ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
?የደራሲ እስከዳር ግርማይ "የፈረንጅ ሚስት" መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ተተረጎመ
የደራሲ እስከዳር ግርማይ "የፈረንጅ ሚስት" የተሰኘ መጽሐፍ "WHITE MAN'S WIFE"በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛ እንደተተርጎመ ተወዳጅ ሚዲያ ዘግቧል።
የእስከዳር ግርማይ አዲሱ የእንግሊዝኛ መጽሀፏ እውነተኛ ታሪኮችን ይተርካል። በተለይም በተለያየ የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሴቶችንና የውጭ ሀገር ዜጋ ያገባ ኢትዮጵያዊ ወንድን ከምሳሌ እና ኹነቶች ጋር እያጣቀሰ የዕለት ተዕለት ህይወታቸውን ያስቃኛል።
መጽሀፉ መጀመሪያ የተጻፈው ''የፈረንጅ ሚስት'' በሚል ርዕስ እንደመሆኑ ተደራሽነቱ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ማዕከል አድርጎ የተነሳ ነበር። ሆኖም ኢትዮጵያውያን ሴቶች ዜጎቻቸውን ሲያገቡ የሚያጋጥማቸውን እይታም ድንበር ተሻጋሪ እንደመሆኑ " WHITE MAN'S WIFE" ወደሚል ተተርጉሟል።
የመጽሀፍ ወደ እንግሊዝኛ መተርጎም የኢትዮጵያ ስነጽሁፍን ለአለምአቀፍ አንባቢያን ተደራሽ በማድረግ ረገድ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያዋጣ ይታመናል ተብሏል።
የፈረንጅ ሚስትን ወደ እንግሊዝኛ መጽሀፉን የተረጎመችው ራሷ ደራሲዋ ስትሆን፣ እንግሊዛዊው የሥነጽሁፍ ባለሙያው ክርስትያን ሀሪፎርድ መጽሀፉን በአርታኢነት ሲሠራው፣ አሳታሚው ጆርጅ ኦፍ ሚድልተን "ይህ የኢትዮጵያን ሴቶች ታሪክ ብቻ ሳይሆን ስለሁላችን እና ስለምርጫዎቻችን ነው" በማለት አስተያየታቸውን መግቢያው ላይ አስፍረውበታል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
?"አዳብና ፌስቲቫል" ለ3ኛ ጊዜ ሊካሄድ ነው
የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት "አዳብና ፌስቲቫል" ከመስከረም 16 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ለሶስተኛ ጊዜ በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ በተለያዩ መርሐግብሮች እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ይህ ፌስቲቫል በዋናነትም በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ኬላ ከተማ መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም በአደባባይ በትልቅ ፕሮግራም እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
በአዳብና ፌስቲቫል ከ30 እስከ 100 ሺህ ጎብኚዎችን የሚጠበቁ ሲሆን በ50 እናቶች የተዘጋጀ 100 ኪሎ ክትፎንና 100 ኪሎ የክትፎ ቅቤ በአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ለማስፈር ስራዎች እየተሰራ እንደሆነ ተነግሯል።
የአዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማኅበር አዳብና የጉራጌ የልጃገረዶችና ወንድ ወጣቶች ባህላዊ ጨዋታ መተጫጫ ፌስቲቫል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ ለማድረግ እየሠራ ይገኛል።
የአዳብና ባህል የልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ጨዋታና መተጫጫ ስነስርዓት ሲሆን ባህሉ በጥናት በተረጋገጠ መረጃ መሰረት 800 ዓመታት በፊት በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ አካባቢ ለዘመናት ሲከበር እንደኖረ ማኀበሩ ገልጿል።
ይህ ድንቅ ባህል በተለያዩ ምክንያቶች ደብዝዞና ለጠፋ ታቃርቦ የነበረ ሲሆን የአዳብና በከስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ከአካባቢው የመንግስት መዋቅሮች ጋር በመሆን ባደረገው ጥረት ባህሉ ጥንታዊ ወጉና ቱባ ባህሉ ይዞ በከፍተኛ ሁኔታ በማንሰራራት በአሁን ሰዓት በአካባቢው ላይ በፌስቲቫልነት እየተከበረ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
?"አፍሪካን እናክብር" ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው
የ2024 "አፍሪካን እናክብር" ወይም "አፍሪካን እናክብር" ፌስቲቫል ከጥቅምት 27 እስከ ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚከበር አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
አፍሪካ ያላትን ባህል፣ ሥነ ጥበብ፣ ቅርስ፣ ቴክኖሎጂ እንዲሁም የቢዝነስ ሀብቶቿን ለዓለም ለማስተዋወቅ ፌስቲቫሉ ጠቀሜታ እንዳለው ነው የተገለፀው።
በተጨማሪም የአፍሪካ ሴቶች እና ወጣቶች እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ እና እንዲገኙ ዕድል እንደሚፈጥርም ታምኖበታል።
የተለያዩ ሥራ ፈጣሪ ባለቤቶችም ስራዎቻቸውን እንዲያስተዋውቁ ያስችላል ተብሏል።
ፈስቲቫሉ ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚህኛው ዓመት ለማክበር በጋራ እንደሚሰራ ታውቋል።
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ኤምባሲዎች በአዘጋጅነት ተሳትፈውበታል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
?ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ አፍሪካ መድረክ!
ሠዓሊ ወንድወሰን ከበደ የአፍሪካ የዘንድሮ 2024 ለፋሽን እና የጥበብ ሽልማት እውቅና ከሚያገኙ100 አፍሪካውያን ምርጥ ጥበበኞች አንዱ ሆኖ ተሰይሟል።
ይህ የሽልማት ዝግጅት ዘንድሮው ህዳር ወር ላይ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
?የዓለም የቱሪዝም ቀን በኢትዮጵያ !
የዓለም የቱሪዝም ቀን ከዛሬ መስከረም 7 እስከ መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም ለሶስት ቀናት በኢትዮጵያ ይከበራል።
የተለያዩ የኢጋድ አባል ሀገራት፣ ክልሎችና የቱሪዝም ተዋንያን የሚሳተፉበት "Origins travel market" የተሰኘ አውደርዕይ እንደሚካሄድ ጠቅሷል።
የቱሪዝም ሚኒስቴር ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ቀኑን በማስመልከት መስከረም 7 2017 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ ኹነት ማዘጋጀቱን ገልጿል።
በሁነት ዝግጅቱ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ይፋ እንደሚሆንም አመልክቷል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
?የመዓዛ ወርቁ አዲስ ድራማ ሊጀምር ነው
ከዚህ ቀደም "ወፌ ቆመች" እና "ደርሶ መልስ" በተሰኙ የሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድራማዎችን ጨምሮ በበርካታ የሬድዮና ቴሌቪዥን ድራማዎች የምናውቃት ደራሲ መዓዛ ወርቁ "አላውቅም አናውቅም" የተሰኘ የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ በቅርቡ እንደሚጀመር ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከደራሲዋ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተከታታይ ድራማው ከሐሙስ መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በዲኤስትቪ አቦል ቻናል 465 ላይ ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ መተላለፍ ይጀምራል ተብሏል።
ለተጨማሪው:https://t.me/EventAddis1
? የ2016 ፊልሞች ዝርዝር
ዛሬ በሚጠናቀቀው 2016 ዓ.ም በርካታ ሀገርኛ ፊልሞች ለእይታ በቅተዋል።
በተለይ በዚህኛው ዓመት ከተለመደው የ"ሮማንስ ኮሜዲ" ፊልሞች ይልቅ በድርጊት የተሞሉ ፊልሞች በብዛት የቀረቡበት ዓመት እንደሆነ ኤቨንት ድረገፅ ያነጋገራቸው የፊልም ባለሞያዎች ይናገራሉ።
በ2016 ዓ.ም ለእይታ ከበቁ ፊልሞች ውስጥ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ እነዚህን ሃያ ፊልሞች ለማስታወስ ያህል አቅርቧል።
2.6:00 ሠዓት ከሌሊቱ:የበኃይሉ እንግዳ ፊልም
ጃናሞራ : የያለው ደስታ (ራስ) ፊልም
ትዝታ : የዳንኤል አንማው ፊልም
አፊኒ: የታሪኩ መኮንን ፊልም
6.ማለዳ: የሳሙኤል ካሣሁን ፊልም
7.ባለቀ ሠዓት: የተሻለ ወርቁ ፊልም
9.ባለ ክራር:የባዩሽ ልጅ(ሳሚ) ፊልም
ዜሮ ድግሪ: የአልዓዛር ሳለልኝ ፊልም
አል-ሞቷል: የፍፁም ክብረት ፊልም
12: ህጋዊ ድሃ: የወንድምአገኘ ለማ ፊልም
13.ጀስቲሺያ : የቅድስት ይልማ ፊልም
አልነጋም :የብዙአየሁ አደነ ፊልም
ቀይ መስመር : የኮኮብ ብርሃኔ ፊልም
ረብራ: የበላይ ፀጋዬ ፊልም
ሁለት ቅጣት: የመዝሙር ዳዊት ፊልም
ካሲናዬ: የብርሃኑ ወርቁ ፊልም
20.ሁለት ዓይነት: የአመሐ ዱጉማ ፀሐይ ፊልም
ለተጨማሪው : https://t.me/EventAddis1
? ከEventAddis/ሁነት አዲስ ምስጋና አለን!
ለቤተሰቦቻችን የላቀ ምስጋና !
ዛሬ በሚጠናቀቀው 2016 ዓ.ም በ"Event Addis/ሁነት አዲስ" ቤተሰብነት አብራችሁን ለዘለቃችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው።
በዚህ ዓመት እጥር ምጥን ያሉ አስተማማኝና ፈጣን የኪነጥበብ መረጃዎች ምንጭ ስለሆንን በጣም ደስ ብሎናል።በተለያዩ መንገድ ሀሳቦቻችሁን( አስተያየቶች ) ስለነገራችሁን ከልብ አመስጋኞች ነን።
ከቴሌቪዥን እስከ ሬድዮ ከጋዜጣ እስከ ማህበራዊ ትስስር ገፆች የምትገኙ ሚዲያዎች በኩነትም በኪነትም በኩል ያሉ ትኩስ መረጃዎቻችንን ስለመርጧችሁልን በየጣቢያዎቻችሁ በስፋት ስላሰራጫቹሁልን ከልብ እናመሰግናለን !!።
እዚህ ጋር ደግሞ የምስራች አለን !
በዚህ ዓመት የድረገፅ አገልግሎታችን በይፋ ተጀምሯል ደግሞም በ2017 አዲስ ዓመት በሬድዮ፣ በዩቲዩብ፣ ቲክቶክን ጨምሮ በአዳዲስ የሚዲያ አማራጮች ወደእናንተ መድረስ እንጀምራለን። ያድረሰን እንኑር ያኑርን።
ለሁላችሁም መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ !
ለአስተያየት: @Tmanaye
ቴሌግራም: https://t.me/EventAddis1
Website: https://eventaddis.com
Facebook:https://www.facebook.com/profile.php?id=100083170462851
? "ሽልማት" የሙዚቃ አልበም ተለቀቀ
አባትና ልጅ በጋራ የሰሩት አልበም ተለቋል።ወላጅ አባት ኤላ ማን እና ልጅ ክርስቲና የተጣመሩበት "ሽልማት" የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ከቀናት በፊት በራሳቸው የዩቲዩብ ቻናልና በዓለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ እንደተለቀቀ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ተመልክቷል።
ይህ "ሽልማት" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የሙዚቃ አልበም አስር የሙዚቃ ስራዎችን በውስጡ ይዟል።
ለተጨማሪው : https://t.me/EventAddis1
?በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት ውስጥ የተገነባው ማዕከል እስካሁን ስራ አለመጀመሩ ተገለጸ
ለዓመታት በግንባታ መጓተት ምክንያት ቆይቶ የነበረው "አሸናፊ ከበደ የሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል" ተመርቆ ለስራ ዝግጁ ከሆነ ወራት ቢያስቆጥርም አሁንም ስራ አለመጀመሩን ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
አዳራሹ ዘመናዊ ሳውንድ ሲስተም ስለሚያስፈልገው መጓተቱን ያስታወቁት ፒያኒስትና በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት የአሸናፊ ከበደ ሙዚቃዊ ጥበባት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ግርማ ይፍራሸዋ ናቸው።
በአዳራሹ የሚገጠመው ዘመናዊ ሳውንድ ሲስተም ከውጭ ሀገር የሚገባ በመሆኑና እስካሁን ባለው ሂደት ገብቶ ባለመጠናቀቁ አዳራሹ ስራ ሳይጀምር መቆየቱን አቶ ግርማ ይፍራሸዋ ተናግረዋል። ከውጭ የሚመጡትን እቃዎች ከመጠበቅ ውጭ አዳራሹ ለስራ ምቹና ብቁ ነው በማለት ከመጪው መስከረም ወር በፊት እንዲጠናቀቁ እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ግርማ አክለው ገልጸዋል።
የያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ሁለገብ አዳራሽ ለተለያዩ የት/ቤቱ የሙዚቃ ተማሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ለተለያዩ ከት/ቤቱ ውጭ ለሚገኙም የሙዚቃ ባለሙያዎች የኦርኬስትሬሽንና መሰል ስራዎች ማሳያ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል።
?መረጃው የመናኸሪያ ሬዲዮ ነው።
ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago