ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ለብቻ ስለማይሆን፣ ለቁጥር የሚያታክት የሰው ሀይል ሰበሰብን። አንድ-ሁለት-ሶስት! እያልን በሕብረት ገፋነው። ጊዜ ግን አልተነቃነቀም።
ትውስታ 2...
አንድ አሮጌ ሳይክል የነበረው ፥ ሽማግሌ ፈረንጅም ትዝ ይለኛል። መቼም ሳስታውሰው ፥ አንድ ከርቭ አስፓልት ጋ ስሙዝሊ እጥፍ... ሲል ነው። እጥፍ... እያለ። ዩኒፎርማችንን የለበስን ህፃናት ‘ፈረንጅ ፈረንጅ’ እንለዋለን። እየታጠፈ... ዘወር ይልልናል። “ዋት ኢዝ ዩር ኔም?” እንለዋለን ከዛ። “ሚን አገባ!?” ይልልናል ጮክ ብሎ። ምስኪን ሳቃችንን እንለቀዋለን። አይሰለቸውም። አይሰለችንም። ፈረንጅ ፈረንጅ... ዋት ኢዝ ዩር ኔም?... ሚን አገባ?... ሚን አገባ?...
አንድ ቀን ግን እንደዛ አላለም። ፈረንጅ ፈረንጅ... ዋት ኢዝ ዩር ኔም?... አየንና ደስ የማይል ፈገግታ ሰጠን። እየታጠፈ እንዲህ አለ። “አይ ሐበሻ!”
አለ። ልጅ ነበርኩ። ደስ የማይል ፈገግታ ሲወጣኝ... ትዝ ይለኛል።
አቶ ማሞ የሚባል ሰው ነበር። ዜና አንባቢውን አማረ ማሞን ይመስላል። ረጅም፣ ጠይም፣ ዘወትር ሱፍ የሚለብስ ሰው ነው። ከስራ ሲመለስ ፥ ተሯሩጠን ሰላም እንለዋለን። ይጨብጠንና ክንዳችንን ያውለበልባታል። ቅጥቅጥቅጥቅጥ ያደርገናል። ፍልቅልቅልቅ እንላለለን። “እኔንም እኔንም...”
ይለናል... ስምህ ማነው?
ፓፒ
ፓፒ ማን?
ፍላቴ
ፍላቴ ማን?
ንጋቱ
ንጋቱ ማን?
ጂራ
ጂራ ማን?
አላውቅም
አላውቅም ማን?
እኔንጃ (ሳቃችን ምጥት ምጥት)
እኔንጃ ማን? (የህፃን ሳቃችን ፍንድትድት)
ሃሃሃ...
ሃሃሃ ማን?...
አቶ ማሞ ፥ ሚሞ የምትባል የሚያሳድጋት መላጣ ልጅ ነበረችው። ግንባሯ መሃል ማርያም ስማታለች።
ሚሞ ማን? ሚሞ ማሞ? ማሞ ማን? የአቶ ማሞን ሙሉ ስም አላውቅም። አላውቅም ማን?
ስማቸው የጠፋብኝ ፥ ዶ/ር ነበሩ ሰፈር። ብቻቸውን የሚኖሩ ፥ ወፍራም ረጅም ሽማግሌ ነበሩ። ሰላምተኛ ሰው ናቸው ዶ/ር። ሚስታቸውና ትልልቅ ልጆቻቸው ፥ ኤርትራ ስትገነጠል ወደዚያ ሄደው ነው ይላሉ ብቻቸውን የሚኖሩ። ግን ታማኝ የቤት ሰራተኛ ነበረቻቸው። በ 15 በ 20 ብር ዶሮዎች ስትሸጥ አስታውሳታለሁ። ምን የሚያካክሉ ዶሮዎች ነበሩ እላለሁ። እቺ ጐልማሳ ሴት እና ዶ/ር ፥ ምን እና ምን ነበሩ እላለሁ ዛሬ።
በእርቁ ወቅት ፥ ኤርትራ የሄዱ አይመስለኝም ዶ/ር። ጉጉት ያላቸው ፥ ናፋቂ ሰው አይመስሉም ትዝ ሲሉኝ። ሰላምተኛ ብቻ ናቸው...
ይቀጥላል...
ትውስታ...
ደጉ ፥ የሚባል ሊስትሮ ነበር። በአንዱ የተንጣለለ የአሶሳ ማንጐ ዛፍ ስር ፥ በሰፈር ጫማዎች ላይ የሚጠበብ ቀይ ወጣት (የዛኔ ትልቅ ሰው) የማይሰራው ጫማዊ አስማት አልነበረም። ሰሞኑን አንዱ ሊስትሮ “ማስቲሽ የለኝም” ሲል ስሰማው ፥ ደጉ ትዝ አለኝ። ደጉ ኃይለኛው ሊስትሮ። ማንጐ ለመቁረጥ ድንጋይ ስንወረውር አይወድም። ግን እንወረውራለን። ምስኪን ሰው ሲበሳጭ ፥ ምንም አይመስለኝም ነበር። ደጉ ሞቷል። ከመሞቱ ቀድሞ ፥ ባጃጅ ነጂ ሆኖ ነበር።
ማቲዮስ የሚባል የሰፈር ጉልቤ ነበር። በእድሜ በጣም ይበልጠናል ሳስታውስ። ግን እየሰበሰበ ፍዳችንን ማብላት ያስደስተው ነበር። ቂም ሳንይዝበት ፥ በነጋታው ቤቱ ድረስ እየሄድን እንጨቆናለን። ሲፈልግ ያሯሩጠናል... ሲያሻው ስፖርት ያሰራናል... ሲያምረው አስከትሎን ይዞራል። “ወፍ በድንጋይ እጥላለሁ እዩ” ይለናል። አንድም ቀን ጥሎ አያውቅም፤ ግን እንፈራዋለን ማቲዮስን። መታን ቀጣን ብለን ለቤተሰብ አንናገርም። ቅድም እኮ እዚህ ሆስፒታል አካባቢ ፥ ህፃናት ኳስ እየተጫወቱ ስናልፍ ፥ እላያችን ላይ ኳሱን ሲመቱት ፥ እላያችን ላይ ሲሮጡና ሲጋፉ ፥ በፍጥነትም ዘወር ስላላልንላቸው ሲበሳጩብን... ማቲዮስ ትዝ አለኝ። ማቲዮስ ሐረር ገብቷል ብለው ነበር። የ10ኛ ክፍል ፈተና ያመለጠው ፥ እንቅልፍ ጥሎት እንደሆነ ሲያወሩ ሰምቻለሁ።
አንድ አሮጌ ሳይክል የነበረው ሽማግሌ ፈረንጅም ትዝ ይለኛል...
(ይቀጥል ያጫውታል ይሄ ነገር?)
መውደቄን አይቶ የሚደርስልኝ ፡ እንቅልፌ ብቻ ነው። እኔ ወረተኛ ግን ፡ እቺን ለመፃፍ ስል አስጠበቅሁት...
ጥሩ መፅሐፍ ነው Norwegian wood.
ታሪኩን አላቡካካውና ፥ አንድ ቦታ ደስ ያለኝን ይኸውላችሁ። አንዲት ካራክተር አለች፤ አንዳች ችግር በህይወቷ ይገጥማትና አካባቢውን ስለመልቀቅ (ሰፈራቸውን ትተው ስለመሄድ) ትለምናለች ባሏን። ‘በፍጥነት በፍጥነት’ ትለዋለች። “አለበለዚያ የአእምሮዬ ነገር ያገረሻል” ትላለች በጭንቀት። ባሏም በሚጠበቅ በምክንያታዊነት “አሁን ድንገት ብድግ ብለን መሄድ አንችልም። ድንገት ስራዬን ማቆምና እና አዲስ ማግኘት አልችልም። ለልጃችን ሌላ ትምህርት ቤት መፈለግ ጊዜ ይወስዳል። ስለዚህ ቢያንስ ሁለት ወር ስጪኝ...” ይላታል።
“ሁለት ወር? አልችልም ሁለት ወር። አሁን እንኳን ስሜቱ እየመጣ ነው። ድምፅ መስማት እየጀመርኩ ነው። እንቅልፍ እምቢ እያለኝ ነው። አሁን ከተነሳብኝ እኮ... በቃ ይጨርሰኛል።” ትለዋለች በጭንቀት።
ከዚያ እንደገና ቢያንስ ቢያንስ አንድ ወር መታገስ እንደለባት ያስረዳታል። ምንም ማለት አልቻለችም።
ነገር ግን አእምሮዋ አንድ ወር መታገስ አልቻለም። በሽታዋ አገረሸ። እና ይሄንን ነው የምለው... ይሄ ነገር ልክ እንደ ሽንት ሊያመልጣት ሲል የተፍጨረጨረችበትን ሁኔታ በደንብ እረዳለሁ። አእምሮ አይደለም ወር ፥ አንድ ተጨማሪ ሰከንድ የማይታገስ ሲመስል ይገባኛል። የጊዜን ዋጋ እና የአእምሮ ጤናን ግንኙነት ጠንቅቄ አውቃለሁ። እና በዚህ precision ደህንነት ሊያመልጥ እንደሚችል ይገባኛል። በተለይ የአእምሮ ደህንነት።
(የቀኑና የመጨረሻው 70 ገፅ ቀረኝ። #በዲሲፕሊን ተነበበ)
ህመም ምንድን ነው?
የሰው ልጆች በመገናኛ።
የሰው ልጆች በአውቶብስ ተራ።
'Workin on the weekend like usual...'
መርዶ
ቡቡ ሆዴ እየሞተ ነው።
አፈር ከመሆኔ በፊት ፥ ድንጋይ እየሆንኩ ነው።
የእርጥብ አፈር ሽታን በተመለከተ ፥ አፍንጫዬ ደደብ ሆኗል።
የምናብ ሩጫዬ ፥ ከማራቶን ወደ 100 ሜትር ፥ ከሩጫነትም ወደ እርምጃ ተቀየረ። በዚህ አላበቃም። ምናቤ ጉዳት አጋጠመው። አሁን ፥ ወደፊትም ወደኋላም መሄድ አይችልም።
ሰውነቴ በስራ ብቻ ሳይሆን ፥ በምግብ ደከመ። ሲርበኝም ሳይርበኝም እየበላሁ። Consciousnessን የምመክተው በምግብ ነው። ተራ አባባል ይመስላል? አሳቢ ክፍሌን ፥ እየገደልኩት እየሞተ ነው።
የጠዋት ፊቴ አስፈሪ ሆነ። ቁርስ በልቶ አይፈካም። የአዲስ ጀምበር መውጣት ፥ ሌላ የትግል ግብዣ እንጂ ተስፋ አይደለም። እና ትግል በአፍንጫዬ ወጥቷል።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana