ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

Description
በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል የምዕመናን መረጃ መለዋወጫና ትምህርት መስጫ አውታር ነው፡፡
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

3 weeks, 5 days ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
3 weeks, 5 days ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
4 weeks ago

መጋቢት ፳፯ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ፤ የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና  ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል። የተሰቀለው የክብር ባለቤት ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀዷል፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯ )፡፡

ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ ጋር ቤተ ክርስቲያን በ15ኛው መ.ክ.ዘ  የነበሩትን አቡነ መብዓ ጽዮንን ታስባለች፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮን  አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን  ‹‹ በዕለተ ዓርብ የተቀበልከውን  መከራ ግለጽልኝ ››ብለው በጸለዩ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ የተቀበላቸውን መከራዎች ሁሉ አሳያቸው፡፡
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስን መከራ ካዩበት ቀን ጀምሮ ሕማሙን መከራውን ግርፋቱን እስራቱን በጠቅላላ አሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል በማሰብ ጀርባቸውን በአለንጋ ይገርፉ ፤ ራሳቸውን በዘንግ ይመቱ ነበር፡፡ 

የጌታችንን ሕማማተ መስቀል እያሰቡ ዘወትር ስለሚያለቅሱ ዐይናቸው ጠፍቶ ነበር፡፡ ነገር ግን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የብርሃን ጽዋ ይዛ መጥታ ዐይናቸውን ቀብታ አድናቸዋለች፡፡ በዚህ የተነሣ ‹‹በትረ ማርያም›› እየተባሉ እንደሚጠሩ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ በዚህ መሠረት ጥቅምት ፳፯ ቀን ለአቡነ መብዓ ጽዮን ቃልኪዳን የገባበት ቀን በመሆኑ በየዓመቱ ጥቅምት ፳፯  ቀን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱ ጋር ይከበራል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

1 month ago
**አደራ አለብኝ!**ዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን …

አደራ አለብኝ!ዓለም አቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን ኅብረት ጉባኤ

የ2017 ዓ.ም 2ኛ ዙር ቨርቹዋል ጉባኤቀን፡ ጥቅምት  24/2017 ዓ.ም

ሰዓት፡ ምሽት 2፡00-3፡00

ሁሌም በየወሩ በግቢ ጉባኤያት ምሩቃን ዓለም አቀፍ ኅብረት የቴሌግራም ቻናል

https://t.me/gibigubayat_mirukan_hibret

1 month ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
1 month, 1 week ago
በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማእከል የኢንዲያና …

በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማእከል የኢንዲያና ግንኙነት ጣቢያ 5ተኛውን ሐዊረ ሕይወት አካሄደ::

የግንኙነት ጣቢያው ጽ/ቤት እንደገለጸው መነሻውን ከኢንዲያና ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በማድረግ ቺካጎ ወደሚገኘው የደብረ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሜ ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ. ም በኢንዲያና ዙሪያ የሚገኙ ከ185 በላይ ምእመናንን ያሳተፈ መንፈሳዊ ጉዞ አካሂዷል።

በዕለቱ ምክረ አበውና በርካታ መርሐ ግብራት መከናወናቸው የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም ክርስቲያናዊ ቤተሰብ ምን መምሰል እንዳለበት የሕይወት ልምድና ትምህርት ተሰጥቷል ተብሏል፡፡

በመርሐ ግብሩ የአሜሪካ ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባልና አቅም ማጎልበቻና የሰው ሀብት ዋና ክፍል ኀላፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ፍስሐ እሸቱ፣ የኢንዲያና ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም ቀሲስ ንጉሤ ገብሬ፣ ሰባኬ ወንጌል ብርሃኑ አድማስ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ኢንዲያና ግንኙነት ጣቢያ አባላት እንዲሁም ምእመናን ተገኝተዋል፡፡

1 month, 1 week ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
1 month, 1 week ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
1 month, 1 week ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
1 month, 2 weeks ago
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago