የሜሪ አጫጭር ተረኮች

Description
እኔ እና ቤቴ ግን ፍቅር የህግ ሁሉ የበላይ መሆኑን እናውቃለን!! ሀይማኖታችንም እምነታችንም ፍቅር ነው!!!
Subscribers

We recommend to visit

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

-የዝዉዉር ዜና
-የአሰልጣኞች አስተያየት
-ጎሎች እና አዝናኝ ቪዲዮዎች
-የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
-ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

አስተያየት ካሎት @ZENA_ARSENAL_BOT

ለማስታወቂያ ስራ +251911052777

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @MKHI7

Last updated 4 months ago

The voice of Ethiopian football

For Adverisment ONLY : +251940018801

Last updated 4 months ago

ይህ እግር ኳሳዊ መረጃዎችን በፍጥነት የሚያገኙበት #DREAMSPORT ነው።

- የሀገር ውስጥ ዜናዎች
- የአውሮፓ ሊግ መረጃዎች
- ትኩስ ትኩስ የዝውውር ዜናዎች
- ጨዋታዎችን ከየስታድየሞቹ በቀጥታ
- የተጫዋቾች የህይወት ታሪክ

ለማስታወቂያ ስራ @Van_Lapara ላይ አናግሩን።

Last updated 4 months ago

4 months, 2 weeks ago

አንድ ጤነኛ የሚባል ሰው በኑሮ ዘመኑ በአቭሬጅ 7 የፍቅር ግንኙነት ሊኖረው ይችላል!!

ሰብሰብ ብለን ባለፈው በጨዋታ መሃል ይሄን ነገር ስነግራቸው ከመሃከላችን አንዱ ወመኔ በጣም ደንግጦ

"በየሱስ ስም! ሰባት?? ሰባት?? ከፊትም ከኃላም ምንም ቁጥር የለም? እርግጠኛ ነሽ?"

"እንግዲህ እኔ የሰማሁትን ነው!!"

"አቤቱ ፈጣሪ እንደፈርኦን 'ህዝቤን ልቀቅ!' ብለህ ተዋጊ እንዳትልክብኝ እንጂ በቁጥር አልለያቸውም!!" ብሎን ተሳስቀን ሌላ ጨዋታ ጀምረን የጦፈ ክርክር ላይ ሳለን... ከመሃከላችን ጭራሽም ለስድ ጨዋታ በጣም ሩቅ የሆነች ጏደኛችን እኮ ናት

"ሜ? ቅድም ያልሽው ግን? አንድ ቀን የሳምሽውም ይቆጠራል?" ስትለን በሳቅ ሞትን... ለካ እስከዛ ሰዓት እየቆጠረች ነው!!

(ህዝቤኮ አይነግረንም እንጂ በሆዱ ቆጠራ ላይ ነው🤣🤣)

ፈገግ ያለ ምሽት አምሹልኝማ❤️❤️❤️❤️

4 months, 2 weeks ago

መቼም እኔ ላይ የማይበረታ የለም..

በቀደም እንደሞላለት ሰው ውንጥ ውንጥ ስል አንድ ሀበሻ ፍጥጥ ብላ ስታየኝ .. .. እዚህ ሀገር ፀጉሬ ነው አይን ውስጥ የሚያስገባኝ ብዬ .. 'ፀጉሬን ወዳው ነው ወይም ፌቡ ላይ ታውቀኛለች ' ምናምን ብዬ ሳስብ ከሀገር ቤት ትኩስ በደረሰ አማርኛ

"እንዲህ አንገትሽን መዝዘሽ ስትሄጂኮ ሀገሩን የገዛሽው ነው የምትመስዪው!" ብላኝ ኮስተር ብላ አለፈች....

አሁን በቀደም ሙሉ ልብስ ለብሼ በወጣሁበት የተገናኘን ወዳጄ የዛን ቀን

"አለባበስሽኮ ይምጣብኝ!! ዝነጣን አንቺ ዘንጫት!" እያለ ሲያሞካሸኝ ቆይቶ ዛሬ ደወለና '5000kr አበድሪኝ' ሲለኝ 'የለኝም' እለዋለሁ! ምን ቢለኝ ጥሩ ነው??

"5000kr የሌለው ሰው እንደዛ አይለብስም!! ወይ ኖርማል ልበሺ ወይ ብር ያዢ!🤪🤣"

🙆🏻‍♀️🙆🏻‍♀️🙆🏻‍♀️🙆🏻‍♀️🙆🏻‍♀️🙆🏻‍♀️🙆🏻‍♀️ ወዮ ሜዬ!!!

4 months, 3 weeks ago

ዲያስፖራው ሀገር ቤት ሄዶ ጎረቤት ሊጠይቅ ሄዶ ነው::

"ውይይ እማማ ታመው ነበር?? በጣም ከሱኮ... በስመአብ ድሮኮ ጢም አድርጎ የጫነ አይሱዙ ይከልሉ ነበር ሃሃሃሃሃ"

"ምን ታደርገው ልጄ ታምሜ ከረምኩና እንዲህ ውልቅ አልኩ!" (በሆዳቸው ጥርስህ ይውለቅ ይሉታል መቼም)

"ጠዋት ተነስተው ሙዝ: ስትሮበሪ: ከተገኘ ብሉቤሪ : እላዩ ላይ የለውዝ ቂቤ ጣል አድርገው በወተት ጁስ እየፈጩ ቢጠጡ ሰውነቶ ይመለሳል:: ከእድሜዎምጋ ስለማይሄድ ስኳር አያድርጉበት:: በማር ይሻልዎታል::"

"አሄሄሄ ልጄ ለአፍ ዳገት የለው አለች ያቺ እናትህ እውነቷንኮ ነው! ስኳሩ የሞት መድሃኒት እንኳን ቢሆን ከየት እንደልብ ተገኝቶ!"

"ይቅርቦት አይጠቅሞትም! ስኳር: ጨው: ጮማ ... መርዛማ ናቸው:: ስጋውንም ቀይ ቀዩን ይብሉ:: በተጨማሪ እንቅልፍ ጥሩ ነው... ትኩስ ወተቶትን ጠጥተው ለሽ ቢሉ ምናለ ይበሉኝ .. በ2 ወር ሰውነቶ ይመለሳል:: ብቻ ይሞክሩት!"

እማማ ያው ይሄን ሁሉ የሚቦተረፈው የ2 ወሯን ሊዘጋት ነው ብለው ወደ አፍ ሁሉ የሚገባውን ሲያስቆጥራቸው ሰሙት.... ሲወጣ 500 ብር ቆጥሮ 'ለአንዳንድ ነገር' ብሎ ሲሰጣቸው ምን አሉ??

"አንዳንድ ነገሮቹንስ በዚህ ገዛኃቸው... ዋና ዋናዎቹን በምን ልግዛቸው?? የጠራሃቸውን የአንድ አትክልት ተራ ገበያ ፍራፍሬዎችስ : ቀይ ቀዩን: ወተቱን: ማሩን... በምን ልግዛቸው?? ምናል ከአፍህ ቆጠብ አድርገህ ከእጅህ ጨመር ብታደርገው??" አሉት..... 🤪🤣🤪🤣

እና ምን ለማለት ነው??

አንዳንዶቻችሁ ብቸኛ መፍትሄያችሁ እኔ ያልኩት ነው የምትሉትን እሺ ይሁን... በዛው መዳረሻውንም እየጠቆማችሁን!!! ምነው ?!!!

ሰላሙን ያምጣልን❤️❤️❤️❤️ ውብኛ ዋሉልኝማ❤️❤️

4 months, 3 weeks ago

«እንደሱ አላስብም! ሰዎች ወደገፉኝ ቢሆንማ የምሄደው በሰዎች አላዝንም ወይም እንዳላጣቸው አልፈራም። ምክንያቱም የእነሱን ፍላጎት ስለሟሟላ ሊከፉብኝ የሚያስችል ምክንያት አልሰጣቸውም!! በመንገዴ ያለፉ ወይም ያሉ ሰዎች በሙሉ ለጉዞዬ የሆነ ስንቅ አቀብለውኛል። አንዳንዱ ወደፊት የሚያስፈነጥር አንዳንዱ ወደኋላ የሚጎትት ሊሆን ይችላል። ችግሬ እኮ ያ ነው!!! ራሴንም ማጣት አልፈልግም በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችንም ማጣት አልፈልግም። ራሴን በመሆኔ ውስጥ የማልመቻቸው ሰዎች የአብሮነት ጉዟችንን ያቋርጡና ትተውኝ ከሚመስላቸው ጋር መጓዝ ይቀጥላሉ። እነርሱ ከእኔጋ ያሳለፉት ነገር ምንም እንዳልሆነ ሁሉ ጉዟቸውን ሲቀጥሉ እኔ ወገቤ ላይ ነጠላ አስሬ እዬዬ እላለሁ።»

«ችግሩ ራስሽን መሆንሽ ብቻ አይመስለኝም! ሰዎችን የምታቀርቢበት መጠን ገደብ አልባ መሆን ነው ችግሩ!»

«እስኪ ንገረኝ ጓደኝነት ገደቡ ምን ድረስ ነው? ቤተሰባዊነት በቃኝ የምትለው የትኛው ነገርህጋ ሲደርሱ ነው? ፍቅረኛህን ከዚህ ገደብ ካለፈች ትሰባብረኛለች እና አላሳልፋትም የምትለው ምንህን ስታልፍ ነው? የተገደበ ከሆነ ምኑን ጓደኝነት? ምኑን ቤተሰባዊነት? ምኑን ፍቅር ሆነ?»

«ሰውኛ የሆነ መረዳት ልንገርሽ! ሁሉንም የሰጠሽው ሰው ካንቺ ብዙ ነገር ይጠብቃል። ሰው ነሽ እና የሆነ ቀን አንዲት ነገር ስታጎድዪበት አልለመደም እና ቅር ይለዋል። ሊጣላሽ ሁሉ ምክንያት ይሆነዋል። ጥቂት የሰጠሽው ሰው ግን ሲጀመር ብዙ አይጠብቅብሽም ሲቀጥል ብታጎድዪበት መጀመሪያም ስለማይጠብቅ አይከፋብሽም። ከሰዎች ጋር ባለሽ ነገር 50 50 ሁኚ! 100 ስትሆኚ ነው ችግሩ!!»

«አልችልም!! ሞክሬ አውቃለሁ! በፍፁም ገደብ ማበጀት አልችልም! ወይ እቀርባለሁ ወይ አልቀርብም! መሃል ላይ መሆን አልችልም። ለቀረብኳቸው ሰዎች ደግሞ <አትስሚያቸው> የሚል ምክር ለእኔ አይሰራም!! ይልቅ ሲሄዱ እንዳልንኮሻኮሽ የሚረዳኝ ምክር ካለህ እሱን ምከረኝ! አምኛቸው እምነቴን ቂልነት ሲያደርጉብኝ ሌላ ሰው የምሆነውን ነገር መተው የምችልበት ምክር ካለህ እሱን ወዲህ በል ፣ አስቀይሚያቸውም አስቀይመውኝም የምናፍቃቸውን ነገር ማቆም የምችልበት መንገድ ካለህ እሱን አሳየኝ!!»

«ከሰዎች ምንም አለመጠበቅ!!»

«ይሄ ኮንሴፕት ይዋጥልሃል? የምልህ ከአባባልነት አልፎ ተግባራዊ የሚሆን ነው? ከፍቅረኛህ ምንም አለመጠበቅ ምን ማለት ነው? የአበባ ጋጋታ ወይም ሰርፕራይዝ አትጠብቅ! ፍቅር ትጠብቃለህ! Respect ትጠብቃለህ። ከልጆችህ ምንም ያለመጠበቅ ማለት ምን ማለት ነው? ቢያንስ ዲሲፕሊንድ እንዲሆኑ ትጠብቃለህ! ከቤተሰብህ ምንም ያለመጠበቅስ ምንድነው? ራሴን እስክችል ከእነርሱ የሚያስፈልገኝን ሁሉ እጠብቃለሁ ከዛ ደግሞ እንደቤተሰብ ፍቅርና ድጋፍ እጠብቃለሁ። ከጓደኛ ምንም አለመጠበቅስ እንዴት ነው? ስፈልገው እንደማይገኝልኝ የማልጠብቅ ከሆነ ሲጀመር ጓደኛዬ ነው? እሺ እንደው የክርስቶስ ልብ ኖሮኝ ምንም ሳልጠብቅ ሁሉንም የምወድ ሆንኩ እንበል። ከጠበቅከው ፖዘቲቭ ይልቅ ያልጠበቅከው ኔጌቲቭ ነውኮ የሚጎዳው!! ለምሳሌ ምንም ሳልጠብቅ የምወደው ጓደኛዬ እኔ በሰጠሁት ልክ አለመመለሱ እኮ አይደለም የሚያመው። የሰጠሁትን እምነት ሲያነክተው ነው የሚያመው። የወደደ ልቤን እንደጅል ቆጥሮ ሲነግድበት ነው የሚሰብረው። አየህ ያልጠበቅከው ነው ቀልጥሞ ቁጭ የሚያደርገው። 77 ጊዜ ሲያስከፋህ ያለፍከው ጓደኛህ አንዴ ስታስከፋው <ባላንጣው> የሚያደርግህ ነው የሚያስነቅለው!»

«መዓዛ ለዛሬ ሰዓታችን አልቋል።»

<hr>

ይለቃ ታዲያ!! እኔም የምፅፈውን ጨርሻለሁኛ!!

እንዴት ናችሁልኝሳ!???? ❤️❤️❤️❤️

4 months, 3 weeks ago

ርዕስ አልባ ምልልስ
(ሜሪ ፈለቀ)

«መዓዛ በዙሪያሽ ያሉ ሰዎች ላይ ከማተኮር ይልቅ አንቺ ላይ እናተኩር?» ይለኛል ሰዎች ስላደረጉኝ ወይም ስላደረጉልኝ ነገር እያወራሁ አሰልችቼው።

«እንደሱ የሚባል ህይወት ግን አለ? ከሰዎች ጋር ያልተገናኘ <እኔነት>? ምናልባት ቁጥራቸውን ትቀንሰው ይሆናል ወይም የቀረቤታህ ገደብ ይለያይ ይሆናል እንጂ ከሰው ያልተሳሰረ <እኔ> ብቻ የሚባል ነገር አለ?»

«አለ! በእርግጥ የቀን ተቀን ህይወታችን በአንድም ይሁን በሌላ ከሰዎች ጋር ያገናኘናል። ያ ማለት ግን ያ ሁሉ ሰው ለመኖር ያስፈልገናል ማለት አይደለም። ስላንቺ እናውራ ስልሽ ወደውስጥሽ እናተኩር ማለቴ ነው! ስለለአንቺ እናውራ?»

«ደስ ይለኛል። ስለእኔ ምን እናውራ? የሁለት ልጆች እናት ነኝ! ብታይ ልጄ 18 ዓመት ሞላት። ወንዱ ደግሞ 13 ሆነው! እሷ ከልክ በላይ በስላ ታሳስበኛለች። እሱ ደግሞ ከልክ በላይ በጥባጭ ሆኖ ያሳስበኛል ……. »

«መዓዛ ስላንቺ! ስላንቺ ነው እናውራ የተባባልነው?»

«እህህ ልጆቼ የሌሉበት እኔ? ካለእነሱ እኔ እኔ ነኝ እንዴ?»

«ለምሳሌ በህይወትሽ ስኬቴ ነው የምትዪው ነገር?»

«ልጆቼን እና ቤተሰቦቼን ጨምሮ በምወዳቸው ሰዎች ልብ ውስጥ በፍቅር መታወስ!! አለ አይደል? ከሚያውቁኝ ሰዎች መሃል ስሜን ሲሰሙ ከሚያንገፈግፋቸው ይልቅ ስሜን ሲሰሙ ልባቸው በፍቅር የሚሞቅ ሰዎች ቢበዙልኝ ያ ነው ስኬት!!»

«አሁንም የምናወራውን ነጥብ እየሳትሽ ነው። እሺ ለምሳሌ ከ career or profession አንፃር የት መድረስ ነው ህልምሽ?»

« እእእ! ወደፊት ሙሉ በሙሉ ስራዬም ሙያዬም እንዲሆን የምፈልገው ፅሁፍ ነው!! ታውቃለህ ልቤ ተራራ ነው። ይህቺ ሰውነቴ ይሄን የሚያህል ግድንግድ ልብ እንዴት ችላ እንደተሸከመች ይገርመኛል። ከሆኑ ዓመታት በኋላ ብዙ ሰዎች ልብ ውስጥ የሚቀሩ ስራዎች እንዲኖሩኝ እፈልጋለሁ። ስራዬ ብዙ ሰዎች ጋር እንዲደርስ እፈልጋለሁ። (አሁን ወደመስመር መጣሽ የሚል አይነት ንቅናቄ ጭንቅላቱን ነቀነቀ!) በሰዎች ቀን ላይ የሆነ ፈገግታ፣ መፅናናት፣ መበርታት ……. ብቻ የሆነች ትርጉም ለቀናቸው የሚጨምር ነገር እንዳበረከትኩ ሲሰማኝ ያኔ ስኬታማ ነኝ ብዬ ነው የማስበው!»

«here we go again! መዓዛ let us focus on just you! ህም እሺ የሚያስከፋሽ ነገር?»

«ሰው!! ካለቀስኩ ፣ ከከፋኝ ፣ ድብርት ውስጥ ከገባሁ …….. ምክንያቱ ሰዎች ናቸው። ወይ ሰው አስቀይሞኛል ወይ ሰው አስቀይሜያለሁ!!»

«እሺ ከሰዎች ጋር ሳይያያዝ የሚያስደስትሽ ነገር? ለምሳሌ ስትፅፊ እንደምታገኚው አይነት ደስታ?»

« ዌል አዎ! ስፅፍ ሌላ ዓለም ውስጥ ነኝ! ግንኮ የምጽፈው ለሰዎች አይደል? እኔ <ውስጤ የሞላውን ለመተንፈስ ነው የምፅፈው እንጂ ታተመ አልታተመ ግድ የለኝም!> እንደሚሉ የድሮ ደራሲዎች መሆን አልፈልግም። የምፅፈው ለማስቀመጥ አይደለም!! ሀቀኛ ወሬ ስናወራ ውስጤ ያለውን መተንፈስ ከሆነ ዓላማዬ ከጓደኞቼጋ አላወራም? ብዙ ጓደኞች አሉኝ እንዳይሰለቻቸው በተራ በተራ ለእያንዳንዳቸው ተንፍሼ መጨረስ እችላለሁ። ይቅርታ አድርግልኝና ደስታዬም ከሰው ጋር የተያያዘ ነው! ከዚህ ሌላ ከምወዳቸው ጋር እና ለምወዳቸው የማደርገው ነገር ደስታዬ ነው። ደስታ አልፈጅም!! አንዲት ዘለላ አበባ ወይም አንድ መታቀፍ ወይም የ30 ደቂቃ የማኪያቶ ጨዋታ ጮቤ የሚያስረግጠኝ ጀዝባ ነኝ!!»

በረዥሙ ተንፍሶ የሚጠይቀኝ የቸገረው ነገር መስሎ ሲያመነታ ከቆየ በኋላ
«እሺ የምትፈሪው? ሰው እንዳትዪኝ በፈጣሪ ስም!»

«ከፍታ፣ ፍጥነት እና ጨለማ እፈራለሁ!! ከእነዚህ እኩል ሰው ማጣት እፈራለሁ! በሞትም ይሁን በመለየት የምወደውን ሰው ማጣት እፈራለሁ።»

«ከሰው አዙሪት እንውጣና እስኪ ባንቺ ዙሪያ ብቻ እንዙር መዓዛ!» አሁን ትዕግስቱን እንደመጨረስ ያለ ይመስላል።

«ችግሩ እኮ እሱ ነው! ሰው የሌለበት ህይወት የለኝም!! እንዲኖረኝም የምፈልግ አይመስለኝም!! ዙሪያዬንም ብንዞር ወደውስጤም ብንሰምጥ ሰዎች ናቸው ያሉት። ሰው የሚባለው ፍጡር በመሰረታዊነት የተገነባው የሆነ ግሩፕ አካል ሆኖ አይደል? ስንመጣ ወደዝህች ምድር እናት እና አባት እኛን ጨምረው ቤተሰብ የሚባል ግሩፕ ነው። ያ ቤተሰብ የሆነ ማህበረሰብ አካል ነው። ያ ማህበረሰብ የሆነ ሀገር አካል ነው። እያለ እያለ ይቀጥላል። ወደድንም ጠላንም ስሪታችን ራሱ በሆነ ሰው ላይ የምንደገፍ እና የሆነ ሰው በኛ ላይ የሚደገፍ ያደርገናል። ዝምንና እና ቴክኖሎጂው ሰዎች በሰዎች ላይ የሚደገፉበትን ዘርፈ ብዙ ምክንያት ለምሳሌ መሰረታዊ የሚባሉትን መጠለያ፣ ምግብ እና ልብስ ለማግኘት ያስፈልጋቸው የነበረውን የድጋፍ እጅ ብዛት ቀንሶላቸዋል። ከቴክኖሎጂ እኩል የፈሉትን የሶሻል ሚዲያ ብዛቶች ስታይ ግን ሰዎች መሰረታዊ ከተባለላቸው ፍላጎታቸው ውጪ የሆነ ግሩፕ አካል መሆን መፈለጋቸው ተፈጥሯዊ መሆኑን አይነግረንም?»

«እሺ ለመጨረሻ ጊዜ ከሰዎች ጋር ያልተያያዘ ለራስሽ ብለሽ ያደረግሽው ነገር ምንድነው?»

«ፊልም ማየት? ያው እሱም ቢሆን ተከታታይ ፊልም ከሆነ ከሁለተኛው ሲዝን በኋላ ተዋናዮቹ ቤተሰቦቼ ሁላ ነው የሚመስሉኝ አብሬያቸው እስቃለሁ አለቅሳለሁ እናደዳለሁ። ተዋናዩ ሞተ ብዬ ፍራሽ አንጥፌ ትኩስ ነገር የሞላበት ፔርሙዝ አጠገቤ አስቀምጬ ሀዘን መቀመጥ እስኪዳዳኝ እኝኝኝ እላለሁ። ተከታታይ ፊልም በተለይ ብዙ ሲዝን ካለው ከሰው ጋር ማየት አልወድም!!»

«ለምን?» አባባሉ ከሰው ጋር ያልተገናኘ ክንውን በማግኘቱ የሚተረትረው የሆነ ፍንጭ የጨበጠ ነገር አስመሰለበት።

«አንደኛ ብዙ ሰዎች ፊልም እያዩ ያወራሉ! ሰው እንዴት ፊልም እያየ ያወራል? ሁለተኛ የእኔ ትንሽ ይበዛል መሰለኝ! ተከታታይ ፊልም ሳይ እንደሰው እያቋረጡ ከዛ ደግሞ መቀጠል አልችልም። ለምሳሌ 5 ቀን ቢፈጅብኝ አምስቱንም ቀን ከቤቴ አልወጣም! ለአምስቱ ቀን የሚሆነኝን ምግብ ገዝቼም ሰርቼም አስቀምጣለሁ። በመሃል የሚያቋርጠኝ ምንም ነገር አልፈልግም! እያየሁ እንቅልፌ ካልደፋኝ በቀር ለ48 ሰዓት ላይ እችላለሁ። በዚህ መጠን ፍቅር ሊያይ የሚችል ሰው እስካሁን ስላላጋጠመኝ ብቻዬን ማየት ነው የምፈልገው።»

«እሺ ሌላስ?»

«መፅሃፍ ማንበብ ወይም አሁን አሁን ኦዲኦ መስማት! ያው እሱም ግን በሰዎች ስሜት ውስጥ መስመጥ ነው። እህል መብላት ከተቆጠረ እህል! ሙዚቃ እሰማለሁ ምናልባት እሱ ለራሴ ብቻ ስል የማደርገው መሰለኝ እርግጥ እሱንም አብሮኝ የሚሰማ ባገኝ በየመንገዱ አንዱን የጆሮ ኢርፎን ባውሰው ደስ ይለኛል!»

«ህምምም ብቻሽን መሆን ትፈሪያለሽ?»

«በፍፁም! ከሰው ጋር መሆንን እንደምወደው ብቻዬን መሆንም እወዳለሁ። አሁን አሁንማ እንደውምኮ ብቻዬን የማሳልፈው ጊዜ ይበዛል። ብቻዬን መሆኔን በጣም ኢንጆይ ከማድረጌ የተነሳ ስልክ እንኳን ማውራት የማልፈልግባቸው ጊዚያት አሉ!! ከሰዎች ጋር ያለኝ ትስስር ሁልጊዜ በአካል የመገናኘት አይደለም። ጥሩ ግንኙነት እስካለን ድረስ በአካል ለብዙ ጊዜ ሳላገኛቸው አጠገቤ ያሉ ያህል ቅርብ እንደሆኑ የሚሰሙኝ ብዙ ወዳጆች አሉኝ።»

«ደስታሽም፣ ሀዘንሽም፣ ፍርሃትሽም፣ ስኬትሽም በሰዎች የሚዘወር ከሆነ ህይወቴን ራሴ እየመራሁት ነው ትያለሽ? ወደ ፈለጉት ሙድ ሰዎች እየገፉሽ አይደለም?»

4 months, 3 weeks ago

እንግዲህ ሰልስትም አለፈ አይደል? ትንሽ በጨዋታ አዋዝተን ቁምነገር እናውራ እስኪ!!
በረታችሁ?

የመሃል ጣትህን ካሳየኸኝ ሶዬ አንስቶ። (ለአዲስ ይሁን ለእኔ አልገባኝም!🤷🏽‍♀️🤷🏽‍♀️ ) አንቺ ማነኝ ብለሽ ነው ህይወቱን የምትነጥቂው? እስካልሽኝ ልጅ ቁጣ ፣ መግደል መሸነፍ ነውን እስከጠቀሳችሁ ኮማቾች ፣ እርግጠኛ ነኝ አዲስን አልተረዳሽውም እሱ እንዲህ አያደርግም የሚል ኮማች ደግሞ እህ ሶዬውን እኔ አይደለሁ እንዴ የፈጠርኩት ብዬ እንድጠይቅ እስካደረጋችሁኝ …….. ደግሞ ከርዕሱ ውስጥ እግዜርን አውጪው ይሄ ያንቺ እና የሰይጣን ስራ ብቻ ነው እስካለኝ ተበሳጭ ....... ብቻ መዓት ኮመንት ታሪኩን ምን ያህል እንደወደዳችሁት ስለሚያሳየኝ እየፈገግኩ ነው ኮመንቶችን ሳይ የነበረው።

እንደኮራ ሞተ እንደተጀነነ
ከኩራቴ ማማ አልወርድም እንዳለ

ህይወትና ፍቅርን የሚያስከፍል
እንዴት ያል ፍርሀት ነው?

ብቻ መዓት ….. በኮመንት ዘና ብዬ ወደኢንቦክስ ዞር ስል አንዳንድ ኢንቦክሶች በጣም የመረሩ ሆኑና አንድ ነገር ማለት አለብኝ ብዬ አሰብኩ። «ከሱጋ የሚመሳሰል ህይወት አለኝ፤ ተስፋዬን አብረሽ ገደልሽው፣ መጨረሻዬን የነጠቅሽኝ መሰለኝ፣ » አይነት ኢንቦክሶች!! እረፉኣ እኔ እንዲህ አይነት ነገር አይመቸኝም!!🤷🏽‍♀️ ራሴን ችዬ የሰራሁት ሀጢያት መች አንሶኝ ነው። አስባችሁታል? <በልብ ወለድ ገፀባህሪ አማካኝነት የግለሰብ ተስፋ በመንጠቅ> ተብዬ ስጠየቅ?

አላውቅም ምናልባት ገፀባህሪው ባለፈበት ሜንታል ክራይሲስ ውስጥ እያለፋችሁ ይሆናል። ያላችሁበትን ሁኔታ በፍፁም እያቃለልኩ አይደለም። ይሄ ሰውዬ እኔ የሆነ ቀን ዦጥ ሲያደርገኝ የፈጠርኩት ገፀባህሪ እንጂ የእናንተን እጣ ፈንታ የምታዩበት መስታወት ሊሆን አይችልም!!

አውቃለሁ ብዙ ወጣት ሀገር ቤት በተለያየ ዲፕረሽን እና ሜንታል ክራይስስ ውስጥ እያለፈ ነው። ክፋቱ የአዕምሮ ጤና ትኩረት ያገኘ አጀንዳ ስላልሆነ እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይደለም። (ምን ትኩረት ያገኘ አጀንዳ አለ? እንዳትሉ) እባካችሁ እንዲህ አይነት ዝቅታ ላይ ስትሆኑ እርዳታ ለማግኘት ሞክሩ!! አንተ ብቻ አይደለህም ያንን ቁልቁለት እያለፍክ ያለኸው! አንቺ ብቻ አይደለሽምኮ ከጨለማሽ ጋር ግብ ግብ የያዝሽው!! ነፍ ህዝብ ተፋፍሮ እንጂ ከጥላው ጋር አባሮሽ እየተጫወተ ነው። አንድ የሆነ ልብወለድ ገፀባህሪ ወይም ፌቡ ከደቂቃ ሞቅታ ያለፈ ተስፋ አይሆንም። የባለሙያ እርዳታ አግኙ!!

የመኖራችሁን ፋይዳ መጠየቅ ስትጀምሩ፣ የቀን ተቀን ህይወት አድካሚ ሲሆንባችሁ፣ መኖር አታካች ሲሆንባችሁ የሚረዳችሁ ሰው ፈልጉ። የሚያሳፍር ነገር አይደለም!! ደህና አይደለሁም በሉ! በውሸት ፈገግታ እና ሁካታ እየተደበቃችሁ ውስጥ ውስጡን አትሙቱ!!

ከዛ ደግሞ እጅግ በብዙ የምታምኑትን አምላክ ለምኑ!! ከዛ ደግሞ እኔን አታፀጽቱኝ 🤦🏽🤦🏽

በተረፈው ውብ ቀን ውብኛ ዋሉልኝ❤️❤️❤️

4 months, 4 weeks ago

የሆነ መፅሃፍ ገፀባህሪ ወይም ፊልም ካራክተር እኮ ነው ነገረ ስራዋ ሁሉ። በ14 ዓመቴ የሆነ ልጅ የፃፈልኝን አሁን ልብ እና አበባ እንዳለው ብቻ የማስታውሰውን ደብዳቤ ደብተሬ ውስጥ አጊንታ እሪሪሪ አለች።

ልጅ ሆኜ ደም የማፈላ በጥባጭ ነበርኩ አላልኳችሁም? ተናገረችኝ ብዬ ከቤት ተነስቼ መጥፋት፤ አዳማ አዳማ በሚል ሚኒባስ አዳማ!! እናትየው ያኔ የሴቶች ጉዳይ ነበረች ከመጥፋቴ በፊት በነበረ ቀን ከኔጋ የታየ ጎረምሳ ሁላ አሳፍሳ ሸቤ! (እስከአሁን ራሱ ሲያየኝ እንደዲያቢሎስ የሚያየኝ ልጅ አለ!!) ያው እኔ ጠዋት ጠፍቼ ማታ ሲናፍቁኝ ደወልኩላቸው እሷ የሰው ሰው አንድ ቀን እስር ቤት አሳደረች እንጂ!!

ሁሉም ሰው የእኔ እናት ትለያለች ነው የሚለው። የኔዋኮ የምር ትለያለች። እኛን ከወለደች በኋላ አይኔ እያየ ከዲፕሎም እስከ ኤም ኤ እንደተማረች ነግሬያችኋለሁ?

የእኔ እናት በሞተርባይክ እንደምትንቀሳቀስስ? አሁን መኪና ነው የምፈልገው ብላ መንጃፈቃዷን ያወጣች ሰው ናት!!

እናትዬ ታማ ተኝታ ወላ እያቃሰተች በጆሮዋ ጠጋ ብዬ «እናቴ ምን ልስራልሽ? ምን ትበያለሽ?» ስላት ካንዳንድ «ጥሬ ስጋ በዳጣ!» እንደምትልስ?

በፊት በፊት ጓደኞቼ እቤት ሲመጡ እንደሌላ እናት <ልጆቼ ምን ይቅረብ > ምናምን አትልምኮ! ሴቶች ከሆኑ! «የምትፈልጉትን ልጆቹን ጠይቁ እና ሰርታችሁ ብሉ። ሁሉም ጓዳ አለ ገልበጥ ገልበጥ በሉ!» ብላ ታስደነግጣቸዋለች። 🤣🤣(እናትዬ አሁን ጓዳ ራሷ ገብታ አብስላ ስታቀርብ ማሚዬማ አረጀሽ! እላታለሁ!!)

በዊልቸር የሚሄድ ወንድም እንደነበረኝ ነግሬያችሁ አውቃለሁኣ? እንደእናት አስቡት!! እቤቷ ነፍ የምትነጫነጭበት ነገር እያላት ቢሮዋ ስትገባ ዝንጥ ብላ ቁርጥ ፀጉሯን ቀለም ተቀብታ ኮቷን ደረብ አድርጋ ውልክፍ ያለ ነገር በህይወቷ ያለ አትመስልም። የሚያውቃት ሁላ <ታድላችሁ እናታችሁ ናት?> ይለናል።

ድፍረት ፣በራስ መተማመን ፣ራስን መቻል ………. መክራኝ ሳይሆን ኖራ ነው ያሳየችኝ።

ድህነት አትወድም! ወየው እንደሷ ድህነት የሚጠላ የለም!! ሽሮ እየበላችኮ አክት የምታደርገው እንደቀዳማዊ እመቤት ምናምን ነው! እግዜሩም የልቧን አይቶ የምትፈልገውን ህይወት ሰጣት! (በነገራችሁ ላይ ፈጣሪ ፀሎቷን ሲሰማት ፤ እሷም ስታምነው! እርግጥ አንዳንዴ <አይ አበዛሽው!> የሚላት ይመስለኛል። ወላኮ ስልክ ተበላሽቶ ስልክ ላይ ጭና የምትፀልይ ሴትዮ ናት!!🤣🤣🤣)

እናቴ ለእኔ ደግሞ ትለያለች። እኔ ቀና እንድልላት እሷ የእኔን ሸክም ተሸክማልኛለች።

በቀደም አባቴ ጥርሱን መታከም ፈልጎ ዴንቲስት ጓደኛዬጋ ላኩት። በኋላ ጓደኛዬ ደወለልኝና

«አባትሽ በጣም ዝምተኛ ፣ ትሁት፣ ሲበዛ ስነስርዓት የሚያበዙ ናቸው። አንቺ ከምንአባሽ ወጥተሽ ነው እንዲህ እሳት የሆንሽው በመድሀንያለም?» አለኝ።

«እናቴን ልላክልህና ይገለጥልሃል።» አልኩታ!!

የእኔ እናት ረጅም አመት ኑሪልኝ!! ልኑርልሽ እና የተመኘሽው ምንም አይቅርብሽ!!

መልካም የእናቶች ቀን!!!

5 months ago

«በጠዋት ስትነሳ ስጫት ብሎ ይሄን ወረቀት ሰጥቶኝ ነበር ትናንት! ምነው አመመው እንዴ?» አለችኝ ወረቀቱን እያቀበለችኝ።
«እባክሽ ይሄ ከንቱ ሞተ ብለሽ እንባሽን አታባክኚ! ሞት መጥፎ ነገር ነው ያለ ማን ነው? ማን ያውቃል ከህይወት የተሻለስ ቢሆን! በህይወቴ አንድ ቁምነገር ሰርቼ ባልፍ ትይኝ አልነበር? መፃፋችንን ጨርሺው። ልጆቼን አደራ! ስወድሽ ኖሬያለሁ!!»
የሆነ ጊዜ ላይ ስለሞት ያወራኝን አስታወስኩት። ከ80 ዓመት በላይ መኖር አልፈልግም ይለኝ ነበር ሁሌ። ምክንያቱም መዝረክረክ ስለማይፈልግ!
«ሞትን እንደመጥፎ ነገር የምናየውኮ ማንም ከሞት በኋላ ያለውን ህይወት ስለማያውቅ ነው! ሰው ሲሞት በህይወት ያለው ሰው የሚቀርበውን ስለሚያጣ ሞትን ክፉ ነገር አድርጎ ያወራዋል። ለምሳሌ አስቢው በህመም ሲሰቃይ ለነበረ ሰው ሲሞት ማልቀስ ልክ ነው? ሰውየውኮ ስቃይ ላይ ነበር? የምናለቅሰው ሰውየው ስለተገላገለ ነው? ለራሳችን ነው ለሰውየው ነው የምናለቅሰው? ደግሞስ ከሞት በኋላ ያለው ምናልባት ከህይወት የተሻለ ሁላ ቢሆንስ?» ብሎኝ ነበር። ጭራሽ ድምፅ አውጥቼ እያለቀስኩ።
«እሺ ይሁንልህ! የተሻለ ይሁንልህ!» ብዬ በቂጤ መሬቱ ላይ ተዘረፈጥኩ!!
……………………………ጨርሰናል!!!! ………………………………………..
(ደስ ይለኝ የነበረው ኮመንት ቦክሱን ዘግቼ ብጠፋ ነበርኮ!! )
ቻዪው ሜዬ ቻዪው 🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️🏃🏽‍♀️

We recommend to visit

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

-የዝዉዉር ዜና
-የአሰልጣኞች አስተያየት
-ጎሎች እና አዝናኝ ቪዲዮዎች
-የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
-ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

አስተያየት ካሎት @ZENA_ARSENAL_BOT

ለማስታወቂያ ስራ +251911052777

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @MKHI7

Last updated 4 months ago

The voice of Ethiopian football

For Adverisment ONLY : +251940018801

Last updated 4 months ago

ይህ እግር ኳሳዊ መረጃዎችን በፍጥነት የሚያገኙበት #DREAMSPORT ነው።

- የሀገር ውስጥ ዜናዎች
- የአውሮፓ ሊግ መረጃዎች
- ትኩስ ትኩስ የዝውውር ዜናዎች
- ጨዋታዎችን ከየስታድየሞቹ በቀጥታ
- የተጫዋቾች የህይወት ታሪክ

ለማስታወቂያ ስራ @Van_Lapara ላይ አናግሩን።

Last updated 4 months ago