ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago
የቀጠለ
`በጦርነት ሜዳ ውስጥ እራሴን አገኘሁት። የባሩድ ሽታ፣ የተቃጠለ ቤት ጭስ ፣ ጥይት እንደቆሎ ሚርከፈከፍበት ፣ እዛም እዚም ተበጣጥሶ የወደቀ የሰውነት አካላት ይታየኛል። አምላክ ምን ሊያስመለክተኝ እንዳመጣኝ አላውቅም ፤ ጦርነት ለማንነት ሲባል የሚደረግ ነው ብዬ አስብ ነበር፤ ታድያ ምኑ ላይ ነው ጥፋቱ?
በሀሳቤ መሀል ድንገት በጭስ መሀከል ሮጦ ሚያልፍ ሰው አየው ፤ ወዳለበት ተጠጋው። በእጆቹ ጠመንጃ ደግኗል።በጥንቃቄ ፣ በትኩረት ቀስ ብሎ ወደ አንድ ቦታ ላይ አፈሙዙን ደገነ። አፈመዙ በተደገነበት አቅጣጫ ተመለከትኩ።የደገነበት ሰው እሱን ራሱን ይመስላል ብቻ ሚለያዩት በለበሱት ልብስ ብቻ ነበር።
ተፋጠጡ። ቀድሞ ጠመንጃውን የደገነው ገደለው ... ገ ደ ለ ው። የራሱን አምሳያ ያለርህራሄ ደጋግሞ ተኮሰበት። ምናልባት ለምን ገደልከው ቢባል የበላይ አካል ትዛዝ ነው ይል ይሆናል። " ወይኔ የሰው ህይወት ወይኔ" አልኩ ።
አንጋጠጥኩ ወደ አምላኬ፤
ተመለከተኝ ቀጥሎ"ይህስ ምንድን ሰው አይደለምን?"
የምለው አልነበረኝም በዝምታ አቀረቀርኩ።
ካለሁበት የጦርነት አውድማ ጭስ እያንሳፈፈ ወሰደኝ። ጨለምለም ያለ ቤት ውስጥ ተገኘው። የላሸቀ አልጋ ላይ የተቀመጠች እናት ትታየኛለች። ልጇን እንደነገሩ ይዛታላች።
"እየውልሽ አንቺ ካለሽ ምግቤን አጣለው መጥፋት አለብሽ መጥፋት" አለቻት።
ጊዜም አልፈጀች አራስ ልጇን አንጠልጥላ ወጣች። ተከተልኳት። አራት በአንድ ሆኖ የተሰራው የቀበሌ ሽንት ቤት ውስጥ ገባች። በሩ በዝገት ምክንያት እንደ አፈረ የተፈረካከሰ ወደ ውስጥ የሚያሳይ ቀዳዳ ነበረው፤ አጮልቄ ተመለከትኩ። አስደንጋጭ ነው። የገዛ ልጇን ያለምንም ርህራሄ በሽንት ቤት ቀዳዳ ለቀቀቻት። የሲቃ ድምፅ ከጉድጓዱ ይሰማ ጀመር። ቆሻሻ እንደጣለ ዞራ ሳትመለከት ወጣች። የእናትም አንጀት ሲጨቅን ተመለከትኩ።
ታመምኩ። ከዚህ በላይ መቋቋም አቃተኝ እግሬ ሲከዳኝ፣ ጀርባዬ ሁሉ በውሃ ሲጠመቅ ፣ ከንፈሮቼ ከተጣበቁበት ሊላቀቁ አቅም አጠራቸው።
አምላኬን ተመለከትኩ። አሁን ግን ለመታበይ አልነበረም ፤ ማለቅስበት ፣ምሸሸግበት ፣ማቅፈው ፈልጌ ነበር።
"ይህም ሰው መሆን ማለት ነው።" አለኝ፤
ተድፍራ የተገደለች ነፍስ ፣ በማያቁት ከላይ ባለ አመራር ምክንያት ወንድም ወንድሙን ሲገል፣ ለመብል እናትነት ሲቀርብ። መቀበል ባልፈልግም አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው እና መራራዬን ፅዋ ተጎነጨው።
ለአሁን ይበቃል።`
—በረከት
፨፨፨አልቦ ርዕስ ፫፨፨፨
`በብዙ ምሰማው ይህ ነበር፤ "አቤት የሰው ልጅ ጥሩነት" የኔ እምነትም ይህ ነበር ። እንዲህም ብዬ ነበር "ምን ያህል መታደል ነው የሰው ልጅ ሆኖ መፈጠር"። ያኔ ነበር ታድያ ይህን ሁሉ ሳወራና ስታበይ አስታየትን ሳይሰጥ አምላክ በትዝብት ተመለከተኝ። ምላሽ አልሰጠኝም። ድንገት ግን ካለሁበት በጭስ ተንሳፍፌ የማላውቀው ጨለምለም ያለ ስፍራ ወሰደኝ። አሁንም ምላሽ አልሰጠኝም።
መጀመሪያው ፤አንዲት ጠየም ያለች፣ ልጅ እግር ፣ ዕድሜዋ ከአስራአንድ ማትበልጥ፣ ወደ እኔ አቅጣጫ ተመለከትኩ። እሷ እኔን ማየት የምትችል አልመሰለኝም። ከምድር ትንሽ ሳፈፍ ብዬ ነው ያለሁት፣ እንዲህ አይነት ነገር ለአይን ግራ ስለሆን ልትደነግጥ ትችል ነበር ፣ግን ምን እንዳልተፈጠረ ከተንሳፈፍኩበት ከእገሬ በታች አልፋ ሄደች፤ ያኔ እያየችኝ እንዳልሆነ አረጋገጥኩ።
ትንሽ ናት ፣ ሰውነቷ ደቃቃ ነው፣ ፊቷ ችግር ያጠወለገው ይመስላል። በጭለማው ለመሮጥ በሚቀርብ እርምጃ እየተቻኮለች ትራመዳለች። ድንገት ግን ከየት መጣ ያላወኩት ከጎኗ ይከተላት ጀመር። ዓይኑን ሚዳቋ እንዳየ ጅብ ያጉረጠርጣል።
"እ ቆንጂዬ" አላት። ቀፈፈኝ። ምግብ እነዳየ ውሻ ላህጩን ሚያዝረበርብ መሰለኝ።
እሷ ግን ምላሽም ሳትሰጠው። ከሱ ቀደም ብላ ፈጠን ፈጠን እያለች መጓዝ ጀመረች።
አሁንም ይከተላታል ፤ በጣም የጨላለመበት ቦታ ተገን አድርጎ ወደግድግዳው ሳባት። ጮኸች ግን ማንም አልሰማት ካለኔ ውጭ። በያዘው ጨርቅ አፏን ጠቀጠቀው፤ ምግቡን እንዳገኘ አውሬ አንገቷን አንቆ፣ እጆቿን ጠምዝዞ ልብሷን ሊያወልቅ ይታገል ጀመር።
ላስቆም ፣ ለመጮህ ሞከርኩ። ነገር ግን እኔ ለማየት እንጂ ጣልቃ ለመግባት አልተፈቀደልኝም።
ወደመሬት ባለው ጉልበት ጣላት።ልብሷን ቀዳዶ አወለቀውና ደፈራት ... ደፈራት ሴትነቷን ፣ ክብሯን ፣ እኔነቷን።
እዛው አፈር ላይ ፣ ባሰቃየበት ቦታ ፣ ትንፋሿ እየተቆራረጠ ፣ ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ፊቱን አተኩሯ ተመለከተችው። ያየችውን ለሌላ ትነግራለች ብሎ ያሰበ ይመስለኛል።
ያላንዳች ርህራሄ አንገቷን አነቀው። መደፈሯ ብቻ ትልቅ ጉዳት ሆኖ ሳለ፤ ባላሰበችው መንገድ ሌላ ጭካኔ ደረሰባት ። ብትታገለውም አዳ'ኝና ታዳኝ አንድ አይደሉምና ገደላት...ገ ደ ላ ት።
የእጆጁን ላብ ከኪሱ በሚገኝ ጨርቅ ጠራርጎ የሞተችው ታዳጊዋ ላይ ወረወረው። ወደመጣበትም ጭለማ እያፏጨ ተመለሰ።
ቃላት አጠረኝ ምን ልል እችላለው ቀና ብዬ አምላኬን ተመለከትኩ። እሱም በዚህ አላበቃም። ያለሁበት በጭስ ተሸፈነ ደግሞ ወደ ሌላ።
ይቀጥላል...`
—በረከት
አደን
አሣዳጄን አመለጥኳት አመለጠችኝ ያሣደድኳት፡፡ ኗሪ ሆንኩኝ እንደፍየል በነብርና ቅጠል መሀል፡፡
አቤት አለች ያልጠራኋት የጠራኋት ድምፅም የላት፡፡ ራቂኝ 'ምላት ጎኔ ወድቃ ቅረቢኝ 'ምላት ከኔ ርቃ፡፡
አንዴ ስታደን አንዴም ሳድን ዕረፍት አጥቼ ስባክን የዕድሜዬን ጀንበር ብታዘባት ልትጠልቅ ምንም አልቀራት።
የደንበኛችን ገድል
*በአንዱ መከረኛ ወቅት የኾነ ነው አሉ፡፡ የዐዲስ አበባ ሰው ኹሉ ሰላማዊ እንቅስቃሴው ታውኮ፣ በየቤቱ በተከተተበት በአንድ አስፈሪ ምሽት፣ ጥንቅቅ ብሎ የሰከረ የእኛው ግሮሰሪ ጀብራሬ: መኻሉን የመኪና መንገድ ይዞ እያቅራራ፣ እያንጎራጎረ፣ እየጮኸ ፣ ቆላና ደጋ እየረገጠ ይኼዳል አሉ፡፡
በዚኽ መኻል ኹለት የጸጥታ ኀይሎች አገኙት። እንኳን ሌሊት ኾኖ በቀንም የሰዉ ሰላማዊ እንቅስቃሴ የተገታበት ጊዜ ነበርና የጸጥታ ኀይሎቹ ተናደውበታል፡፡ ከተማዋ እንዲኽ ባለ ጭንቅ ተይዛ እሱ ሰክሮ በመለፋደዱ በግነዋል፡፡
<<ና አንተ!›› ጠራው አንደኛው በቁጣ፡፡
<<አቤት!›› አለ ትከሻውን በትዕቢት እያማታ፡፡
‹‹ለምንድነው ከተማውን የምታውከው!? ... ጸጥ ብለኽ አትኼድም?››
‹‹ምን ጎደለብኝና ጸጥ እላለኹ!?›› አለ ቀብረር ብሎ ስካር ያዝ ባደረገው አንደበት፡፡
‹‹እንደዚያ ነው!?›› አለና አንዱ ፖሊስ በጥፊ አጮለው።
የእኛው ደንበኛ ደንግጦ፣ ‹‹ምን ነካችኹ! ... አባል እኮ ነኝ!›› አለ መታወቂያውን ለማውጣት እጁን ወደ ኪሱ እየሰደደ፡፡
<<የምን አባል?›› ፖሊሶቹ ጠየቁ፡፡
<<የገዥው ፓርቲ ነዋ!>>
‹‹እና ብትኾንስ!?›› አለና ኹለተኛው ፖሊስ ተናድዶ በጠረባ ቢያነጥፈው፣ ወዳጃችን መሬት ላይ እንደተንጋለለ እንዲኽ አለ አሉ፤
<<ኧረ ጉድ ነው ! ሳልሰማ መንግሥት ተቀየረ እንዴ!?>>*
—የማምሻ ወጎች
*አንድ ሰው ሉካንዳ ሄዶ ፣ ሥጋ ቆራጩን
"ጥሩ የምትለውን ሥጋ ስጠኝ" ሲለው፥ ምላስ ሰጠው።
በል ደግሞ መጥፎ የምትለውን ሥጋ ስጠኝ" ሲለውም፥ ምላስ ሰጠው።
"ጥሩም ሥጋ ስጠኝ፣ መጥፎም ሥጋ ስጠኝ ብልህ ምላስ ሰጠኸኝ። ምነው?" ሲለው
"ጥሩም ነገር፣መጥፎም ነገር የሚመጣው ያው በምላስ ነው።"ብሎ መለሰለት።*
—በከንፈርሽ በራ'ፍ
ሕይወት ቀላል ነበረች።
ቀላልም ትሆን ነበር።
ሞታችንን እንደሞታችን እንጂ እንደሞታቸው ላንሞት፣
ሕይወትን እንደሕይወታችን ከመኖር ይልቅ እንደ ሕይወታቸው ለመኖር መረጥን።
ለምን?
፨፨፨
እኔነቴን ሳልወድ ፥ ሳልስመው አቅፌ
ሞትህ አይግደለኝ ፥ ከሕይወት ተርፌ
፨፨፨
የተአምራት ልጅ
በጣም በጣም ሰፊ
እጅግ እጅግ ትልቅ
እንኳን ከፈለግሁሽ
ከተውሁሽ የሚልቅ
(ሰማይ ነው ሕይወቴ)
በጣም በጣም ጠባብ
እጅግ እጅግ ትንሽ
እንኳን ከእንቅብ ላይ
አይወጣም ከጋንሽ
(ብርሃን ነው ሕይወትሽ)
ሂጂ...
መሄድሽ ሕይወቴን ፥ ውጋገን አይቀማው “አይንጋለት” ስትይ ፥ ያበራል ጨለማው።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago