ሀሳቦች....

Description
ለcomment @HassabochBot
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

4 days, 2 hours ago

ተክሉ የሚባል አይምሮው የተነካ ሰው ሰፈራችን ውስጥ አለ።
ተክሉ እሳት የላሰ የእንጨት ቤት ሰራተኛ ነበር ይባላል።እንጀራውን እንጨት ላይ የሚጋግር።
"የተከበረውን የክርስቶስ ስራ የምሰራ "ብሎ ራሱን የሰየመ።

ሁሌ ጠዋት ጠዋት የእንጨት ቤት ዩኒፎርሙን በጨርቅ ቦርሳው ሸክፎ ጥድፍ ጥድፍ እያለ ሲሄድ መመልከት የተለመደ ነበር። ጥድፊያ መለያው ቢሆንም  እግረመንገዱ ላይ ያለው እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ሲደርስ ግን ርምጃውን ገታ ያደርግና በረዢሙ ያማትባል። በለሆሳስ ፀሎቱን አድርሶ ይሄዳል።

አንድ ሮብ ቀን ለዚሁ ለእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን በስጦታ መልክ ሊሰጠው ያሰበውን ትልቅ የእንጨት መስቀል እየሰራ ነበር።
በውስጡ 'ይህቺ ለእግዚሀር ምኑ ናት? ያው መቼስ ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም ብዬ እንጂ' እያለ።
ወደማገባደዱ ሊደርስ ጥቂት ሲቀረው የእንጨት መቁረጫ ማሽኑ ሳት ብሎ የቀኝ እጁን  አውራጣትና ሌባ ጣት ላፍ አረገበት።
የዚያን ቀን ማታ ሆስፒታል ላገኘው ዶክተር ምን አለው?
"እ/ር የፈቀደውን አደረገ"
ዶክተሩም " እ/ር ለምን የተሟላ እጅ እንዲኖርህ አልፈቀደም?" አለው
"እንጃ"

ተክሉ ለወራት ተደበረ። ስራውን ትቶ ቁጭ አለ። ከብዙ ጊዜ በኋላ ከቤት ወጥቶ ወክ ሲያረግ እዚያ ቤተክርስቲያን ጋር ደረሰ። እንደለመደው ቀኝ እጁን ከኪሱ አውጥቶ ለማማተብ እጁን ሲያመቻች ለካ አውራ ጣትና ሌባ ጣት ከሌለ ማማተብ አይቻልም።ማሽኑ የቆረጠው እለት ያላወጣውን እዬዬ ደጀሰላም ፊት ለቀቀው።

ከዚያ ቀን ጀምሮ ተክሉ ከቀሩት ሶስት ጣቶች መካከል የመጨረሻዎቹን ሁለቱን ያጥፍና የመሀል ጣቱን ወዳገኘው ሰው እየጠቆመ ይሳደባል።
ሰዎች ትኩር ብለው ሲያዩት
"የተወልኝን ጣት እንኩ ፤መቸስ ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም" እያለ እየሳቀ ይሮጣል።
                               D.T

2 weeks, 3 days ago

ወይ ባጥፍቶ ጠፊ፣
ወይም ባንድ ቫይረስ፣ አደገኛ ጥፊ
በተባራሪ እርሳስ፣ ባልፎ ሂያጅ ቀለሀ
ወይ በጣም ተርበህ፣ አጥተህ ጭላጭ ውሃ
በምንም ይሁን ምን፣
ጉድጉድ ስትዪ፣ ወይ በተኛሽበት
ሮጠሽ ሳትደክሚ፣ ወይም ወርሶሽ ሽበት
መቀበል አይከብድም፣ "ሞት" የሚባል እውነት?
D.T

2 weeks, 3 days ago
2 months, 3 weeks ago

አሮጌ ክራር
.................................
አሮጌ ክራር ነኝ፣
ግድግዳው ላይ ተሰቅዬ፣
አርጅቷል ተብዬ፣
ድር እያደራብኝ፣ ማዜም ጠፍቶ ከጅማቴ
ተንጠፍጥፎ ያለቀብኝ፣ ያዘቦት ቅኝቴ
ምንም ባላጫውት፣ በረገበው ክሬ
ሰቅጣጭ ሙሾ ቢያፈልቅ፣ ዘልዛላው አውታሬ
ኧረ እሰይ አበጀሁ፣
እንኳንም አረጀሁ፣
በማርጀቴ አይደል ወይ፣
ገራፊ ጣት የቀረልኝ፣ ዕረፍቴን የዋጀሁ።
                           D.T

2 months, 3 weeks ago
የዲያብሎስ ዱካክ፣ ድብርቱ ቢጠና

የዲያብሎስ ዱካክ፣ ድብርቱ ቢጠና
እንዲህ ይለው ጀመር፣ ወደግዜር ሄደና
"እዮብ የምንለው፣ ያንተ ብርቱ አገልጋይ
አንዳች ሳይጎድልበት፣ ከደስታው ሙዳይ
አንተን አመስግኖ፣ ቢደንቅም መኖሩ
ቢደላው እኮ ነው፣
የማያልቅ ውዳሴ፣ ሁሌ መገበሩ
ትንሽ ልቆንጥጠው፣ በአንተ ይሁንታ
አብረን እናያለን፣ ማን እንደሚረታ"
እግዜሩም ፈቀደ፣
የእዮብም አለም ፣ቀስ በቀስ ተናደ
ከጎተራው ግድም፣ ጠኔ ተወለደ
ልጆቹ ረገፉ ፣በሽታም አገኘው
የምድር ሰቀቀን፣ በጅምላ ጎበኘው

በላይኛው ቤት ፣ውርርድ አለ የማያበቃ
አጫዋቿ አለም፣ ታልፈዋለች ስቃ
የሰው ልጅ ሲሆን፣
የቁማር ሳንቲም፣ መጫወቻ እቃ።
                         D.T

3 months, 3 weeks ago
በመስከረም ብራ ሰማይ፣ ጠሀይ ተሞናድላ

በመስከረም ብራ ሰማይ፣ ጠሀይ ተሞናድላ
እከኳ ተራግፎ፣ መሬት ባደይ ተኳኩላ
ሚስቴ ለብሳ ጥበብ፣ አምሮባት እያለ
ከጓሮዬ ሳይኖር፣ አንዳች የጎደለ
ጋኖቼ ጢም' ብለው፣ በጠጅና ጠላ
ጓዳዬን ሞልቶት፣ የአገር ተድላ
መንታ ልጆቼ፣ ውድማዬ ላይ እየቦረቁ
ከብቶቼ ሁሉ፣ መስኩን ሲያደምቁ
ታዲያ ምን ይሆን፣
ካይኖቼ ግድም እንባ መፍለቁ?
                      D.T

3 months, 3 weeks ago

ለ"ነገ" ማለቴን፣ ተውኩ እርግፍ አድርጌ
የአገልግል ስንቄን፣ በላሁ ጠርጌ
አነደድኩኝ እሳት፣ ፈልጬ ምሰሶ
ሙቀት ቢበልጥብኝ ፣ቤቱ እላዬ ፈርሶ።
                       D.T

4 months ago
ጥረት

ጥረት
...............................................
እንደ ምንም ብዬ፣
ራሴን አባብዬ፣
ዝግ አፌ ተከፍቶ፣
ሞራል እንዳረቄ፣ አናቴ ላይ ወጥቶ
ወዳንቺ ቀርቤ፣
"እንደምነሽ" ስልሽ ፣ቆሜ ካንቺ በራፍ
በኔ ሲመነዘር፣ እኩል ነው ከ"ዘራፍ"።
                        D.T

4 months, 1 week ago

ነዲድ ሀሩሩ
ቀዝቃዛ ቁሩ
ምንተዳዬ እኔ
መፍራት ለምኔ

አውቅበታለሁ
                    ደራሽ ውሃ ሲሄድ፣ ከላይ መንሳፈፉን
እችልበታለሁ
                      ቁልቁል ተወርውሮ፣ ወደላይ መክነፉን
ብቻ ይያዙልኝ
                 አላህና እግዜር፣ የሰው ልጅ አፉን።
                                   D.T

4 months, 1 week ago

አንድ ሰሞን ስቦኝ፣ ኩነኔ ጥላቻ እከውን ጀመረ፣ ፅድቅ ፅድቁን ብቻ። "የመልካምነት ጥግ"፣"የፅድቅ ጎተራ" "የርግብ መንትያ ገፅ"፣ "የደግነት ጣራ" ነበረ ምኞቴ፣ ተብዬ እንድጠራ። ሒሳብ ላወራርድ፣ በስተመጨረሻ ካምላኬ መንበር ፊት፣ ምስጋናዬን ስሻ ሠፊ መዳፍ ሰጠኝ፣ አመዴን ማፈሻ። D.T

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana