እውነት ለሁሉ

Description
በዚ ሁሉም ነገር አላፊ በሆነው ዓለም ውስጥ እየኖርን ፣ ለማያልፈው ዘላለማዊ ለሆነው ለክርስቶስ እንኑር "እርሱ ብቻ የማይሞት ነውና" (1ኛ ጢሞ 6፡16)
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago

1 month ago

Church Infallibilityን ያልተረዳ ሙግት

"ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ጠባቂና ባለ አደራ ናት ነገር ግን ይህ ብቻ ቤተክርስቲያንን infallible አያደርጋትም በአንድ ነገር ትክክል ኾነች ማለት በኹሉ ነገር ትክክል ናት ማለት አይደለምና።" የሚለው የፕሮቴስታንቶች ሙግት ነው። ነገር ግን ይህ ሙግት የቤተክርስቲያንን አይሳሳቴነት የተረዳ አይመስልም እኛ ቤተክርስቲያን በኹሉ ነገር ትክክል ናት አላልንም እኛ ያልነው ቤተክርስቲያን በአባቶች ስምምነት ባስተማረችው አስተምህሮ ላይ ስህተትን ልትሠራ አትችልም ነው።

ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ስትወስን ከተጠቀመቻቸው መሥፈርቶች ውስጥ "ሐዋርያዊ ጸሐፊነት (ከሐዋርያትና የእነርሱ ቅርብ ደቀ መዛሙርት) ፣ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትና ትክክለኛ አስተምህሮ" ይገኙበታል። መሥፈርቶቹ እነዚህ መኾናቸውን ፕሮቴታንቶች ራሱ የሚቀበሉት ነው። እስቲ ከነዚህ መሥፈርቶች ትክክለኛ አስተምህሮን ለይተን እንየው። ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ስትወስን ከነበሩት መጽሐፍት ውስጥ ትክክለኞቹን የለየችው ከሐዋርያት በተቀበለችው ትክክለኛ አስተምህሮ መዝና ነው የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ደግሞ ሊሳሳት ስለማይችል መጽሐፉም ሊሳሳት አይችልም እንላለን።

ፕሮቴስታንቶች ግን ቤተክርስቲያን በአስተምህሮዋ ልትሳሳት ትችላለች ብቻ ሳይኾን ተሳስታለች ብለው ያምናሉ ስለዚህ ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን የመረጠችው በተሳሳተ መሥፈርት ነው። መሥፈርቱ ከተሳሳተ ደግሞ የመሥፈርቱ ውጤትም ስህተት ያለበት ነው የሚኾነው። Fallible list of infallible books ነው የምንቀበለው ቢሉ ራሱ እነዛ listኡ ብቻ ሳይኾን መጽሐፍቱም ጭምር ከመጀመሪያውኑ infallible ለመኾናቸው ምሥክርነት አይኖራቸውም መጽሐፍቱ ራሱ የተመረጡት በተሳሳተ መሥፈርት ላይ ተመርኩዘው ነውና።

{ኪዳን ዘኢየሱስ} እንጻፈው!!

1 month ago

{አህመዲን ጀበል} ጠየቂ👀
መጽሐፍ ቅዱስ በሉቃስ ወንጌል 22: 3 -5 “ሰይጣንም ከአሥራ ሁለቱ ከተቆጠረው አንዱ በነበረው የአስቆሮቱ በተባለው በይሁዳ ገባበት፤  ሄዶም እንዴት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከመቅደስ አዛዦች ጋር ተነጋገረ፡፡ እነርሱም ደስ አላቸው፥ ገንዘብም ሊሰጡት ተዋዋሉ፡፡ እርሱም በነገሩ ተስማማ” ይላል፡፡ ሰይጣን በይሁዳ ገብቶ ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ካደረገውና ክርስቲያኖች እንደሚሉት ኢየሱስም ተይዞ ከተሰቀለ ሰይጣን ለክርስቲያኖች ባለ ውለታ ሆኗል ማለት ነው፡፡?ለምን ቢሉ ክርስቲያኖች እንደሚሉት በኢየሱስ መሰቀል ነውና “ድነው ከኃጢአት ነጻ የወጡት፤ ገነትም ወራሽ የሆኑት፡፡”  ይህ ነው የክርስትና መዳኛ መንገድ፡፡ ስለዚህ ሰይጣን በይሁዳ ገብቶ ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ አደረገው፡፡ ከዚያም ክርስትና እንደሚለው ኢየሱስ ተይዞ ተሰቀለ፡፡ በጥሞና ካስተዋልነው ክርስቲያኖች “ድነናል” ያሉበት “ስቅለት” እንዲሳካ ሰይጣን ግንባር ቀደም አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ የመዳኛውን መንገድ ዘርግቷል፡፡ ታድያ የክርስትና አብዩ አስተምህሮትና መዳኛው የሰይጣን ሊሆን አይደል? ሰይጣን በይሁዳ ገብቶ ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ባያደርግ ኖሮ ስቅለት ይሳካ ነበር? ክርስትና እንደሚለው ክርስቶስ ባይሰቀል ክርስትያኖች ከኃጢአት ይነጹ ነበርን? ክርስትና የሚባል እምነትስ ይኖር ነበርን? በፍፁም!! ታድያ እንደ ሰይጣን ማን መልካም ሰሪ አለ? ኢየሱስን አሰቅሎ ክርስትያኖችን አድኖ የለም እንዴ?

አሕመዲን ጀበል ይህንን ጥያቄ ያቀረቡበት መንገድ ከምሑራዊ አካሄድ ያፈነገጠ፣ ድፍረትና ንቀት የታከለበት እንዲሁም የክርስትናን ትምህርት በሚያንቋሽሽ አነጋገር ነው፡፡ አካሄዳቸውን በማበላሸት ገና ከጅምሩ ኩሬውን መርዘውታል፤ የማስተማር ፍላጎታቸውንና ቅንነታቸውንም እንድንጠራጠር አድርገውናል፡፡ የክርስቶስ ወደ ምድር መምጣትና ስለ ሰው ልጆች ኃጢኣት መሞት የእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እቅድ እንጂ የየትኛውም ፍጥረት ዕቅድ አልነበረም (ራዕይ 13፡8፣ የሐዋርያት ሥራ 4፡27-28)፡፡ ወደ ምድር የመጣውም በገዛ ፈቃዱ ነፍሱን ስለ ብዙዎች ቤዛ ለማድረግ እንጂ ተገዶ አይደለም (ዮሐንስ 10፡11፣ 10፡15፣ 10፡17-18 15፡13፣ ማርቆስ 10፡45)፡፡ ስለ ሞቱና ስለ ትንሣኤው አስቀድሞ መናገሩን በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ እናነባለን (ማቴዎስ 12፡38-40፣ 16፡21፣ 17፡22-23፣ 20፡18-10፣ 21፡33-46፣ 26፡21-32፣ 26፡36-40፣ 26፡61-62፣ ማርቆስ 8፡31፣ 9፡9፣ 9፡30-31፣ 10፡33-34፣ 10፡45፣ 12፡1-12 14፡18-28፣ 14፡32-40፣ ሉቃስ 9፡22፣ 11፡29-30፣ 13፡32-33፣ 20፡9-19፣ 22፡15-20፣ 22፡39-46፣ ዮሐንስ 3፡13-14፣ 8፡28፣ 12፡32-34)፡፡ ስለዚህ የክርስቶስ ሞት በሰይጣን የታቀደ አልነበረም፡፡ ሰይጣንም ሆነ በአፅናፈ ዓለም ውስጥ የሚገኝ የትኛውም ፍጥረት በእግዚአብሔር እንደተፈጠረ፣ በእርሱ ሉኣላዊ ሥልጣን ስር እንደሚገኝና እግዚአብሔር አምላካችን የሁሉ የበላይ እንደሆነ ክርስትና ያስተምራል (ዳንኤል 4፡35፣ 2ዜና 29፡14፣ 20፡6፣ ዘዳግም 10፡14፣ ነህምያ 9፡6፣ ራዕይ 4፡11)፡፡ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ቁጥጥር ውጪ እንደሆነ ማሰብና የእግዚአብሔር ተፎካካሪ አካል አድርጎ መሳል የእግዚአብሔርን ሉኣላዊ ሥልጣን ያለማወቅ ነው፡፡ ሰይጣን የይሁዳን ክፉ ምኞት በመጠቀም ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ሲያደርገው የእግዚአብሔርን ዘለዓለማዊ ዕቅድ በመረዳትና የራሱን የሽንፈት መንገድ እያመቻቸ መሆኑን በማወቅ አልነበረም፡፡ ይህንን በማድረጉ እንደ ይሁዳ ሁሉ ሰይጣንም ራስን የማጥፋት ተግባር ፈፅሟል፡፡ የኢየሱስ ሞት ሰይጣንን አዋርዶታ፡፡ ትንሣኤው ደግሞ እስከ ወዲያኛው ኃይሉን አንኮታኩቶታል! ሰይጣን በየዘመናቱ የእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ ጣልቃ በመግባት ለማበላሸት ቢሞክርም እግዚአብሔር ግን የዕውቀቱን ምጡቅነት እና የጥበቡን ልቀት በማሳየት ሰይጣንን ሲያዋርደው እንመለከታለን፡፡ ለምሳሌ ያህል ሰይጣን ኢዮብን ሲፈትነው ፃድቅ የሆነውን ኢዮብን ከእግዚአብሔር በመለየት ለማጥፋ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ግን የሰይጣንን ፈተና የኢዮብን እምነትና ፅድቅ ለመግለጥ እና ለትውልዶች ሁሉ ማስተማርያ ለማድረግ ተጠቅሞበታል፡፡ ሰይጣንም ዕቅዱ ግቡን ሳይመታ ቀርቶ አፍሯል፡፡ የኢየሱስም ስቅለት እንደዚያው ነው፡፡ የተዋረደው ሰይጣን ዛሬ በእነ አሕመዲን በኩል በመምጣት ውርደቱንና ሽንፈቱን ለማስተባበል ቢሞክር አንሰማውም፣ አንቀበለውም፡፡

ምንጭ {ewnet lehulu} ድኀረ ገፅ!!

1 month ago
***🚩*** የዕብራውያን ጸሐፊ

🚩 የዕብራውያን ጸሐፊ

https://t.me/TheTriune/1184 (ክፍል 1)

https://t.me/TheTriune/1186 (ክፍል 2)

https://t.me/TheTriune/1192 (ክፍል 3)

https://t.me/TheTriune/1215 (ክፍል 4)

3 months, 2 weeks ago
እውነት ለሁሉ
3 months, 2 weeks ago

ሼሁ ቁርአን ላይ በተፃፈው መሠረት እውነቱን ነው የተናገረው
ቁርአን ከ20 በሚበልጡ አንቀፆቹ በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ተዋጉ ነው የሚለው
አላህ ከምእመናን ነፍሶቻቸውንና #ገንዘቦቻቸውን_ገነት_ለእነሱ_ብቻ ያላቸው በመሆን ገዛቸው ሱራ 9:111

በቁርአን ሶላትና ግዴታ ምፅዋት ጂዚያ ወይም ግብር  እኩል አብሮ ነው የሚሄዱት ሶላት ሚሰግድ ከሆነ ዘካት ግዴታ ምፅዋት መክፈል አለበት

እስልምናን የማይቀበል ሶላት የማይሰግድ ከሆነ ደግሞ ጂዚያ ግብር መክፈል አለበት
ከሀዲዎች ወይም ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች በተገኙበት ቦታ ሁሉ መገደል አለባቸው ነገር  ግን ገንዘብ ከከፈሉ ተውዋቸው ነው የሚለው ሱራ 9:5 ?
ከኡስታዝ ዮሱፍ

3 months, 3 weeks ago

*✝️#ይደንቀኛል_ዘላለም✝️*

ይደንቀኛል ዘላለም የሰለጠነ ስም ሰምቼ
እኔም ወጣሁ ከስራት ይሄን ስም ጠርቼ
❤️#ኢየሱስ እስኪ ሞት ይደንግጥ ይህንን ስም ልጥራ
ገዳዬን ላድነው ልውጣ ልሰማራ
ተው አታቅልሉብኝ  አትግፏት እውነቴን
በጽናው አለት ላይ ላንጽበት ቤቴን(2)
❤️#ኢየሱስ ማልጄ ልገስግስ ሰልፍ አለብኝ ዛሬ
ወንጭፌና ቀስቴ አንተ ነህ ጠጠሬ
ከሞት የዳንኩብህ ማምለጫ አለቴ
ሀይል አስታጣቂዬ ቅደምልኝ ፊቴ(2)
❤️#ኢየሱስ ወይኒው ተናወጠ  ወለል አለ ደጁ
ነፃነት ነው ስሙ ፅድቅ ነው አዋጁ
መታመን በዚህ ስም መደገፍ በጌታ
እፌይታ ነው ትርፉ የማታ ማታ(2)
❤️#ኢየሱስ የጌታን ስም ጥሩ የጠሩት ድነዋል
የቀደሙት ሁሉ በዚህ ስም ታምነዋል
ሰማይና ምድር ፀኑ ለዘላለም
ኢየሱስ ነው ሁሌም ቤዛዋ ለአለም(2)
❤️**#ኢየሱስ

3 months, 3 weeks ago

እስራኤል ሱላማጢስ ከሞተ በኩር ተርፈው ከግብጽ ባርነት ወደ ከነዐን በበጉ መሥዋዕት እንዲመለሱ ፤አማናዊቷ ሱላማጢስ ድንግል ማርያም ኹላችንን የሚዋጀን የዓለሙን ኃጢአት የሚያስወግደውን (ዮሐ1፡29) የእግዚአብሔርን በግ ታቅፋ ከተሰደዱበት ከግብፅ ወደ እስራኤል ተመለሰች ለዚኽም ሰሎሞን ምልሰቷን አስመልክቶ “አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። ”መኃል 7፥1 ሲል በምሥጢር ተቀኘ.....እኛም ድንግል ኾይ የታቀፍሽውን መድኃኒት ይዘሽ ወደ ሕይወታችን ተመየጢ ተመየጢ እንበላት........እርሷም ከከበረው ልጇ ኢየሱስ ጋር ወደ ኃጢአተኛው ሕይወታችን ትመለሳለች ?

"ሄሮድስም ከሞተ በኋላ፥ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፦
የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ። እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ያዘና ወደ እስራኤል አገር ገባ።"ማቴ 2፡20-21

………………………………………………
https://t.me/orthodoxawitewahdo
ቻናሉን ተቀላቅለው ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ወንጌል ይማሩ...!

ይቆየን

3 months, 4 weeks ago

‹‹ልብሱን ብቻ የዳሰስኹ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ›› ማቴ 9፡21
ጊዜው አብዛኛው ማኅበረሰብ በጨለማ ፤ ተስፋ በመቁረጥ እና በአጋንንት እስራት ውስጥ የነበረበት የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ነበር ወቅቱ በኃይልና በስልጣን ሙታንን የሚያነሳ ፤ ጎባጣን የሚያቀና ፤ ሽባን የሚተረትር ፤ ዕውራንን የሚያበራ ፤ ከአጋንንት እስራት የሚፈታ ፤ በበሽታ በደዌና በሰይጣን ላይ ስልጣን ያለው በጥቂት እንጀራና አሳ ብዙሃኑን የሚመግብ ብርቱ መሲህ ኢየሱስ እንደተነሳ በመንደሩ በሃገሩ ሁሉ የሚወራበት በችግር ላይ ያሉ በርሱ ለመዳን የሚመኙበት ነፍሳት አጥብቀው እርሱን የሚሹበት ጊዜ ነበር፡፡
በእርሱ ለመዳን ከሚመኙ ህሙማን መካከል 12 ዓመታት ሙሉ ያለማቋረጥ ደም ሲፈሳት ብዙዎች ተፀይፈዋት ርቀዋት እና ሸሽተዋት በሽታዋም ከኃጢአቷ የመነጨ እንደሆነ አስበው እንደ እርኩስ ይቆጥሯት ይነቅፏት የነበረች አንዲት ሴት ነበረች፡፡ ባለ መድኃኒቶችን ጎብኝታ ፤ ብዙ ሐኪሞችን አማክራ ገንዘቧን ከስክሳ (ማር5፡26) ለደዌዋ መፍትሄ ለበሽታዋ ፈውስ አላገኘችም፡፡ ተስፋ ቆርጣ ለብቻዋ በቤቷ ተቆራምዳ ረዳት አጥታ በለቅሶና በሐዘን በእንባና በችግር ትኖር በነበረበት በእለታት በአንደኛው ቀን ሰዎች ሁሉ ስለ እርሱ የሚያወሩለት ስለ መሲሁ ጌታ ኢየሱስ በወሬ በወሬ ሰማችና ከተጣለችበት አልጋ ተስፋ ከቆረጠችበት ቤቷ በፍጥነት ተነስታ ወደ አዳኟ መገስገስ ጀመረች፡፡
ታላቁ መሲህ ኢየሱስ በሚያልፍበት መንገድ ሁሉ ከሚከተሉት ሰዎች ብዛት የተነሳ ሁካታ ፤ ግርግር እና ግፊያ የበዛበት ሐዋርያቱም ማንም ወደ እርሱ እንዳይቀርብ የሚከለክሉበት ነበር፡፡ይሄ ሁሉ ግፊያ ሳያግዳት ፤ ግርግሩ ተስፋ ሳያስቆርጣት ፤ የሐዋርያቱ ክልከላ ሳያስቆማት ፤ የሰዉ መጠየፍ ግድ ሳይሰጣት እየወደቀች እየተነሳች ጌታዋ አዳኝዋ የሥጋና የነፍስ መድኃኒት ወደሆነው መሲህ ኢየሱስ ደረሰች ቃል ማውጣቱን ሳትጠብቅ ፤ በእጆቹ እንዲዳስሳት ሳትጠይቅ ‹‹ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ፥ እድናለሁ›› ማቴ 9፡21 በማለት በእምነት ቀርባ ምናልባት ልብሱን ዳሰው የዳኑ አብነቶች(እማኞች) መኖራቸውን ሳታነብ ሳታይ ‹‹በሰዎች መካከል መጥታ ልብሱን ዳሰሰች›› ማር5፡27 በዚህ ጊዜ የ አስራ ሁለት ዓመታት ሙሉ ሲያስጨንቃት ፤ በሰው ዘንድ እንድትጠላ አድርጎ ብቻዋን ያስቀራት ክፉ ደዌ ደም ‹‹ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች››የዚህች ሴት እምነት ታላቅ ነበር ፡፡ ከእምነቷ ጽናት የተነሳ የተጠየፏትን ፤ የሚያንቋሽሻትን ፤ የሚተፋና የሚሰድባትን ሳትሰማ ጋሬጣውን አልፋ አጥሩን ሰባብራ በእምነት አልፋ የጌታ ኢየሱስን ልብስ ዳስሳ የ12 ዓመታት ችግሯ ተቀረፈላት ጋሬጣዋ ተሰበረላት ስብራቷ ተጠገነላት፡፡
ወዳጆቼ በሐዘን ፤በድካም ፤ ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ፤ በጭንቀት ፤ በመከራ ፤ በበሽታና በስቃይ ያላችኹ በእምነት ኢየሱስ ኾይ የልብስኽኝ ጫፍ ዳስሳ የተፈወሰችውን ሴት አድርገኝ በሉት፡፡ ያለመጠራጠር በእምነት ኾናችሁ ልንካኽ ከአንተም ኃይል ወጥቶ ይፈውሰኝ ፤ መከራዬን ያርቅልኝ ነቀፌታዬን ያስወግድልኝ በሉት ፡፡እርሱ ለድካማችን ብርታት ፤ ለማጣታችን ማግኘት ፤ ለበሽታችን ፈውስ ፤ ለጭንቀታችን መፍትሔ ፤ ሰላም ለማጣታችን ሰላም ፤ ለመከራችን እረፍት ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ብሎ ያፈረ አንዳች የለም ፤ ስሙን ጠርቶ የወደቀ ማንም የለም ለዚህም ነው ቤተክርስቲያናችን ፡-
“ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብስተ ሕይወት ለዘይበልዖ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ጽዋዐ መድኀኒት ለዘይሰትዮ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በግዐ መድኀኒት ለዘይሠውዖ ከመ ይባርኩነ ይፈኑ አርዳኦ ለጸባኢነ ይጽብኦ ወልታሁ ነሢኦ”
‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠራው ስሙ ጣፋጭ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚበላው የሕይወት እንጀራ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚጠጣው የመድኃኒት ጽዋ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚሠዋው የድኅነት በግ ነው፤ ይባርኩን ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን ይላክ፤ ጋሻውን አንሥቶ የሚጣላንን ይጣላው››ተአምረ ኢየሱስ
እያለች የምታመሰግነው ፡፡ ይሄ መድኃኒት ስሙ ፈዋሽ ቀዳሽ ፤ ሥጋው የሕይወት መብል ደሙ የሕይወት መጠጥ ነው፡፡ስሙን አብዝተን እንጥራው ፈውሰኝ አድነኝ እንበለው እርሱም “እርሱ ራሱ አልለቅህም፣ ከቶም አልተውህም ብሎአልና” ዕብ 13፡ 5 አይተወንም አይጥለንም ፡፡ጌታ፣ እርሱ ራሱ፣ አልተዋችሁም ስላለን፣ ‹‹አድነን›› ባልነው ጊዜ፣ ጩኸታችንን ስለሰማልን፡ ስለራራልን፣ ከምናውቀውና ከማናውቀው፣ ከምንገምተውና ከማንገምተው ውርደት እና ጉድ ሁሉ ጠብቆን፣ እነሆ ዛሬን ለማየት በቃን።
አባት ሆይ፣ የልመናችንንን ድምጽ ሰምተሃልና እንወድሃለን፤ ጆሮህን ወደ እኛ አዘንብለሃልና በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ስምህን እንጠራለን (መዝ 116)። አላሳፈርከንም፣ ሞት ሲገባን ሕይወትን ሰጠኸን፣ ውርደት ሲጠብቀን በክብር አቆምከን፣ መጠጊያ እና መሸሸጊያ ሁነን ባልንሕ ጊዜ ሁሉ ከጠላት ክፋትና አመጻ ሰውረኸናልና ተመስገን። ምስጋናችን ወደ ማደሪያኸ ይግባ። እንወድሃለን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እናመልክሃለን!!
የሕመሞች ሁሉ መድኃኒት የኾነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈውስ ይኹነን አሜን፡፡
ዲያቆን ሸዋፈራው
………………………………………………
https://t.me/orthodoxawitewahdo
ቻናሉን ተቀላቅለው ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ወንጌል ይማሩ...!

ይቆየን

3 months, 4 weeks ago

*?#Na_ilaali_maalo?*

Na ilaali maalo anoo nama hin qabu
Of biraatin dhabee namaa ol na qabu
Beekumsiif humnikoo si'idha abdin koo
Na bira hin darbinii na fayis uumakoo
?#Ceesisa ?
Beela'ee dheebodhe yoon bules hagabuu
Marromaan koo maree yemmuuttin gaggabuu
Nama si waamatee si'i kan qaaqabu
Maalo naa gargaari anoo nama hin qabu
?#Ceesisa ?
Jaamadha naan jedhee hundumtu na gatee
Anis naman dhabe namnis natt hammaate
Boolla dukkanatti gadi na daarbatu
Si qofadhaa gofta kan na fayyifatuu
?#Ceesisa ?
Si barbaachun dhufe mana kooti ka'e
Si arguun barbaade mukaattan olba'ee
Na dura gorani na dhoksun fuula kee
Anoo nama hin qabu na fayis ilma kee
?#Ceesisa ?
Nama of biraa dhabee yoon dhabees fayinaa
Fayyuu osoon barbaadu ciisee bishaan cinaa
Dhukubsadhee ciisee waggoota hedduu kanaa
Fayyii galii jettee deemi garaa mana

ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲደርስ
?#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ
?**@enatachinmaryam

6 months, 4 weeks ago

"ለምድራዊ መንግስት መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ የሚወጡ  ፣ ሰውም እንዲወጣ የሚናገሩ የወንጌል ተቆርቋሪ ነን ባዮች እኛ ለእግዚአብሔር መንግስት ሰራዊት ለቅዱሳን መላእክት እና በመንግስቱ ላሉ ቅዱሳን ክብራችንን እና ፍቅራችንን ለመግለጽ የምናከብራቸውን የቤተክርስቲያን በዓላት ስናከብር ግን ከሚቃወሙ የሃሰት አገልጋዮች እና የዲያብሎስ ስራ አስፈጻሚዎች ራሳችሁን ጠብቁ ፣ የሚሉአችሁንም አትስሙ!!"

ፍቅረ ማርያም

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago