ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
ቆሜ ከታየኋችሁ ያቆመኝ እግዚአብሔር ነው። ኢኼ ልጅ ተሳካለት ሆነለት ካላችሁ ያደረገልኝ እግዚአብሔር ነው። አንዳች ከኔ የሆነ የለም ። እደግመዋለሁ ጥሬ ተመራምሬ በትጋቴ በድካሜ ነው አልላችሁም የሰበሰብኳትን አንዷን ሺህ አርጎ ሺውን በሚሊየን እያጠፈ ከፊቴ ለቀደመው እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። 2ተኛው የዩቲዩብ ቻናሌ 1 ሚሊየን ሰብስክራይበር ደረሰ። ሁሌም በሁሉም ሁኔታ ውስጥ አብራችሁኝ ላላችሁ ሀሳብ አስተያየታችሁ ወንድማዊ እህታዊ ቁጣችሁን ሁሉ ላልነፈጋችሁኝ በሙሉ በጣም አመሰግናለሁ ። ፕሮግራሞቼን ስፖንሰር በማድረግ ለደገፋችሁ ምርትና አገልግሎታችሁን በቻናሌ ላስተዋወቃችሁ በሙሉ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ።
እግዚአብሔር ይመስገን !??
#NewsAlert
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በሬክተር ስኬል 4.8 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦፊዚክስ፣ ህዋ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
በበና ፀማይ ወረዳ የተከሰተው ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ አጎራባች በሆነው አሪ ዞን እንዲሁም ባለፈው ሳምንት ተመሳሳይ ክስተት ያስተናገደው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሉ ዳውሮ ዞን ጭምር የደረሰ እንደሆነ ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትናንት እሁድ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም. የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ የመዘገበው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ከ36 ደቂቃ ላይ እንደሆነ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሶሲሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.8 ሆኖ መመዝገቡን የሚያስረዱት ፕሮፌሰር አታላይ፤ ይህ መጠን “መካከለኛ” የሚል ደረጃ የሚሰጠው መሆኑን ገልጸዋል። የትናንቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ልኬት ባለፈው ሳምንት በዳውሮ ዞን ከተመዘገበው 3 ሬክተር ስኬል ከፍ ያለ መሆኑን የሶሲሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊው አስታውሰዋል።
“ይን [የመሬት መንቀጥቀጥ] ዝቅተኛም፣ ከፍተኛ አይባልም። መካከለኛ ነው። [የሚያስከትለው] ውድመት እና ጥፋት ግን እንደ አካባቢው ቅርበት [የሚወሰን] ነው። ይህ ከተማ ውስጥ ቢፈጠር ብዙ ጉዳት ያደርሳል” ሲሉ የክስተቱ ሊያደርስ የሚችለውን የጉዳት ጠቅሰዋል።
BBC
ቪዲዮው ተለቀቀ - ከጣሊያን እስከ አርመን ተጉዤ ከትውልድ አካባቢዋ ሮም ሰማዕት እስከሆነችበትና መቃብሯ እስካለበት ኸረቫን ተጉዤ ለብዙ ክርስቲያኖች ምሳሌ ፅናት ጥንካሬ የሆነችውን የእናታችን ቅድስት አርሴማን ታሪክ እንዲህ በቪዲዮ አቅርቤዋለሁ በዚህ ሊንክ እየገባችሁ ተመልከቱት
https://youtu.be/P7MOvSFC2vg?si=zRy9U5QHPnT-f2zt
Canada Times
The story of an Ethiopian man, Abel Birhanu who shot to fame with his YouTube channel
An article based on a well-known YouTuber named Abel Birhanu. He makes information-based videos and has over 1.3 million subscribers.
ሼር
አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ!
የሁለተኛው ዩቱዩብ ቻናላችንን ቪዲዮ ተምኔሎች መስራት የሚችል ጥሩ የግራፊክስ ዲዛይነር እንፈልጋለን -
ብዛት 1
የስራ ቦታ ከቤትዎ ኦንላየን የኮንትራት ስራ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እንደሁኔታው በስምምነት ሊቀጥል የሚችል
ክፍያ - በስምምነት
መስራት የምትፈልጉ ስማችሁን አድራሻችሁን ችሎታችሁን ከሁለተኛው የዩቲዩብ ቻናላችን ላይ ካሉ ተምኔሎች አንዱን የመረጣችሁትን በራሳችሁ መንገድ አሻሽላችሁ በዚህ ኢሜል አድራሻ ኢሜል ያድርጉ [email protected]
የሁለተኛውን ቻናል በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ
https://youtube.com/@abelbirhanu1?si=kQiCWaiGIKFbbBwL
እናመሰግናለን
አቤል ኢንተርቴይመንት
የስራ ማስታወቂያ!
ግራፊክስ ዲዛይነር - ብዛት 1
ኢንቴሬር ዲዛይነር - በኮንትራት የሚሰራ 1
የስራ ቦታ
ለግራፊክስ ከቤትዎ ኦንላየን
ለኢኔቴሬሩ የስራ ቦታ ቦሌ
ክፍያ - በስምምነት
መወዳደር የምትፈልጉ ስማችሁን አድራሻችሁን ችሎታችሁን ለስራው ያላችሁን ሙሉ ዝግጁነት ከተቻለ ከዚህ በፊት የሰራችኋቸውን ስራዎች በማያያዝ በዚህ ኢሜል አድራሻ ኢሜል ያድርጉ [email protected]
እናመሰግናለን
አቤል ኢንተርቴይመንት
ዋትስ አፕ አዲሱን የቻናል ሥርዓቱን ጀመረ።
በአዲስ የዋትሳፕ ቻናሌ እንገናኝ አዳዲስ ስራዎች ሀሳቦች መልዕክቶች ይጋሩበታል በዚህ ሊንክ ያገኙኛል
https://whatsapp.com/channel/0029Va9PwDZ1XquZRS6bQR2X
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተፈታ
ዛሬ ጠዋት ሰኔ 20 ቀን፣ 2015 ዓ.ም. ጠዋት 12: 30 ላይ በፀጥታ ኃይሎች ከመኖር ቤቱ እንደተወሰደ የተነገረለት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዳግም መፈታቱ ተገለጸ ። ተመስገን በአዲስ አበባ ሜኪሲኮ አካባቢ በሚገኘው በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለ6 ሰዓታት ታስሮ እንደነበረም ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለዶቼ ቬለ (DW) ገልጾ ነበር። ከዚህ ቀደም ተከሶ ነጻ በተባለበት ክስ ለሐምሌ 7 ዳግም ታስሮ እንዲቀርብ ትእዛዝ እንደሰጠበትም ተዘግቧል ።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago