ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
እለታዊ ማስታዎሻ - 310
"قُل لَّا يَسْتَوِي الْخَبِيثُ وَالطَّيِّبُ وَلَوْ أَعْجَبَكَ كَثْرَةُ الْخَبِيثِ ۚ فَاتَّقُوا اللَّهَ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
'የመጥፎው ብዛት ቢያስደንቃችሁም እንኳ መጥፎውና ጥሩው አይስተካከሉም፡፡ ባለልቦች ሆይ! አላህንም ፍሩ፤ እናንተ ልትድኑ ይከጀላልና፤' በላቸው፡፡" [ ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 100 ]
"ጀማሪነት ክፋቱ
ያለ የሌለውን ማስወራቱ!" - Hudhud
ጀማሪ ዋናተኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋና ሊለማመድ ገንዳ ውስጥ ሲገባ ሙሉ ገንዳው በእርሱ ምክንያት ይረበሻል:: እስኪችልበት ድረስ ውሐውን ያ ን ቦ ጨ ራ ር ቀ ዋ ል::
ከንግግር ቦታም ተናግሮ የማያውቅ ጉጉ ጀማሪ ይቁነጠነጣል:: የሚያውቀውን ሁሉ ለመናገር ምቹ አጋጣሚዎችን ያስሳል:: እድሉንም እንዳገኘ ያለ የሌለውን ይናገራል:: ነገሩ ሁሉም ይንቦጨራረቃል::
••••• በጀማሪነት ጊዜ ዝምታን ያክል ውበት ማድመጥን ያክል ጌጥ የለም::
ዝም እያልን ••• ለጌጣችን!
አዲሱ የሶሪያ መሪ አሕመድ አልሸርዕ ከቢቢሲ ጋር ካያደረገው የግማሽ ሰዓት ቃለ ምልልስ:-
የቢቢሲ ጋዜጠኛ:- ሴት ልጅ እንድትማር ትፈቅዳላችሁ?
አሕመድ:- ለ8 ዓመታት ኢድሊብን ባስተዳደርንበት ወቅት በከፈትነው ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች ከ60% በላይ ነበሩ
የቢቢሲ ጋዜጠኛ:- አስካሪ መጠጥንስ አስመልክቶ?
አሕመድ:- ይህ ጉዳይ ሕዝባችን በስምምነት ለሚያጸድቀው ህግ የሚተው ነው::
የቢቢሲ ጋዜጠኛ:- ሴኩላር ሴቶችን ሒጃብ እንዲለብሱ ታስገድዳላችሁ?
አሕመድ:- የምትሰነዝራቸው ጥያቄዎች በሙሉ አሁን ሶርያውያን ላሉበት ሁኔታ የሚመጥን አይደለም:: (ሶርያውያን ያለፉበትን ሰቆቃ በዝርዝር ካብራራ በኃላ)
የምታነሳቸው ጥያቄዎች በሙሉ ምላሽ የሚያገኙት ሶርያውያን በስምምነት በሚያጸድቁት ህገ-መንግሥት ውስጥ ነው::
የቢቢሲ ጋዜጠኛ:- ያለሒጃብ አብራህ ፎቶ ለመነሳት የጠየቀችህን ሴት ሒጃብ እንድትለብስ መጠየቅህ አግባብ ነውን?
አሕመድ:- በመጀመሪያ ከእኔ ጋር ፎቶ እንድትነሳ አላስገደድኳትም:: በመቀጠል ጉዳይ ከግል መብቴ ጋር የተያያዘ ነው:: ፎቶ እንዴት መነሳት እንዳለብኝ የምመርጠው እኔ ነኝ::
የቢቢሲ ጋዜጠኛ:- የተለያዩ የውጭ ሀይላት ለሕዝብህ እየሰጠህ ያለው ተስፋ ተግባራዊ ስለመሆኑ እንዴት ይመኑህ? ምንስ ማረጋገጫ አለ?
አሕመድ:- እኔን የሚያሳስበኝ ሕዝቤን ስለማሳመን ነው:: ከውጭ ስለኔ የሚባለው ነገር ብዙም አያስጨንቀኝም:: ሌሎች እንዲያምኑኝ የማድረግ ግዴታ የለብኝም::
••••• የቢቢሲ ሰዎች ገና በቅጡ ካላገገሙ ሶርያውያን በላይ የአስካሪ መጠጥ ጉዳይ ነበር ያሳሰባቸው:: የምዕራባውያንን ንፍቅና በግላጭ ያሳየ ኢንተርቪው ነበር:: የቻላችሁ ሙሉውን ተከታተሉት::
https://youtu.be/3lfnP9H9ojM?si=WyIc6Uk3TP6ptjvf
©️ Ustaz nesru
ጀመዓ በሀይስኩል ወይም በካምፓስ ....
■ ለማቋቋም ስታስቡ አብሯችሁ ለመስራት ፈቃደኛ የሚሆን ሰው አለማግኘት ፈተና ከሆነባችሁ ብቻችሁን ለመጀመር አታመንቱ:: በቃል ለማሳመን ከቸገራችሁ ጥቂት ስራን ጀምራችሁ በተግባር ለማሳመን እና ለመሰብሰብ ሞክሩ:: ማሠባችሁ ለራሱ በአላህ መመረጥ ነውና::
■ ከጀመርኩስ ቡሃላ ባይሳካልኝ የሚል እሳቤ ፈተና ከሆነባችሁ እሳቤውን ወደሗላ በሉትና ተግባራችሁን አስቀድሙ:: የሚቆጠረው በዛሬ ውስጥ የለፋችሁት እና ለነገ ያቀዳችሁት ነው:: በዲን ውስጥ ምን ሰራህ ነው እንጅ ምን አሳካህ ጥያቄ አይደለም:: አላህ በለፋኸው እንጅ ባሳካኸው አይጠይቅም::
በጀመዓ ውስጥ መንቀሳቀስ ከጀመራችሁ ቡሃላ
■ በተቻለ መጠን ጀመዓችሁ ሊሰራባቸው ያሰባቸውን ሰዎች ምን አይነት ነገር እንዲያጎለብቱ እንዳሰበ ለዩ:: ከለያችሁ ቡሃላ ያሉበትን ሁኔታ አጥንታችሁ በመካከል የሚኖረውን ክፍተት ሊገነቡ የሚችሉ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት አድርጋችሁ ስሩ::
እንደ ተማሪ ጀመዓ
■ "ሙስሊም ተማሪ በትምህርቱ ጠንካራ መሆን አለበት::" የሚለው ቃል መርህ ነው:: ስለሆነም ማንንም ተማሪ ሊያጠነክሩ የሚችሉ እንደ ቲቶሪያል እና መሠል አይነት ፕሮግራሞች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል::
■ "ሙስሊም ተማሪ በዲኑ ጠንካራ መሆን አለበት::" ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ መርሆ ነው:: ስለሆነም ዲኑ ላይ ጠንካራ የሚያደርጉትን እንደ ቂርዓት: ሙሐደራ ፕሮግራም: ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍን ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል::
■ "ሙስሊም ተማሪ መብቱን እና ግዴታውን የሚያውቅ እና የሚያስከብር ትውልድ መሆን አለበት::" የሚለውም ሌላ የግዴታ መስመር ነው:: ስለሆነም ስለመብቱ እና ግዴታው የሚነገርበት ፕሮግራም እነርሱንም የሚለማመድበት ማዕቀፍ መዘርጋት አለበት::
■ "ሙስሊም ተማሪ በንባብ እና በእውቀት የበለፀገ መሆን አለበት::" የሚለውም አንገብጋቢ ድንበር ነው:: ስለሆነም በጀመዓ የሚነበብበት በጀመዓ ውይይት የሚደረግባቸው እና አንዱ ሌላውን የሚያግዝበት ክልል መሠመር አለበት::
🔺 ሌላም ሌላም ብዙ መሠራት ያለባቸው አሉ:: ሆኖም ግን ቁጥር ከአንድ ነውና እያመነታችሁ ያላችሁ አንድ ብላችሁ ጀምሩ:: በአላህም ፈቃድ የሆነ ቀን መቶ ትሉ ይሆናል:: እየጀመርን......
ጥቅመኛ እና ራስ ወዳድ ማለት ••• ጓደኝነት እና ወዳጅነትን ለውዴታ ሳይሆን ለጥቅሙ ሲል የሚመሰርት ••• ወዳጅነት ለጥቅም ሽፋን እንጅ በራሱ ዋጋ ያለው እንደሆነ የማያምን ••• ጥቅሜ አለቀ ብሎ ሲያስብ ወዳጅነትን ለማፍረስ ወደሗላ የማይል ••• አጣሁ ብሎ በሚያስብ ሰዓት ችላ ለማለት እንደማያቅ እንደማይተዋወቅ ለማስመሰል አይኑን የማያሽ ሰው ነው:: ደግሞ ይጎዳልና ••• ራቁት::
ቲላዋ ግብዣ ••• ከወንድም ቢላል!
ድምፁ የእኔ ነው!
Record አድርጌ ያስቀረሁት ነው ብሏል:: አላህ ያክብርልኝ😍*😍***
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ከኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ጋር ተወያየ!
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ትኩረቱን በሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሁለንተናዊ ችግር እና መፍትሔዎቻቸው ዙሪያ አድርጎ የሚሰራው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በመጅሊስ በኩል ከተቋቋመው የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ከፍተኛ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት አድርጎል:: በውይይቱ የተለያዩ ነጥቦች የተነሱ ሲሆን በዋናነትም ከሙስሊም ተማሪዎች የመብት ትግል እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮች በጥልቅት ተጠቅሷል::
በአላህ ፈቃድ ተማሪዎቻችንን አቅፈን ከሙስሊም ተቋማት ጋር በመተባበር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሙስሊም ተማሪዎች ዙሪያ እየደረሱ ያሉ መግፋቶችንና በደሎችን የምንፈታ ይሆናል::
አላህ መልካም ለውጦችን ከሚያመጡት ያድርገን!
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት!
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana