ቬኒሲያ

Description
ተወዳጇ ቬኒሲያ በአዲስ መልክ ጀምራለች። ይህ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን አስተምህሮ በጣፋጭ ታሪኮች እያዋዛ የሚያቀርብ መንፈሳዊ ቻናል ነው

ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ
https://t.me/Get_loza ያድርሱን።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 years, 3 months ago

እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን እባካችሁ ሼር አድርጉላት ? እባካችሁ ???

መሰረት ዲባባ ትባላለች። በተደረገላት የጤና ምርመራ ሁለቱም ኩላሊቶቿ ከጥቅም ውጪ መሆናቸው አዲስ አበባ ዘውዲቱ ሆስፒታል በህክምና በመረጋገጡ አሁን ላይ የኩላሊት እጥበት በሳምንት ሶስት ቀን የኩላሊት እጥበት እየተደረገላት ትገኛለች።
በአሁኑ ሰዓት በዘውዲቱ ሆስፒታል ከአቅም በላይ በመሆኑ ወደ ግል ሆስፒታል ሄዳ እንድትታከም በሆስፒታሉ በመታዘዙ ግሩም ሆስፒታል ትገኛለች።

መሰረት ከህመሟ ለመዳን  የኩላሊት እጥበቱንም ሆነ ወደውጪ ሄዶ ለመታከም  የገንዘብ አቅም
ቤተሰቦቿ ስለሌላቸው የድረሱልኝ ጥሪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በሀገር ውስጥም በውጭም የምትኖሩ ወገኖቼ እርዱኝ በማለት ትጠይቃለች

መሰረት ዲባባን ለመርዳት

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት
1000502420988

ስልክ :-

0912702724     0922175972   0913748378  
???

???

2 years, 6 months ago
  • ለምን ትቀናለህ? +

በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል። መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር። የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ። ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉት። በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ። አልተሳካም። በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም።

አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ይህንን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት። በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት። እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ከአንተ ጋር ያደገውና ከአንተ ጋር የተማረው

ጓደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ' ብዬ ነገርኩትና

ወጣሁ። አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው አላቸው፡፡ አጋንንቱ በደሰታ

ጨፈሩ፡፡

ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል። መጽሐፈ ቅዳሴ ሞትን

ሲገልጸው በሰይጣን ቅናት ወደ ዓለም የገባ ይለዋል። ሰይጣን በሰው

ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን

እንዲመኙ አድርጎ ዓለምን ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል

ለሺህ ዓመታት ብዙዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት።

መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው::

ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው፡፡ ነው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው::

ቅናት ግን በምታስተውል ነፍሱ ውስጥ የሚበቅል መርዝ ነው፡፡ ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር፡፡ የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ። ዮሴፍ የለበሳት ቀለምዋ ብዙ የሆነ ጌጠኛ ቀሚስ በወንድሞቹ ዘንድ የመረረ ጥላቻን አትርፋለት ነበር። አንዱ አጊጦ አምሮ ሲታይ ቢሞትና

ቢገላገሉት ደስ የሚላቸው የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ።

ዮሴፍም አርፎ አልተቀመጠም። እየሔደ ሕልሙን ይነግራቸው ነበር፡፡

ስለ ሕልሙም የበለጠ ጠሉት ይላል። ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ፡፡ ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ ራእይህን ፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ። ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል፡፡ ምንም ነገር ሳታደርግ እንኳን "ለምን አለምከው?" ብለው ጥርስ ይነክሱብሃል። ዮሴፍ ግን ይኼ ስላልገባው ነገራቸው፡፡ ወዳጄ አንተም ሕልምህን እንደ ዮሴፍ በየዋህነት የምትዘራ ከሆንህ እንግዲህ የዮሴፍ አምላክ ይጠብቅህ።

ቅናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ እረኛው ዳዊት ጎልያድን የገደለ ዕለት

የተዘፈነለት መዘዘኛ ዘፈንም ነበረ፡፡ “ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ

ብለው ዘፈኑለት፡፡ ይህች ዘፈን በሳኦል ጆሮ ስትደርስ ዳዊት ላይ ብዙ ጦር

አስወረወረች። ሳኦሎች ሌላ ሰው ከእነርሱ በላይ ሲመሰገን የሰሙ ዕለት

በቅናት ታውረው ገበታ ላይ ሳይቀር ሰይፍ ይመዛሉ፡፡

የጠፋው ልጅ ወንድምን አስበው። (ሉቃ 15:20) ወንድሙ ከጠፋበት

ተመልሶ ደስታ ሲደረግ እርሱ ግን ከፍቶት ውጪ ቁጭ አለ። ወዳጄ ቅናት

ከቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር መንግሥት ያስወጣል። የሌላው

ስኬት ካበሳጨህ እንደጠፋው ልጅ ወንድም ውጪ ቁጭ ብለህ አፈር

እየጫርክ 'እምቢየው አልገባም' እያልክ እያልጎመጎምክ ትቀራለህ።

ክርስቶስ ላይ አይሁድ ያቀረቡት ትችት ሁሉ ለሕግ ከመቆርቆር ሳይሆን ከቅናት ነበር። ጲላጦስ እንኳን “በቅናት አሳልፈው እንደሠጡት ያውቅ ነበር ይላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ቅናታቸውን በሌላ ነገር እንደ አይሁድ ሸፍነው ትችት ያቀርባሉ። ለእግዚአብሔር ሕግ እንደተቆረቆሩ ፣ ለሥርዓቱ እንዳዘኑ መስለው ውስጣቸው ያለውን ቅናትና ጥላቻ ያንጸባርቃሉ። የሰንበት መሻር ፣ ለቄሣር ግብር መክፈል ፣ የመቅደሱ በሦስት ቀን ፈርሶ

መሠራት እንዳንገበገባቸው እርር እያሉ ቢናገሩም እውነታው ግን ቅናት ነው፡፡ “የቤትህ ቅናት በላኝ እንዳለው ጌታ በየዘመኑ የሰዎች ቅናት ብዙ ንጹሐንን ትበላለች።

ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆን አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ

ካንሰር ራስህን አድን።

ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር። በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም። ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃው ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር።

ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ፡፡ ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው። ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ። መብለጥ ከፈለግህም አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ

አንተን ሁን።

በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎችን ሰዎችንም ውደዳቸው። ከወደድሃቸው ፍቅር አይቀናም'ና የእነርሱ ስኬት የደስታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ የቅናት ስሜት ሲሰማህም ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ' ብለህ ለምነው፡፡ በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን' ሮሜ 13፡13

✍️ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

2 years, 8 months ago

አዲስ ዝማሬ
Watch "በልደትሽ ዜና ምድር ተደሰተች ?ዘማሪ ያሬድ አበበ (ዘሎዛ) ?ወይ የድምጽ መመሳሰል?⭕️ተጨማሪ ዘማሪ ዲ/ን እንዳለ ደረጀ እና ዘማሪ ዲ/ን ዘላለም ታከለ እንዲሁም ዘማሪት ታሪኳ በቀለ" on YouTube
https://youtu.be/svmc8gj5H7Y

YouTube

በልደትሽ ዜና ምድር ተደሰተች 🔴ዘማሪ ያሬድ አበበ (ዘሎዛ) 🔴ወይ የድምጽ መመሳሰል?⭕️ተጨማሪ ዘማሪ ዲ/ን እንዳለ ደረጀ

ከራማ ቲዩብ ጋር በሚገናኝ በየትኛውም አገልግሎት ዙሪያ የግል መልዕክት ለማስቀመጥ በTelegram @rama1621 ዘማሪ ኢንጂነር ታዴዎስ በማለት መልዕክት ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ 🆂🆄***🅱***🆂🅲🆁🅸***🅱***🅴 Contact us via telegram --@rama1621/0928311773 Get Other New and Recent Songs here ► https://www.youtube.com/watch?v=6w4O6... ►htt…

3 years, 1 month ago
  • ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +

የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::

ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::

እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::

ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::

ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::

ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::

የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::

ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?

እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::

ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም

3 years, 2 months ago
  • ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +

ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"

ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::

ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)

ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::

ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::
ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::

"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)

እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::

ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?

ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል::
እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::

ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: በጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::

ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::

ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

3 years, 4 months ago
  • እግዚአብሔርን ለምን - አልለምንም! +

‘እነሆ ድንግል ትጸንሳለች’ የሚለው ትንቢት ከመነገሩ አስቀድሞ ምክንያት የሆነ አንድ ክስተት ይህ ነበር፡፡
የይሁዳ ንጉሥ አካዝ ዙሪያውን በጠላቶች ተከብቦ ነበር፡፡ ሁለት ነገሥታት ሊወጉትና ኢየሩሳሌምን ሊወርሯት አሰፍስፈው እየጠበቁ ነው፡፡ የጦር ምክራቸውም ‘ወደ ይሁዳ እንውጣ እናስጨንቀው እንስበረው በላዩ ላይም ሌላ ንጉሥ እናንግሥበት’ የሚል ነበር፡፡ ይህን ምክራቸውን አስቀድሞ ይነግረው ዘንድ እግዚአብሔር ነቢዩ ኢሳይያስን ወደ ንጉሥ አካዝ ላከው፡፡ ኢሳይያስም የሚመጣበትን የጠላት ከበባና መጻኢ ፈተናውን ነገረው፡፡

እንደመፍትሔም እንዲህ አለው ‘ከጥልቁም ወይም ከከፍታውም ከእግዚአብሔር ምልክትን ለምን’ የሚል ምክር ነበር፡፡ እግዚአብሔር ወይ ከሰማይ ወይ ከምድር አንዳች ተአምር አድርጎ ከዚህ ጭንቅ እንዲያወጣህ ፈጣሪህን ለምን ብሎ የነገረው ከእግዚአብሔር በቀጥታ የተላከው ነቢይ ነበር፡፡ ‘’ለምነኝ አሕዛብን ለርስትህ እሰጥሃለሁ’ እንደማለት ያለ ዕድል ቀርቦለት ነበር፡፡
ንጉሥ አካዝ ግን ግልጽ እና አጭር ምላሽ ሠጠ ፦ አልለምንም ፤ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም! /ኢሳ 7፡13/

እርግጥ ነው በኦሪት ጌታ አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ተጽፎአል፡፡ ራሱ እግዚአብሔር ነቢዩን ልኮ ለምነኝ ተአምር ልፈጽምልህ እያለህ ‘አልለምንም እግዚአብሔርን አልፈታተንም’ ማለት ግን በራሱ እግዚአብሔርን መፈታተን ነው፡፡

ንጉሥ አካዝ እንዲህ በጠላት ተከብቦ እያለ ‘ወደ ፈጣሪ ለምን’ ሲባል እምቢ ያለው እርሱ እንዳለው እግዚአብሔርን ላለመፈታተን አልነበረም፡፡ በዚያ ጦርነት እንዲረዳው ወደ አሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መልእክተኛ ልኮበት ስለነበር ነው፡፡ በታላላቅ ተአምራት ሕዝቡን የታደገ እግዚአብሔርን እንዲለምን ጥሪ እየቀረበለት አካዝ ግን ከፈጣሪ ይልቅ በአሶር ንጉሥ እርዳታ ተስፋ አድርጎ ነበር፡፡ ኢሳይያስም ጸልይ ሲለው የልቡን ሃሳብ ደብቆ ፣ ከፈጣሪ ይልቅ በሰው ለመመካቱም መንፈሳዊ ካባን አልብሶ ‘ፈጣሪን አልፈታተንም’ ብሎ ተናገረ፡፡

አካዝ ይረዳኛል ብሎ የተማመነበት በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ ርዝመት ሁለተኛ የሆነው ቴልጌልቴልፌልሶር በጥያቄው መሠረት ወደ ይሁዳ ቢመጣም እንኳን አስጨነቀው እንጂ አልረዳውም፡፡ ይረዳኛል ብሎ ከቤተ መንግሥቱ ፣ ከመኳንንቱ ግማሹን አሳልፎ ለአሶር ንጉሥ እስከመሥጠት ቢደርስም ቴልጌልቴልፌልሶር ግን እንደ ስሙ የተንዛዛ ቆይታ ቆይቶ በዘበዘው፡፡ ችግር በመፍታት ፈንታ ችግር ሆነበት ፤ አካዝም በዚህ ተበሳጭቶ ‘ለምነኝ‘ ብሎ ሲጠይቀው አልፈልግም ያለውን እግዚአብሔርን መንቀፍ ጀመረ፡፡ ጭራሽ ጠላቶቼ እኔን ድል ያደረጉት አማልክቶቻቸው ከእኔ አምላክ ቢበልጡ ነው ብሎ ለጠላቶቹ አማልክት መሥዋዕት አቀረበ፡፡ መጨረሻውም እጅግ የከፋ ሆነ፡፡ /2ዜና 28፡20/

‘’አልለምንም እግዚአብሔርን አልፈታተንም’’ ብዙ ጊዜ የእምነታችንን ማነስ የምንደብቅባት ሽፋን ናት፡፡ ሀገር ሲታመስ ፣ መከራ ሲጸና ፣ ነገሮች ድብልቅልቅ ሲሉ ፣ ጠላት ከግራና ቀኝ ሲበዛ ምንድን ነው መፍትሔው? አካዝን ለምነኝ ያለ አምላክ ለእኛም ‘‘በመከራህ ቀን ጥራኝ እኔም አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ’’ ብሏል፡፡ /መዝ 49፡15/ በደስታችን ቀን ትዝ ብሎን የማያውቀው ፈጣሪያችን ግድ የለም በመከራህ ቀን ጥራኝ ብሎ ለሁላችን ጥሪ አቅርቧል፡፡ ምንም ዓይነት ፈተና በግላችን ፣ በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ሲመጣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መፍትሔዋ ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ምልክትን ከእግዚአብሔር መለመን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዕንባዋን ትረጫለች ፤ የኃያላን ኃያል ፣ ብርቱዎችን ከዙፋናቸው የሚያዋርድ ፣ ትዕቢተኞችን የሚሰብር አምላክ እንዲደርስላት እንደ ኢሳይያስ የፈጣሪ አንደበት የሆነች ቤተ ክርስቲያን ጸልዩ ትላለች፡፡

ይህን ጊዜ አካዞች እንበሳጫለን ‘አልለምንም ፣ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም’ እንላለን ቤተክርስቲያንን የላካት ኢሳይያስን የላከው አምላክ መሆኑን አናስተውልም፡፡ የጾም ፣ ጸሎት ፣ ስግደት ፣ ምሕላ ጥቅም አይታየንም፡፡ ሌላ መፍትሔ መፈለግ ነው እንጂ ዝም ብሎ ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ ጊዜ ማጥፋት የለብንም እንላለን በሆዳችን፡፡ አፋችን ግን ለታዛቢ ይጠነቀቃል ስለዚህ ‘ዝም ብሎ መጸለይማ እግዚአብሔርን መፈታተን ነው’ እንላለን፡፡ እነ እገሌ ቢረዱን ብለን የምናስባቸው ቴልጌልቴልፌልሶሮች ብዙ ናቸው፡፡ ማናቸውም ግን መጥተው ያስጨንቁናል እንጂ አይረዱንም፡፡ ሰውን ተስፋ ከማድረግ ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ምልክትን ብንለምን ጥሩ ነው፡፡

እኛ ባንለምንም ግን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደሚሆን እንዲህ ብሎ ተጽፎአል፦

ጌታ ራሱ ምልክትን ይሠጣችኋል ፤ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል /ኢሳ 7፡14/

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

3 years, 4 months ago

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

#ጾመ_ዮዲት

በናቡከደነጾር ዘመነ መንግሥት ንጉሡ ሥልጣኑን መከታ በማድረግ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በግድ እያስገደደ እጅ መንሻ ይቀበል ነበር፡፡
የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበለውንም እየገደለ፣ ጭፍሮቹ ኃያልነቱንና ገናናነቱን በዓዋጅ በጦር አዛዦች ጭምር እያሳወጀ፣ በርካታ የጦር ሠራዊቶችን አሰልፎ ከአይሁድ ከተማ ገባ፡፡

በዚያም ነዋሪዎችን በማስፈራራት የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበሉትን ሁሉ እያሳደደ ስላስጨነቃቸው ማቅ ለብሰው፣ አመድ ነስንሰውና ድንጋይ ተንተርሰው ወደ ፈጣሪያቸው በመጮህ መለመን ጀመሩ። በጭካኔ የተሞላው የጦር አበጋዙ ሆሎፎርኒስም ይበልጥ እጅግ እንዲሰቃዩ ውኃ የሚቀዱበትን ስፍራ ተቆጣጠረው፤ በግዴታ ማርኮም እጅ እንዲሰጡ እንዳደረጋቸው በመጽሐፈ ዮዲት ፪፥፪ ላይ ተጽፏል፡፡

በአካባቢው ይኖር የነበረ ዖዝያን የተባለ አንድ ሰው የአባቶቻቸው አምላክ ጸሎታቸውን እንዲሰማቸው ለአምስት ቀናት በትዕግሥት ይጾሙና ይጸልዩ ዘንድ ሕዝቡን መከራቸው፤ እነርሱም በትዕግሥት ሊጠብቁ ተስማሙ፡፡

የእስራኤል ልጆች የናቡከደነጾርን ጦር ብንችል ተዋግተን እንረታለን፤ ካልሆነም እጅ እንሰጣለን በማለት ይመካከሩ ጀመር። በዚያን ጊዜ ባሏ የሞተባትና በንጽሕና ተጠብቃ፣ በጸሎትና በሕገ እግዚአብሔር የምትኖር ዮዲት የተባለች ሴት ነበረች። (ዮዲት ፯፥፲)

እግዚአብሔርን የምትፈራ ብቸኛዋ ሴት እርሷ ነበረችና ምክክራቸውን ስትሰማ ለምን «እግዚአብሔር ያድነናል አትሉም» ብላ ገሠጸቻቸው፡፡

ማቅ በመልበስ፣ አመድ በመነስነስና ድንጋይ በመንተራስም ሱባኤ ገባች። በሦስተኛው ቀንም እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቧን የምታድንበትን ጥበብ ገለጸላት፤ ዮዲትም እግዚአብሔር የሰጣትን ውበት ተጠቅማ ሕዝቧን ከጥፋት የምትታደግበትን ጥበብ ተረዳች።

የክት ልብሷን ለብሳ፣ ሽቱ ተቀብታና ተውባ የጠላት ሠራዊት ወዳሉበት የጦር ሰፈር በድፍረት አመራች፡፡ ሠራዊቱም ውበቷን አይተው እጅግ በመደነቅ «ይህችስ ለአለቃችን ትገባለች» ተባብለው ከጦር መሪያቸው ዘንድ ወሰዷት።

እርሷም ቀድማ ማምለጫ መንገድ አዘጋጅታ ነበርና ወደ አዛዡ ከገባች በኋላ «ክቡር ጌታዬ ሆይ ርስት ተወስዶብኛል፤ እንድትመልስልኝ አስቀድሜ ደጅ ልጠና መጥቻለውና ርዳኝ፤ ትብብርህ አይለየኝ» አለችው፡፡ በስሜት ፈረስ ታውሮ የነበረው የሠራዊቶቹ አዛዥም የጠየቀችውን እንደሚፈጽምላት ቃል ገባላት።

ባማረ ድንካን እንዲያስቀምጧት ሎሌዎቹን አዘዘ። ዮዲትም የተሰጣትን ጥበብ ተጠቅማ፣ መውጣት ስትፈልግ የምትወጣበትን እና የምትገባበትን ዕድል በእግዚአብሔር አጋዥነት ዐወቀች፡፡ ከቀናት በኃላ የጦር አበጋዙ ለሠራዊቱ የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ ዮዲትን ከጎኑ አስቀመጣት፤ ከበሉና ከጠጡ በኋላም ሁሉን ሰው አስወጣ፤ እልፍኙን በመዝጋት ከእርሷ ጋር ብቻውን ሆነ፤ ነገር ግን እንቅልፍ ጣለው፡፡ (ዮዲት ፰፥፪)

እርሷም ወደ አምላኳ ጸለየች፤ ፈጣሪዋ እንዲረዳትም አጥብቃ ለመነች። በኋላም ከራስጌው ሰይፍ አንስታ አንገቱን ቀላችው፤ በድኑንም ከመሬት ጣለችው። የሆሎፎርኒስን ሞት ሠራዊቱ ሲሰሙ አውራ እንደሌለው ንብ ተበተኑ፤ ከፊሎቹ ሞቱ።

እስራኤላውያንም ከሞት ተርፈው በእግዚአብሔር ኃይል ድል አደረጉ፤ በደስታም ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ።
ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ የሚያስረዳን ዮዲት ጠላቶቿን ድል ያደረገችው በጾምና በጸሎት እንደሆነ ነው፡፡

ለእኛም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ምንም እንኳ ወርኃ ጳጉሜን የፈቃድ ጾም ቢሆንም በሀገራችን የተጋረጠውን ችግር እናልፍ ዘንድ በፈቃደኝነት እንጾማለን። እግዚአብሔር አምላካችን ለሁላችንም ጥበብ ሰጥቶናል።

ይህም ችግሮችን ሁሉ የምንፈታበት መንገድ ነው። በዚህም የዓመተ መሸጋገሪያና የክረምቱ ወር ማብቂያ በመሆኑ ዕለተ ምጽአት ስለሚታሰብበት በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ከሌሊት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን ተገኝተን ጠበል በመጠመቅ፣ በማስቀደስና በመጸለይ እንዲሁም ሥጋ ወደሙን በመቀበል ልናሳልፍ ይገባል።

ዕለተ ምጽአትም ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው ዓለም መሸጋገሪያችን ነውና በቀኙ እንቆም ዘንድ እንጾማለን፡፡

የሚመጣውን አዲስ ዘመንም በንጽሕና ለመቀበል ስላለፈው ዓመት ኃጢአታችን ንስሓ የምንገባበት ጾምም ነው።
ከተጋረጠብን ችግር «እግዚአብሔር ያድነናል» በማለት ልክ እንደ ዮዲት ሱባኤ ገብተን፣ ማቅ ለብሰን፣ አመድ ነስንሰንና ድንጋይ ተንተርሰን አብዝተን ልንጾምና ልንጸልይ ይገባል፡፡ ሊለያየን፣ ሊነጣጥለን፣ ሊበታትነን እና ሊገድለን ካሰበው እንዲሁም ፍቅርን፣ መተሳሰብንና አንድነትን ሊነፍገን ከቃጣው ጠላትና ሃይማኖታችንን ሊያስተወን ከሚመጣ ፀረ ሃይማኖት እንድናለን።

ስለዚህ ከፊታችን ያለችውን ስድስቱን የጳጉሜን ቀን በፍቅር፣ በአንድነትና በሃይማኖት ጸንተን፣ ጾመን፣ ጸልየን ለዘመነ ማቴዎስ እንድንደርስ እግዚአብሔር አምላካችን ይርዳን፤ አሜን።

ምንጭ፦ ከማኅበረ ቅዱሳን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

3 years, 4 months ago
  • በእግዚአብሔር መንግሥት አንድ ቀን +
    ጸአተ ነፍስ (The departure of Soul) ከተሰኘው የኦርቶዶክስ ቴዎሎጂ ምሁራን የጋራ
    ሥራ የሆነ ዳጎስ ያለ ድንቅ መጽሐፍ መግቢያ ላይ አንድ አባት ስለ አንድ ሰው ታሪክ የጻፉት
    ነገር በጣም አስገራሚ ሆነብኝ:: እጅግ መጥፎ የነበረ አንድ ሰው ድንገት በጠና ይታመምና
    በአልጋ ላይ ይውላል:: ሕመሙ እጅግ የጠና ቢሆንም የማይገድለው ሆነና ለሠላሳ ዓመታት
    ተሠቃየ:: በክፉ አመል ላይ ክፉ ሕመም ተጨምሮ ለሌሎችም ችግር ሆነ:: በአልጋው ላይ
    ሆኖም ደጋግሞ ሰውንም ፈጣሪውንም ይሳደብ ነበር::
    ከሠላሳ ዓመታት ሥቃይ በኁዋላ ግን ይህ ሰው ነፍሱ ከሥጋው ተለየች:: የመንደሩ ሰው
    ተሰበሰበና ማልቀስ ጀመረ:: "ውይ ተገላገለ" "ይኼ ክፉ አረፈ? ያረፍነውስ እኛም ነን!"
    እያለ በልቡ እያሸሞረ ቁጭ አለ:: አጅሬው ግን ሞተ ከተባለ ሦስት ሰዓታት ቆይታ በኁዋላ
    ድንገት እንደ እንቅልፍ ነቃ:: ሰዉ ድንጋጤም ደስታም ተቀላቅሎበት ተቀበለው::
    ከዚያች ዕለት ጀምሮ ሞገደኛው ሰው እንደቀደመው መናከሱን ትቶ ትሑት ለሰው አዛኝ ሆኖ
    አረፈው:: የጠሉት ሁሉ ይቅርታ እስኪያደርጉለት ድረስ እጅግ መልካም ሰው ሆነ:: አንድ
    አባት በሰውዬው መለወጥ ተደንቆ ሞቶ በነበረበት ጊዜ ምን እንደገጠመው ጠየቀው::
    እርሱም
    እንዲህ አለ :-
    "ከሞትሁ በኁዋላ ለሦስት ሰዓታት ያህል በሲኦል ሥቃይ ውስጥ ቆይቼ ነበር:: በሲኦል
    ካሳለፍሁት የሦስት ሰዓታት ሥቃይ የምድር ላይ የሠላሳ ዓመት ሥቃይ እጅግ ይሻለኛል::
    በሲኦል ሦስት ሰዓት ከመቆየት በምድር ላይ የዕድሜ ልክ ሥቃይ ይሻላል"
    በእርግጥ የሲኦል የአንድ ሰዓት ሥቃይ ከዚህ ዓለም የዐሥር ዓመት ሥቃይ ከበለጠ ከዚህ
    ዓለም የዕድሜ ልክ ደስታም የመንግሥተ ሰማያት የአንዲት ቀን ደስታ ይበልጣል::
    ንጉሥ ዳዊት "ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች" እንዳለ በመንግሥተ
    ሰማያት አንዲት ቀን መቆየት ደግሞ በዚህ ምድር ላይ ሺህ ዓመት ከመደሰት ይበልጣል::
    “በዚህ ዓለም ብዙ ዘመን ከመኖር በገነት አንዲት ቀን ደስ መሰኘት ይሻላል:: ከብዙ
    ዘመኖችም አቤቱ ይቅርታህን ማግኘት ይሻላል" 2 መቃ. 13:4

•••••••••••••፨፨፨፨•••••••••••••••
@Venisiya21 @Venisiya21
•••••••••••••፨፨፨፨•••••••••••••••

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana