ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 day, 23 hours ago
Last updated 3 days, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 1 day ago
*? የከፍተኛ ትምህርት መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ‼️*
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ፦
#ለመጀመሪያ_ዙር_ተፈታኞች** !
↘️ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር
• ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351
• በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339
• ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ 300
• በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ 380
↘️ በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300
• ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254
• በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250
• ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች 250
• በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ ነጥብ 280
↘️ በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250
(የ2ኛው ዙር ተፈታኞች የመቁረጫ ነጥብ ሙሉ መረጃ ከላይ በምስሉ ተያይዟል ያንብቡ)
? • ይቀላቀሉን • ? ???
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
https://t.me/+2g72gKcjS_E4Mjdk
*? በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከነገ ህዳር 27 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 3 ድረስ ለአንድ ሳምንት ይዘጋሉ ‼️*
↘️ እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ መምህራን ፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች ለሀገራዊ ትግል እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ አስተዋጽኦ ያድረጋሉ።
↘️ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ቀናት ያልተሰበሰቡ የዘመች ሰብል መሰብሰብ እና ቤተሰብን የመርዳት ዘመቻዎች በስፋት ይካሄዳል።
?ፈተናው ተሰረቀ?
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተሰርቋል ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት እና ፈተናውን ለማግኘት ከታች ባለው ሊንክ በቴሌግራም ተለቋል ???
https://t.me/joinchat/Fdr1-SpzBylmYTk0
https://t.me/joinchat/Fdr1-SpzBylmYTk0
የዪኒቨርስቲ ምደባ
----------------
ለመቐለ ፤ አክሱም ፤ አዲግራት ፤ ራያ እና ወልዲያ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ
ከላይ በተጠቀሱት ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና በፀጥታ ምክንያት ትምህርታችሁን መቀጠል ያልቻላችሁ ተማሪዎች ተቋርጦ የነበረዉን ትምህርታችሁን እንድትቀጥሉ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በወሰነው መሰረት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በጊዜያዊነት የተመደባችሁ ስለሆነ በተቀመጠዉ አድራሻ https://www.placement.ethernet.edu.et/ የተመደባችሁበትን ዩኒቨርስቲ ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የተመደባችሁበት ዩኒቨርስቲ ጥሪ ሲያደርግላችሁ ብቻ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
ምደባዉ እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. የነበረዉን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳን ጨርሰው የወጡት ተማሪዎችን ብቻ ይመለከታል፡፡
ምደባዉ የተካሄደዉ መረጃዎችን በትክክል ላሰገቡ ተማሪዎች ሲሆን፣ በተጠየቀዉ መሰረት መረጃዎችን በትክክል ያላስገቡ ተማሪዎችና የኦን ላይን ፎርሙን በተለያየ ምክንያት በወቅቱ መሙላት ያልቻላችሁ ተማሪዎች ስማችሁን ኦንላይን ምደባ በሚረጋገጥበት ሶፍትዌር ላታገኙ ስለምትችሉ፣ በነበራችሁበት የትምህርት ክፍልና ዩኒቨርሲቲን መነሻ በማድረግ በዲፓርትመንት ስለተመዳባችሁ፣ የተመደባችሁበት ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ፡፡
ተመዝግባችሁ ሳትመደቡ የቀራችሁ ተማሪዎች በቂና ግልፅ መረጃ ያላቀረባችሁ በመሆኑ ያልተመደባችሁ መሆኑን በመገንዘብ ትምህርት ክፍላችሁ የተመደበበትን ዩነቨርስቲ በአካል በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳዉቃለን፡፡
ያልተመዘገባችሁ እና ቅሬታ ወይም አቤቱታ ያላችሁ ተማሪዎች በተቀመጠዉ የቴሌግራም ቦት አድራሻ(@moeplacementbot) አቤቱታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን አቤቱታዎችን በአካል የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
በዩኒቨርስቲዎቻችሁ ተፈቅዶላችሁ እረፍት(Withdrawal) ላይ የነበራችሁ ተማሪዎች የትምህርት ክፍላችሁ ለተመደበበት ዩኒቨርስቲ ማስረጃቻዉን አቅርባችሁ የሚታይላቸዉ ይሆናል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር
ጥቅምት 25/2014 ዓ.ም
" ይህንን ጊዜ እናልፈዋለን ፤ ሀገር ይቀጥላል" ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ
---------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች አሸባሪው የህወሃት ቡድን በሀገር መከላከያ ሰሜን እዝ ላይ ጥቅምት 24 /2013 ዓ.ም ባደረሰው ክህደት ለተሰው የሰራዊት አባላት መታሰቢያ ቀን አክብረው ውለዋል ፡፡
ቀኑም ” አልረሳውም ፤ እኔም የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ” በሚል መሪ ቃል ታስቦ ውሏል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) ከአንድ ዓመት በፊት በሀገራችን የተከሰተው ጉዳይ በማንኛውም ሀገር ያልሆነ በኢትዮጵያ ታሪክም የማይረሳ ነው ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ በመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ይህንን ጊዜ እናልፈዋለን ሀገርም እንደ ሀገር ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።
አሁንም በርካታ ዜጎች መሰዎት እየሆኑ መሆኑን ገልፀው ትግሉ የሀገር መኖርና አለመኖር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህ ቡድን እኔ ካልገዛሁ አጠፋችኋለሁ የሚል፣ ሞራል የሌለው ነው ሲሉም ገልፀውታል፡፡
ሚኒስትሩ ይህንን ጦርነት ቶሎ አጠናቆ ወደ ስራ መመልስ እንደሚገባ ጠቅሰው እንደ ሚኒስቴር መስሪያቤት በተሰማራንበት ስራ ውጤታማ መሆን ይገባል ብለዋል፡፡
በመታሰቢያ ስነ ስርዓቱም የሻማ ማብራት እና የመታሰቢያ የህሊና ፀሎት መርሃ-ግብር ተከናውኗል።
በመቀሌ ፣ በአዲግራት፣በአክሱም ፣በራያና በወልድያ ዩኒቨርስቲዎች የ 2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ለመመደብ ያስችለን ዘንድ አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃችሁን በሚከተለው ሊንክ ተጠቅማችሁ ከዛሬ ጀምሮ እስከ አርብ 26/2/2014ዓ.ም እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን። link-
https://forms.gle/33My9GLyykYHg6K49
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 day, 23 hours ago
Last updated 3 days, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 1 day ago