ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
`አንድ ድሃ ኬክ ሻጭ ወደ ታዋቂው ግሪካዊ ቢሊየነር ኦናሲስ (በቅፅል ስሙ የነዳጅ ታንከሮች ንጉስ) ወደሚባለው ባለሃብት ጋር ቀረበና ኬክ እንዲገዛው ጠየቀው። ኦናሲስ አንድ ሳንቲም አውጥቶ ሻጩን እንዲህ አለው። "ጎፈር ወይስ ሰው? ከተሸነፍኩ በኪሴ ውስጥ ያለውን ሁሉንም ገንዘብና አንድ የቼክ ፊርማ እሰጥሃለው። ከተሸነፍክ ደግሞ የተሸከምከውን ኬክህን በጠቅላላ ጠረጴዛው ላይ ታስቀምጣለህ።"
ሻጩም እንዲህ ሲል መለሰ፡- -ጌታዬ እኔ ድሃ ነኝ፤ ያለኝን ሁሉንም ኬክ ከሰጠው ዛሬ ቤተሰቤን መመገብ አልችልም።
ኦናሲስ ወደ ኋላ በመዞር ጀርባውን ለነጋዴው ሰጥቶ እንዲህ አለ፡-`ኬክ ሻጩ ተወልዷል ፥ ኬክ ሻጩ ይሞታል..
😎
በእድሜ የገፋች አንዲት አሮጊት ሴትዮ ገንዘብ ለማውጣት ወደ ባንክ ሄደችና የባንክ ቡኳን ለገንዘብ ያዡ እየሰጠች
10 ዶላር ማውጣት እፈልጋለሁ
`አለችው።
ካሸሪውም፡-
"ከ$100 በታች ገንዘብ ለማውጣት እባክዎን ኤቲኤም ይጠቀሙ።"
አሮጊቷም```ለምን?```
ካሸሪውም በቁጣ የባንክ ቡኩን መልሶ እየሰጣት "እነዚህ መመሪያዎች ናቸው፤ እባክዎን ከኋላ የሚጠብቁ ብዙ ደንበኞች አሉ! ሌላ ትዕዛዝ ከሌለ መንገድ ይልቀቁልኝ!"
️️አሮጊቷ ለጥቂት ሰኮንዶች ዝም ካለች በኋላ የባንክ ቡኩን ወደ ካሸሩ እየመለሰች፦```እባክህን አካውንቴ ውስጥ ያለውን ገንዘብ በሙሉ ማውጣት ብትረዳኝ!```
ካሸሪውም አሮጊቷ በአካውንቷ ያስቀመጠችውን ገንዘብ ሲመለከት በጣም በመገረም እንዲህ አላት፦"በአካውንቱ ውስጥ 500,000 ዶላር አለ እና ባንኩ በአሁኑ ጊዜ ያን ያህል መጠን የለውም ነገ ተመልሰው መምጣት ይችላሉ?"
ሴትየዋም በመቀጠል ምን ያህል ገንዘብ ወዲያውኑ ማውጣት እንደምትችል ጠየቀች ገንዘብ ተቀባዩ፦ "ማንኛውም መጠን ቢኖር የሚቻለው እስከ 30,000 ዶላር ብቻ ነው።"
አሮጊቷም ሴትዮ ይህንን ስትሰማ እንዲህ አለችው፦```ይሁን መልካም አሁን 30,000 ዶላር እንድወስድ ብትፈቀድልኝ?```
ካሸሪውም በንዴት ወደ ካዝናው ተመልሶ 20 እና 10 ዶላር ቁልል አውጥቶ አስር ደቂቃውን 30,000 ዶላር በመቁጠር አሳለፈ። ከዚያም ገንዘቡን እየሰጠ እንዲህ አላት፦"ተጨማሪ የማደርግላችሁ ነገር አለ?"
አሮጊቷም በእርጋታ ከተቀበለችው ገንዘብ 10 ዶላር መዝዛ ቦርሳዋ ውስጥ እያስገባች እንዲህ አለች፡-`አዎ ጌታዬ $20,990 ወደ አካውንቴ ማስገባት እፈልጋለሁ።
አስተምሮቱም፡- ከአረጋውያን እና ልምድን ከተካኑ ሰዎች ጋር እልህ አትጋባ ህይወታቸውን በመማር አሳልፈዋልና
😑
ታላላቆቻችን እንዲህ ይሉ ነበር
"በመንገድ ላይ ሳለህ ወደ ኋላ የማየት ፍላጎት ካለህ በቅድሚያ ሰዓትህን ቃኝ እየሄድክበት ያለው ጉዳይህ ጊዜ ሚሰጥህ ከሆነ ቁም ወደኋላም ዙረህ ያለፍከዉን ተመልከት
ነገር ግን ፊትለፊትህ ያለው ጉዳይ ሚበልጥብህ ከሆነ እና ሰዓትህ ዞረህ ኋላህን ለማየት ማይበቃህ ከሆነ አትዙር
አንተ ግን ሁለቱንም በ አንድ ላይ አስኬዳለው ብለህ ኋላህን እያየህ ወደፊት የተራመድክ እንደሆን እንቅፋት አግኝቶህ እንደምቶድቅ አትርሳ "
አባቶቻችን በ እግራችን ስለምንራመድበት መንገድ አይደለም ያወሩት
በርግጥ መሳካት አለመሳካቱ ላይ እርግጠኛ አደለሁም ግን እሞክራለሁ፤ ይከብዳል፣ይደክማል አውቃለሁ ግን እሞክራለሁ የልቤን ምኞት ለፈጣሪዬ ነግሬ በቃሉ በረታለሁ በቃ ከዛ የመጣው ይምጣ ባንዱ መንገድ ባይሄድልኝ ሌላ አላጣም፤ እጄን አጣጥፌ አልተክዝም።
ስሞክር ይረዳኝም አይደል🤲🏼
ማንም ሰዉ እኛ የፃፍነውን
ሊያነብ ይችላል ...
ግን ማንም እኛ የሚሰማንን
ሊሰማዉ አይችልም ።
ተሳሳትኩ?
`ንጉሡ ለባለሟሎቹ ከተማው መሀል ላይ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ አዘዛቸው። ባለሟሎቹም በታዘዙት መሠረት ከተማው መሀል ትልቅ ጉድጓድ ቆፈሩ።
ንጉሱም የተቆፈረውን ጉድጓድ ካየ በኀሏ ማታ ላይ የከተማው ሰው ሁሉ አንድ ብርጭቆ ወተት አምጥቶ ጉድጓዱን እንዲሞላ አዘዘ። አንድ ሰው ግን አንድ እኩይ ሀሳብን አሰበ።ወደ ጉድጓዱ በወተት ፋንታ ውሀ መውሰድ። ሁሉም ወተት ስለሚወስድ የኔ ውሀ መውሰድ አይታወቅም በዛ ላይ ምሽት ስለሆነ ማንም አያየኝም ብሎ አንድ ብርጭቆ ውሀ ጉድጓዱ ውስጥ ጨመረ።
በማግስቱ ንጉሱ በወተት የተሞላውን ጉድጓድ ለማየት ሲሄድ ባየው ነገር ተደናገጠ። ጉድጓዱ በወተት ሳይሆን በውሀ ነበር የተሞላው። ልክ በወተት ፋንታ ውሀ እንደወሰደው ሰው የከተማው ሰው ሁሉ "ሌላው ወተት ስለሚያመጣ እኔ ውሀ ብወስድ የሚያውቅ የለም"ብሎ ወተት ሳይሆን ውሀ ነበር የወሰደው።`
[ የህይወት መርሆዎች በተለያዩ ፈላስፎች አንደበት ]
*1. የበለጠ ለማወቅ ጣር (Platonism)
መልካም ሰው ሁን (Aristotelianism)
ራስህን ቻል (cynicism)
ዛሬ ተደሰት ነገ ለራሱ ይጨነቅ (hedonism)
ራስህን ከስቃይ አግልል (epicureanism)
ምክንያታዊ ሁን መቀየር ማትችለው ነገር አያስጨንቅህ (stoicism)
የግለሰብ ነጻነትን አክብር (classical liberalism)
ሌሎች እንዲያደርጉልህ ምትፍለገውን ነገር ለሌሎች አድርግ (kantianism)
የምትፍለገውን ነገር አድርግ ምክንያቱም ህይወት ትርጉም የለውም (nihilism)
ሃሳብህ ላይ ሳይሆን ተግባርህ ላይ ትኩረት አድርግ (pragmatism)
የፈጣሪህን አላማ ኑር (Theism)
ያንተ ውስኔ ያንተን ህይወት ይመራል (Existentialism)
13.የህይወት ትርጉም ምንድነው እያልክ
አትፈላሰፍ፣ ዝም ብለህ ኑር (Absurdism)
ለሰው መድሃኒቱ ሰው ነው (humanism)
ህይወት ትርጉም የለውም አነተ ትርጉም ካልሰጠኸው logical (positivism)
ሰዎችን ሁሉ እኩል ውደድ (Mohsim)
ከቅንጦት የጸዳ ተራ ህይወት የበለጠ ትርጉም አለው (Confucianism)*
- የቱን ህግ ወደዳችሁት?
መናገር ፈልጋችሁ ግን ቃል አጥሯቹ አያውቅም? .... ማለት የፈለጋችሁት ሌላ ሆኖ ግን ተቃራኒ response ሲደርሳችሁ ያለው feeling ughh..... አንደሰማን ሳናመዛዝን ግን ባናወራ ምን አለበት ቆም ብለን ብናስብ... ምነው? ለምን? ብለን በእርጋታ ብናጤን ምን ይጎልብናል..... ሁሉም ያማረውም process ላይ ያለውም ሚፈርሰው እኮ በዚ ባህሪያችን ነው...... ለመፍረድ በመቸኮል.... በመሰለን ተርጉመን በመረዳታችን..... ጊዜ ሰተን ለማዳመጥ ባለመሞከራችን ብዙ ብዙ...
`ጅል የሚነቃው ሲዘንብ ነው። ያኔ ይበሰብሳል እንጂ መጠለያ አያገኝም። የሚወዱን ሰዎች በፍቅር እንደ ዣንጥላ ከበላያችን የሚዘረጉበት ዘመን አለ፤ ከብቸኝነት ዶፍ ከመልከስከስ ንዳድም ጠባቂዎቻችን የሚሆኑበት። ሁል ጊዜ ግን እንደዚያ አይቀጥልም፣ አንድ ቀን ግፋችን ከብዷቸው ቸልተኝነታችን አድክሟቸው እንደ ዣንጥላ ይታጠፋሉ።
ወይም አያያዛችንን አይቶ ጠንካራ ንፋስ ከእጃችን ይነጥቃቸዋል። ዶፍ ውስጥ ካለመጠለያ የመቆሚያ ዘመን አለ። ጅል ግን ይኼን ቀድሞ አይረዳም። ጅል ከጅልነቱ ይፈወስ ዘንድ፤ በመከራ መጠመቅ አለበት። በመከራ ያልተፈወሰ ጅል፤ ሞት ብቻ ነው የሚገላግለው።
አሌክስ አብርሃም
አልተዘዋወረችም
ገፅ 29`
እርጋታ ዝምታ አይደለም። የቱጋ ዝም ማለት እንዳለብን ማወቅ ነው። የሁሉም መልስ ያለው ሁሉንም ጥያቄ ጠይቆ የጨረሰ ነው። የቱን መምረጥ እንዳለበት የሚያውቅ፤ ችላ ባለው ትርምስ ውስጥ እርጋታ የልቦናው በር ይጎበኘዋል። ጠቢብ ግን ባንቀላፉት መኃል መንቃትን ፥ ከብዙ ሰው ጫጫታ ዝምታን ይሰርቃል
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana