሣ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ወጥቶ ጻድቁ ሰማዕትነት በተቀበሉበት አካባቢ በተሠራው መቃኞ ቤተ ክርስቲያናቸው በታላቅ ክብር ገብቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑም ከኢቲሣ በእግር የአንድ ሰዓት ተኩል ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
(ዋቢ፤ ገድለ ታዴዎስ፣ በ2009ዓ.ም. የዋሊ ተጓዦች የቦታው አባቶች በቃል የነገሩን፣ በቦታው የተዘጋጀች በራሪ ጽሑፍ፣ ከገድላት አንደበት)

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

3 months, 2 weeks ago
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ …
3 months, 2 weeks ago
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ …
3 months, 2 weeks ago

ሥርዐተ ማኅሌት ዘኅዳር ፲፫
በዓለ አዕላፍ መላእክት

ልዩ አዋጅ ዘኅዳር አእላፍ መላእክት

የኅዳር አዕላፍ መላእክት የማኅሌቱ ሥርዐት በዋነኝነት ‹‹የመልክአ አዕላፍን›› የሚከተል ነው፡፡ ነገር ግን እንደ አዲስ አበባ ደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ያሉት ደግሞ ‹‹መልክአ እግዚአብሔር አብን›› ይከተላሉ።

በዚህ ሥርዓተ ማኅሌት ውስጥ ‹‹የመልክአ አእላፍ››ን ቁመት የሚቆሙ አድባራት ያስቀደምን ሲሆን በመቀጠልም የአዲስ አበባ ደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያንን ሥርዓተ ማኅሌት አያይዘን አስቀምጠናል።

‹‹የመልክአ አዕላፍ››ን ቁመት የሚቆሙ አድባራት እንደ አጣጣሚ ሚካኤል እና ፊት ሚካኤል ያሉትን ከነዚቆቻቸው አስቀምጠንላችኋል።

✤ መልካም በዓል ይሁንላችሁ✤

3 months, 3 weeks ago
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ …
3 months, 3 weeks ago
ለቀጣይ ሦስት ዓመታት (ከ 2017 - …

ለቀጣይ ሦስት ዓመታት (ከ 2017 - 2019 ዓ.ም )የፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምሕርት ቤትን ለመምራት በዕጣ የተመረጡ

ሥራ አመራሮች እና አስፈጻሚዎች

መልካም የአገልግሎት ዘመን ይሁንላችሁ!
https://t.me/finotehiwott

3 months, 4 weeks ago
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ …
4 months ago
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ …
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago