ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 weeks, 3 days ago
Last updated 2 weeks, 5 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month, 1 week ago
በአዲስ አበባ ከ184 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ንግድ ፍቃዳቸዉን አላደሱም ******(ኢ ፕ ድ)
በከተማዋ ከ184 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ንግድ ፍቃድ ዕድሳት አለማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አሰታወቀ።
የቢሮው ሀላፊ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለጹት፤ ቢሮዉ ከሀለምሌ አንድ እስከ ታህሳስ 30 ድረስ ባሉት ቀናት እድሳት የሚያደርግ ሲሆን እስካሁን 211ሺ ነጋዴዎች ፍቃዳቸዉን አድሰዋል።
ከ184ሺ በላይ ነጋዴዎች የንግድ ፍቃዳቸዉን አላደሱሙ፤ በቀሪ 21 ቀናት እንዲያድሱ ጥሪ አቅርበዋል።
ነጋዴዎች አገልግሎቱን ከጠዋቱ 1:30 እስከ ምሽቱ 1:00 በኦንላይን መጨረስ የሚችሉ መሆኑ ተናግረዋል።
ባለፉት አምስት ወራት 47ሺ 700 ነጋዴዎች አዲስ ንግድ ፍቃድ ወስደዋል። ከ15ሺ በላይ ነጋዴዎች ደግሞ ከንግድ ስርአቱ ወጥተዋል ብለዋል።
በመስከረም ሰይፉ
ታህሳስ 9 ቀን 2017
በፈለስ^ጢን እና በሌሎች ሙስሊሞች ሀገራት ውስጥ እንዲህ ያለ ግፍ ሲፈጸም በኃይማኖታችን ሳይሆን በደደ^ብነታችን ነው:: ይህንን ማመን የግድ ነው:: በእኔ ዘርፍ በፋይናንስ ብናወራ, ምዕራባውያን ዶላርና ዩሮን ይዘው እያንዳንዱን ግብይት ይቆጣጠራሉ:: ለጦር መሳሪያ ግብዓትነት የሚውል ቀርቶ ሩዝና ሰንደል ከየትኛው ሱቅ እንደገዛህ ያውቃሉ:: ዶላር ገንዘብ ሳይሆን ቢል ነው:: የሌሎች ሀገርይት መገበያያዎች የቢሎች ዝርዝሮች ናቸው:: ምእመኑን "ዶላርና ብራችን ቦኖ እንጂ ገንዘብ አይደሉም" ብትለው ቀርቶ እኮ በድሮን ብትመታው እንኳ ጆሮው አይሰማም:: ከዚያ በኃይማኖቴ ነው የምገ^ደለው ይልልሃል:: ወንድሜ የሆነ ነገር በተፈጠረ ቁጥር ወደ አላህ ማቃጠርህን ተው:: የማያውቀውን ነው እንዴ የምትነግረው? እኔም ልወደድ ባይ ሆንኩ መሰለኝ:: እና ከነቢ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم ሕይወትና ልፋት ከምንማራቸው ነገሮች ዋነኛው ተዓምርን ረስተህ በተሰጠህ ግብዓት ጥበበኛ መሆንን ነው:: ባይሆን ኖሮ ስደት, ጂሃድ, ረሃብ, መሰደብ, ማዕቀብ ባላስፈለጉ ነበር:: ብቻቸውን የቲም ሆነው ተነሱ:: ዐለም ላይ ነገሡ:: ወንድሜ ብዙ ግብዓት ተለግሰናል:: የእኛ ድርሻ ከአንገት በላይ ያለው የሰውነታችንን ክፍል ለማጼምጼሚያ ብቻ እንዳልተፈጠረ ማወቅ ነው::
በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አንዳንድ ኃላፊዎች ብዙም ሳይቆዩ ሲቀየሩ ልታስተውሉ ትችላላችሁ:: ቦታው የሚበላበት ስለሆነና የተቀየረውም ሰው ሆዳም በመሆኑ የተነሳ ይመስላችሁ ይሆናል:: ማጠቃለልና የተቀየረ ሁሉ በልቶ ነው ማለት ባይቻልም ግን አንድ ነገር አለ:: የተነሳው ሰውዬ ጉቦ በመብላቱ ሳይሆን የኪራይ ዘመኑ ስላለቀና የተሻለ ከፋይ ስለተገኘ ሊሆን ይችላል:: ለምሳሌ ለቦታው ለአንድ ዓመት 500,000 ብር ከፍሎ ተመድቧል እንበል:: ስለዚህ ለቦታው ስለከፈለበት ጉቦ እየተቀበለ ማትረፍ አለበት:: የደም ዋጋ የሚከፍሉ ሁላ አሉ:: አንዳንዱ ጫካ የሚገባው ለምን ሆኖ? ሀብት ማፍሪያ ስለሆነ ነው:: የሥራ አየር ከጠረረ አፋኝ መመሪያ ሊወጣ ይችላል:: እናንተ ስትመጡ "መመሪያው ነው" ተብላችሁ ትጉላላችሁ:: ያው እንግዲህ የሻይ ትከፍላላችሁ:: ሻይ 100 ሺህ ብር የሚሸጥበት ሀገር ላይ ነን:: "ጉቦ በልቶኛል" ብለህ ለአለቃው ብትከስ ያው አከራዩ ጋር ነው የከሰስከው:: አለቅየው ግፋ ቢል ቦታ ነው የሚቀይረው:: እርምጃ ከወሰደማ በቦታ ተከራዮቹ ላይ እርምጃ እንደመውሰድ ነው:: ምርት ሳይጨምር ሕግና መመሪያ ሲበዛ ለበይ ይመቻል::
እንደመፍትሔ:- ታክስ ላይ depend ከመሆን እንውጣ:: ዜጋውን ታክስ በማድረግ ያደገ ንጉሥ የለም:: ታክስ የቁጥር ቻት ነው:: ታክስ እሴት አይደለም:: ታክስ የፍጆታ እቀባና የኢንፍራስትራክቸር ኪራይ ነው:: ኪራዩን በፍጆታ በኩል ማድረግ:: VATን አጠናክሮ መሰብሰብና አሰባሰቡንም ለነጋዴው አለመተው:: ክፍያው እንደተፈጸመ ማለትም transactions እንደተካሄደ Immediately ወደ ገቢዎች ወይም ገንዘብ ሚኒስቴር (Central treasury) አካውንት እንዲገባና ባንኮች ሶፍትዌራቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ:: በሥራ የተጠመዱ ሰዎች ታክስ እንደከፈሉ ማሰብ:: ልክ ብር ሊያጠፉ ሲሄዱ የታክስ ወጥመድ ማዘጋጀት:: ይህም ቢሆን ምርት እየጨመረ ሲመጣ እየታየ ይስተካከላል:: ለታክስ ያለንን አመለካከት ካልቀየርን አንቀየርም::
በአሁን ወቅት እኮ ጉቦ የሚቀበል የለም ወደሚባል ደረጃ ተደርሷል:: ጉቦ የሚቀበል ማስፈጸም የማይችል ልክስክስ ኃላፊ ነው:: አካውንትህን ላክልኝና ላስገባ የፋራ ነው:: Already ቋሚ ጉቦ አለው:: ጉቦ መስጠት አቅም አጥቶ የጉቦ ፔይሮል ሁላ ተጀምሯል:: ቋሚ ጉቦ ወይም "የወንበር" ማግኘት ሐቁ ነው:: እርሱም ጉቦ በላሁ ... ምእመኑም አበላሁ አይሉም:: ድሮ ተቀባዩ ነበር እቁብ የሚጥለው:: አሁን ሰጪዎች ናቸው እቁብ የሚጥሉት:: ከየሱቁ ወርሃዊ የጉቦ ተመን አለ:: የጉቦ መዋጮ ሰብሳቢ ፕሬዝዳንትና ጸሐፊ ሁላ ሳይጀመር አይቀርም:: መንግሥትና ሕዝብን ከመሃል ቆርጠውታል::
ሕዝብ እንደሆን በቀደድክለት ቦይ ይፈሳል:: ችግር የለበትም:: "መመሪያው ነው, አልገቡም" ካልከው ይመለሳል:: እንዲሳካለት ወደ ቤተእምነቱ ሄዶ ዱዓና ጸሎት ያደርጋል:: መሳሪያ አይዝም:: አተኳኮስ እንኳ አያውቅም:: አደገኛውማ ቢሮክራቱ ነው:: እጁ ላይ ማኅተም, መሳሪያና የመንግሥት ምሥጢር አለ:: ወንድሜ "ቢሮክራቱ ካበለ, ሥልጣን ዘነበለ" ነው ነገሩ:: አዛዡ ካልታዘዘ ነገር አበቃ:: መሬት ማኔጅመንት ብትሄዱ ለመሃንዲስ በደረሰኝ ለመንግሥት (ለሕዝብ) 1,500 ብር ስትከፍሉ በተቃራኒው ለመሃንዲሱ 150,000 እና ለኃላፊው 300,000 ብር ደንብ ነው:: ካልሆነ የማይጋጨውንም መመሪያ ያጋጩብሃል:: የትም ብትሄድ የእነርሱ ነው የሚሰማው:: ካልከፈልክ በአንድ ፊደል ምክንያት ይቆልፉሃል:: በሀሌታው "ሀ" እና በሐመሩ "ሐ" ይወግሙሃል:: << የመታወቂያህ ስም ሐብቴ ሲሆን ውክልናህ ግን ሀብቴ ይላል >> ብለው ይሸኙሃል:: ፓስፖርቴ ጋር ይገጥማል ብትለው "ቤሩት ሒድበት" ይልሃል:: ገቢዎች ዘንድሮ ለአንዳንድ ኃላፊዎች harvesting year ነበር ተብሏል::
--> እንደ መፍትሔ:- ከሀገር ያልወጣ ብር የትም አይሄድም:: መንግሥት እና የመንግሥት ኃላፊዎች ማወቅ ያለባቸው በአገር ውስጥ ታክስ የወደቀ እንጂ ያደገ መንግሥትም ይሁን ኢምፓየር ታይቶ አይታወቅም:: አሜሪካ ግብር የምትሰበስበው ከዓለም ሲሆን የሀገሯን ሕዝብ ታክስ የምታደርገው ከውጭ ዞረው የሚገቡ ዶላሯን ለማስወገድና ሕዝቧን ለመቆጣጠርና ኃላፊነት እንዲሰማቸው ለማድረግ ነው:: የኢትዮጵያ መንግሥት በሴኮንድ የሚፈጥረውን ቁጥር (ፊያት) ሲል አስተዳደሩን ባይጎዳ ጥሩ ነው:: ዘንድሮ ድንገት 521 ቢሊዮን ብር በጀት ፈጥሯል:: ችግር የለብኝም:: ችግሩ ያንኑ ቁጥርን ነው ዞሮ እያስለቀሰ የሚሰበስበው:: ይህንን አዲስ ቁጥር (በጀት) ክፍተት እያየ እንደ ዝናብ ማርከፍከፍና mobilize ማድረግ ነው ያለበት:: አንድ ሰው በሥራ ተወጥሮ ከወንጀል ከራቀ ብዙ ታክስ ከፍሏል::
መንግሥት በፈጠረው ባዶ በጀት (ፊያት) ኢንፍራስትራክቸር ይገነባል:: ሥራው ነው:: መንግሥት ሲያትም ወይም በጀት ሲፈጥር ግሽበት ትሉ ይሆናል:: ታክስም ባዶ ቁጥር ነው:: የተሻለውን ግሽበት መምረጥ ያባት!!! ግሽበት ደግሞ ምንጊዜም የሚበላው ቦዘኔውን ነው:: የሚሠራ ሰው ካሽ ስለማይዝ ከግሽበት ያመልጣል:: የራሱን ንብረት ላይ አውሎ በቆጣቢዎች ብር ሲሠራ ደግሞ almost ያመልጣል:: ግሽበት ይብላኝ ያለ ይቀመጣል ወይም አንድ ሥራ ላይ ብቻ ተወዝፎ እስከጡረታ ይጠብቃል::
ብዙዎቻችን ድሎትን እንመኛለን:: እንፈልጋለን:: እንጥራለን:: እናግኘው:: ይሳካልን:: ሆኖም ግን ሁሉም ነገር ቢመቻችልን እኮ አይመቸንም:: ከችግር ሁሉ ቀፋፊው ችግር የድሎት ውስጥ ችግር ነው:: ስለዚህ ነገር ፍለጋ እንወጣለን:: አባታችን አደም ከጀነትና ከድሎት መውጣታቸውን እናስታውስ:: ችግር ተፈጠረችላቸው:: ሴት !!! ብዬ ከአስፈላጊ ችግሮቻችን ጋር አልጋጭም:: (እንደውም አንድ ሦስት እፈልጋለሁ:: ኑ):: ለምን እንደሆነ ባይታወቅም የሰው ልጅ የሚዝናናው በችግር ነው:: በ adventures ይከየፋል:: በዓለም ትልቁ የቱሪዝም እንቅስቃሴ የችግር ፍለጋ ጉዞ ነው:: ምግብ, ቆንጆ ሴት, ቆንጆ ጀት ሞልቶ ተርፏቸው የሚፈልጉት ግን "ተዓብ"ን ነው:: በቃ ችግርን feel ማድረግ:: አንዳንድ የሰፈራችን ሴቶች ነጠላ ለብሰው ነገር ፍለጋ ታች ምቀኛ ሰፈር እንደሚሄዱት ... የናጠጡ ሀብታሞች ችግርን በገንዘብ ያስሳሉ:: አንድ ችግር አሳሽ Multi millionaire ሆኖ ችግር ቢያጣ እንኳ የበላበትን ሳይከፍል ወጥቶ ታስሮ መንገላታትን ይፈልጋል:: በዚህ የሀገሩን ምንነት ያውቃል:: አንተ ቸግሮት ነው ልትል ትችላለህ:: እርሱ ግን ሻንጣውን አዝሎ የወጣው ችግር ፍለጋ ነው:: አባታችን አደም ችግር ፍለጋ እንደወጡ ልጆቻቸው ሁላ የጨሰ adventures ውስጥ ነን::
ትምህርት ቤት ፈተና ከጨረስክ በሗላ ያለ ድብርት, ሰቅለህ ከተመረቅህ በሗላ ያለው የሥራ ፍለጋ ስቃይ, ጾመህ ውለህ ካፈጠርህና ከፈሰክህ በሗላ ያለው ቁንጣን እኮ ከባድ:: በእርግጥ ይህንንም እንደ ችግር ከቆጠርከው ድሎት ነው:: ገንዘብ ካገኘህ በሗላ ያለው ድብርት የጉድ ነው:: በከተማው ያሉ ሆቴሎች ያልቁብሃል:: ገጥሞኝ አውቃለሁ:: ነጋ ደግሞ ልንበላ ያስብልሃል:: በዚያ የሀብት ችግር የወጣሁት በአንድ ምግብ ስወሰን ነው:: ይህች ሀገር ሸራተንና ሀያት ብቻ ነው እንዴ ያላት? ፑ! እሺ ቁርስ የት እንብላ? ቢዝነስ ክላስ እዚያው ደውሎ ቲኬት ይዞ ዱባይ የሄደ ሀብታም አውቃለሁ:: በዚያው ዞሮ የሆነ ሀገር ገባ:: ወንድሜ ጠጥተህ ሰክረህ ግን አላሰክር ሲሉህ ሽቶ ሁላ ልትጠጣ ትችላለህ:: በትንሹ እያመሰገንክ ካልኖርክ መቼም አትጠግብም:: አንዲት ሴት ላይ ካልረጋህ መቼም አትረካም:: ሴቶችን በቀማመስክ ቁጥር ጣዕም አልባ ሆነውብህ ወንድ ፍለጋ ትወጣለህ:: ትላ ትሎቹ ሲወሰውሱት ውሻ ነገር ይሆናል:: ከዚያም ያነሰ::
አላህ ይበቃሃል ባለህ ላይ እርጋ::
#ለመረጃ (ፌስታል ያስቀጣል!)
በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም፣ ማምረት እና ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት በገንዘብ እና በእስራት የሚያስቀጣ ድንጋጌ የተካተተበት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።
በረቂቅ አዋጁ መሠረት የፕላስቲክ ከረጢት የተጠቀመ ወይም ለመጠቀም ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው ከ5 እስከ 10 ሺህ ብር ገንዘብ ይቀጣል።
በተመሳሳይ የፕላስቲክ ከረጢት ማምረት፣ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ ለገበያ ማቅረብ፣ መሸጥ ወይም ለንግድ ዓላማ ማከማች ከሃምሳ እስከ መቶ ሺህ ብር ያስቀጣል። ከዚህ በተጨማሪም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።
አነዚህን "የወንጀል ድርጊቶች" የፈጸመው ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት በሚሆንበት ጊዜ ቅጣቱ ሦስት እጥፍ እንደሚሆን ረቂቁ ያትታል።
"ከሰው ምንም አትፈልግ" ይልሃል::
እና ከቢምቢ ነው የምንፈልገው ወይስ ከገበሎ?
ከሰውማ ብዙ ነገር እንጠብቃለን:: አንድን ሰው በጠበቅነው ቦታ ካላገኘነው ቦታ ተሳስተን ነው የሚሆነው::
እና ይታረም::
ጎበዝ በርታ የሚሉህን ሰዎች ካልሰማሃቸው ጥሩ እና ጠንቃቃ ሰው ትሆናለህ:: ትክክለኛ ማንነትህን የምትነግርህ ሰው ማለት ሚስትህ ነች:: በተለይ ቁመቷ አጭር ከሆነ:: ቦታህ ላይ ታወርድሃለች:: እና ሌላው ሰው ሙና ^ ፊቅ ነው:: ጎኦኦበዝ, ጀግና, ድንቅ ምናምን ሲሉህ እንደ ስ^ድብ ብትቆጥረውና ሚዛንህን ጠብቀህ ብትኖር አሪፍ ነው:: ጀግናዬ ጎሽ ሲሉህ የዱሩን እንስሳ buffalo ን 🦬 ይሆን እንዴ? ብለህ ነው ማሰብ ያለብህ:: የመንግሥት ሚዲያም የተቃዋሚ ሚዲያም የሚፈልጉትን እንጂ ሐቂቃውን መች ይነግሩሃል? ምእመኑም እንደዚያ ነው:: ጠቅላላ ሐበሻ አጥር ላይ ነው የሚቀመጠው:: ወዳሸነፈው በኩል ዘሎ ዱብ ይልና ተመልሶ አጥሩ ላይ ወጥቶ ይጠብቃል::
የሰርግ መህር (ጥሎሽ) ዑምራ ጠይቂው ይላል አንዱ የጉዞ ወኪል ማስታወቂያ::
ሰርጉ ሪያድ እነጂኒፈር ሎቤዝ ጋር ሊሆን ነው?
የሀጅ ጠጠር ውርወራ እየጨፈርን ዊስኪ መረጫጨት ይሆን?
ከስዑዲ ቀድመው ያፈሉትና ዑምራውን ያረከሱት የእኛ ሀገራት ኡስታዞች መሆናቸው ይገርማል:: ኡስታዙ ሁሉ የመስጂድ ፈረሳና የሂጃብ ገፈፋ ረስቶ አስጎብኚ ሲሆን ስንቃወም የሚቃወሙ ነበሩ::
አላህ ይርሃማችሁ
https://vt.tiktok.com/ZSjVPne5X/
ኡስታዝ ሀሰን
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 weeks, 3 days ago
Last updated 2 weeks, 5 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month, 1 week ago