Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

Description
The best fiction is far more true than any journalism

📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ

👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56



👉 https://www.facebook.com/mik0Man
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

1 week ago

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር ሲተዳደሩ የቆዩት የራያ አካባቢዎች ያለ አስተዳዳሪ ወደ ሁለተኛ ሳምንታቸው እየተሻገሩ ነው

ከየካቲት ጀምሮ አልፎ አልፎ ሲከሰት የነበረው “በህወሓት ታጣቂዎች” እና “በአካባቢው ሚሊሺያዎች” መካከል ሲደረግ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከፍ ባለ ሁኔታ ተካሂዶ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወዲህ የነበረውን መዋቅር ቀይሮታል።

ላለፉት ሦስት ዓመት ገደማ አካባቢዎቹን ሲመሩ የነበሩት ከአማራ ክልል በኩል የተሾሙ አስተዳዳሪዎች፤ ከሚመሯቸው የራያ ወረዳ እና ከተሞች ሸሽተው ቆቦ ከተማ እና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ውስጥ ተጠልለዋል።
በቆቦ ከተማ የሚገኙት ከራያ አካባቢዎች የሸሹት የመንግሥት ሹመኞች ብቻ አይደሉም።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በወጣው ሪፖርት 50 ሺህ ሰዎች ከራያ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች እንደተፈናቀሉ አስታውቋል። ከተፈናቃዎቹ ውስጥ 42 ሺህ ያህሉ የሚገኙት በሰሜን ወሎ ዞን ስር በምትገኘው ቆቦ ከተማ እንደሆነ ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። ሌሎች የራያ አካባቢዎች ነዋሪዎች ግን አሁንም ባሉበት ኑሯቸውን ቀጥለዋል።

የአማራ እና ትግራይ ክልሎች የየራሳቸው አስተዳዳሪዎች የተሾሙላቸው የአላማጣ እና የኮረም ከተሞች ያለምንም አስተዳዳሪ ከቀሩ ሁለት ሳምንታት ተቃርበዋል። ከሁለቱም ክልሎች የተሾሙ አመራሮች የሚገኙት በየክልላቸው ውስጥ በሚገኙ አጎራቦች አካባቢዎች ውስጥ ነው።

በአላማጣ እና ኮረም ከተማዎች ውስጥ የፌደራል እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት እንደሚገኙ ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሁለቱ ከተማዎች አምስት ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በከተሞቹ ውስጥ የሚገኙት የፌደራል መንግሥት እንዲሁም የአካባቢ አስተዳደሮችን ተቋማት እና ቢሮዎች እየጠበቁ ያሉት በሁለቱ የፀጥታ አካላት መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች በአሁኑ ሰዓት ከተማዋ ውስጥ አንጻራዊ ሰላም እንዳለ ጠቅሰዋል። ባንኮች፣ የኢትዮ ቴሌኮም ቢሮዎች እንዲሁም የተወሰኑ መደብሮች መከፈታቸውን ሦስት ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ መደብሮች ያልተከፈቱት አካባቢዎቹን ላይ አስተዳዳሪ አለመኖሩ በፈጠረባቸው ስጋት ምክንያት መሆኑን የሚናገሩ አንድ የአላማጣ ነዋሪ፤ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙት የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሠራዊት አባላት እየተንቀሳቀሱ ያሉት በዋና የአስፓልት መንገዶች ላይ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከትግራይ ክልል በኩል የተሾሙት የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ዝናቡ ደስታም በተመሳሳይ በከተማዋ ሁለቱ የፌደራል መንግሥት ኃይሎች ቢኖሩም የፀጥታ ሁኔታው በበቂ ሁኔታ እየተሸፈነ አለመሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በኩል የተሾሙት የአላማጣ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋ ውስጥ መኖራቸውን አንስተው በአሁኑ ሰዓት ስላለው ሁኔታ ግን “ዝርዝር መረጃ” እንደሌላቸው ጠቅሰዋል።

ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ የመንግሥት ኃላፊዎች ከአላማጣ መውጣታቸውን ተከትሎ በመንግሥት ተቋማት ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶች እስካሁን ድረስ እንደቆሙ መሆኑን ሦስት ነዋሪዎች ገልጸዋል። የከተማዋ አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነም ጠቅሰዋል።

አንድ የከተማዋ ነዋሪ*፤ “[የጤና አገልግሎት] የለም ማለት ይቻላል። አሁን በቅርብ አንዲት ወላድ ነበረች፤ ደም [ያስፈልጋል] ተብላ ወደ ወልዲያ ሄዳለች። ምንም ዓይነት አገልግሎት የለም። በጣም ተቸግራ እዚህ ያሉ ዶክተሮች በግል ተባበሯት፤ …ወደ ቆቦ በትራንስፖርት ሄዳ፣ ከቆቦ ወደ ወልዲያ ወሰዷት” ሲል በከተማዋ ላለው ሁኔታ ማሳያ ጠቅሷል።

በኮረም ከተማም በተመሳሳይ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ መሥሪያ ቤቶች ዝግ መሆናቸውን ሦስት የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። የቀድሞ አስተዳዳሪዎች ለቀው በወጡባት ኮረም ከተማም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ተቋማት እየተጠበቁ ያሉት በፌደራል ፖሊስ እና በመከላከያ ሠራዊት አባላት መሆኑን ተናግረዋል።

ይሁንና ከአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ሦስት ነዋሪዎች ገልጸዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ታጣቂዎቹ በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ “ዝርፊያ ፈጽመዋል” ሲሉ ከሰዋል።

ታጣቂዎቹ የሰፈሩት በከማው ውስጥ በሚገኙት ስድስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ መሆናቸውን የሚናገሩ አንድ ነዋሪ፤ “የትምህር ቤት መጽሐፍት ‘የአማራ ክልል ናቸው’ በሚል ተቀድደዋል” ሲሉ በትግራይ ታጣቂዎች ተፈጽሟል ያሉትን ድርጊት ጠቅሰዋል።
ሌላ ነዋሪ በበኩላቸው፤ በከተማዋ ውስጥ በታጣቃዎቹ በሚፈጸሙት ድርጊቶች ሳቢያ ነዋሪዎች አሁንም ወደ ቆቦ ከተማ እየሸሹ መሆኑን ተናግረዋል። በቆቦ ከተማ የሚገኙት በአማራ ክልል የተሾሙት የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉም የኮረም ከተማ ነዋሪዎች አሁንም ወደ ቆቦ ከተማ እየገቡ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

በትግራይ ክልል በኩል የራያ አካባቢ ወረዳ እና ከተማዎችን በስሩ የያዘው የደቡባዊ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀፍቱ ኪሮስ፤ በኮረም ከተማ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ገብተዋል ስለመባሉ እና ታጣቂዎቹ ፈጽመዋቸዋል ስለተባሉ ድርጊቶች ከቢቢሲ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

በአሁኑ ሰዓት በኮረም “በጣም የተረጋጋ ሰላም እና ደኅንነት” መፈጠሩን የሚናገሩት ዋና አስተዳዳሪው፤ “ኮረም እና አላማጣም ላይ በአሁኑ ሰዓት የፌደራል ኃይሎች የፀጥታ እና ሰላሙን የመጠበቅ ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ እየፈጸሙ ነው” ብለዋል።

አቶ ሀፍቱ፤ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ስለመግባታቸው እና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለ መስረፈራቸው ማረጋገጫ ከመስጠትም ሆነ ከማስተባበል ተቆጥበዋል።

እንደ ራያ ባሉ አካባቢዎች ላይ ከዚህ ቀደም በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳደር መካከል የነበረው “ከመከላከያ ሠራዊት ውጪ ሌላ ታጣቂ ኃይል አይኑር” የሚለው “ንግግር” በአሁኑ ሰዓት “መቀየሩን” ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል።

የፕሪቶሪያ ስምምነትን የተፈራረሙት የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት ከስምምነቱ በታች ያሉ ጉዳዮችን በፖለቲካዊ ንግግር እየፈቱ እና “እያሻሻሉ” እየሄዱ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሀፍቱ፤ “ለምሳሌ አሁን ማሻሻያዎች አሉ።

በዚያ አካባቢ ከመከላከያ ሠራዊት እና ከፌደራል ፖሊስ ውጪ ማንኛውም ታጣቂ መኖር የለበትም የሚል የውይይት ሀሳብ እንደነበር ይታወቃል። አሁን እሱ ተቀይሯል። ሌላ እድገት አለው” ብለዋል።

ዋና አስተዳዳሪው “ተቀይሯል” ያሉት የታጣቂዎች ጉዳይ የሚወያዩት አካላት ይፋ እንደሚያደርጉት በመጥቀስ ዝርዝሩን ከመናገር ተቆጥባዋል።

ሁለቱ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች ባለፉት ሳምንታት የተፈጠረውን ሁኔታ የአፍሪካ ኅብረት እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ አገራት ተወካዮች እንዳሰሰባቸው እና ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

የአማራ እና የትግራይ ክልሎች በይገባኛል በሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች ላይ የህወሓት ታጣቂዎች ወረራ ፈጽመዋል ብሎ ባለፈው ሳምንት የአማራ ክልል መንግሥት መክሰሱ ይታወሳል።

ለወሰን እና ለማንነት ጉዳዮች መፍትሄ ለመስጠት እየሠራ መሆኑን የገለጸው የፌደራል መንግሥቱ የህወሓት ኃይሎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው ሲል ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

Via ቢቢሲ
#ዳጉ_ጆርናል

1 week ago

የካሊፎርኒያ ኮሌጅ በጋዛ ያለውን ጦርነት በመቃወም የተነሳውን ውጥረት ተከትሎ ተጠባቂውን የተማሪዎች የምረቃ ስነስርአት ሰረዘ

በሎስ አንጀለስ የሚገኘው የደቡባዊ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ያለውን የደህንነት ስጋት በመጥቀስ ዋናውን እና በግንቦት 10 እንዲካሄድ ቀጠሮ የተያዘለትን የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ሰርዟል።

ይህ እርምጃ የተወሰደው በእስራኤል እና በጋዛ ጦርነት ምክንያት በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ካምፓሶች ተቃውሞ በተቀሰቀሰበት ወቅት ነው። በአትላንታ ኤሞሪ ዩኒቨርሲቲ 28 ተቃዋሚዎች ግቢውን ለቀው ለመውጣት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሐሙስ ዕለት ተይዘዋል ። በኒውዮርክ ከተማ፣ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በግቢው ውስጥ ያለውን ተቃውሞ ለማስቆም ቀነ ገደብ ተጥሏል።ተማሪዎች ግን ድንኳን ሰርተው ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል።

በመግለጫው የደቡባዊ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ እንዳስታወቀው 65,000 ተማሪዎች፣ ቤተሰብ እና ጓደኞቻቸው የሚታደሙበት የምረቃ ሥነ ሥርዓት ግቢው ማስተናገድ እንደማይችል ይፋ አድርጓል። እሮብ እለት፣ ፖሊስ ግቢውን ጥሶ በመግባት ከ93 ያላነሱ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ እንደነበር ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል። በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች ተቃውሞ የፍልስጤም ኬፊህ ወይም ሻርፕ እና በፍልስጤም ባንዲራ የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የጆርጅ ዋሽንግተን ሀውልት ለብሶ ታይቷል።

በሌላ በኩል በጋዛ በቀጠለው ውጊያ ዙሪያ አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን ወታደሮቹ በታቀደው የምድር ጦር ዘመችም መሰረት “ወደ ፊት እየገሰገሱ ነው” ነው ብለዋል። የራፋህ ምስራቃዊ ክፍል በየጊዜው በመድፍ እየተደበደበ ይገኛል። ከደቡብ ሊባኖስ በተነሳው የሂዝቦላ የሚሳኤል ጥቃት አንድ እስራኤላዊ የጭነት መኪና ሹፌር መገደሉን የእስራኤል ጦር አስታውቋል።

የእስራኤል ሚዲያዎች አካባቢው በተመታበት ጊዜ ሰውዬው ወደ እስራኤል ሰሜናዊ ድንበር አቅራቢያ ለወታደሮች የመሠረተ ልማት ስታዎችን ሲያከናውን ነበር ብለዋል ። በሊባኖስ እና በእስራኤል ድንበር ላይ በሄዝቦላህ እና በእስራኤል ጦር መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የእስራኤል ጦር አስታውቋል። በኢራን የሚደገፈው ቡድን ከጋዛውያን ጎን መቆሙን በተደጋጋሚ አሳይቷል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

1 week ago

"እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው።"
መዝሙር 68፤35

ገዳመ ወንያት
መንታዎቹ ደብር
አቡነ ሐራ ድንግል ገዳም

ወር በገባ በ11ኛው ቀን ጻድቁ አቡነ ሐራ መታሰቢያ በዓላቸው ነው።ገዳሙ የተአምራት የበረከት የፈውስ ቦታ ነው።ከጻድቁ መቃብር ተዝቆ በማያልቅ ሞልቶ በማይፈስ አፈር እጹብ ድንቅ ተአምራት ይደረጋል።

በጻድቁ መካነ መቃብር ላይ የሚገኘውን ቤተክርስቲያን ያሰሩት አፄ ዮሐንስ፬ኛ በጽኑ ነቀርሳ በሳይንሳዊ አጠራር ካንሰር በሽታ ተይዘው የእግዚአብሔር ቸርነት የጻድቁን አማላጅነት ተስፋ አድርገው ከመቀሌ ድረስ ገስግሰው መጥተው በጻድቁ ጸበል ድንቅ ስለተደረገላቸው ፈውስን ስላገኙ የክብር አልጋና ዘውዳቸውን ሰጥተዋል ቤተክርስቲያኑንም አሰርተዋል።

ጻድቁ ዛሬም ውሉደ ጥምቀትን ሁሉ ከክፉ ደዌ በጸበላቸው ይፈውሳሉ።ከባሕር ዳር ወደ ጎንደር መንገድ ስንወጣ ዘንዘልማ የምትባል አነስተኛ ከተማ አለች ከዘንዘልማ በስተቀኝ ታጥፎ በ12ኪሎሜትር ላይ ይገኛል።ብዙዎች በጻድቁ አማላጅነት ከደዌ ስጋ ድነዋል መካኖች ወልደዋል እውሮች በርተዋል ለምጻሞችም ነጽተዋል።

የጻድቁ በረከት ይደርብን በቃልኪዳናቸው ይጠብቁን ከእለት እኪት ከቀሳፊ ነገር ይሰውሩን ከፍቅር ረሐብ ከዘረኝነት ደዌ ከዝሙት እሳት ከምንፍቅና አሽክላ ይታደጉን።የገዳመ ወንያት አቡነ ሐራ ድንግል አንድነት ገዳም በዓላውያን መንግስታት ዘመን በደረሰበት መከራና ፈተና የተነሣ ተዳክሞ በመቆየቱ የገዳሙ የይዞታ ቦታ በመሉ በአካባቢው አርሶ አደር እና በሌሎች ጥቃቅን ነጋዴዎች እጅ ከገባ አያሌ ዘመናትን ያስቆጠረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንድነት ገዳሙ ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን ተከትሎ በርካታ አባቶች መነኮሳትና እናቶች መነኮሳይያት ወደ ገዳሙ በመግባት በመልሶ ማቋቋም ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ቢሆንም የገዳሙ ይዞታ ለረጅም ዘመናት በሌሎች ግለሰቦች እጅ ተይዞ በመቆየቱ ምክንያት እንኳንስ ለገዳሙ ልማት ይቅርና ለመነኮሳቱ መጠለያ ቤት መሥሪያ ቦታ በመጥፋቱ ገዳሙ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል፡፡

ይህን መሬት ለማስመለስ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ የካሳ ክፍያ ተጠይቋል።ለዚህም ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ታላቅ የገቢ ማሰባሰብያ መርሀ ግብር በካፒታል ሆቴል ለማካሄድ ቀን ተቆርጧል

በሐገር ቤትም በውጭም ያላችሁ የፃድቁ ወዳጆችና ህዝበ ክርስቲያን እንድትረባረቡ ገዳሙ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጠይቋችኃል

#ዳጉ_ጆርናል

2 months, 1 week ago
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
2 months, 1 week ago
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
2 months, 1 week ago

በጣሊያን በ60ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የታጠቁ አዛዉንት ዘራፊዎች ቡድን በቁጥጥር ስር ዋሉ

በ60ዎቹ እና 70ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ስድስት አዛውንቶች የሚመራ የታጠቁ ዘራፊዎች ቡድን በጣሊያን ውስጥ በሮማ ፖስታ ቤት ዝርፊያን ከፈጸመ በኋላ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቁጠጥር ስር የዋሉት የ70 ዓመቱ ኢታሎ ዴ ዊት በቅጽል ስሙ “ጀርመናዊው”፣ የ68 ዓመቱ ሳንድሮ ባሩዞ፣ እና የ77 ዓመቱ ራኒዬሮ ፑላ ሲሆኑ ለተመለከታቸዉ ርህራሄ የሚያሳዩ አያቶች እንጂ ጉዳት የሚያደርሱ ጠንካራ ወንጀለኞች ናቸዉ ብሎ ማንም ሊጠረጥራቸዉ አይችልም። የጣሊያን አቃቢ ህግ ቢሮ እንዳስታወቀዉ ግን ግለሰቦቹ በሮም ፖስታ ቤቶች ውስጥ ዝርፊያ የፈጸሙ የታጠቁና የተካኑ ወንበዴ ቡድን መሪዎች እንደነበሩ ይፋ አድርጓል ።

የወንበዴው ቡድን ግልጽ የሆነ መዋቅር ያለዉ ሲሆን ሦስቱ አዛውንት ከላይ የሚመሩት ሲሆን ሌሎች ሦስት ባለሙያዎች ናቸዉ አንዱ የ66 ዓመቱ ግለሰብ ቁልፍ ሰሪና ቁልፍ ገንጣይ ሲሆን የተቀሩት የ51 ዓመቱ ጎልማሳ እና የ56 ዓመቱ ጎልማስ ግንብ ሰሪዎች ናቸዉ፡፡ሁሉም የወንጀል ቡድኑ አባላት ከዚህ ቀደም የወንጀል መዝገብ ነበረባቸው፡፡የቡድኑ መሪዎቹ ከ1970ዎቹ ጀምሮ የክስ መዝገብ ያለባቸዉ ስለመሆኑ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

የጣሊያን አቃቢ ህግ እንዳለዉ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው አንዳንድ ሰዎች ፈጽሞ አይለወጡም ሲል አስታዉቋል፡፡የጣሊያን ባለስልጣናት ባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይ የፖስታ ቤት ዝርፊያ ከተፈጸመ በኋላ የቡድኑን እንቅስቃሴ መመርመር ጀምረዋል፡፡ሶስት ግለሰቦች እንዳይታወቁ ጭምብል፣ ኮፍያ እና መነጽር በመጠቀም ጠመንጃ በመያዝ በ211 ሺ የአሜሪካን ዶላር ዝርፊያ ፈጽመዋል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መርማሪዎች እንዳሉት የወንጀለኛ ቡድኑ ቢያንስ ሁለት ተጨማሪ ዘረፋዎችን ለመፈጸም አቅዶ የነበረ ቢሆንም ሁለቱም በተለያዩ ምክንያቶች ተሰርዘዋል።

ከተሰረዙት ዝርፊያዎች መካከል አንዱ የጣሊያን ጋዜጣ ላ ሪፑብሊካ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ከአዛውንቶች ዘራፊዎች መካከል አንዱ የ 66 ዓመቱ ቁልፍ ሰሪ ሊቆጣጠረዉ የማይችለዉ የፕሮስቴት ቀዶ ህክምና ያስፈልገዋል ስለነበር የዝርፊያዉ እቅድ እንዲዘዋወር ምክንያት ሆኗል፡፡ባለፈዉ ዓመት የወንበዴው ቡድኑ ፖስታ ቤትን ዳግም ለመዝረፍ ሞክሮ በኤቲኤም ውስጥ አነስተኛ ገንዘብ በመኖሩ እቅዳቸዉን እንዲሰርዙ ምክንያት ሆኗል፡፡

በምርመራው ወቅት አቃቢ ህግ እንዳስታወቀዉ ሦስቱ አረጋውያን የወንጀለኛ ቡድኑ መሪዎች ዴ ዊት ፣ ፑላ እና ባሩዞ ፖሊስ ሊሰማ ይችላል ብለው ስለሚያስቡ በስልክ ብዙም በስልክ እንደማይነጋገሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ይልቁኑ ቀጣዩን እቅዳቸውን ለማውጣት ብዙ ጊዜ ግልጽ ባልሆነ ባር ዉስጥ ይገናኙ ነበር።በትጥቅ ዝርፊያ ከተከሰሱት መካከል ሦስቱ መሪዎች የአራት አመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

2 months, 2 weeks ago

" በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ስርቆት በመፈፀሙ ምክንያት በአምስት ዞኖች ኃይል ተቋርጧል " የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል

ከወላይታ ሰዶ ወደ ሳውላና ጂንካ የሚሄደው ባለ 132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ስርቆት እንደተፈፀመበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል።

ትናንት ምሽት 2፡00 ሰዓት አካባቢ ከወላይታ ሶዶ በ91 ኪሎ ሜትር ርቀት አካባቢ በተፈፀመው ሥርቆት በደቡብ ክልል አምስት ዞኖች ኃይል የተቋረጠ ሲሆን ከቀናት በፊት በመስመሩ ላይ በተፈፀመ ስርቆት አምስቱ ዞኖች እስካለፈው እሁድ ድረስ ለአንድ ሳምንት ያህል በጭለማ ውስጥ መቆየታቸው ተገልጿል።

ቀደም ሲል በተፈፀመው ስርቆት የተነሳ የገጠመው ችግር በተጠገነ በቀናት ውስጥ በኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በድጋሚ ስርቆት በመፈፀሙ ምክንያት በአምስት ዞኖች ኃይል ተቋርጧል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዳግም ስርቆቱ የአካባቢው መስተዳድርም ሆነ ህብረተሰቡ ለችግሩ ትኩረት እንዳልሰጡት የሚያሳይ መሆኑን የጠቆመ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት ለመሰረተ ልማት ጥበቃው ትኩረት እንዲሰጡ አሳስቧል።

ትናንት ምሽት ስርቆት የተፈፀመበት አካባቢ ጫካና ገደላማ በመሆኑ የጥገና ሥራውን አስቸጋሪ ሊያደርገው ስለሚችል ህብረተሰቡ በትዕግስት እንዲጠብቅ ሲል መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

#ዳጉ_ጆርናል

2 months, 2 weeks ago

ሜክሲኮ ደብረወርቅ ህንፃ ጀርባ ድንጋይ ተንዶ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ሶስት ሰዎች ጉዳት ደረሰባቸዋል

ዛሬ የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:52 ሰዓት ላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ደብረወርቅ ህንጻ ጀርባ ለህንጻ ግንባታ የመሰረት ብረት እያሰሩ የነበሩ ሰራተኞች ላይ ድንጋይ ተንዶ የአንድ ሰዉ ህይወት ሲያልፍ ሶስት ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት አደጋዉ የደረሰዉ  ሰራተኞቹ  ለመሰረት በተቆፈረዉ አስር  ሜትር ጥልቀት ባለው ቦታ በስራ ላይ እንዳሉ ድንጋይ ተንዶባቸዉ ነዉ።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች  ህይወቱ ያለፈዉን ሰዉ አስከሬን ለማውጣት
ከአንድ ሰዓት በላይ  የፈጀባቸው ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸዉ  ተጎጂዎች  ህክምና አየተደረገላቸዉ ይገኛል።

ዛሬ አደጋ የደረሰበት ቦታ አሁንም ለአደጋ የተጋለጠ በመሆኑ ተመሳሳይ አደጋ እንዳያጋጥም የሚመለከታቸዉ አካላት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ በግንባታ የስራ ላይ አደጋ በ20 ቀናት ዉስጥ  የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ  ስድስት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል።

በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል

2 months, 2 weeks ago

አጫጭር መረጃዎች በአሌክሲ ናቫልኒ ሞት ዙሪያ

🇷🇺 የናቫልኒ ወላጅ እናት በህልፈቱ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። የአሌክሲ ናቫልኒ እናት ሉድሚላ ለኖቫያ ጋዜጣ እንደተናገሩት ከአራት ቀናት በፊት ልጃቸውን ለመጨረሻ ጊዜ እንዳዩት እና "ህያው፣ ጤናማ እና ደስተኛ ነበር" ብለዋል። "ምንም ዓይነት ሀዘን መስማት አልፈልግም" ሲሉም አክለዋል።

🇷🇺 በእስር ላይ የሚገኘው የሩሲያ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ አሌክሲ ናቫልኒ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የማረሚያ ቤት አገልግሎት አስታወቀ። በፕሬዚዳንት ፑቲን ላይ በግልጽ ትችት የሚታወቀው ዋ ናቫልኒ ከ 2021 ጀምሮ በሩሲያ እስር ቤት ውስጥ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ተፈርዶበት በእስር ላይ ይገኝ ነበር።

🇷🇺 የናቫልኒ ቃል አቀባይ ኪራ ያርሚሽ በበኩላቸው ቡድናቸው ስለሞቱ ማረጋገጫ ገና እንዳላገኘ ነገር ግን ጠበቃው ወደ ሳይቤሪያ እየተጓዘ ነበር ብለዋል። የፑቲን ቃል አቀባይ የሩስያ ማረሚያ ቤት የናቫልኒ ሞት እየተከታተለ ቢሆንም ምንም ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። በነሀሴ ወር ናቫልኒ ፅንፈኛ ድርጅት በመመስረት እና በገንዘብ በመደገፍ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

🇷🇺🇬🇧ቭላድሚር ፑቲን ለናቫልኒ ሞት ተጠያቂ መሆን አለባቸው ሲሉ የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን በኤክስ ወይም በቀድሞው ትዊተር ላይ አጋርተዋል።ካሜሮን በሙኒክ የፀጥታ ኮንፈረንስ ጎን ለጎን በሰጡት መግከጫ  ናቫልኒ ላመነበት ነገር "ሁሉንም ነገር የተወ" እና "በሙስና ላይ በሚያስደንቅ ሁኔታ ደፋር ተዋጊ" ነበር ብለውታል።

🇷🇺 የመጨረሻው የናቫልኒ የኢንስታግራም ፖስት ለባለቤቱ በቫለንታይን የተጋራ ነበር። ከሁለት ቀናት በፊት የእርሱ የኢንስታግራም ገፅ በሚያስተዳድሩ ባለሙያዎሽ በኩል ለዩሊያ በተላከ የቫለንታይን ቀን መልእክት "በእኛ መካከል ከተሞች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች አሉ" ይላል "ነገር ግን በእያንዳንዱ ሰከንድ አቅራቢያ እንዳለሽ ይሰማኛል እናም የበለጠ እወድሻለሁ" ሲል አጋርቷል።

🇺🇸🇷🇺የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ አንቶኒ ብሊንከን የናቫልኒ ሞት "ፑቲን የገነቡትን ስርዓት ድክመት እና መበስበሱን ብቻ ያጎላል" ሲሉ ተናግረዋል። የአውሮጳ ህብረት ለናቫልኒ ሞት ፑቲንን ተጠያቂ አድርጓል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

2 months, 3 weeks ago

ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ግለሰቦች የነዋሪነት መታወቂያ እና የልደት ማስረጃ ሲሰጡ የተገኙ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅት  ላይ የተሰማራ ህገ-ወጥ ደላላ እና አንድ የሌላ ተቋም ሰራተኛ  እንዲሁም ላልተገባ ግለሰብ በገንዘብ አገልግሎት የሰጠ የተቋሙ ሰራተኛ እና ተገልጋዮችን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ኤጀንሲው አሳውቋል።

ኤጀንሲው ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በደረሰው ጥቆማ መሰረት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 4 እና አዲስ ከተማ ወረዳ 9 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ ጽ/ቤት  ሰራተኛ የሆኑ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ግለሰቦች የነዋሪነት መታወቂያ እና የልደት ማስረጃ በመስጠታቸው በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ዋና ዳይሩክተሩ እንደተናገሩት፤ በሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅት የተሰማሩ በድምሩ 12 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል፡፡ ከአቃቂ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በተደረገ ኦፕሬሸን  የአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8  የስራ ዕድል ፈጠራ ጽ/ቤት ሰራተኛ የሆነ ተጠርጣሪ 30ሺ ብር በመቀበል  በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት  ስም የተዘጋጀ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት  መታወቂያ እና  የጋብቻ ሰርትፍኬት  ማዘጋጀቱ የተደረሰበት በመሆኑ በህግ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በተመሳሳይ በኮልፌ ቀራንዮ  ክ/ከተማ ወረዳ 8 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት  ስም የተዘጋጀ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የልደት ሰርተፍኬት እና የመሸኛ ማስረጃ  እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን አቶ ዮናስ ዓለምአየሁ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas