ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 days, 23 hours ago
Last updated 4 days, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 2 days ago
ሞቅ ሞቅ አድርጉት ግዙፉን የሀገሪቱን ማስልጠኛ ተቋምኮ ነው የተቆጣጠርነው💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
ብርሸለቆ መኮድ ታሪክ ተሰርቷል💪💪💪💪
ሰከላ‼️
በአሁኑ ሰዓት መከላከያ እየተንቀሳቀሰ ስለሆነ ጥንቃቄ አድርጉ።
አሁን አምቢሲ አካባቢ እየደረሱ ነው።
በአስገዳጅ ብሔራዊ ውትድርና ስም በሚደረግ ጭፍጨፋ እና በኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ደም የሚፀና ስልጣን አይኖርም!!!
አፋጎ (AFG)
`````````````
የውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኘው የብልጽግናው አገዛዝ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በከተሞች የሚገኙ የቀን ሰራተኞችን፣ የትምህርት ገበታ ላይ የተቀመጡ ህጻናትን፣ አስተማሪዎቻቸውንና የመንግስት ሰራተኞችን የፋኖ ደጋፊ ናችሁ በሚል ሰበብ በገፍ እያፈሰ የተሀድሶ ስልጠና በሚል ያዘጋጀውን ማደናገሪያ በመጠቀም አስገድዶ ወደ ማጎሪያ ካምፖች ሲያግዝ የቆያቸውን ወጣቶች ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት በማጓጓዝ ላይ ነው።
ከአማራ ክልል እያፈሰ ወደ አልታወቀ ቦታ የሚወስዳቸውን ወጣቶች በርሃብ፣ በበሽታና በድብደባ አለፍ ሲልም ሰበብ እየፈጠረ በመረሸን እንደሚያጠፋቸው የታወቀ ነው። ለዚህም በአማራው ህዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በጀግናው የአማራ ፋኖ ሃይል በተደመሰሰ ቁጥር በመኖሪያ ቤታቸው፣ በአደባባይ ቦታዎችና በቤተ እምነቶች የሚማሩ የአብነት ተማሪዎችን፣ ህፃናትና አረጋውያንን አማራ በመሆናቸው ብቻ በጅምላ ሲረሽን መክረሙ በቂ ማሳያ ነው። ሰሞነኛው የአብይ አህመድ አፈሳም የጀርመኑ ናዚ በአይሁዳውያን ላይ ሲፈፅመው እንደነበረው የኦሺዊትዝ የእገታ ማዕከል የሚታይ አማራን ወጣት አልባ ህዝብ በማድረግ ለማጥፋት የሚደረግ አፈሳና እመቃ በመሆኑ የተለመደ የውትድርና አፈሳ ነው ብሎ መዘናጋት በራስ ላይ ሞት እንደማወጅ ያለ ነው።
ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን ሁሉ የስልጣን ማስጥበቂያ ዕቃዎች እንደሆኑ አድርጎ የሚቆጥረው ይህ አገዛዝ ይህንን የአፈሳ ተግባሩን እንደ አማራ ክልሉ ሁሉ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያለምንም ሃፍረት በማናለብኝነት እያከናወነ ይገኛል። ይህ የአገዛዙ ተግባር የሃገሪቱን አምራች ዜጎች በጅምላ በመጨፍጨፍና ወደ ወታደራዊ ካምፕ በማጋዝ እርስ በእርስ በማጫረስ ወጣት አልባ ሃገር ለመፍጠር አረመኒያዊ ተግባር እየፈፀመ መሆኑን በግልፅ ያሳየበት ነው።
ከኦሮሚያ አካባቢ የሚያፍሳቸውን ወጣቶች በዘረኝነትና በፀረ አማራነት እየቀሰቀሰ "የኦሮሞ መንግስት ነው፤ መንግስታችሁን ከመውደቅ አድኑት" እያለ አገሪቱን ወደ ባሰ የእርስ በርስ ጦርነት ለማስገባት ቆርጦ መነሳቱንና የወጣቶችን አዕምሮ እየበረዘ በማታለል ማሰለፍ ያልቻለው ብልፅግና በግድ እና በሽብር የሃሰት የግድያ ፈጠራዎችን አቀናብሮ ቪዲዮ በማሳየት፣ በካድሬዎቹ በኩል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በግድ ሰልፍ በማስወጣት ሽብርና ግርግር በመፍጠር የኦሮሞን ህዝብ ጭምር እረፍት እየነሳ ይገኛል።
ስለሆነም-
ሰሞነኛው አፈሳ አስገዳጅ ብሄራዊ ውትድርና ሳይሆን አማራን በአንድ ላይ ማመቅና ሲስተማቲክ በሆነ መልኩ በተለያዩ ስልቶች ወጣት አልባ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተረድቶ መላው የአማራ ህዝብ የአገዛዙን ህገ ወጥ ድርጊት ተቃውሞ እንዲቆም፣ በተለይ ወጣቱ ጨርቄን ማቄን ሳይል በየአካባቢው በሚገኘው የፋኖ አደረጃጀት ውስጥ በመካተት ራሱንና ህዝቡን ከጥፋት እንዲያድን ጥሪ እናቀርባለን።
የደርግ ዘመን ብሄራዊ ውትድርና ማንኛውም ዕድሜና ጤናው የሚፈቅድለት ዜጋ አገሩን በውትድርና የማገልገል ግዴታ አለበት በሚል በአዋጅ የተደገፈ ነበር። ይሁንና ከመብት አኳያ ያለ ግለሰቦች ይሁንታ የሚፈፀም ትክክል ያልሆነ ተግባር ቢሆንም በይፋ የታወቀና ሌላ የተለየ ሥጋት የሚፈጥር አልነበረም። የደርግ ብሄራዊ ውትድርና ተቀባይነት ስላልነበረው ውጤት ማምጣት አልቻለም። ይልቁንም ውድቀቱን እንዳፋጠነው የቅርብ ታሪካችን ነው። "በፊት የበቀለውን ጀሮ በኋላ የበቀለው ቀንድ በለጠው" እንዲሉ የብልፅግናው አገዛዝ ከደርግ ዘመን በከፋ ሁኔታ ወጣቶችን በጅምላ እያፈሱ ወደ ወታደራዊ ካምፖች እያስገባ ነው። ድርጊቱም የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለመጠበቅ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንን እርስ በእርስ ለማጫረስ ያለመ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ይህንን የአገዛዙን ሴራ ተረድቶ በጋራ በመቆም ድርጊቱን እንዲያወግዝ ጥሪ እናቀርባለን።
በኦሮሚያና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች የምትገኘ ኢትዮጵያውያን አፈሳው አብይ አህመድን ስልጣኑን ለማስጠበቅ የሚፈፅመው አረመኒያዊ ተግባር እንጅ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል በመፍጠር የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ በማሰብ አለመሆኑን ተገንዝባችሁ በአማራ ህዝብ ላይ ለከፈተው ጦርነት ተባባሪ እንዳትሆኑ፣ ልጆቻችሁንም እንዳታስጨርሱ ይልቁንም ከአማራ ህዝብ ጎን እንድትቆሙ ጥሪ እናቀርባለን።
ዓለምአቀፉ ማህበረሰብና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ይህን ይፋ የሆነ ህገ ወጥ ድርጊት እንዲያወግዝና ከህዝባችን ጎን እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን።
ፎቶው:- በዘመቻ መቶ ተራሮች እጅ የሰጡ ምርኮኞችን ለአንድ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኛ ስናስጎበኝ የተወሰደ ነው።
አስረስ ማረ ዳምጤ
የግልባጭ ትርጉም‼****
በጦር እያመሰ ሰላም ነው ማለቱ፣
ድህነት ገብቶብን እድገት ነው ማለቱ ፣
ይህ ነው ማይገናኝ ትርጉም መምታታቱ።
ደመወዝን በስልት ቀንሶ በግማሽ ፣
ጨመርኩልሽ ይላል ህዝቤ ሆይ ሲያሞኝሽ ፣
ገነባሁሽ ይላል ሀገሬ ሲያፈርስሽ።
የሰው ቤቱ ፈርሶ ወጥቶ ጎዳና፣
የግልባጭ ትርጉም ይህ ነው ብልፅግና።
ቤት ፈርሶ መዝናኛ ሆድ ተርቦ ውበት፣
ይህ ነው ብልፅግና ይህ ነው የሀገር እድገት።
ሰው ከሰውነቱ ከክብሩ ተዋርዶ፣
በቀለም ዘርፍ ስንጥቅ በብሔር ተቀዶ፣
ፍቅር ተሸርሽሮ አንድነት ተንዶ፣
ይህ ነው ...
የግልባጭ ትርጉም ደስታ መሳይ መርዶ።
ታሪክን አጥፍቶ ትርክትን ፈጣሪ ፣
የእድገት መንገድ ብሎ ተንኮልን ቀማሪ፣
በፊደላት ፋንታ ብሔር አስቆጣሪ፣
ይህ ነው...
የግልባጭ ትርጉም የመርዶ ዱብዳ ደስታ ብሎ አብሳሪ።
ወደ ጥልቁ ስንወርድ በላያችን ጭነን የዘመናት መርገም ፣
ሀገር እድገት ላይነች ፈጥረናል ይለናል ፍፁማዊ ሰላም።
ከአለም ፍጥረታት የሰው ልጅ ክብሩ አንሶ ፣
በመደመር ስሌት ሰውን በመሳሪያ በመግደል ተቀንሶ፣
የመዋኛ ገንዳ መዝናኛ ይለናል መቃብርን ምሶ።
ሀገር ስትመራ ፊደላት ባለዬ በእኔ አውቃለሁኝ ባይ ፣
ህዝብ ሲስተዳደር በአሸባሪ ቡድን በንፁሀን ገዳይ ፣
አያገባችሁም አታውቁም ስንባል በሀገራችን ጉዳይ።
ገነት መሳይ ሲኦል ሲገነባ ሲሰራ ገሀነም፣
ታድያ ይሄ እኮ ነው ፍፁም ማይገናኝ የግልባጭ ትርጉም።
አስቼኳይ መረጃ‼****
አመሻሹን ጨለማን ተገን በማድረግ ብዛት ያለው የአገዛዙ ጥምር ጦር ከአድስ ቅዳም ከተማ ወደ ፋግታ አቅጣጫ መንቀሳቀሱን የአይን እማኞች አረጋግጠውልናል። ፋግታዎች የኤፍሬም አጥናፉ ፍሬዎች ጥንቃቄ አይለያቹህ ስንል እናሳስባለን‼
መረጃ‼️
ከባህርዳር የተነሳ አራዊት ሠራዊት በጥዋቱ 12:43amወደ ጎንደር 👉 አቅጣጫ ወጧል 1ዙ 23 ሌሎች በካሱኔ የተጫኑ ናቸው በ 5መኪና ፍጥነት አላቸው እስኪ share አድርጉት እንደ ተለመደው በስልክም አድርሱ‼️
#የአማራ ድምፅ ሚዲያ
ይጠረግ መንገዱ‼
ለአንድነቱ ጉዞ ይጠረግ መንገዱ፣
አንድ ሁነን እንጥረግ ቆሻሻወች ይፅዱ።
ይዞ የሚያስቀረን ወደፊት እንዳንሮጥ፣
እሾኹ ይነቀል ቀንጣፋው ይቆረጥ፣
ይጥፋ መሰናክል ከሴራው ለማምለጥ፣
ጩኸታችን ይርገብ እስኪ እንደማመጥ።
በሀሳብ ብንለያይ አንድ ሁኖ አላማችን፣
እየተጓተትን ሳንደርስ እንዳንቀር ካሰብንው ግባችን፣
ንግግር እናድርግ የችግሩ መፍቻ መክፈቻ ቁልፋችን።
በሀሳብ ልዩነት መንገዳችን ጠቦ ከምንገፋፋ፣
እስኪ እንነጋገር ችግሩን እንፍታ መንገዳችን ይስፋ።
ድር ቢያብር አይደለ አንበሳ የሚያስር፣
እኛም እንደ ድሩ በአንድ እንጋመድ እስኪ እንተባበር።
ስለዚህ ወገኔ ወሎዬው ጥራና ንገረው ለሸዋ፣
ጥቁር ጣሊያን ጥለህ ታሪክ እንድትሰራ ዳግማዊ አድዋ።
የሸዋው ጥራና ንገረው ለጎጃም፣
ለመብትህ ሚቆም የሚታገልልህ ከአንተ በላይ የለም።
ጎጃሜው ጥራና ንገረው ለጎንደር፣
የሀገሬ ሰው ይላል ሀገር ነፃ አይወጣም ሀገር ሳይሸበር።
ታሪካችን ሳይሆን እንዴ ሶስቱ በሬ፣
አንድነትን አብስር አንድ ሁን ሀገሬ።
ወሎዬ ነው ሸዋ ይሔኛው ከጎንደር፣ይሔ ደግሞ ጎጃም፣
ጠላት የሚገድልህ በጎጥህ ከፋፍሎ እየጠራ አይደለም፣
አማራ ብሎ ነው በምትኮራበት በማንነትህ ስም።
በአሳምነው ፅጌ፣በእነ ጎቤ መልኬ በአስቻለው ብላችሁ፣
በሞላ ደሰዬ፣፣በአሸናፊ አለሙ በጀግናው ብላችሁ፣
በቢሆን መሀመድ፣በውባንተ አባተ በጀግናው ብላችሁ፣
በሁሉም ሰማዕታት በጓደኞቻችሁ፣
በእየሱስ ክርስቶስ ፣በማርያም ብላችሁ፣
ኧረ እደው በአላህ በዘወልድ ብላችሁ፣
ብስራትን አብስሩን አንድ ላይ ሁናችሁ።
መልዕክቴ ይተላለፍልኝ.....
ሰሞንኛ ጉዳዩ በመንግስት እጅ የተያዘ ነው ፤ በ highschool ያሉ ተማሪዎችም አመፁን እንዲቀላቀሉ እየተደረገ ነው ፤ ለምሳሌ በአራዳ ክ/ከተማ ካሉት ፪ኛ ደረጃ ት/ቤቶች አንዱ piassa 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፊትለፊት የሚገኘው ቤተልሔም ት/ቤት ነው ። በዚህ ት/ቤት በtiktok ከ500,000 follower በላይ ያላቸው ሴት የኦሮሞ ዲጂታል የመንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ ተማሪዎች አሉ ፤ ትላንት ሰላሌ በተፈጠረው ጉዳይ የቤተልሔም ተማሪዎቹ ለዛሬ ጥቁር ለብሰው እንዲመጡ መልዕክት አስተላልፈው ዛሬ ሁሉም ኦሮሞዎቹ ጥቁር ለብሰውና ልጁን ተነቅሰውት በታቶ መጡ....
ዛሬ ከሰዓት ደሞ የኦሮሞ ር/መ/ራንና ኦሮሞ የሆኑት አስተባባሪ unit leaders ለማታ 11:00 አዳነች አበቤ ቢሮ ለተልዕኮ ተጠርተዋል ....ምን ተልዕኮ ይዘው እንደሚመጡ ፈጣሪ ይወቀው ....
ነገሩ የተያዘው በመንግስት ነውና አማራ የሆነ በተለይ አ/አ እና ኦሮሚያ ራሱን ያዘጋጅ....
አፈሳውም የዛሬው ይለያል ለምሳሌ piassa ሲያፍሱ ነበር በተለይ አማራ እና ኤርትራዊያንን እያደኑ።
ከተመልካች
መረጃ‼
በደቡብ ጎንደር ስማዳ ወረዳ ከ10 በላይ የአገዛዙ ኮማንዶዎች ፋኖን ተቀላቅለዋል!!
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 days, 23 hours ago
Last updated 4 days, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 2 days ago