መንዙማ ሀድራ||Menzuma Hadra|| PDF

Description
ምንዳዬና ምንዳችሁ ይበዛ ዘንድ ወደዚህ ቴሌግራም ቻናል በገባችሁ ቁጥር በነብያችን(ﷺ) ላይ ሰለዋት አዋርዱ በብዕርህ✍️
መጣራት ባትችል በሰው ብዕር ተጣራ
ሰሉ ዐለ ነቢ💛

✍️Temam Al hadra

ለበለጠ መረጃ በዚህ አናግሩኝ
👇👇👇
@al_hadraw
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

4 weeks ago
ቃጥባሬ ሀድራ እንኳን አደረሳችሁ

ቃጥባሬ ሀድራ እንኳን አደረሳችሁ

ለመላው የሀገራችን የሙስሊሙ ዑማ መውሊድ ታዳሚዎች በሙሉ!
የዘንድሮው የቃጥባሬ ሐድራ መውሊዳችን ታኅሣሥ 12 & 13/ 2017 (( ጀማዱ ሣኒ 17 ና 18/ 1446)) የሚከበር  መሆኑ ተገልጿል።
አሏህ በሰላም አድርሶ በሀቂቃው ከሚሀድሩት ያርገን።

ኢንሻአላህ ማንም እንዳይቀር።

4 weeks ago

ሰይዱል ዓሪፊን ኑርሁሴን ባሌ

ክፍል ስድስት

የአናጂናው ጸሃይ ገድልና ዝና እንዲሁም አበርክቶ እንዲህ በቀላሉ የሚዘለቅ አይደለም። የሳቸው ከራማ ቁጥር ስፍር የሌለው ነው። ከራማ ማለት ባጭሩ አላህ ለደጋግ ባሮቹ የሚሰጠው ተለምዶን የሚጻረር ተዐምር ማለት ነው። አቢዮ ደግሞ ይህ ገጸ በረከት በስፋት የታደላቸው ነበሩ።

እርሳቸው በመንደራቸውና በአካባቢያቸው ዝናቸው እየናኘ ሲምጣ ጠምደው በያዟቸው ዑለማኦች ላይ ያሳዩት ጥበባዊ ከራማም እዚህ ይጠቀሳል። እኒያ ዑለማኦች ዝናቸው በአቢዮ በመወሰዱ የተከፉ ነበሩና በየቦታው እርሳቸውን ያጥላሉ ያዙ። በግልጽም አወገዟቸው። አቢዮ የተጎናጸፉት ክብር ለኛ የሚገባ ነው ባዮች ነበሩ። የዚህን ጊዜ አቢዮ ከመንደራቸው ራቅ ባለ ስፍራ ሸለቆና ወንዝ  በተንተራሰው ስፍራ ላይ ከፍተኛ ድግስ ደግሰው እኒህ ዑለሞች ይጋበዙላቸው ዘንድ አመሻሹ ላይ በክብር ጠሯቸው። ይሄን ተከትሎም ጉዱን ለማየት ጥበቡን ለመረዳት የናፈቁት ዑለማዖች በተጠሩት ጊዜና ቦታ ተገኙ። ድግሱ ማለፊያ ነበር። እድምተኛውም ተደስቷል። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ እለቱ በእጅጉ መሸ። ከየት መጣ የተባል ነጎድጓድ አዘል ደመና ዳምኖም ዝናቡን ይለቀው ገባ። ጨለማውም ከናካቴው ድንግዝግዝ ብሎ ደቀደቀ። መተያየት ቸገረ። በዚህ ጊዜ ጋባዡ አቢዮ ከነ እድምተኛቸው በጨለማ እና በጎርፍ መሃል ሊጠፉ ሆነ። አቢዮም '' እናንት ሊቃውንት ታላላቆች ናችሁና ከዚህ መከራ አውጡን '' በማለት ጥያቄ አቀረቡ።

በዚህ መሃል ዑለማዖቹ ሁሉም የአቢዮ ዕቅድ መሆኑ ገባቸው  እናም '' ሁሉም ገብቶናል አንቱ ነዎት ትልቅ አደቡን ጥሰናል ይቅር ይበሉን ቀጥለውም እርሰዎ ያትርፉን '' በማለት አግባቡ። በዚያን ጊዜ የሚያዩትን ለማንም እንዳይናገሩ አስምለው በቀላሉ በምላሳቸው አንዳች ዚክር እየዘከሩ ትከሻቸውን ምታ አደረጉት ። ውዲያውም ክትከሻቸው ቦግ ያለ ብርሃን ወጥቶ አካባቢውን አደመቀው። ይህንንም ሁሉም እንዲያደርግ አዘዙና ዚክሩን ነገሯቸው። እነሱም በተመሳሳይ ብርሃኑ ወጣላቸው። መንገዳቸውንም በዚህ መልኩ ትጉዘው  ወደ ብርሃናማው ቦታ ደረሱ። እንደደረሱም አቢዮ ' መቼም ማብራት እንጂ ማጥፋት አይከብድም በመሆኑም አሁን ብርሃኑን አጥፉት '' ሲሉ ዳግም ዑለሞቹን ጠየቁ። ዑለሞቹ አቅመቢስ መሆናቸውን ተረድተው ነበርና '' ዳግመኛ አናስቸግረዎትም  ለስካሁኑም ዐውፍ ይበሉን መብራቱንም እንዳበሩ ያጥፉት '' አሉ። አቢዮም አጠፉት ።

ዋናው ነገር አቢዮ ሁሌም ጥበበኛና ለአላህ ያደሩ መሆናቸውን፣ ብዚህ ዒባዳቸውም ዝናና ዓለማዊ መሻታቸውን ሳይሆን የአላህን ውዴታ ብቻ ፈልገው የተጉ መሆናቸውን አንጸባረቁ። በኢስላም ውስጥ እንዲህ ያሉ ከራማዎች ወይም መልካም ምግባሮች እንዳንናገር በባለቤቱ ቃል እንድንገባ ከተደረግን ባለቤቱ በህይወት እስካሉ ድረስ መናገሩ ቃል ማፍረስ ነው። ባለታሪኩ ከሞቱ ግን እንደማንኛውም ስምምነት በሞት ምክኛት ውሎች ስለሚፈርሱ የተፈቀደ ይሆናል የሚል ሸሪዐዊ ትንታኔ መኖሩን መገንዘብ ይገባል።

ይቀጥላል (7)............................

S U A L I H   A S T A T K E

@Menzu_m
👆👆Joine

4 weeks ago

"ተበድያለሁ ብለህ ለበደል አትሩጥ!
ብቻ ራቅ በልና በሶብር ሁኔታዎችን ተከታተል።ጊዜ ሃያል ነው በደንብ አድርጎ ሒሳቡን ሲያወራርድልህ ታገኘዋለህ።"

1 month ago

#የረቡዕ_መጅሊስ_ወግ
#አወሊያዎቹ

ይህ ሰአት ዱዓ ተቀባይነት የሚገኝበት ወቅት ነው። ረቡእ በዝሁር እና ዐሥር መካከል ዱዓ ተቀባይነት እንዳለው በሐዲስ መጥቷል። ከእያንዳንዱ ቀናት ጀርባ በርካታ ምሥጢሮችን የተረዱ ዓሊሞች ቀናቱን ከፋፍለው ዱዓና ሰለዋቶች በማደረግ ዘመን የሚበትነውን ጘፍላ መርታት ችለዋል።

በመጅሊስ ኒያ ሥራ ላይ ላላችሁ፣ እንዲሁም ተመችቷችሁ ዱዓ ለተቀመጣችሁ ሰዎች የሁለት አውሊያዎችን ገጠመኝ ላወጋችሁ ወደድሁ።

በቅርብ ዘመን ግብጽ ውስጥ የነበሩት ኢማም ሻዕራዊ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) መዲና ዚያራ በማድረግ ላይ ሳሉ የሰይዲን ዶሪሕ ተበሩክ ሲያደርጉ አንድ ሹርጣ (ፖሊስ) መጥቶ ይህ "ቢድዓ" ነው ብሎ ይከለክላቸዋል። አውሊያ መች የክርክር ናዳ ውስጥ ይገባል። ብዙ ካስረዱት በኋላ እንኳን እርሳቸውን በከበበው ነገር ቀርቶ አንተ እዚህ ኺድማ ላይ ባለኸው እንኳን እባረካለሁ ብለው ሰውነቱን አሻሽተው በረካውን ወሰዱ። :-D  (ዝርዝር ጭውውታቸውን ከዚህ ቀደም አጋርቼው ነበር።)

አይ ዑለማ! ልባቸው ሰፊ ነው፣ ከማይረዳቸው ሰው እንኳን መወሰድ ያለበትን ያውቃሉ። ፖሊሱ እምነቱን በተዳረዳው ልክ ነበር ግና ያላየው ዕይታ ነበር እርሱን አስተማሩት ምን አልባትም ልቡን ጠረጉለት

አንጋፋዊው ዛሒድ የነበሩት ኢብራሂም ቢን አድሀም (ረዲየላሁ ዐንሁ) አንድ ጊዜ ወደ ሻም ጉዞ ሲያደርጉ የገጠማቸውን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦ በመንገድ ላይ ሳለሁ ውሃ ጠማኝና አንድ ፍየል ጠባቂ እረኛ ስመለከት ተጠጋሁና እንዲህ አልኩት፦ የሚጠጣ ወተት ወይም ውሃ ይኖርሀል?
እንዲህ አለ፦ የትኛው ቢመጣልህ ትወዳለህ?
"ውሃ" ስል መለስኩ። በያዘው ልምጭ መሬቱን ሲወጋው ውሃ መፍለቅ ጀመረ! በጣም ተገረምኩ።
"አትገረም ጠጣ" አለኝ። ውሃውን ጠጣሁት ከበረዶ የቀዘቀዘ ከማር የጣፈጠ ውሃ ነበር። እያየሁት ቆሜ ቀረሁ። ከዚያም ይህ እረኛ እንዲህ አለኝ፦ « ኢብኑ አድሀም አንድ ባርያ አላህን ከታዘዘ ሁሉም ነገር ይታዘዘዋል።»

ምንጭ፦ [ሲየር ኢዕላም አኑበላእ ወሒሊየቱ አልአውሊያ]

አላህ የአውሊያዎችንና የዑለማዎችን ቀድር ያሳውቀን 🤲

1 month ago

ከመኝታ በፊት ...

ከቁርኣን ጋር ዕለታዊ ቆይታ አለህ ማለት ትርጉሙ፦ የውስጥህን የሚረዳልህ እንዲሁም የሚገስጽህ የሚመራህ ወዳጅ አለህ ማለት ነው። ይህ ወዳጅ ይተችሐል፣ ያበቃሀል፣ ያግዝሀል፣ ይረዳኻል። በየዕለቱ ልብህ በእነዚህ ነገሮች መታገዝ ከፈለገ ዕለታዊ የቁርኣን ዊርድህ ላይ ጽና!!

ቁርኣን ለማንም የተገራ ሙስሐፍ ነው። ይህን ውድ መጽሐፍ ለመማር፣ ለማስተማር፣ ለመረዳትና ለማስረዳት የሚሞክር ኹሉ ከሞላው በረከቱ ሳያገኝ አይቀርም። ከመጽሐፎች ኹሉ በመጀመሪያው ገጹ ላይ ጥርጥር የሌለበት ለመኾኑ ተናግሮ የጀመረ ቅዱስ ሙስሐፍ ነው።

በዱንያ ፍቅር ሰበብ ለገጠሙን የተለያዩ ውስጣዊ ቀውሶች ወደ አላህ ለመመለስ የሚረዳን፣ ዐቅጣጫ የሚሰጠን መንፈሳዊ ብርሀን ነው። ይህን የአላህ ቃል እንቅረበው፣ በፈለግነው ልክ እንጠቀምበታለን። ቁርኣን ለመማርና ለመረዳት ከበረከቱ ለመቋደስ የሚፈልገው ንጹሕ ልብ ብቻ ነው።

አላህ ይክፈትልን ያስረዳና 🤲

1 month ago

ኢንሻአላህ ኸሚስ አመሻሹን በአላህ ፊቃድ ትልቅ ዱአ ይኖረናል።

1 month, 1 week ago

የተከበረው ወር 🌙
87 ቀናት ብቻ ቀርተውታል
አላህ ደርሰዉ ከሚፆሙት ያድርገን 🤲አሏህ በስላም ያድረስን😍👌

1 month, 1 week ago

ፍልቅልቁ ዮርዳኖሳዊው ፈርጥ #ዶክተር_ሸይኽ_ማዚን_ዐብዱረሕማን_ሷሊሕ_ጛኒም
الشيخ الدكتور مازن غانم
በ1972 በሀገሪቱ ዋና ከተማ "አማን" የተወለዱ ሲሆን ዑሉሙል ቁርኣን ወተፍሲሪህ፣ኡሱሉዲን ወፉሩዒህ እና አተሰውፉል ኢስላሚይ በሚባሉ ፊልዶች ድግሪያቸውን፣ማስተርሳቸውን እና ዶክትሬታቸውን በጥሩ ሁኔታ አጥንተዋል። #ከታላቁ_ኢማምና_ሙጅተሂድ_ሸይኽ_ዐብዱሏህ_አል_ሀረርይ ዘንድም በሚገባ ተምረዋል።
#ሰዪዲ_ሸይኽ_ማዚን_ጛኒም ወደ #ሸይኹል_ኢስላም_ሸይኽ_ዐብዱሏህ_አል_ሀረርይ ዘንድ እንዴት መጡ? ...
በጊዜው የዮርዳኖስ ሙፍቲ ወደ ነበሩት #ሸይኽ_ኑሕ_አል_ቁዷት ዘንድ በመሄድ "ሸይኺ ሸይኽ ዐብዱሏህ አል ሀረርይ ስለሚባለው ሰው ምን ትላላችሁ? አንዳንዶች ሲያወግዙት፣ሲሰድቡት፣ሲያፌዙበትና ሲዋሹበት እመለከታለሁ አንዳንዶች ደግሞ ታላቅ ዓሊም ነው፣የሐዲስ ሊቅ ነው ሲሉ እሰማለሁ እንደሚባለው አይነት ዓሊም ከሆነ ደግሞ እኔ ከእርሱ ዒልምን መማር እፈልጋለሁ" በማለት ይጠይቃሉ። የዚህን ጊዜ ሙፍቲውም(ሸይኽ ኑሕ አል ቁዷት) {"እንዴታ ተማርበት እንጂ እኔም ሶሪያ በነበረት ወቅት ሐዲስ ተምሬበታለሁ።ሸይኽ ዐብዱሏህ ማለት እኮ ኢማም፣ሓፊዝ እና ሙጅተሂድ ነው። በእኔ የህይወት ዘመን ከእርሱ የበለጠ በዒልም፣በጥንቁቅነት፣በዙህድም ሆነ በተቅዋ አይቼ አላውቅም።"} በማለት ምስክርነታቸውን ይሰጧቸዋል ... ከዛም ሸይኽ ማዚን ጛኒም እንዲህ ይላሉ "#ከሸይኽ_ኑሕ_አል_ቁዷት ይህን ምስክርነት ከሰማሁ በኋላ ዒልምን ለመማር ወደ ሸይኽ ዐብዱሏህ አል ሀረርይ ጉዞየን ቀጠልኩ" ... ።

አሕሰንተ ያ ሸይኽ ማዚን አዎ እንዲህ ነው የተማሪ አደቡ ስለ አንድ ሰው ውዳሴም ሆነ ውግዘት ስሰማ የተማርከው ዒልም ሰውየውን ለመመዘን በቂ ካልሆነ በጭፍን አይኬድም እውነታውን ከተገቢ ሰው በመጠየቅ መረዳት የተማሪ ወጉ ነው።

رحمك الله يا شيخ نوح القضاة
ورحمك الله يا معلم التوحيد يا هرري
وحفظك الله يا شيخ مازن غانم

#ወዳጆቼ ከሸይኽ ማዚን ተግባር የምንረዳው ነገር ያለ ይመስለኛል። በአሁኑ ስዓት ስለ መውሊድ አሊያ ደግሞ ስለ ተወሱል ወይም ስለ ተንዚህ ሲያወራ የሰማነው ሁሉ የአህሉ ሱናህ ተከታይ ነው ማለት አይደለም። ማንነቱን የማናውቀው ሰው የሚናገረው ነገር [ዲን ነው] ብለን ከመቀበላችን በፊት ማንነው? ሰንሰለቱስ የት ድረስ ነው? ብለን ከተገቢ ሰዎች ማረጋገጥ ተገቢ ነው። ራሱን ወደ አሻዒራና ማቱሪዲያህ ያስጠጋ ሁሉ ሆኗል ማለት አይደለም። አልሐምዱሊሏህ በሚዲያው ዓለምም ጥርት ያለ ዒልምን የሚያስተላልፉ በርካታ መሻይኾችን አሏህ ሰጥቶናል እዛም እዛም መደናበር አያስፈልግም።

ወደ ዋናው ርዕስ ስንመለስ የእኒህን ወርቅየ ሸይኽ ደርስ በፔጃቸው እየገባችሁ ተከታተሉ። አትቦዝኑ ዐቅለኛ ስራ አይፈታም።

1 month, 1 week ago

ስህተትን ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ እባካችሁ ጀዛኩሙል'ሏህ ኸይራ

✍️Temam Al hadra

1 month, 2 weeks ago

#የረቡዕ_መጅሊስ_ወግ
#አወሊያዎቹ

ይህ ሰአት ዱዓ ተቀባይነት የሚገኝበት ወቅት ነው። ረቡእ በዝሁር እና ዐሥር መካከል ዱዓ ተቀባይነት እንዳለው በሐዲስ መጥቷል። ከእያንዳንዱ ቀናት ጀርባ በርካታ ምሥጢሮችን የተረዱ ዓሊሞች ቀናቱን ከፋፍለው ዱዓና ሰለዋቶች በማደረግ ዘመን የሚበትነውን ጘፍላ መርታት ችለዋል።

በመጅሊስ ኒያ ሥራ ላይ ላላችሁ፣ እንዲሁም ተመችቷችሁ ዱዓ ለተቀመጣችሁ ሰዎች የሁለት አውሊያዎችን ገጠመኝ ላወጋችሁ ወደድሁ።

በቅርብ ዘመን ግብጽ ውስጥ የነበሩት ኢማም ሻዕራዊ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) መዲና ዚያራ በማድረግ ላይ ሳሉ የሰይዲን ዶሪሕ ተበሩክ ሲያደርጉ አንድ ሹርጣ (ፖሊስ) መጥቶ ይህ "ቢድዓ" ነው ብሎ ይከለክላቸዋል። አውሊያ መች የክርክር ናዳ ውስጥ ይገባል። ብዙ ካስረዱት በኋላ እንኳን እርሳቸውን በከበበው ነገር ቀርቶ አንተ እዚህ ኺድማ ላይ ባለኸው እንኳን እባረካለሁ ብለው ሰውነቱን አሻሽተው በረካውን ወሰዱ። :-D  (ዝርዝር ጭውውታቸውን ከዚህ ቀደም አጋርቼው ነበር።)

አይ ዑለማ! ልባቸው ሰፊ ነው፣ ከማይረዳቸው ሰው እንኳን መወሰድ ያለበትን ያውቃሉ። ፖሊሱ እምነቱን በተዳረዳው ልክ ነበር ግና ያላየው ዕይታ ነበር እርሱን አስተማሩት ምን አልባትም ልቡን ጠረጉለት

አንጋፋዊው ዛሒድ የነበሩት ኢብራሂም ቢን አድሀም (ረዲየላሁ ዐንሁ) አንድ ጊዜ ወደ ሻም ጉዞ ሲያደርጉ የገጠማቸውን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦ በመንገድ ላይ ሳለሁ ውሃ ጠማኝና አንድ ፍየል ጠባቂ እረኛ ስመለከት ተጠጋሁና እንዲህ አልኩት፦ የሚጠጣ ወተት ወይም ውሃ ይኖርሀል?
እንዲህ አለ፦ የትኛው ቢመጣልህ ትወዳለህ?
"ውሃ" ስል መለስኩ። በያዘው ልምጭ መሬቱን ሲወጋው ውሃ መፍለቅ ጀመረ! በጣም ተገረምኩ።
"አትገረም ጠጣ" አለኝ። ውሃውን ጠጣሁት ከበረዶ የቀዘቀዘ ከማር የጣፈጠ ውሃ ነበር። እያየሁት ቆሜ ቀረሁ። ከዚያም ይህ እረኛ እንዲህ አለኝ፦ « ኢብኑ አድሀም አንድ ባርያ አላህን ከታዘዘ ሁሉም ነገር ይታዘዘዋል።»

ምንጭ፦ [ሲየር ኢዕላም አኑበላእ ወሒሊየቱ አልአውሊያ]

አላህ የአውሊያዎችንና የዑለማዎችን ቀድር ያሳውቀና 🤲

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana