መንፈሳዊ ትምህርት እንዲህ እየተማርን እናስተምር እንማማርም፡፡ (በመ.ኅ. የማነ ብርሃን ጌታሁን ዘበአታ ታዕካ ነገሥት)

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 weeks ago
ሳይፈርስ ይኽ ነበር።

ሳይፈርስ ይኽ ነበር።

ምንም ዕንኳ ፍትሕን ማጣት አሳዛኝና አስከፊ ቢሆንም፤ ከጠላትህ ፍትሕን መለመን ግን የበለጠ ያማል።
ግን ምን ይደረግ?
እያለው የሌለው ሕዝብ እንዲህ ነው።

የቱንም ያኽል ብዙ ብትሆን በአግባቡ ተደራጅተህ መብትህን ማስከበር ካልቻልህ  የጥቂቶች መዘባበቻ ትሆናለህ።
ልክ እንደእኛ።

2 weeks ago
**ኹሉም ነገር ተፈጸመ።**

ኹሉም ነገር ተፈጸመ።

ዛሬ ታኅሣሥ 22 ቀን 2017 ዓ.ም የ92 ዓመተ ምሕረቱ አንጋፋው የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ መንፈሳዊ ትምህርት  ቤት በዕለተ ሠሉስ በሦስት ሰዓት ማፍረስ ተጀመረ።

በውስጡ ያሉት ካህናት፣ አዳሪ ተማሪዎች፣ ጡረተኞች፣ መምህራንና ልዩ ልዩ በገዳሙ ውስጥ ነዋሪ የሆንን ኹሉ አንዳችም ማረፊያ ሳይሰጠን ነው ገዳሙ እየፈረሰ ያለው።

እኔም አዘጋጅቼ የነበረውን አስፈላጊ የሆኑ መጻሕፍቶቼን ብቻ ይዤ ለዐርባ ዓመት የኖርሁበትን፣ የተማርሁበትንና ያስተማርሁበትን ቦታ ለአፍራሹ ቡድን ትቼ ወደ ዘመድ ቤት ተጠጋሁ።

ይኽን አንጋፋና እድሜ ጠገብ፣ የመንፈሳዊ ትምህርት ኹሉ ማእከል የሆነ ተቋቋም እነሆ ሲፈርስ ዐይኖቼ አዩ።
ምን ማድረግ እችላለሁ?
ነገም ሌላ ቀን ነው።

2 weeks, 6 days ago

ዛሬ ታኅሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ነው፤ እንደ ሌላው ቀን ቢሆን ኖሮ በዚህ ሰዓት ጉባኤ ዘርግተን ትምህርት ላይ ነበር።

አሁን ግን ጉባኤ አጥፈን ትምህርት ዘግተን የዘጠና ዓመቱን አንጋፋ የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ መንፈሳዊ ትምህርት ቤታችን በልማት ሰበብ እንዲፈርስ ስለተወሰነብን እቃችንን እያዘጋጀን እንገኛለን።
ለማን አቤት ይባላል?
ጉባኤ አጥፎ፣ ማስተማርን ትቶ፣ ተፈናቃይ መሆን ምንኛ ያማል?
ስሳ ወይም ሰባ ሚሊየን አማኝ ሕዝበ ክርስቲያን ያላት ቤተ ክርስቲያን በመቶ የሚቆጠሩ አባቶች ጳጳሳት ያላት ቤተ ክርስቲያን እንዴት ለምን? ብሎ የሚጠይቅ አባት አጣች?
አሳዛኝ ነው።
ለማኛውም ዕቃዬን ላዘጋጅ።

2 weeks, 6 days ago
መንፈሳዊ ትምህርት እንዲህ እየተማርን እናስተምር እንማማርም፡፡ …
3 weeks, 3 days ago
ይኽ የአንቀጸ ቅዳሴ መጽሐፍ የአንቀጹን ዜማ …

ይኽ የአንቀጸ ቅዳሴ መጽሐፍ የአንቀጹን ዜማ ታርሞና ተስተካክሎ ከመያዙ በላይ የቅዳሴ ስረዮችን የዜማና የንባብ ጠባይ ጠንቅቆ የያዘ በመሆኑ ለመማር፣ለማስተማርና በጥልቀት ለማወቅ በእጅጉ ይረዳል፤
ስለዜህ መጽሐፉ ሊኖርዎ ይገባል።
ከዜህ ቀደም በዜህ መልኩ ታትሞ አያውቅምና፤

መጽሐፉን ከፈለጉ 0911691953 ብለው ይደውሉ።

1 month ago
1 month ago
መንፈሳዊ ትምህርት እንዲህ እየተማርን እናስተምር እንማማርም፡፡ …
1 month ago
መንፈሳዊ ትምህርት እንዲህ እየተማርን እናስተምር እንማማርም፡፡ …
1 month ago

ታኅሣሥ ፯(7) ቀን  ፳፻፲፯ (2017) ዓ.ም

እነሆ የታኅሣሥ በአታ ለማርያም ዓመታዊ በዓልን እንደተለመደው በደማቅና በከፍታ ሆነን ካከበርን በኋላ ዛሬ መደበኛ የሆነውን የቅዳሴ ትምህርታችንን ዠመርን።

ምንም እንኳ የ92 ዐመቱ አንጋፋው መንፈሳዊ ት/ቤታችን በላያችን ላይ እያፈረሱብን ቢሆንም፤

ለምሳሌ፤
አሁን በዜህ ሰዓት እኛ በተለመደው ክፍላችን ውስጥ ሆነን እየተማርን ቢሆንም የአፍራሽ ቡድኑ በእስካባተር የትምህርት ቤታችንን  መውጫ በር በሚቆፍረው አፈር ዘግቶ አርማውን አፍርሶ ዙሪያ ገባውን እየቆፈረው ይገኛል።

ከዜህ መከራ ማን ያድነናል?
ቅዱስ ሲኖዶስ?
ጠቅላይ ቤተ ክህነት?
ሀገረ ስብከት?
ማንም?
እግዚአብሔር ግን ታላቅ ነውና ፈቃዱ ከሆነ ያድነን ይሆናል።

እኛ ግን ትምህርት ቤታችን ሙሉ በሙሉ እስከሚፈርስ ድረስ እንማራለን።

መኑ የኀድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ፤
እንደተባለው።

1 month ago
መንፈሳዊ ትምህርት እንዲህ እየተማርን እናስተምር እንማማርም፡፡ …
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana