ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
🔺የታሰሩ ሙስሊም ተማሪዎች ዜና!
እለተ ማክሰኞ ጥቅምት 2017
----------------------------
በኒቃብ ጉዳይ ከታሰሩት የአዲስ ከተማ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ተማሪ አሚር አ/ከሪም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር፤ ተማሪ አሚር በት/ቤት ውስጥ ት/ቱን በአግባቡ በመከታተል እና ተማሪዎች በአካዳሚም ይሁን በዲናዊ ህይወታቸው የተሻሉ እንዲሆኑ በመምከር የሚታወቅ አርአያ ተማሪ ሲሆን፤ ከት/ቤቱ ሙስሊም ተማሪዎች ጋር አብሮ እህቶቻችን ለምን ኒቃብ መልበስ ይከለከላሉ ብሎ በሰላማዊ መንገድ በመጠየቁ ብቻ ት/ቤቱ በከፈተው የውሸት ክስ እለተ አርብ በትምህርት ገበታ ላይ እያሉ ስም ዝርዝራቸው ለፖሊስ ተሰጥቶ በየክፍላቸው እየተዞረ ከተለቅሙት ሙስሊምች ተማሪዎች አንዱ ነበር።
በዛሬው እለት በዋለው ችሎት አቃቢህጉ ት/ቤቱን በማስረበሽ እና የት/ቤት ንብረትን በማውደም የሚል የውሸት ክስ በተማሪ አሚር አ/ከሪም ላይ ያቀረበ ሲሆን ከአዲስ አበባ መጅሊስ ተወክሎ የቆመለት ጠበቃ ሁሴንም በችሎቱ ላይ ባቀረበው ብርቱ ክርክር የዋስ መብቱ ተጠብቆ በመጨረሻም በ5ሺ ብር ዋስ እንዲፈታ ተወስኗል፤ በቅድሚያ አላህን እናመሰግናለን በመቀጠል ለአዲስ አበባ መጅሊስ እና ለጠበቃ ሁሴን ምስጋናችን ይድረስ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተማሪ ነቢል እና ተማሪ ሰሚር በመጪው ሀሙስ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ሲሆን የክስ መዝገብ ላይ ስማቸው ሰፍሮ ያልተያዙ ሙስሊም ተማሪዎች አሁንም ድረስ በፖሊስ እየተፈለጉ በመሆኑ ሁሉም የት/ቤታችን ሙስሊም ተማሪዎች በነፃነት የመማር መብታቸው ተከብሮ ወደ ቀድሞው የትምህርት ገበታቸው እስኪመለሱ ድረስ ሁሉም ሙስሊም የሚችለውን አስፈላጊ ትብብር እንዲያደርግልን በአላህ ስም እንጠይቃለን።
ኒቃቧንም ትለብሳለች‼️
ትምህርቷንም ትማራለች‼️
©የአዲስ ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዐ
⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA
t.me/GHUREBAMEDIA
🔺አዲስ ሙሓደራ
🔸የነብያት ውርስ
🌸 በኡስታዝ አብዱልዋሲእ ነስሮ
🗓 24/2/2017 በአሷሊህን መስጂድ የቀረበ ሙሓደራ
🅾 ቀጥታ መከታተል ያልቻላቹ ይህን ድንቅ ሙሓደራ ተጋብዛቹሃል።
⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA
t.me/GHUREBAMEDIA
የታሰሩ የአዲስ ከተማ ሙስሊም ተማሪዎችን በተመለከተ ጉዳዩ የተብራራበት የድምፅ ፋይል ነው።
ለሚመለከታቸው አካላት ሼር አድርጉልን በማለት ይህን ድምፅ ልከዋል ሁላችንም ሼር በማድረግ እናዳርሰው።
🔸በኒቃባቸው ምከንያት ከትምህርት ገበታ ታግደው የነበሩ ተማሪዎች ወደትምህርት ገበታ እንድመልሱ ከስምምነት መድረሱን የአዲስአበባ መጅሊስ ገለፀ!
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰሞኑን በከተማችን በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በመዋቅሮቻችን አማካኝነት በየደረጃው ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርግ መቆየቱ ገልጿል።
በትላንትናው እለት ጥቅምት 20/2016 የከፍተኛ ምክር ቤታችን ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣የአ/አ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።
በዚሁም መሰረት ችግሩ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለና ዘላቂ መፍትሔ የሚያሻው ከመሆኑ አንጻር የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፌደራል መጅሊስ እንዲሁም ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ ዘላቂ እልባት የሚያመጣ የመፍትሔ ሀሳብ እንዲያቀርብ ከስምምነት ተደርሷል ተብሏል።
ከያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ ከትምህርት ገበታቸው የተገለሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ግን በጊዜያዊነት ከመገለላቸው በፊት ይስተናገዱ በነበረበት ሁኔታ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከስምምነት ተደርሷል።
ከፍተኛ ምክር ቤታችን ቀሪውን ስራ በትኩረት የሚያከናውን ሲሆን በውይይቱ የተካፈሉ የከተማዋ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በሙሉ ችግሩን ለመፍታት ላሳዩትን ተነሳሽነት በከተማዋ ሙስሊም ማህበረሰብ ስም ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን ሲል የአዲስ አዲስ አበባ መጅሊስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባስተላለፈው መልክት አስተዋቋል። [ሀሩን-ሚዲያ]
⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA
t.me/GHUREBAMEDIA
በአዲስ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም የየካቲት 23 ትምህርት ቤት ሙስሊም ሴቶችን ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ማስክም ማድረግም አትችሉል በማለት የግል ጥላቻቸውን በማንፀባረቅ ሙስሊም እህቶቻችን ላይ ከትምህርት ገበታቸው እንዳይገኙ ግፍ እየፈፀሙ ያሉ የትምህርት ቤቱ አስተዳደሮች ናቸው። የሚመለከተው አካል በህግ ሊጠይቃቸው ይገባል።
የአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት አስተዳደር
https://t.me/GHUREBAMEDIA/151
የየካቲት 23 ትምህርት ቤት አስተዳደር
https://t.me/GHUREBAMEDIA/153
⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA
t.me/GHUREBAMEDIA
? የኡዱሕያ መስፈርቶች!!
1ኛው, ከቤት እንስሳ መሆን አለበት።
እነርሱም
✅ ግመል
✅ ከብት
✅ በግ
✅ ፍየል
2ኛው, በሸሪዐ ለተገደበው እድሜ መድረስ አለበት።
? ግመል ከሆነ ?? 5 ዓመት
? ከብት ከሆነ ?? 2 ዓመት
? ፍየል ከሆነ ?? 1 ዓመት
? በግ ከሆነ ?? 6 ወር የሞላው
3ኛው, ከነውር (ከዓይብ) የጠራ መሆን አለበት።
? ግልፅ ከሆነ መታወር
? ግልፅ ከሆነ በሽታ
? ግልፅ ከሆነ አንካሳነት
? መቅኔ የሌለበት ከሆነ ከሲታማነት
አንድ ሰው ኡዱሒያ ማረድ ከፈለገ በሚያርደው እንስሳ ላይ ከተጠቀሱ ነውሮች መጥራት አለበት።
?ቅርጫ ማድረግ የፈለገ ሰው……
በግ ወይም ፍየል ከሆነ ለ1 ሰው ብቻ
በሬ ለ7ወይም ግመል ከሆነ ለ10 ሰው መካፈል ይቻላል።
⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA
t.me/GHUREBAMEDIA
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana