ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ሰሞኑ በሶሎዳ ሚድያ ያየሁት የአቶ መሐመድ ሲራጅና የምስጉን አብርሃ ታሪክ የሚከተሉትን እውነቶች አስታወሰኝ።
ኤድዋርድ ኦለንዶርፍ (Edward Ullendorff) የተባለ የታሪክ አጥኚ ስለ ኢትዮጵያውያን ሲመሰክር:-
"ኢትዮጵያን ... ኩሩዎች ናቸው፤ ነገር ግን ትሑታንም ናቸው። በእነርሱ ዘንድ መልካም ሰብእና በእጅጉ ይደነቃል። በዚህም ላይ የተዋጣላቸው ነገር አዋቂዎችም ተጠራጣሪዎችም፤ ሰጥቶ ለመቀበል ያይደለ እውነተኛ ለጋሦችም ናቸው። የፍትሕ ወዳጆች፤ በነገር ተምዋግቶ መርታት ወይም መረታትን የሚመርጡ ሀቀኞች ናቸው። . . . ጨዋታ አዋቂነታቸውን ያጣጣሙት እንደሚናገሩት ድንቅ ነው።" ብሎ እንደ ነበር መምህር ግርማ ባቱ ያስታውሱናል (የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ከጥንት እስከ 6ኛ ክፍለ ዘመን ገፅ 116)።
የ'የሐበሻ ጀብዱ' ጸሓፊ ደግሞ በአምባላጌ አንድ በዐፄ ሚኒልክ ዘመን ከራስ መኮንን ጋር ዘምተው የነበሩ አዛውንት ያጫወቱትን እንዲህ ተርኮታል
"አምባላጌን ከዛሬ 40 ዓመት በፊት ይዟት የነበረውን የጣሊያን ሻለቃ ቶለሲን ራስ መኮንን እንዲህ ብለውት ነበር።
"ውድ ወዳጄ ሻለቃ ቶለሲ: ጀግንነትህና ቆራጥነትህ አውቃለሁና አከብርሃለሁ ። አደንቅሃለሁ። ይሁን እንጂ በዚህ ጦርነት ትሸነፋለህ። ስለዚህ አምባላጌን ለቀህ ወደ መቀሌ ሽሽ። . . . ወዳጄ ቶለሲ ያለህን ጦር አውቃለሁ። እኔ አስር እጥፍ ጦር አለኝ። እና ኋላ በወታዶሮቼ ብትገደል ልቤ ያዝናልና እባክህ አምባላጌን ለቅቀህ ውጣ" ብለው መልእክት ቢሉኩበትም ሻለቃ ቶለሲ "ከአለቆቼ ተጨማሪ ትዕዛዝ ካላገኘሁ አምባላጌን መልቀቅ አልችልም" ብሎ የራስ መኮንን ልመና ባለመቀበሉ ራስ መኮንን ለሻለቃ ቶለሲ ለሁለተኛ ጊዜ መልእክት ሲልኩ እንዲህ ብለው ነበር " ነገ ማለዳ ጦሬ ይዘምትብሃል። አሁንም ደግሜ ልንገርህ ጦርህን ይዘህ ሂድ። ልቤን አታሳዝነው።"
ሻለቃ ቶለሲ በድጋሚ የራስ መኮንን ደግነት ባለመቀበሉ የራስ መኮንን ጦር የሻለቃ ቶለሲን ጦር ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር አጨደው።"
በኋላ ራስ መኮንን የሻለቃ ቶለሲን ሬሳ አስፈልገው ወታደሮቻቸውን ለአንድ ጀግና በሚገባ ክብር እንዲቀብሩት አዘው ዓይናቸው ያዘለውን እንባ ለመዋጥ ሲጥሩ ታይተዋል።" ይላል። (አዶልፍ ፓርለሳክ፣ የጀበሻ ጀብዱ፣ ገጽ 111- 112 - ትርጉም ተጫነ ጆብሬ)
የኢትዮጵያዊነት መልኩ ይህ ነው።
ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ናቸው። የጅግኖች ስለሆኑ ርሕሩሆች ናቸው። አይደለም በብዙ ነገር የተዛመዱ ለማለያየት ምክንያት የማይገኝላቸው አቶ መሐመድ ሲራጅና ምስጉን አብርሃ አሸንፎ ክብራቸውን ዝቅ ለማድረግ በርስታቸው ባርያ ለማድረግ የመጣው ቶለሲንን እንኳ ይራሩለታል።
ኢትዮጵያዊያን ጀግንነታቸውና ርሕራሔያቸው የተገናዘቡ ናቸው። የመሐመድ ጀግነንትማ እዩልኝ። ምስጉንን በመደበቁ ስጋት አለባት - በወቅቱ አጠራር አሸባሪ ደብቋልና። በነበረው መዘጋጋት የምግብ እጥረት ስጋት አለበት። በዚህ ሁሉ መኻል ሚስቱ መንታ በመውለዷ የቀለብ ጥያቄው ከባድ አድርጎበታል። ይህ ሁሉ ግን ርሕራሔውን ማሸነፍ አልቻለም።
ኢትዮጵያዊያን ለሚዋጋቸው ጀግኖች ናቸው ተዋግቷቸው ለቆሰለ ደግሞ ርሕሩሆች። ወቅቱንማ አስቡት! መሐመድ በየቀኑ "TDF ከመጡ ያጠፏቹሃል" ይባላል። ምስጉን "አማራ ከያዘህ በአሰቃቂ ሁኔታ ይገድልሃል" ተብሏል። በዚህ መሃል እንደፖለቲከኞቹ የጥፋት መዝገበ ቃል መሐመድ "አጥፊህ" የተባለውን ይንከባከባል፤ ምስጉን በገዳዩ ቤት ተረጋግቶ ተኝቷል።
ኢትዮጵያውያን የመከባበርና የልግስና ምልክቶች ናቸው። መሐመድና ምስጉን አሁን ጥል ላይ ናቸው። መሐመድ "ምስጉን ካልታከመ ሞቸ እገኛለሁ" ሲል ምስጉን ደግሞ "ሳይኖረው እንድኖር ያደረገኝን ብቻ አግዙልኝ" ይላል - አስታራቂ ይሻሉ - ሁለቱም ምልክቶቻችን ሆነዋልና።
አዎ ኢትዮጵያውያን ኩሩዎች ናቸው። ራስ መኮንን አስቧቸው የጣልያኑን ሻለቃ እንዲህ ያሉትን
"ውድ ወዳጄ ሻለቃ ቶለሲ: ጀግንነትህና ቆራጥነትህ አውቃለሁና አከብርሃለሁ ። አደንቅሃለሁ። ይሁን እንጂ በዚህ ጦርነት ትሸነፋለህ።" ያስደንቃል! እንዲህ ሲሉ እኮ ነው።
✅ በተልእኮህ ጠላቴ ሆነው ብትሰለፍም፣ አንተ ሀገሬንና ህዝቤን ለመግዛት ተልከህ ብትመጣም በሰውነትህስ ወዳጄ ነህ - ሰውነት
✅ አንተ በአገርህ ጀግና ብትሆን ነው "ሻለቃ" ተብለህ የመጣሃው። ይህ አከብራለሁ። ግን ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነኝና አሸንፍሃለሁ - ልበ ሙሉነት።
መሐመድ ሲራጅና ምስጉን አብርሃ የእነ ራስ መኮንን ምልክቶች ናቸው። የታመመው ፖለቲካ ዘለሉት፤ የአክቲቪስቱና የካድሬው ጥላቻ አወረዱት፤ የቋንቋና ድንበር አጠፉት፤ የሃይማኖቶች ማሕበራዊ ሚና ቀና አደረጉት።
ፖለቲከኞች የፈጠሩት የትርክት እንጂ መሬት የወረደ የህዝብ ጥል የለም። የፖለቲከኞች የጥላቻ ስካር (በኢትዮጵያ ጠላቶች የተቀዳላቸው የጥላቻ መጠጥ) ህዝቡ ዘንድ እንዲጋባ ወደ ህዝቡ ቢያገሱም በእነ መሐመድ ሲራጅና ምስጉን አብርሃ "ነውራችሁ ወድያ" ይባላሉ።
ፖለቲከኞች ሊያፍኑት ቢሞክሩም መሐመድ ሲራጅ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ታገኙታለችሁ። ትግራይ፣ ኦሮሞ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ሲዳማ፣ ቤንሻንጉል፣ ጉምዝ፣ አደሬ፣ ሃረሬ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ሺናሻ፣ አርጎባ፣ . . . አለ። ጥቂት ክፉ ጯኺዎች በጩኸት አየሩን በከሉት እንጂ እጅግ ብዙ ደጋጎች በሁሉም አለን።
እናም
ምስጉን አብርሃ ይታከም፤
መሐመድ ሲራጅ ይሸለም!
መልካም ዜና የምንሰማበት ጊዜ ያቅርብልን።
ሞትን በሞት መግደል በቀራንዮ አይተናል፤
በሞት ሞትን መውለድ ዘመኔን ወርሶታል😭
#እትጉዓዘሉ_መንገዲ_ናብ_ዝሓሰብካዮ_ዘየብፅሕ እንተኮይኑ "#ካብ_ጀመርክዎ" ኣይትብልን።
መምህር /መጋቤ ሐዲስ/ አምሃ ማርቆስ ሐዚ 'አቡነ ናትናኤል' ንህዝቢ ትግራይ ይኹን ንካሊእ ከባቢ ብወንጌል ብስፍሓትን ብትግሃትን ከገልግሉ በዚ ድማ ብዙሓት ነፍሳት ኣብ ሃይማኖት ክጸንዑ፣ ኣብ ክሕደት ዘለዉ ናብ ርትዕት ሃይማኖት ከምልሱ ብዙሕ ተስፋ ካብ ዝገበርኩሎም ብትሕትናን ትግሃትን ዝግለፁ መምህራን ሓደ እዮም።
ፍልጠቶም ሰፊሕ እዩ። እዚ ክብል ከለኹ ፍልጠቶም ክልክዕ ዘኽእል ሙያ ስለዘለኒ ኣይኮነን። ኣብ ዝኣተውሉ ኩሉ ግና ኩሉ ዝምስክረሎም ኣገልግሎቶም ግዘፍ ረኺቡ ዝምስክሮ ጉዳይ እዩ። ሐዚ'ውን ትግሃቶምን ጭንቀቶምን ከም ዘሎ ይመስለኒ።
እንተኾነ ግን ህዝቢ ከድሕኑ ዝሓሰብሉ መንገዲ ግጉይ ብምዃኑ ከርክብሉ ኣይከኣሉን። መንገዲ እንተስሒትካ ኣብ ዕንክሊል ኢኻ ትኣቱ። ብዝተጋገየ መንገዲ ኣብ ዝሓሰብካዮ ኣይትበፅሕን።
እንተኾነ ግን መፃምዲ ኣይመረፁን። መፃምዶም መንገዶም ናብ ሰሜን እዩ - ምብራቕ ኣይፈልጥዋን። እናተጓተቱ እዮም ክነብሩ።
እንተኾነ ግን ሃፂፆም ። ስለዝሃፀፁ ኣብ ዘይቦታኦም ተረኺቦም። ኣብ ዘይቦታኦም ስለዝተረኸቡ ቦታኦም ክሳብ ዝረኽቡ ብዙሕ ክደኽሙ እዮም።
እንተኾነ ግን መሳርሒ ሴረኛታትን ጥቕመኛታትን ኮይኖም (ንሶም ጥቕመኛ ኮይኖም ንጥቕሚ ከም ዘይኣተዩ እየ ተስፋ ዝገብር)።
'ሊቀ ጳጳስ' ኮይኖም ብፕሮቶኮል ካብ ክእሰሩ እቲ ብዙሕ ዘትርፍሉ ሰባኺ ወንጌል ኮይኖም (ንሶም'ውን ይሐሸኒ ነይሩ ከም ዝበልዎ) ብዘይ ገደብ ተጓይዮም ህዝቦም ተዘምህሩ ክንደይ ጥዑም ነይሩ፤ ክንደይ ህዝቢኸ መድሐኑ ነይሮም፤ ክንደይ ህዝቢኸ መራኸቡ ነይሮም።
ሓዘንኩም ሓዘን ብዙሓት እዩ፤ ብኽያትኩም ብኽያት ብዙሓት እዩ፤ ፀገምኩም ፀገም ብዙሓት እዩ፤ ድሌትኩም ድሌት ብዙሓት እዩ። መንገዱ ግና እዚ ዝሓዝክሞን እትኽተልዎን ኣይመስለንን።
እትጉዓዘሉ መንገዲ ናብ ዝሓሰብካዮ ዘየብፅሕ እንተኮይኑ "ካብ ጀመርክዎ" ኣይትብልን፣ ካሊእን ትኽክለኛን መንገዲ ክትኽተል ግድን እዩ።
"እዛም ቤት እሳት አለ።" ያለው ማን ነበር?
ሐዚ ኣብ ትግራይ ዘሎ ካብ መናእሰያት ሓሊፉ ኣብ ኣዴታትን ኣቦታትን ዝበፅሐ ብናይ ሓሶት ትምህርቲ ናብ ኣዳራሽ ምውሓዝ ዋላኳ ዝተፀበናዮን ብዙሕ ዝበልናሉን እንተኾነ ሽፋኑን ፍጥነቱን ግና መሰከፊን ከቢድን እዩ።
ሐዘንና ከቢድ ዝገብሮ ድማ ነዚ ንምምካት ዝግበር ምንም ዓይነት ሥራሕ የለን ጥራሕ ዘይኮነስ እቲ ምንቅስቓስ ድጋፍ ዝረኽበሉ መንገዲ እዩ።
ሐዚ'ውን ንርእስና ንሕተት:-
✅ ብዙሕ ሰብ ኣብ ዝርከበሎም (ብፍላይ ወለዲ) ዓውደ ምሕረታት (ኣብ በዓለ ንግሢታት) ዝወሃብ ትምህርት ኣሎዶ? ብመን ይወሃብ (ናይዚ ዘመን ኩነታት ብዝተረድአን ነዚ ዘመን ብዝምጥን ጉዳይንዶ ይወሃብ?
✅ ንአብያተ ትምህርቲ ሰንበት፣ ንካህናት፣ ንመንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ወዘተ ዝወሃቡ ሥልጠናታት ብመን ይወሃቡ? ኣብ እንታይከ የድህቡ?
✅ ብዙሓት አብያተ ትምህርቲ ሰንበት ዘዳልውዎም ጉባኤታት ስልታዊ ድዮም ዋላስ መፈፀሚ ዓመታዊ ትልሚ?
✅ ብዙሓት አብያተ ትምህርቲ ሰንበትከ ብመን ይምራሑ ኣለዉ?
✅ ኣብ ስራሕ ፈፃሚ "መንበረ ሰላም" ነዚ ዝድግፉ መናፍቃን ንምንታይ በዚሖምን?
✅ ደፊሮም ነዚ ኩነታት ዘሙግቱ ኣካላት ንምንታይ ብዙሕ ምንግልታዕ፣ ካብ ስራሕ ምቕናስ፣ ማሕበራዊ ምግላል ይበፅሖም ኣሎ?
እልካ ምሕታትን ነዚ ንምምላስ ብስፍሓት ምስራሕ እምበር ኣብ '#ቤተ_አምልኮ'ን '#ኣመንት'ን ጥቕዓት ምብፃሕ #ርሑቕ_ኣየኺድን። ክሳብ መዓዝከ ብዙሕ ግዜ ብዝዓንቀፈና እምኒ እናተቐጥቀጥና ንነብር?
============
#ጴጥሮስ_ወጳውሎስ
=============
ቤተክርስቲያናችን የነዚህን ቅዱሳን ሐዋርያት የሰማዕትነታቸው መታሰብያ በዓል ሐምሌ 5 በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፡፡
እነዚህ እንደ ደመና የከበቡን ምስክሮች በዓላቸውን ስናከብር ምስክርነታችው ምንድን ነው? ብሎ ማሰብ የተገባ ነው።
==============
ቅዱስ ጴጥሮስ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጀመርያ ከጠራቸው ደቀ መዛሙርት አንዱና ቀዳሚው ነው። ቅዱስ ጳውሎስ በአንጻሩ ከ 12ቱ ሐዋርያት መካከል ያልነበረ፥ ክርስቶስ ከትንሣኤ በኋላ የጠራው ነው። እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት ክርስቶስን በመዋዕለ ሥጋዌው የተከተለውና በቃሉ የተማረ አይደለም፡፡ ምንም እንኳ ዘግይቶ የተጠራ ቢሆንም ከሁልም ይልቅ በብዙ የደከመ (ብዙ የሠራ) ነው። 1ኛ ቆሮ 15፡10)
#ሰው በመጠራት ቀዳሚ ላይሆን ይችላል። ነገር ግን እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ከተጋ ከሁሉም ይበልጥ ጠንካራና በብዙ የሚያተርፍ ይሆናል
--------------------------
ቅዱስ ጴጥሮስ በቅዱስ ጋብቻ ተወስኖ የኖረ ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ በድንግልና ጸንቶ የኖረ ነው፡፡ ማቴ 8፡ 14፥ 1ኛ ቆሮ 9፡5፥ 1ኛ ቆሮ 7፡1-2
#ሰው በድንግልናም ኖረ በቅዱስ ጋብቻ ሁሉም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ በጋብቻ በቅድስና መኖር ይቻላል እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ፥ ሳያገቡም በቅድስና መኖር ይቻላል እንደ ቅዱስ ጳውሎስ።
--------------------
ቅዱስ ጴጥሮስ ያልተማረና ዓሣ አጥማጅ (ማቴ 4፡18፥ ግሐ 4፡13) ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ በገማልያል እግር ሠር በጤርሰስ ዩኒቨርሲቲ የተማረ ባህሉን በመጠባቅ የተመሰከረለት (የታወቀ) ነው፡፡ ግሐ 26፡24
#እግዚአብሔር ሁሉንም ይጠራል - ቢማርም ባይማርም
-----------------------
ቅዱስ ጴጥሮስ አገልግሎት የጀመረው በእርጅና ዘመኑ ነው፡፡ 1ኛ ጴጥ 5፡13 ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ በጉልምስናው የተጠራ ሐዋርያ ነው፡፡
#እግዚአብሔር ሰው ሲጠራ አይዘገይም
--------------------------
ቅዱስ ጴጥሮስ በባሕርይው ችኩል ነበር፡፡ ማቴ 16፡23፥ ማቴ 26፡51፥ ዮሐ 13፡ 8-10 ክርስቶስ ችኩሉን ቅዱስ ጴጥሮን ለሊቀ ሐዋርያነት፥ አሳዳጅ የነበረው ቅዱስ ጳውሎስን ወደ የአሕዛብ ሐዋርያነት አበቃቸው፡፡
#ክርስቶስ የቀደመ ስማችን ይቀይራል፡፡ ስምዖንን ጰጥሮስ፥ ሳውልን ጳውሎስ እንዳለ፡፡
ካሐዋርያቱ ከቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ በረከት ያድለን፡፡
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን።
የትንሣኤው ብርሃን ኃይለ መቃብርን ድል እንደነሳልን የድህነት፣ የድንቁርና፣ የዘረኝነት፣ የቂመኝነት፣ የትዕብት፣ የስስት፣ የአፍቅሮ ነዋይ . . . በአጠቃላይ የክፋት መቃብርን ድል እንነሣ ዘንድ ይርዳን።
?አይሁዳውያን ከስሑታን ሁሉ ስሑታን የሚያደርጋቸው ከቀደመ ስሕተታቸው የሚማሩ ባለመሆናቸው ነው (እንደ አማኞች)። ከጥንት ጀምሮ በብዙ ተአምርና ድንቅ ሥራ የሚጠብቃቸውና የሚመግባቸውን ፈጣሪያቸውን እየረሱ በብዙ ወድቀዋል። አሁንም ይህን ሲያደርጉ እናያለን - ታሪካቸው ሳያስተምራቸው 'እውቀታቸው' ሲያጠፋቸው (አወቅን ብለው ሀገር እንደሚያጠፉት 'ባለነጠላ ደግሪ' የሀገሬ ምሁራንና ዘረኛ ፖለቲከኞች)።
?ክርስቶስ ሞትን ድል ነስቶ እንደሚነሳ ደጋግሞ ስለነገራቸው (ስላመኑም ጭምር) መቃብሩን ለማስጠበቅ ተነሳሱ። ቁንጹል እውቀታቸው ወደ ሌላ ስሕተት መራቸው። ራሳቸውም እንዳሉት የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ሆነች (ማቴ 27፡64)። እንደሚነሳ አምነው በጥበቃ ሊያስቀሩት እንደ ማይችሉ ማመን ተስኗቸው ጠባቆች (ጠባቂዎች) ቀጠሩ።
?እናንት አይሁድ እርሱ ሰው የተባለ በኃጢአተኞች እጅ ተላልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሳ ግድ እንደሆነ ያስተማረውን አልሰማችሁም? ሉቃ 24፡ 6-7 ጠባቂ ከመቅጠር ይልቅ ውጡና ወደ ገሊላ ሂዱ በዝያም ታገኙታላችሁ። ማቴ 28፡10
?እውነትን ቀብራችሁ በሐሰተኞች ለማስጠበቅ አትታትሩ - አይቻላችሁምና። እናንት ተቀበረች ብላችሁ እንዳትወጣ ስትጠብቁ እውነት ደግሞ ለወዳጆቿ በከፍታ ትገለጣለች።
?ሐሰተኞች እውነትን በሐሰት ዶሴ አትሸፍኗት - በአደባባይ በከፍታ ስትገለጥ ታስጨንቃችኋለች።
❤አቤቱ ጌታ ሆይ ከውድቀታችን መነሳትን እንነሳ ዘንድ የትንሣኤ ልቡና አድለን❤
22/08/2014
#ስምዖንን_ባረገኝ ➕ ዐበጥዎ ለስምዖን ከመይፁር መስቀሎ➕
✍️ክርስቶስ መስቀል ተሸክም ስለኔ መከራ ሲቀበል ተገርሜ ከማለፍ ፣ ኮንፈሬን ከመምጠጥ ከዚህም አልፎ ከመዘባበት ክርስቶስን አሳርፈው ዘንድ መስቀሉን ለመሸከም በተገደድኩ። ማቴ 27:32፣ 27:39
✍️ሰዎች ያለማመዱኝን (የግድም የሚሉኝ) የዘረኝነት ቀንበር አውልቄ ስለ ዓለም በመስቀል የሚንገላታውን የክርስቶስን መስቀል እሸከም ዘንድ ማን ግድ ባለኝ?
✍️ክርስቶስ በመስቀል ሲንገላታ እንዳላየ ሆኘ ለግል ጉዳዬ አልፈው እንዳልሄድ መስቀሉን እንድሸከም የግድ ይጫንብኝ ዘንድ ስምዖንን ባረገኝ።ሊቃ 23:26
ሚያዝያ 14/2014 ዓ.ም
ረቡዕ የተመከረው ሐሙስ ላይ ንጹሕ የሆነውን፣ ምንም በደል የሌለበትን እንደ ወንጀለኛ በወታደሮች ለመያዝ ነው። ሐሙስ ብዙዎች ይበተናሉ። ዓርብ ጽኑዕ መከራ አለ። ትንሣኤው እሁድ ነው። እስከ ትንሣኤ ክፉ መካሪውና መከራው ብዙ ነው።፡የጸናው መከራው ሁሉ እያለፈ ለትንሣኤ ይበቃል።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana