ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
🎯ከዚህ አመት ጀምሮ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል የፈተና ምዝገባ የሚደረገው በዲጅታል መሆኑ ተገለፀ።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከቀጣይ አመት ጀምሮ የፈተና ምዝገባ የማደርገው በዲጅታል ነው ብሏል።አገልግሎቱ በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር በጋራ በሰጠው መግለጫ ነው ይሄን ያስታወቀው።በየአመቱ በሃገር አቀፍ እና የክልል አቀፍ የፈተና ምዝገባዎች ሲደረጉ አገልግሎቱ በርካታ ሚሊየን ብር እንደሚያወጣ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ተናግረዋል።
አሁን የፈተና አገልግሎቱ የፈተና ምዝግባዎችን በዲጅታል እንዲደረጉ የሚያደርግ በመሆኑ ይሄን ወጪ እንደሚያስቀር አንስተዋል።ይህንንም ማሳካት እንዲቻል በተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ለዚህም ከ32 ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞች ተመልምለው ወደ ተለያዩ አከባቢዎች ተደልድለዋል ብለዋል።ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመን በ2015 ዓ.ም የሙከራ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ በሙሉ ኃይል ወደ አገልግሎት መግባቱን ገልጿል።
📚 Mathematics different universities worksheet 📝
👨💼 ስለ Grade እና Grade አሰራር ትንሽ ነገር እንበላችሁ።
A+ =90-100👉4
A =85-89 👉4
A- =80-84 👉3.75
B+ =75-79 👉3.5
B =70-74 👉3
B- =65-69 👉2.75
C+ =60-64 👉2.5
C =50-59 👉2
C- =45-49 👉1.75
D =40-44 👉1
Fx =35-39 👉Final Exam ድጋሜ መፈተን ይቻላል። ግን ተመልሶ Fx ከሆነ Fxሱ ወደ F ይለወጣል።
F 👉 0-35 🫴 በሚመጣው ዓመት (Nex Year) Courseን ድጋሜ እንደ አዲስ ይወሰዳል።
📌 የ grade አሰራር
🟢ሁሉም Grade በ Credit Hour ተባዝቶ ከዛ አንድ ላይ ተደምሮ በሴሚስተሩ ተማሪዉ በወሰደዉ Credit Hour ይካፈላል።
Example🔺
"A" ቢሆን Gradeዱ እና የCourseሱ Credit Hour 5 ቢሆን:-
4×5=20
If The other course Grade is "A-" and the Credit Hour is 5
3.75×5=18.75
If The third course Grade is "B" and the Credit Hour is 3
3×3=9
So the Grade of this student will be
20+18.75+9=47.75
5+5+3=13 (Credit Hour)
47.75÷13=3.67 or (B+)
ስለዚህ ይሄ ተማሪ በሴሚስተር 3.67 አመጣ ይባላል።
ይቀላቀሉን 👇👇
በሚቀጥለው ዓመት 10 ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች የራስ ገዝ አስተዳደር ማዕቀፉን እንዲቀላቀሉ እቅድ ተይዟል
በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሠረተ ልማት ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ሥርዓት በከፍተኛ ደረጃ እየሰፋ መምጣቱን ጠቅሰው ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ተቋማቱ ከ2 ዩኒቨርሲቲዎች ወደ 51 የመንግስት እና 315 የግል ተቋማት ማደጋቸውን እንዲሁም የተማሪዎች ምዝገባ ወደ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን ገልጸዋል።
ነገር ግን የትምህርት ጥራት ማሽቆልቆሉን አምነው፣ ተቋማቱ ብቁ ተመራቂዎችን ለመፍጠር፣ችግር ፈቺ የሆኑ ተግባራዊ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ጥናትና ምርምሮችን ለማድረግ እንዲሁም ውጤታማ አስተዳደርን ለማስፈን እየሰሩ ነው ብለዋል።
አክለውም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ በ2011 ዓ.ም የወጣው የትምህርት ፍኖተ ካርታ የዩኒቨርሲቲዎች ራስን በራስ ማስተዳደርን እንደ ቁልፍ ማሻሻያ ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 1294 መሠረት የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ በመሆን የሁለት ዓመት ሽግግር ያደርጋል ተብሏል።
በሚቀጥለው ዓመትም 10 ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች የራስ ገዝ አስተዳደር ማዕቀፉን እንዲቀላቀሉ እቅድ መያዙን አመልክተዋል። እነዚህ ማሻሻያዎች ከፍተኛ መዋቅራዊ ለውጦችን እና በባለድርሻ አካላት መካከል የትብብር ጥረቶችን ይጠይቃሉ ብለዋል። ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ይህን የገለጹት የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ዘጠኝ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ራስ ገዝ ለማድረግ የሚያስችል የግማሽ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ባደረገበት ወቅት ነው።
በ2017 ዓ.ም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡
(አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምትመዘገቡበት ካምፓስ እና ከተማ ከላይ ተያይዟል።)
በ2017 የትምህርት ዘመን በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የአቅም ማሻሻያ መርሐ-ግብር (Remedial Program) ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ህዳር 12 እና 13/2017 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ!
ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፤ ከ9-12ኛ ትራንስክሪፕት፤ የ8ኛ ክፍል ስርተፊኬት ዋናውን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር እንዲሁም 3x4 የሆነ 4 ጉርድ ፎቶ በመያዝ እንድትገኙ እናሳውቃለን።
የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ አሟልታችሁ እንድትገኙ ዩኒቨርሲቲው ያስታውቃል።
በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ስትከታተሉ የቆያችሁ ተማሪዎች በነበራችሁበት ካምፓስ ብቻ የምትስተናገዱ ይሆናል፡፡
ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡
በ2017 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በ2017 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 9 እና 10/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንሰክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- ስድስት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ
በ2017 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago