ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago
ጠቅላላ ጉባዔ
ቀን የካቲት 30
ሰዓት 3:00
ቦታ በካቴድራሉ አዳራሽ
የእውቀት ብትሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
"ኹለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይኽ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለኹ፡፡"
ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት
በትላንትናው ዕለት ቅዱስ ጋብቻችኹን በቅድስት ቤተክርስቲያን የፈጸምማችኹት የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባል የሆንሽው ወ/ሮ አስናቁ ወርቁ እና አርገኔ ተሾመ የፈጸማችኹትን ጋብቻ የአብርሃምንና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ የትዳር ሕይወታችኹን ይባርክላችኹ፥ ይቀድስላችሁ። ያዋሕዳችኹ፤
እውቀት ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤታችን መልካም ምኞቷን ትገልጽላችኋለች ።
መልካም ጋብቻ
" አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። " (ኢዮ 2÷12)
ጾመ ነነዌ የካቲት 11/ 2011 ዓም ይገባል።
ጾሙ ለእኛ የምንባረክበትና በረከትን የምናፍስበት፤ ለሀገራችን፣ለቤተክርስቲያናችን እና ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት... እንዲሰጥ አበክረን የምንጸልይበት ያድርግልን።
ጾም የነነዌ ሰዎችን በዮናስ አማካኝነት በሦስት ቀን ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት አማካኝነት የዳኑበት ሲሆን፣ የሰው ልጅም ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ከተጸጸተ እግዚአብሔር መልስ እንደሚሰጥ የተረዳንበት ጾም ናት፡፡
ይህች ጾም የሦስት ቀን ብትሆንም ብዙ በረከት እና ረድኤት የምናገኝባት ጾም ነች፡፡ በዚህም ጾም የነነዌ ሰዎች ከትልቅ እስከ ትንሹ ንጉሡንም ጨምሮ ልባቸውን ሰብረውና ተጸጽተው አምላክ ምሕረትን
ይሰጣቸው ዘንድ ማቅ ለብሰው አመድ ነስንሰው የጸለዩበት ጊዜ ነው፡፡
ፈጣሪያቸው እግዚአብሔርም ከልብ መጸጸታቸውን አይቶ ከቁጣው ተመልሶ
ሊመጣባቸው ከነበረው ጥፋት ድነዋል፡፡
(ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1 እና 2 ይመልከቱ)
እኛም ክርስቲያኖች ይህን በማዘከር
ንስሐ ብንገባ እንደ ነነዌ ሰዎች ከተቃጣው ማንኛውም መቅሰፋት እንድናለን፡፡ በማለት በየዓመቱ ከዐብይ ጾም መግቢያ ሁለት ሳምንት አስቀድሞ ካለው ከዕለተ ሰኞ ጀምሮ እስከ ረቡዕ ድረስ “ጾመ ነነዌ” በማለት እንጾማለን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ አስቀድሞ የሚመጣብንን መቅሰፍት የሚያይ አምላክ
ከሚመጣብን መከራና መቅሰፍት ሁሉ ይጠብቀን !
የነነዌ ህዝብን በምህረቱ የጎበኘ ቸር አባት ለሀገራችንም ለህዝባችንም ምህረትና ቸርነቱን ያብዛልን ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን
ለመንፈሳዊነት ቅድሚያ እንስጥና የእግዚአብሔርን ብድራት እንጠብቅ እግዚአብሔር ፆማችንን ፆመ ድህነት ፥ፆመ ስርየት፥ ሰይጣንን ድል መንሻ ፥የኃጢአት መደምሰሻ፥ መንግሥተ ሰማያትን መውረሻ ያድርግልን አሜን።
የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያም እና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል የእውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት መረጃና መዛባት ክፍል
በሸርካ ወረዳ 11 ኦርቶዶክሳውያን በጥምቀት ማክበሪያ ቦታ ላይ ተገደሉ፡፡
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሽርካ ወረዳ ኅዳር 19/2017 ዓ/ም በታጣቂዎች 11 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል፡፡
ከግድያው በእግዚአብሔር ፈቃድ ማምለጣቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የገለጹት መረጃ ሰጭው የ13 ዓመት አዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተወስደው በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያው ላይ መገደላቸውንና 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡
እየተገደሉ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን አርሰው የሚያድሩና ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎና ግንዛቤ የሌላቸው መሆናቸውን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሞቱትን ከመቅበር ባለፈ የተሻለ መፍትሔ አላመጡልነም ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በርካታ የአካባቢው ምእመናን ከአካባቢው የሸሹ መሆኑን ያነሱት መረጃ ሰጭው ሰው ተወልዶ ባደገበት ሀገር በሃይማኖቱ ምክንያት እየተገደለ ነው ያሉ ሲሆን ሀብት ንብረታችንን ጥለን ለመኖር ተገደናል ብለዋል፡፡
አሁን ላይ ከ20 በላይ አብያተ ክርስቲያናት የተዘጉ ሲሆን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን በስደት ላይ ናቸው ሲሉም አክለዋል፡፡
በመጨረሻም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ ወረዳ 140 የሚደርሱ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን ገልጸው መላው የዓለም ሕዝብና ኦርቶዶክሳውያን ሞታችንን ባታስቆሙልን እንኳን የነዚህን ሰማዕታት ምስክርነት በማሳወቅ የድርሻችሁን ተወጡ ሲሉ አሳስበዋል፡፡
©MK TV
??????????????
"ቤተክርስቲያንን አንተዉም"
ከ20 ሺህ ሰው በላይ የሚሳተፍበት
10ኛው ማዕዶት ለኢትዮጵያ
ልዩ ኦርቶዶክሳዊ የኪነጥበብ መርኃግብር
ሕዳር 29 – 2017 ዓ.ም ይደረጋል፡፡
ቦታ ሰዓሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ በተዘጋጀ ልዩ ቦታ
መግቢያ ዋጋ 200 ብር
ገቢዉ
የደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ለሚያሰራው ህንፃ የሚዉል
አዘጋጅ
ማዕዶት የኪነጥበብ እና መንፈሰዊ ኩነቶች አዘጋጅ ከእውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት ጋር በመተባበር
ከአሁኑ ቀጠሮዎን ያስተካክሉ፡፡
ትኬቱን
በቴሌ ብር
በአሐዱ ባንክ ቅርንጫፎች
- ጊዮርጊስ ምንሊክ አደባባይ ቅርንጫፍ
- አያት አያት ቅርንጫፍ
- ቦሌ ማተሚያ አፍሪካ ጎዳና ቅርንጫፍ
- ሣርቤት አፍሪካ ሕብረት ቅርንጫ አምስት ኪሎ መንበረ ፓትሪያርክ ቅርንጫፍ
- ቦሌ መድኃኔዓለም ቅርንጫፍ
- ፊላሚንጎ መስቀል አደባባይ ቅርንጫፍ
- ማዐድን ሚኒስቴር አጠገብ ሰአሊተ ምሕረት ቅርንጫፍ
- ሰዓሊተ ምህርት ቅርንጫፍ
- ጎሮ ቅርንጫፍ
- 5 ኪሎ ቅርንጫፍ
- አሐዱ ባንክ ጀሞ ቅርንጫፍ
- አሐዱ ባንክ ገርጂ እምፔሪያል
- መገናኛ ቤተልሔም ፕላዛ ካንጋሮ ጫማ
- 6 ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በር ላይ
- 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ 1ኛ ፎቅ hanny mobile
- ልደታ ቤተክርስቲያን ጽናጽል መዝሙር ቤት
- አስኮ ኪያ በርገር
- መርካቶ ራጉኤል ልዳ( ዘአብ) መዝሙር ቤት
- ዑራኤል ቤተክርስቲያን ቤተ መርቆሪዎስ መዝሙር ቤት
- ሳሪስ አርጋኖን ነዋየት ቅድሳት
- ቦሌ አራብሳ በ +251920487968 ወይም
+251929008255
ለበለጠ መረጃ
በቴሉግራም https://t.me/maedot1212 እና
በዌብሳይታችን www.etartmedia.com አድራሻዎችን ይጎብኙ
መርሐግብሩን ማገዝ እና መደገፍ ለምትፈልጉ
በ 09 03 41 12 12 ወይንም በ 0938 60 61 62 ይደዉሉ ወይንም በቴሌግራም ያናግሩን፡፡አሐዱ ባንክ
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ሊቀ ጳጳስ በተለያዩ ቦታዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ባጡና በተጎዱ ወገኖች የተሰማቸውን ኀዘንና የማጽናኛ መልእክት አስተላለፉ።
ነሐሴ ፳፬/፳፻፲፮ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ሊቀ ጳጳስ በተለያዩ ቦታዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ባጡና በተጎዱ ወገኖች የተሰማቸውን ኀዘንና የማጽናኛ መልእክት አስተላለፉ።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት የኀዘንና የማጽናናኛ መልእክት በነሐሴ ወር በብዙ ቦታዎች የተፈጥሮ አደጋዎች መከሰታቸውን አስታውሰው ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች በእጅጉ ማዘናቸውን ገልጸዋል።
ብፁዕነታቸው ቀጥለውም ጉዳቱ በጎፋ ዞን፣ ወላይታ፣በሲዳማ ፣ በምዕራብ ጎንደር በጠለምትና በመቐለ አደጋው መከሰቱን አብራርተዋል።
በቅርብ አመታትን እንዲህ የመሰለ አደጋ በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች ተከስቶ እንደማያውቅ ያስታወሱት ብፁዕነታቸው ይህ ሰው ከሰው መጠላቱ አልበቃ ብሎ ተፈጥሮ እንኳን ምንያልህ እንደተጣላን ማሳያ ነው ብለዋል።
ይህ ዓይነቱ የተፈጥሮ መከራ የሚያስታግሰው የሥጋዊ ቀመራችንና መላምታችን ሳይሆን መሐሪው አምላክ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ተረድተን ወደ እርሱ መጮህና ማንጋጠጥ ይገባል ብለዋል።
በተለይም የአሮጌው ዓመት መካተቻ የመጪው አዲስ ዓመት መሸጋገሪ በሆነችው የኢትዮጵያ ጳጉሜን ወር ቀናት ሁላችን በእውነተኛ ንስሐ፣ በተሰበረ ልብ፣ ነገርን በተው ሕሊናና ነውር በሌላው ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመንበርከክ ምሕረት ልንጠይቅ አዲስ ዓመት ልንቀበል ይገባል ብለዋል።
ከዚሁ ጋር በአደጋው ምክንያቱም ለተጎዱ፣ ከሞቀ ቤታቸው፣ ከለመዱት ቀያቸው ተፈናቅለው #ስደታቸው በክረምት የሆነባቸውን ወጎኖቻችን አለንላችሁ በማለት በተግባር በተገለጠ ርኅራኄ ልንደርስላቸው ይገባል በማለት አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አደጋ በደረሰባቸው ቦታዎች በተለይም በጎፋ ዞን በብፁዓን አባቾች የተመራ ልዑክ በአካል ሔደው ማጽናናታቸውን ያስታወሱሰቱ ብፁዕነታቸው በሌሎች ቦታዎችም የቤተ ክርስቲያናቸን አባቶችና ልጆች የበኩላቸውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም አክለውም የሀገራችን ዜጎች ከተፈጥሮ ጋር እንዲህ ባለ ብርቱ የሕይወት ሰልፍ ላይ መሆናቸው እየታወቀ አሁንም ችግሮችን በሆደ ሰፊነትና በውይይት ለመፍታት አለመቻሉ ሌላው ኀዘን መሆኑን ገልጸዋል።
ስለሆነም ይላሉ ብፁዕነታቸው የሀገርን ክብር በመጠነ፤ የትውልድን አደራ ተሸካሚነትን ባገናዘበና ዘለቂታዊ አንድነትና አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ ችግሮችን በውይይትና በመነጋገር በመፍታትን የአዲስ ዘመንን በእውነተኛ አንድነት ልንቀበለው ይገባል በማለት አሳስበዋል።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው በመጪው ዘመን ያቀድነው እንዲሳካና ተስፋችንን እንድናገኝ ይቻል ዘንድ የሀገረ ሰላም በእጅጉ አስፈላጊ ነው። ስለሆነም ባለፈው ዘመን ያለፈብን ዋይታ፣ መፈናቀል፣ ጦርነትና ችግር ሁሉ በቃ በማለት ወደ ሰላም ልንመጣ ይገባል ሲሉ አባታዊ መልእክታቻውን አስተላልፈዋል።
ምንጭ ፦ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago