ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 weeks, 2 days ago
Last updated 2 weeks, 4 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago
🚨በጋዛ ዙርያ - ሊቀ ፓፓሱና የእስራኤል መንግስት ተናቆሩ! ___
👉"እስራኤል በህጻናት ላይ የፈጸመችው ጭካኔ ነው ! ይህ ጦርነት አይደለም" ፖፕ ፍራንሲስ
.
👉"ፓፓሱ ስለ ታገቱብን ከ100 በላይ ዜጎች መናገር አይፈልጉም" የእስራኤል የዉጭ ጉዳይ መ/ቤት ___
.
ወደ 1.4 ቢልዮን ገደማ የሚጠጋ የአለም ካቶሎክ እምነት ተከታይን በበላይነት የሚመሩትና መቀመጫቸዉን በቫቲካን ያደረጉት ፓፓስ ፍራንሲስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እስራኤል በጋዛ ዉስጥ የምታደርገዉን ወረራና ግድያ ሲተቹ መስማት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ለወትሮው በዚህ ጉዳይ ብዙም ሲናገሩ የማይደመጡት እኚህ ፓፓስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አልፎ አልፎ እያነሱ ያሉት የተቃዉሞ ሃሳብ በምላሹ የእስራኤል ባለስልጣናት ቁጣና ትችት እያስከተለ ይገኛል፡፡
.
ፓፓሱ በትላንትናው ቅዳሜ እንደፈረንጆቹ ዲሴምበር 21/2024 ተከታዩን የገና በአል አስመልክቶ ለፓፓሶችና የተለያዩ የእምነቱ መምህራን ባደረጉት ንግግር
እስራኤል በሰሜን ጋዛ ህጻናትን ጨምሮ ከአንድ ቤተሰብ ብቻ 10 ሰዎች በአንዴ የተገደሉበትን የሰሞኑን የእስራኤል ጥቃት በማንሳት "እስራኤል የምታካሂደው ጦርነት ሳይሆን ጭካኔ ነው!" ሲሉ ተችተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባለፈው ወር በታተመ መፅሃፍ ዉስጥ "በጋዛ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር አንዳንድ አለም አቀፍ ባለሙያዎች የዘር ማጥፋት ባህሪ አለው ብለዋል" የሚል ሃሳብ ማካተታቸው ሌላው የእስራኤልን ባለስልጣናት ያስቆጣና ለምላሽ የጋበዘ ጉዳይ ሆኗል፡፡
.
ፓፓሱ አያይዘዉም ገናን አስመልክቶ የእየሩሳሌም ፓትርያርክ ወደ ጋዛ ለመግባትና የእምነቱን ተከታዮች ለማግኘት ቢጠይቁም በእስራኤል መከልከላቸዉን አጥብቀው ኮንነዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " እስራኤል እየታገለችና ራስዋን እየተከላከለች ያለችው የእስራኤልን ልጆች ከሚገድሉ፣ ከህጻናት ጀርባ ከሚደበቁ፣ እንዲሁም ከ 100 በላይ ታጋቾችን በመያዝ እና በማንገላታት ላይ ካሉት ከሀማስ አሸባሪዎች ጋር ነው፡፡ ጭካኔ ከተባለም ይህ የሃማስ ስራ ነው ጭካኔ፣ ግን እንደ አለመታደል ሆኖ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ እነዚህን የሃማስ ወንጀሎች ሁሉ ከመናገር ችላ ማለትን መርጠዋል” ሲል ሊቀ ፓፓሱን ወቅሷል፡፡
.
በፍልስጤም በተለይም በጋዛ የሚገኙ የካቶሊክና ሌሎች ክርስትያኖች እንደ ሙስሊም ወንድሞቻቸው ሁሉ በራሳቸዉና በልጆቻቸው ላይ ቤቶችን በቦምብ እያፈረሱባቸዉና እየተገደሉ ከመሆኑም በላይ ታሪካዊ ቤተ እምነቶቻቸዉም ሆን ተብሎ ኢላማ ስለመደረጋቸው ሲናገሩ ይደመጣል፡፡
.
እየሱስ የተወለደበት ነው የሚባለው የፍልስጤም ምድር ቤተልሄም ዉስጥ እንኳ ከአለፈው አመት ጀምሮ በእስራኤል የጋዛ ዘመቻ ምክንያት የገናን በአል ለሁለተኛ ጊዜ ማክበር እንዳልቻሉ የካቶሊክና የኢቫንጄሊካል ቤተ እምነቶች ተወካዮች ለተለያዩ የመገናኛ አውታሮች ተናግረዋል፡፡
https://t.me/minilikcom
🚨በዛሬዋ ኢትዮጵያ የሚሠሙ የቀን ዜናዎች:-♨️*
"ደመወዛችን የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም ስላልቻለ የዶሮ እርባታ መጀመሪያ ካፒታል ተባበሩን"
©***ሀኪሞች
"በህንፃዎች ላይ እስከ 300,000 ብር የሚያወጣ አብረቅራቂ መብራት እንዲገጠም መንግስት አስገድዶናል"
©የአዲስአበባ የመንገድ ዳር ህንፃ ባለንብረቶች
"በ200 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ከ10,000 በላይ ቀረጥ እንድንከፍል እየተደረገ ነው"
©ሹፌሮች
"በተኮሱ ከባድ መሳሪያዎች ሰብላችን እየወደመ፣ እንስሳቶቻችን እየተገደሉ ነው"
©አርሶአደሮች
"ህፃናት ልጆች በግዳጅ እየታፈሱ ወደመከላከያ ማሰልጠኛ እየተጋዙ ነው"
©ወላጆች
"መንግስት በግዳጅ የሚጥልብን መዋጮ የባንኮችን ወጪ በማናሩ ይህም ትርፋማነታችን ላይ አደጋ በመደቀኑ ሰራተኛ ለመቀነስ ተገደናል"
©ባንኮች
"ልጆቻችንን ይዘን ጎዳና ልንወጣ ነው" ©መምህራን
"የኑሮ ወድነቱ በፈጠረብን ጫና የተጠቀምንባቸውን ጫማዎች በጎዳና እያዞርን እየሸጥን ነው"
©መሃንዲሶች
.
.
.ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/minilikcom
ሁለቱ የጎንደር ፋኖ ዕዞች ውህደት ጉዳይ |የጎንደር ህዝብ እና የፋኖ ውይይት|“በዶላር እሚደለል ታጋይ ልጅ የለንም
በመቐለ ከተማ ውጥረት ነግሷል‼️****
በፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የተሾመ የመቐለ ከንቲባ ወደ ፅህፈት ቤቱ እንደይገባ ፥ በጀነራል ታደሰ ወረደ የሚመራው የህወሓት ጦር የመቐለ መዘጋጃ ቤት ከቧል።
ጀነራል ታደሰ ወረደ ፕሬዝዳንት የመሆን ህልሙ ስለተጨናገፈ ፥ በፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ የተሾመውን የመቐለ ከንቲባ ወደ ፅህፈት ቤቱ እንዳይገባ አድርጓል።
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ ከስር የሉ Link join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ👇👇https://t.me/minilikcom
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሳምንቱ መጨረሻ ኢትዮጵያን እና ጁቡቲን ይጎበኛሉ ተባለ።
ፕሬዝዳቱ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በኢትዮጵያ እና ጁቡቲ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ተገልጿል።
ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ታህሳስ 12 እና 13 ቀን 2017 ዓ.ም በሚኖራቸው ቆይታ ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ተጠቁሟል።
ማክሮን በተጨማሪም በአዲስ አበባ በፈረንሳይ ድጋፍ የታደሰውን የብሔራዊ ኢዮቤልዩ ቤተመንግስትን መርቀው ለጎብኚወች ክፍት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
የፈረንሳይ አለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (AFD) ለብሔራዊ ኢዮቤልዩ ቤተ መንግስት እድሳት 12 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉ የተጠቆመ ሲሆን ከአንድ አመት ተኩል እድሳት በኋላ በማክሮን ተመርቆ ክፍት ይሆናል ተብሏል።
የመጀመሪያው ዙር የቤተመንግስቱ እድሳት አጠቃላይ 20 ሚሊዮን ዩሮ ይፈጃል የተባለ ሲሆን ትኩረቱም ለጎብኙዎች ክፍት በማድረግ የቱሪስት መስህብ እንዲሆን ማስቻል መሆኑን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከአምስት አመታት በፊት መጋቢት 3 እና 4 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጉብኝት ማካሄዳቸው ይታወሳል።
https://t.me/minilikcom
በ2025 ምዕራባዊያንን የሚበላ ሶስተኛው የአለም ጦርነት ይጀመራል!”-ባባ ቫንጋ
ባባ ቫንጋ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት 2025 ምን ይከሰታል ብለው ተነበዩ? ከ28 አመት በፊት ህይወታቸው ያለፈው ባባ ቫንጋ እስከ 2030 ድረስ አለማችን የምታስተናግዳቸውን አበይት ክስተቶች ተንብየዋል ።
ቫንገሊያ ፓንዴቫ ጉሽቴሮቫ ወይም በተለምዶ ባባ ቫንጋ እየተባሉ የሚጠሩት ቡልጋሪያዊት ጠንቋይ አዲስ አመት ሲቃረብ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ይስባሉ።
አይነስውሯ ባባ ቫንጋ በ85 አመታቸው በፈረንጆቹ 1996 ህይወታቸው ቢያልፍም እስከ 2030 አለማችን የምታስተናግዳቸውን አበይት ክስተት ተንብየዋልና አሁንም ድረስ ይነሳሉ።
በ12 አመታቸው የአይን ብርሃናቸው ካጡ በኋላ የወደፊቱን የመተንበይ ብቃት እንዳዳበሩ የሚናገሩት ባባ ቫንጋ የመስከረም 11ዱን የኒውዮርክ መንትያ ህንጻዎች ጥቃት፤ የሶቪየት ህብረት መፈራረስና ካንሰር የተባለ በሽታ ቀጣይ ስጋትነትን አስቀድመው ተንብየዋል።
ከ16 ቀናት በኋላ በሚገባው 2025ም በአለማችን የሚከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችን ከህልፈታቸው በፊት ተንብየዋል ብሏል ዴይሊ ስታር በዘገባው።
ባባ ቫንጋ የፈረንጆቹ 2025 ምዕራባውያንን ክፉኛ የሚጎዳ አስከፊ ጦርነት የሚከሰትበት መሆኑን ተንብየዋል። በሶሪያ ጉዳይ አስቀድመው ተናገሩት የተባለውም የቡልጋሪያዊቷን እንስት የመተንበይ ችሎታ በጉልህ አሳይቷል። "ሶሪያ በመጨረሻ በአሸናፊዎች እጅ ትወድቃለች፤ አሸናፊው ግን አንድ አይሆንም" ያሉት ባባ ቫንጋ፥ "በምስራቁ ምዕራባውያንን የሚያጠፋ ሶስተኛ የአለም ጦርነት ይጀመራል" ሲሉ ተንብየዋል።
ባባ ቫንጋ "በ2025 የሰው ልጆች ምንነታቸው ከማይታወቁ በራሪዎች (ዮፎ) ጋር ግንኙነት ይጀምራሉ፤ ይህም ምናልባትም አለማቀፍ ቀውስ ያስከትላል" ይላሉ።
የአሜሪካዋ ኒው ጀርሲ ከአንድ ወር በላይ ዩፎ ይሁኑ ድሮኖች እስካሁን በውል ያልተለዩ በረሪ አካላት በሰማይ እያንዣበቡባት ነው።
ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ካሸነፉ የአሜሪካ መንግስት በዩፎዎች ዙሪያ ያለውን ዝርዝር መረጃ ይፋ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። የትራምፕ መመረጥም የባባ ቫንጋ ትንበያ እውን ሊሆን እንደሚችል አመላካች ነው ተብሏል።
https://t.me/minilikcom
የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች የምግብ ወጪ መጋራት በሦስት ዓይነት አሠራሮች እንደሚተገበር ተገለፀ፡፡
በመንግሥት ምደባ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ የወጪ መጋራት ግዴታ እንደሚመለከታቸው በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአስተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ አብዱ ናስር ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ሦስት ዓይነት ተማሪዎች እንደሚገኙ የገለፁት ኃላፊው፤ ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸውን የሚችሉ፣ ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸውን የሚሸፍንላቸው እና የወጪ መጋራት የሚመለከታቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
የተማሪዎች ዝቅተኛው የትምህርት ቆይታ ጊዜ አራት ዓመት ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ የአንድ ተማሪ የምግብ ወጪ መጋራት ሲሰላ 120,000 ብር እንደሚሆንና የሰባት ዓመት ቆይታ ያለው የሕክምና ትምህርት ደግሞ 210,000 ብር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የተማሪዎች የምግብ ወጪ መጋራት ተመን በየትምህርት ዘርፍ የዋጋ ልዩነት ያለው ሲሆን፤ ይህም በተማሪዎች የትምህርት ፕሮግራም ቆይታ ስሌት መሠረት እንደሚሆን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
ራስ ገዙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ 5,000 ተማሪዎች የተቀበለ ሲሆን፤ 2,500 በራሳቸው ከፍለው የሚማሩና ወጪ መጋራቱ የማይመለከታቸው ናቸው፡፡ የተቀሩት 2,500 ተማሪዎች ደግሞ መደበኛው የመንግሥት ወጪ መጋራት የማይከመለታቸው ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸውን የሚሸፍንላቸው እንዳሉ አስረድተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ተመን ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 ብር እንዲሆን ተወስኗል። ትምህርት ሚኒስቴር ወጥ የሆነ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መላኩም ይታወቃል፡፡ #ሪፖርተር
https://t.me/minilikcom
ስበር ዜና‼
የአማራ ፋኖ በጎጃም እና የአማራ ፋኖ በጎንደር በጋራ ያሰለጠኑትን የኮማንዶ ኃይል ዛሬ ሕዳር 07 ቀን 2017 ዓ. ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቀዋል።
ከጎጃም እና ከጎንደር ጠቅላይ ግዛቶች ለተመለመሉ ነባር የፋኖ አባላት እና ምልምል ወጣቶች ለወራት የተሰጠው ልዩ ወታደራዊ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
የነገውን የአማራ ትግል አንድነት ታሳቢ ያደረገ የውህዱን ሰራዊት እርሾ ለመፍጠር ከጎንደር ወንድሞቻችን ጋር ተገቢዉን ጥረት አድርገናል። የአማራ ዘቦች ጥንስስ የተጣለበት ወሳኝ ወታደራዊ ስልጠናም ተከናውኗል።
ደረጃውን የጠበቀ የኮማንዶ ስልጠና የወሰዱት ከአንድ ሺህ በላይ ኮማንዶወች ድርጅቶቹ በጋራ ለሚያካሂዱት ወታደራዊ ኦፕሬሽን ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ ተሰጥቷል።
የፋኖ አንድነት በተግባር በፅኑ አለት ላይ ይገነባ ዘንድ ተመሳሳይ ስራወች ይቀጥላሉ።
አዲስ ትዉልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
✍️አስረስ ማረ ዳምጤ
https://t.me/minilikcom
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 weeks, 2 days ago
Last updated 2 weeks, 4 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago