ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 недели назад
Last updated 2 недели, 2 дня назад
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 месяц назад
ቃላትን ምረጥ
ቃላት ሰዎችን ማዳን እንደሚችሉት ሁሉ መግደልም ይችላሉ ፣ ከአንደበትህ የሚወጡትን ቃላት ከመውጣታቸው በፊት ለሰሚው አዎንታዊ ስሜት የሚሰጡ ተስፋን የሚያለመልሙ እና እምነቱን የሚያጠነክሩ መሆናቸውን እርግጠኛ ሁን! ቃል ሰውን ያድናል ፤ ቃል ሰውን ይገድላል !
በየቀኑ 1% እደግ!
የተሻለ ሕይወት ለመፍጠር ግዴታ ትልቅ ነገር ማድረግ አይጠበቅብህም በየቀኑ ራስህን በእውቀት ፣ በባህሪ ፣ በልምድ እና በአስተሳሰብ 1% ማሳደግ ከቻልክ የምትፈልገውን ሕይወት መኖርን ግዴታ ነው ፣ የአንድ ቀን ልፋት ሳይሆን የአመታት የማያቆም ጥረት ነው ወደምትፈልገው ከፍታ የሚያደርስህ!
የልብ ጓደኛችሁ
ሕይወት እንደዚህ ናት
በሕይወት ጉዞ ሁልጊዜ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ብቻ አታገኝም ፤ አንዳንዴ ይሆናሉ ብለህ የማትጠብቃቸው ጥሩ ስሜት የማይሰጡህ ክስተቶች ሊገጥሙህ ይችላሉ ምንም ማድረግ አይቻልም ሕይወት እንደዚህ ነው ካንተ የሚጠበቀው ከእያንዳንዱ ክስተት መማር ያለብህን ትምህርት በአግባቡ እየወሰድክ ሕይወትን መቀጠል ነው ።
ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ እንዴት ናችሁ? በአንዳንድ ምክንያቶች ሰሞኑን ፖስት ማድረግ አልቻልኩም ነበር በጣም ይቅርታ ፤ ከዛሬ ጀምሮ እንደወትሮው በየቀኑ ምርጥ ምርጡን ፖስት አደርጋለሁ አመሰግናለሁ ?
ሁላችሁም ከታች ያለውን ሊንክ ቢያንስ ለ 10 ሰዎች forward (ሼር) እንድታደርጉልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ አመሰግናለሁ ?**
????????*?*????
ጣፋጩ በቀል
ዋጋህን ያልተረዱትን ፣ የሚገባህን ክብር ያልሰጡህን ፣ ለመለወጥ ስትሞክር ሙድ የያዙብህን ፣ የናቁህን ፣ ያቆሰሉህን ፣ የተሳለቁብህን ፣ አይንህ እንባ እስኪያቀር ድረስ ያፌዙብህን ሰዎች ልትበቀላቸው ትፈልጋለህ?
እንግዲያውስ ምንም አይነት ቃል መናገር ሳይጠበቅብህ ፣ ምንም አይነት የጥይት ቀልሀ ማባከን ሳይጠበቅብህ ፣ ምንም አይነት ጎራዴ መምዘዝ ሳይጠበቅብህ አንገታቸውን የሚያስደፋ ፣ ልባቸውን በፀፀት የሚያቃጥል ፣ የተዘባበቱበትን አንደበት እንዲያደንቁበት የሚያደርግ ምርጥ በቀል ልንገርህ? ዝምብለህ አንገትህን ደፍተህ ሕልምህ ላይ ስራ እና ስኬትህን አሳያቸው ያንተ ስኬት ለነሱ እንደ እሳት ነበልባል ነው ።
The best revenge is massive success.
መልካም ቀን?
ከባዱን አድርግ!!
በዚህ ዓለም ላይ ቀላል እና ነፃነት ያለው ሕይወት መኖር ትፈልጋለህ እንግዲያውስ ከባዱን ነገር ማድረግ ይጠበቅብሃል! ሰዎች በብዛት የሚያደርጓቸውን የተለመዱ ነገሮች የምታደርግ ከሆነ የተለመደውን ተራና በትግል የተሞላ ሕይወት መኖርህ የማይቀር መሆኑን አስብበት ፤ ግን በተቃራኒው ብዙ ሰዎች ለማድረግ የማይፈልጓቸውን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ ብዙ ሰዎች የማይኖሩትን ኑሮ ትኖራለህ ። ነቃ በል አንበሳው ?****
መልካም ቀን?
ይምከሩሽ ግን አይወስኑልሽ!
ባንቺ ሕይወት ላይ ሌሎች ሰዎች እንዲወስኑ በፍፁም እንዳትፈቅጂላቸው! ካንቺ በልምድ በዕውቀት ወይም በእድሜ የተሻሉ ሰዎችን ምክር መጠየቅ ብልህነት ነው ምክንያቱም ስህተቶችን ለመቀነስ ስለሚያግዝ ነገር ግን ሰዎች ከመምከር አልፈው ውሳኔ ለመስጠት ሲዳዳቸው እንዳትሰሚያቸው ፤ ባንቺ ሕይወት የመወሰን መብት ያለሽ አንቺ ብቻ ነሽ ምክንያቱም ያንቺ ሕይወት ያንቺ ኃላፊነት ብቻ ስለሆነ ፤ ነቃ በይ እህቴ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 недели назад
Last updated 2 недели, 2 дня назад
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 месяц назад