Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

Description
በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የምዕመናን መረጃ መለዋወጫና ትምህርት መስጫ አውታር ነው፡፡
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

4 days, 18 hours ago

https://www.youtube.com/live/W5Pcegye1Cs?feature=shared

YouTube

MK TV || ቀጥታ ሥርጭት || ሰሙነ ሕማማት ከመ/ፓ/ቅ/ቅ/ ማርያም ገዳም - ዕለተ ሰኑይ

Subscribe and share https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s...... https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s...... #MKTV #MahibereKidusan #EOTCMK https://www.facebook.com/eotcmkidusan/

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
5 days, 21 hours ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
6 days, 7 hours ago

ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም፣ ቤተ ፋጌ በቀረበ ጊዜ ከቅዱሳን አባቶቻችን ሁለቱን ሐዋርያት ወደ ቤተ ፋጌ ልኮ የታሰረች አህያ እንደሚያገኙና ፈትተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፤ ነገር ግን ጥያቄ የሚጠይቅ ሰው ከመጣ ‹‹…ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ…›› አላቸው፤(ማቴ.፳፩፥፫)ፈትታችሁ አምጡ ማለቱ ሕዝቡን ከማዕሰረ ኃጢአት የሚፈቱበት ጊዜ እንደ ደረሰ ሲያጠይቅ ነው፡፡ ዛሬ ዓለም በሥጋዊ ጥቅም በኃላፊ ደስታ ዓይነ ልቡናችንን ጋርዳ፣ ሥጋዊ ፈቃዳችን ከፈቃደ ነፍሳችን አይሎ በኃጢአት ማዕሰር ታስረናል፡፡ ጌታችን በትምህርቱ ‹‹…ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው፤ ባርያም ለዘለዓለም በቤት አይኖርም…›› በማለት እንደገለጸው በበደላችን በኃጢአት ባርነት ቀንበር ሥር ወድቀን በዲያብሎስ ባርነት ታስረናል ፤ (ዮሐ.፰፥፴፬) ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን››፤ ከታሰርነበት የጥላቻ፣ የቂም፣ የዘረኝነት፣ የጎጠኝነት የኃጢአት ማሰሪያ ይፈታን ዘንድ ‹‹እባክህ አሁን አድነን!›› እንበለው፡፡

‹‹እባክህ አሁን አድነን››፡- አይሁድ፣ ጸሐፍት ፈሪሳውያን የምስጋና ባለቤት ከሆነው ዘንድ በተሰጣቸው ኃላፊነት ምስጋና የባሕርይው የሆነን ፈጣሬ ዓለማት መድኅን ዓለም ክርስቶስን ማመስገን፣ አመስግነው መመስገን፣ ቅዱስ ስሙን ጠርተው መቀደስ ሲገባቸው በተቃራኒው ልባቸው በጥላቻና በቅናት ተመልቶ የሚያመሰግኑት ዝም ይሉ ዘንድ ጠየቁ፤ አንደበትን ለምስጋና የፈጠረ ጌታ ግን ‹‹እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ›› አላቸው፤ ምንም የሚሳነው የሌለ ጌታም ድንጋዮች ያመሰግኑት ዘንድ አደረገ፡፡ (ሉቃ.፲፱፥፵)
ጌታችን በትምህርቱ ‹‹ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ ክፉም ስለሆነ ሥራው እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም›› በማለት እንደገለጸው የክፋት ሥራቸውን የሚገልጥ፣ ጨለማ አስተሳሰባቸውን የሚያበራ የብርሃን ጌታ ሲመጣ የእርሱ መገለጥና መመስገን እነርሱን የሚያሳንስ ስለመሰላቸው ተቃወሙ፡፡ ክህነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነና  የሰጣቸውም እርሱ እንደሆነ ማስተዋል ቢሳናቸው የራሱን ገንዘብ ምስጋናውን ለማስቀረት ፈለጉ፤ (ዮሐ.፫፥፳) ማድረግ የማይቻላቸውን ሊያስቀሩ ደፈሩ፤ ክፉዎች  የቅኖች ደግነት፣ የመልካሞች በጎ ሥራ፣ የትሑታን የተሰበረ መንፈስና  የአመስጋኞች ምስጋናቸው ይረብሻቸዋል፡፡ ልቡናቸውን ለጠላት ዲያብሎስ ማኅደር ስላደረጉ የቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ስሙ ሲጠራና ምስጋናው ሲደመጥ ሰላም ይነሳቸዋል። ዲያብሎስ  እግዚአብሔር ሲመሰገን፣ ሰው ንስሐ ሲገባ፣ የምሥራቹ ወንጌል ሲነገር፣ ምእመናን በቤተ እግዚአብሔር ሲበዙ፣ ሰላም ሲሰፍን፣ ሰዎች ሲፋቀሩ አንድነት ሲጸና፣ ሕገ እግዚአብሔር ሲከበር፣ ክርስትና ሲሰፋ፣ በዓላት ሲከበሩ ማየትና መስማት አይሻም፤ የግብር ልጆቹን እያሰማራ መንፈሳዊውን ዓለም ያውካል፤ ሁሉም እንደ እርሱ ከፈጣሪው ተጣልቶ በክህደት እንዲኖር ይፈልጋሉ። ዓለም ሳይፈጠር ባሕርይው ባሕርይውን እያመሰገነ ምስጋናው ሳይቋረጥ የኖረውን ጌታችንን በእናታቸው እቅፍ ያሉ ሕፃናት፣ አዕባን (ድንጋዮች) “ለምን አመሰገኑት” ብለው የቅናት ጥያቄ እንደጠየቁት ማለት ነው።

ዛሬም በሥጋ ለባሹ የሰው ልጅ አድሮ “ለምን አመሰገናችሁ? ለምን አምልኮተ እግዚአብሔር ፈጸማችሁ” በማለት ምስጋናውን ሊያስቀር ይጥራል፤ ግን አይቻለውም! እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በስሙ እንዳያስተምሩ፣ ባስፈራሯቸውም ጊዜ  ‹‹… ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል…›› አሉ፡፡ (የሐ. ሥራ ፭፥፳፱) እኛም ልጆቻቸው የአሠረ ፍኖታቸው ተከታይ ነንና! ዛቻና ማስፈራራቱን ሳንፈራ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ  አሁን አድነን››  እንላለን፡፡ አመስግነን እንመሰገን፣ ቀድሰን እንቀደስ ዘንድ ከባለጋራችን ዲያብሎስ የተቃውሞ ዛቻና በትር እንዲታደገን ዘንድ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን…መድኃኒት ሁነን›› ብለን እንዘምራለን፡፡

ዲያብሎስ በግብር ልጆቹ ልቡና አድሮ በግፍ በትር ሊሸነቁጠን በተስፋ መቁረጥ ገመድ አስሮናልና  ቅዱሳን በቃል ኪዳናቸው ይፈቱን ዘንድ ይልክልን ዘንድ ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን›› እንበለው፤ በነቢዩ ዘካርያስ  አማካኝነት ‹‹…የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በይ፥ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል…›› በማለት በተናገረው ቃል መሠረት መምህረ ትሕትና የዓለም ጌታ መድኅን ክርስቶስ በአህያይቱና በውርንጭላይቱ  ዘባን ( ጀርባ) ተቀምጦ ሲመጣ  በኢየሩሳሌም የነበሩ ልብሳቸውን ከምድር አነጠፉ፤ (ዘካ.፱፥፱) “እንኳን ለአንተ ለተቀመጥክባት አህያም ክብር ይገባል” ሲሉ! ትሕትናን ከእርሱ በተግባር ተምረዋልና በትሕትና የለበሱትን ልብስ አውልቀው ከምድር አነጠፉ፤ በጥቂት የትሕትና ሥራቸው ዝቅ ካሉበት ከሰጠሙበት የበደል አዘቅት ከፍ ያደርጋቸውና ያከብራቸው  ዘንድ  ‹‹ሆሣዕና በአርያም፤ እባክህ አሁን አድነን…!›› በማለት ተማጸኑት፤ እኛም ከልቡናችን እልፍኝ በጎ ሥነ ምግባር ልብሳችንን አንጥፈን ይገባበት ዘንድ ‹‹በሰማይ ያለ መድኃኒት ናልን›› ብለን እንጋብዘው፡፡

በሆሣዕና በዓል ዕለት በምስጋናው ጊዜ ዘንባባን እንይዛለን፤ ጌታችን በአህያና በውርንጭላይቱ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ከልብሳቸው በተጨማሪ የዘንባባ ዝንጣፊም ይዘው ነበር፤ በብሉይ ኪዳን ዘንባባ የደስታ መግለጫ ነው፤ አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ ደግሞ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ወጡ፤ ዮዲት ወገኖቿን ሲያስጨንቅ ንጹሐንን በግፍ ሲገድል የነበረውን ሆሎፎርኒስ የተባለን ሰው ገድላ በተመለሰች ጊዜ ዘንባባን ይዘው ደስታቸውን ገልጠዋል፡፡ አንድም ይላሉ መተርጉማነ አበው ‹‹ዘንባባ እሾኻማ ነው፤ ትእምርተ ኃይል (መዊእ) አለህ›› ሲሉት አንድም ዘንባባን እሳት አይበላውም፤ ለብልቦ ይተወዋል፤ ባሕርይ አይመረመርም›› ሲሉ ነው፡፡ የሰላም አለቃ፣ ኃያል፣ ልዑል፣ ባሕርይው የማይመረመር አምላካችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒት ይሆነን፣ ያድነን ዘንድ በሕጉ ተጉዘን፣ ትእዛዙን፣ አክብረን፣ በትሩፋት ሥራ አጊጠንና የምግባር ዘንባባን ይዘን ጠላት ዲያብሎስን ድል አድርገን ‹‹ሆሣዕና›› እንበለው፡፡ (የማቴዎስ ወንጌል አድምታ ትርጓሜ ፳፩፥፰) ዝቅ ካልንበት ከፍ ያደርገን ዘንድ ከእግሩ በታች ራሳችንን እናዋርድ፤ ‹‹… በመጠን ኑሩ፤ ንቁም ባለጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና …››እንደተባለው፤(፩ኛጴጥ. ፭፥፰)በአህያ ውርንጭላ ጀርባ ተቀምጦስለ እኛ ራሱን ዝቅ አድርጎከፍ አድርጎናል፤ ዳግመኛ በኃጢአት ቀንበር ወድቀን በባርነት እንዳንያዝም በጾምና በጸሎት ልንተጋ ያስፈልጋል፡፡

‹‹አምላካችን ሆይ! እባክህ አሁን አድነን!››
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ! አሜን
 

1 week, 5 days ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
1 week, 5 days ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
1 week, 5 days ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
2 months, 2 weeks ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
2 months, 2 weeks ago

• ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ “#ሦስቱ ፍሬ ቢሶች “በማለት ፍሬ ካላፈራን ደግሞ መርገም እንደሚከተለን ፤ ሦስቱን ፍሬ ብሶች በዝርዝር ይዳስሳል፡፡

• በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#ባሕረ ወርቅ መስመስ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካል "ቤተ ክርስቲያን ይዘው ስለመጡ ጠንካራ አባቶች ይተርካል፣ያስተዋውቃል፣ ባሕረ ወርቅ መስመስ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካል ቤተ ክርስቲያን ከመስመስ ሕዝብ ጋር ያለውን ቁርኝት ያሳያል። ባሕረ ወርቅ መስመስ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካል ቤተ ክርስቲያን ለሀድያ ሕዝብ የክርስትና መሠረት ማዔከሉ መሆኑ እሙን እንደሆነ ያስተዋውቃል ።

• በነገዋ ቤተ ክርስቲያን ዐምድ ሥር “ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ተረካቢ እናዘጋጅላት _ክፍል ፪“ በሚል ለልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት ባለድርሻ አካላት የሚሆኑት ወላጆች፣ ጎረቤት፣ ማኅበረሰብ፣ ትምህርት ቤት ወዘተ. ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመላለሱ ምን መሥራት እንዳለባቸው ፣መንፈሳዊ ትምህርት እንዲማሩ ፣ የሚኖራቸውን ሚና ያስነብባል፡፡

• በኪነ ጥበብ ዐምድ “ ምን በጀኝ ? “ በሚል ርእስ ይዳስሳል፡፡(ገጽ _፳፫)

• የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “#ምሥጢረ ሥጋዌ”ክፍል ፫ በምሥጢረ ሥጋዊና ተያያዥ ጉዳች የመጻሕፍተ ሐዲሳት መምህር ከሆኑት መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩሜዳ የወሎ ዪኒቨርስቲ የልሳነ ግእዝ መምህር እና በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪ ጋር መሠረታዊ ትምህርት ይሰጣል፡፡

መ/ር ኃይለ ማርያም ".በዘመናችን ሙሉ ብንኖርበትም ምሥጢረ ሥጋዌ ተነግሮ የማያልቅ ትምህርት እንደሆነ ገልጸዋል።

#ማእከላት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት ቁጥር ፪ ዕትም ለአንባቢያን እንድትደርስ የድርሻችሁን እንደትወጡ ምክንያቱም .ሐመር መጽሔት ትምህርተ ወንጌል ለመላው ዓለም ለማዳረስ አንዱ መሣረያ ናት፡፡

ሐሳብ አስተያየታችሁን ወደ ዝግጅት ክፍላችን በ magazine @eotcmk.org በኩል አድርሱን

ሐመር መጽሔት ከፍተኛ የሆነ የዕቅበተ እምነት ሥራ ሠርታለች ወደፊትም ትሠራለች፡፡

• ሐመር መጽሔት ፴፩ኛ ዓመት ቁጥር ፪ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ ዘመኑነም በመዋጀት የድርሻችን እንወጣ!

magazine @eotcmk.org ሐመር መጽሔት ዝግጅት ክፍል

2 months, 2 weeks ago

ማኅበረ ቅዱሳን ባሉት በጎ ፈቃደኛ ባለሙያዎች ከምሥረታው ጀምሮ በፈጸመው አገልግሎት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያተረፈችባቸውና ባለሙያዎችም በረከት ያገኙባቸው ውጤቶች እንደተመዘገቡ በጥናቱ ተብራርቷል፡፡ ይሁን እንጂ ሙያን በመስጠት ሂደት ከቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ከባለሙያዎች የሚመነጩ ችግሮች እንደሚስተዋሉ ዶ/ር ታደሰ ያነሱ ሲሆን የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችንም አቅርበዋል፡፡ ተሳታፊዎችም በቀረበው ጥናት እና ባካሄዱት የቡድን ውይይት ጥሩ ልምድና ግንዛቤ እንዳገኙበት ተናግረዋል፡፡

የውይይት ማጠቃለያ ያቀረቡት በማኅበረ ቅዱሳን የሙያና ማኅበራዊ አገ/ት ማስተባበሪያ ኀላፊ ዲ/ን ዶ/ር ቱሉ ቶላ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ሊያሻግር የሚችል መዋቅር ለመፍጠር እና የሉላዊነትን ተፅዕኖ ለመቋቋም ሙያን መንከባከብ፣መጠበቅና ማበጀት ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም በማኅበረ ቅዱሳን የአዳማ ማእከል ሰብሳቢ አቶ ከተማ ቢተው ባስተላለፉት መልእክት እየጎዳን ያለው እኛ ያልሠራነው ሥራ ነው፤ ከምክንያት እና ልማዳዊ አሠራር ተላቀን የቤተ ክርስቲያንን ችግር መፍታት አለብን ብለዋል፡፡

2 months, 2 weeks ago
**አደራ አለብኝ!**

አደራ አለብኝ!

የ 2016 ዓ.ም 2ኛ ዙር ጉባኤ

ዓለም ዓቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ

• ቀን፡ መጋቢት 08/2016 ዓ.ም
• ሰዓት፡ ከ 7፡00 ጀምሮ
• ቦታ፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas