ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 6 days ago
Last updated 2 weeks, 1 day ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago
Day 13
ከኃጢአትህ ብትናዘዝ እግዚአብሔር ከአመፃ ሁሉ ያድንሀል:: ምክንያቱም ክርስቶስ ኢየሱስ አስቀድሞ ለአንተ ቅጣት ስለከፈለው ነው። እግዚአብሔር ሀጢአትህን፣ ጥፋትህን፣ አስወግዶ ከራሱ ጋር ሊያስታርቅህ፣ ከፈቃዱ ጋር ሊያስማማህ ፣ ደግሞም ከአመፃ ሊያድንህ የምህረት ደጁን ከፍቶ ይጠራሀል:: ዛሬ የኃጢአትን እና የአመፃን እድል ንቀህ ነፃ ወደሚያወጣህ አባት መምጣት ትፈቅዳለህ? ልንረዳህ በዚህ አለን::
1 ዮሐንስ 1:9፤ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት | ዩትዩብ|ፌስቡክ | ቴሌግራም | ኢንስታግራም |ሊንክድኢን | ትዊተር | ፓይንተረስት | ዋትስአፕ | ቲክቶክ
Day 7
አንድ የጠፋብህ ውድ እቃ ላንተ እጅግ ዋጋ እንዳለው ሁሉ የጠፋ ሰው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ትልቅ ዋጋ አለው። ምክንያቱም የሰው ባበቤቱ እርሱ እግዚአብሔር ነውና። ዛሬም የአንተ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር አንተን ሊፈልግህ መጥቷል:: ደግሞም ይህ ደግ እግዚአብሔር አንተ ወደ እርሱ እስክትመጣ ድረስ እንኳን አልጠበቀም። የጠፋኸውን አንተን፣ ከእግዚአብሔር የራቅከውን አንተን፤ ፈልጎ በልጁ ሊያገኝህ መጥቶ ድነትን አዘጋጅቶልህ። ከራሱ ጋር በማስታረቅ የዘላለም ህይወትን አቅርቦልሀል:: ከመቅበዝበዝ ህይወት ተርፈህ ወደሚፈልግህ አባት ልትመጣ ትወዳለህ? ዛሬ ቀኑ ነው::
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት | ዩትዩብ|ፌስቡክ | ቴሌግራም | ኢንስታግራም |ሊንክድኢን | ትዊተር | ፓይንተረስት | ዋትስአፕ | ቲክቶክ
Day 6
ይህ የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅ ጥሪ እውነተኛ እረፍት እና እፎይታ የሚገኝበት ነው። በአካል፣ በስሜት ፣ በሀጢያት ወይም በመንፈሳዊ ህይወትህ ደክመሀል? ኢየሱስ እኔ ዕረፍት እሰጥሃለሁ ይልሀል:: እርሱ የሚሰጥህ እረፍት: ከጥፋተኝነትና ከበድለኝነት ነፃ የሚያወጣ እረፍት፣ ከጭንቀትና ከፍርሃት ነፃ የሚያወጣ እረፍት ደግሞም እርሱ የሚሰጠው እረፍት ግዜያዊ ብቻ ያልሆነ የዘላለም ዕረፍት እና ከእርሱ ጋር የዘላለም ሕይወት ነው። ወደዚህ እረፍት ኢየሱስ ይጠራሀል!
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
ዌብሳይት | ዩትዩብ | ፌስቡክ | ቴሌግራም | ኢንስታግራም |ሊንክድኢን | ትዊተር | ፓይንተረስት | ዋትስአፕ | ቲክቶክ
#የኢትዮዽያ_ሙሉ_ወንጌል_አማኞች_ቤተክርስቲያ_ኢየሱስ_ሰውን_ሁሉ_ይወዳል_በሚል_መሪ_ቃል_በአዲስ_አበባ_ስታዲየሚ_የሚካሄደውን_ኮንፍራስ_በማስመልከት_ህዳር_20_ቀን_2017_ዓ/ም_ጋዜጣዊ_መግለጫ_ተሰጠ።
በመግለጫው ከታህሳስ 4 እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2017ዓ/ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ኢየሱስ ሰውን ሁሉ ይወዳል በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ስታዲየም ኮንፍራንሱ እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን ከአዲስ አበባ እና ከሸገር ከተማ የተሰባሰቡ 206 የሚሆኑ የሙሉ ወንጌል አጥቢያ አብያተክርስቲያናት ኮንፍራንሱን በጋራ እንዳዘጋጁት ተገልፃል።
በጀማ ስብከቱ #15ሺህ ሰዎች ወደ ጌታ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለ3 ቀናት የሚካሄደው የምስጋና እና የወንጌል ስርጭት፡ ጀማ ስብከት ሙሉ ወጪው በአጥቢያዎቹ የሚሸፈን ይሆናል። አጥቢያዎቹ በእነዚህ ቀናት ዝግ ሆነው ይቆያሉ።
የጀማ ስብከቱ በተመለከተ የቤተ ክርስቲያኗ ፕሬዝዳንት መጋቢ ላኮ በዳሶ፡ ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው እና የፕሮግራሙ አስተባባሪ መጋቢ አበራ በላይ አዋሬ በሚገኘው ዋናው ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥተዋል።
የጀማ ስብከቱ የአዲስ አበባ እና ሸገር ክልል አጥቢያዎች ናቸው በጋራ ያዘጋጁት። ያለፉትን 10 ወራት የወንጌል ስርጭት ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል። ለ20 ቀናት የሚቆይ በወጣቶች የሚመራ የማህበራዊ ሚድያ የወንጌል ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል።
ከጀማ ሰብከቱ ጋር በተያያዘ በዳለቲ፡ ቂሊንጦ እና ቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ለታራሚዎች ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።
ለ230 ወጣቶች ከሱስ፡ መጤ ባህል እና ጎጂ ልማዶችን በተመለከተ ስልጠና ተሰጥቷል። ታህሳስ 2 እና 3 በቂርቆስ ጤና ጥቅቢያ የነጻ ህክምና አገልግሎት ይሰጣል።
ቤተ እምነቷ ከ3800 በላይ የሚሆኑ አጥቢያዎቿ እና ከሃገር ውጪ በጅቡቲ፡ ሶማሊያ፡ ደቡብ ሱዳን፡ ደቡብ አፍሪካ እና ሰሜን አሜሪካ የወንጌል ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች።
ለበለጠ መረጃ፡
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/@efgbc
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 6 days ago
Last updated 2 weeks, 1 day ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago