Elias Meseret

Description
Journalist-at-large

We recommend to visit

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

-የዝዉዉር ዜና
-የአሰልጣኞች አስተያየት
-ጎሎች እና አዝናኝ ቪዲዮዎች
-የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
-ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

አስተያየት ካሎት @ZENA_ARSENAL_BOT

ለማስታወቂያ ስራ +251911052777

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @MKHI7

Last updated 2 days, 13 hours ago

3 days, 16 hours ago

ከማህበራዊ ሚድያ አልፎ አልፎ ራቅ ማለት (detox) ለጤናችን እና ለማህበራዊ ግንኙነታችን መልካም ነው!

በሉ ቻናሉ ለትንሽ ሳምንት 🔒 ነው!

ቸር ሰንብቱ 👋👋

3 days, 17 hours ago

ጠዋት ስለ ጅግጅጋ ባቀረብኩት መረጃ ላይ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ መልስ ሰጥቷል!

በደፈናው ከማስተባበል እና ሀሰት ነው ከማለት ይልቅ "አልፎ አልፎ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ የሚሞክሩ አካላት ላይ [ክልሉ] ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ እናስታውቃለን" የሚለው ለመፍትሄው ቅርብ ነው።

@EliasMeseret

3 days, 20 hours ago

ጥቆማ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ!

ማህበራዊ ሚድያ ላይ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ተከታትሎ መልስ በመስጠት ኢትዮ ቴሌኮምን የሚያክል መስሪያ ቤት እስካሁን በሀገራችን አላየሁም። በጎረቤት ሀገራት እንኳን ዜጎቻቸው ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ ጥያቄዎችን በማቅረብ ይስተናገዳሉ... በተለይ ውሀ፣ መብራት፣ ባንክ፣ አየር መንገድ፣ ቴሌኮም ወዘተ አገልግሎቶች።

የሀገር ኩራት የሆነው አየር መንገዳችን በዚህ ዙርያ መልሶችን አንዳንድ ግዜ ሲሰጥ ብንመለከትም በቂ እንዳልሆነ መታዘብ እንችላለን። በምስሉ ላይ እንደሚታየው በአለም ዙርያ ያሉ ግለሰቦች ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ ተከታትሎ መልስ የሚያቀርብ አሰራር ማደራጀት የዘመናዊ ተቋም አንዱ መለያ ነው።

በቅርቡ ለውጥ እንደምናይ ተስፋ አረጋለሁ።

@EliasMeseret

2 weeks, 5 days ago

⬆️
በኢድ- አልፈጥር በዓል ላይ የጭስ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተጠረጠረው የፖሊስ አባል ፍርድ ቤት ቀረበ!

የፌደራል ፖሊስ አድማ ብተና ዘርፍ አባል የሆነው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ከትናንት በስቲያ ሰኞ በአዲስ አበባ በተከበረው የኢድ- አልፈጥር በዓል ላይ በመስቀል አደባባይ የሰማዓታት መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ ከፈነዳው የአድማ በታጭ የጭስ ቦንብ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውሎ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ዛሬ ረፋድ ላይ ቀርቧል።

መርማሪ ፖሊስ ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በኢዳል አፍጥር በዓል ዕለት በተመደበበት ወንጀል የመከላከል ምደባ ላይ እያለ የታጠቀውን አድማ በታኝ የጭስ ቦንብ በአግባቡ መታጠቅ ሲገባው በአግባቡ ባለመታጠቅ የጭስ ቦንቡ እንዲፈነዳና ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር አድርጓል ያለው መርማሪ በዚህ በተፈጠረ ሁከትና ብጥብጥ የመንግስትና የግለሰብ ንብረት ጉዳት መድረሱንም አብራርቷል።

በተጠረጠረበት ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት ወንጀል ለተጨማሪ ማስረጃ አሰባስቦ ለመቅረብ 14 ቀን እንዲሰጠው መርማሪው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በበኩሉ በዕለቱ አስቀድሞ በተመደበበት ቦታ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ እንደነበር እና በሰዓቱ በቦታው ላይ የነበሩ ሰዎች ቁጥር መጨመርና መጨናነቁን ተከትሎ ከታጠቀው ሶስት አድማ በታኝ የጭስ ቦንብ ውስጥ አንደኛው በማያውቀው ሁኔታ መሬት ላይ ወድቆበት በድንገት መፈንዳቱን ገልጿል።

ሆኖም ምንም አይነት ተንኮልም ሆነ ክፋት በውስጤ አልነበረም ወድቆ ሲፈነዳ እኔ እራሴ ደንግጬ ነበር ሲል እያለቀሰ ሁኔታውን ለችሎቱ አስረድቷል።

በተጨማሪም ተጠርጣሪው ወላጆቹን በሞት ማጣቱን ገልጾ እህትና ወንድሙን በሱ እርዳታ እያስተማራቸው እንደሆነ እና ከለሊት 7:00 ጀምሮ ለጥበቃ ስራ ከመሰማራቴ ውጪ ሌላ ክፋት በውስጤ የለም ሲል ለችሎቱ አብራርቷል።

ጉዳዩን የተከታለው ፍርድ ቤቱ ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ 14 ቀን የፈቀደ ሲሆን ለግንቦት 10 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ምንጭ : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ/Tikvah
@EliasMeseret

2 weeks, 5 days ago

⬆️
የዛሬውን የአለም የፕሬስ ነጻነት ቀን ሳስብ...!

ልክ የዛሬ ሶስት አመት በዛሬው ቀን የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ግዜ ተከብሮ ነበር። መሪዎች፣ የሚድያ ሰራተኞች፣ ዲፕሎማቶች፣ የሲቪክ ማህበራት እና የሀይማኖት አባቶች የተገኙበት ይህ ዝግጅት እጅግ ተስፋ ያረግኩበት ብቻ ሳይሆን በጋዜጠኝነት ሙያዬ ያጋጠመኝን ችግር ሁሉ ያስረሳኝ ነበር ማለት ይቻላል።

በወቅቱ ይህን ተስፋ የሚሰጥ ዜና እሰራበት ለነበረው አለም አቀፍ ሚድያ ፅፌ ነበር: https://apnews.com/article/9591968b2a804c009a04da9edc8dc6f0

አሁንስ?

የዛሬ ሶስት አመት "አንድም ታሳሪ ጋዜጠኛ የሌለባት ሀገር" ተብላ ተወድሳ የነበረችው ሀገራችን አሁን ላይ ወደቀደመው፣ ወይም ከቀደመው ወደባሰው ስፍራ ተመልሳለች። ጋዜጠኞችን ማሰር ብቻ ሳይሆን ለበርካታ ቀናት እና ሳምንታት ደብዛቸውን ማጥፋት፣ ለወራት አስሮ ቆይቶ መፍታት፣ ዛቻ እና ማስፈራርያ መስጠት፣ በተከፋይ አክቲቪስቶች ስም ማስጠፋት ወዘተ ፋሽን ሆኗል። አሁን ላይ ትንሽ ለየት የሚያረገው ጋዜጠኛ ሲታሰር "ጥሩ ነው፣ እሰየው" የሚለው መብዛቱ ነው።

በግሌ የሚገርመኝ ደግሞ ከዛሬ አራት፣ አምስት እና ስድስት አመታት በፊት በየቢሯቸው እየጠሩ ጋዜጠኞችን ለማስፈራራት ይሞክሩ የነበሩ ቱባዎች አሁን ማልያቸውን ቀይረው ይህንኑ ስራቸውን ቀጥለዋል፣ እኛም ትዝብታችንን መዝግበን ይዘናል።

እርግጥ ነው ጋዜጠኝነት የትኛውንም አይነት ወንጀል ለመፈፀም መሸሸጊያ ሊሆን አይገባም፣ ሊሆንም አይችልም። ጋዜጠኞች ሲያጠፉ እንደማንኛውም ዜጋ በህግ ሊጠየቁ ይገባል። ነገር ግን የጋዜጠኞችን ደብዛ ማጥፋት እና ስሜ ለምን ተነሳ በሚል ቂም በቀል ጭምር የሚፈፀሙ ወንጀሎች ሊቆሙ ይገባል። ሁሉም ጋዜጠኛ እንደሌላው ዜጋ ፍርድ ቤት የመቅረብ፣ በቤተሰብ የመጎብኘት እና ፍትሀዊ ዳኝነት የማግኘት መብት አለው።

Period!

@EliasMeseret

3 weeks, 3 days ago

ግድ የለም፣ ለሚያልፍ ቀን የማይሽር ጠባሳ ትተን አንለፍ!

ለማህበረሰብ አንቂ ተብዬ አቀሳሳሪዎች ፈጣሪ ልቦናውን እና ማስተዋሉን ይስጥልን። ያሉብን ችግሮች ያነሱን ይመስል አብዝተው ሊጨምሩልን ለሚታትሩት ደግሞ በቃችሁ እንበላቸው... በትክክል ስለበቃን፣ ቋቅ ስላለን።

@EliasMeseret

1 month ago

ከሰሞኑ ባጋራሁት የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙርያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ አንድ የስራ ሀላፊ ጋር ዛሬ አውርቼ ነበር!

ኤጀንሲው በዚህ ድርጊት የተሳተፉ በርካታ ሰራተኞች ላይ ክትትል እያረገ እንዳለና በአንዳንዶች ላይም ክስ እንደመሰረተ ሀላፊው ጠቁመዋል። ህብረተሰቡ ጥቆማ ሲኖረው 7533 የነፃ የስልክ መስመር ላይ መረጃ መስጠት እንደሚችል ተናግረዋል።

@EliasMeseret

1 month ago

ልጆቹ የተሸለሙት እስከ 2.5 ሚልዮን ዶላር ሳይሆን ከአንደኛ ባች ለተካፈሉ እና አንደኛ ለወጡ 3,000 ዶላር፣ ሁለተኛ ለወጡ 1,500 ዶላር እንዲሁም ሶስተኛ ለወጡ 1,000 ዶላር ነው!

ያልተሰጣቸውን ገንዘብ ተሰጥቷል ማለት የልጆቹ ሞራል ላይም ጉዳት ያደርሳል፣ ይታሰብበት።

Story via @EthiopiaCheck
@EliasMeseret

1 month ago

ትናንት በቦሌ ኤርፖርት ከተጓዦች በህገወጥ መንገድ ስለሚጠየቅ ገንዘብ ያጋራሁትን መረጃ ተከትሎ እጅግ በርካታ ተመሳሳይ ድርጊቶች እዛው ኤርፖርትም ሆነ ሌሎች መስሪያ ቤቶች ውስጥ ያጋጠማቸው ግለሰቦች መረጃ አጋርተውኛል።

አንዳንዶቹ አሳዛኝ፣ አስደንጋጭ እና ለማመን የሚከብዱ ጭምር ናቸው። አቅም በፈቀደ መጠን አንዳንዶቹን ተከታትዬ ለማቅረብ እሞክራለሁ፣ ሚድያዎችም ይህንን እየተከታተሉ ቢያቀርቡ መልካም ነው። ህዝቡ በሙሰኞች እና ህገወጦች ምርር ብሎታል።

የሚመለከታቸው አካላትም ራሳቸውን ሊፈትሹ ይገባል። ማህበራዊ ሚድያ ላይ መረጃ ስለወጣ ብቻ ሳይሆን በራሳቸው ግዜ እና አቅም ምርመራዎችን በማድረግ እነዚህ የህዝብን አንገት አንቀው ያሉ ህገወጦችን ሊያስወግዱ እና በህግ ሊጠይቁ ይገባል።

አንድ ሰው በዜግነቱ ሊያገኝ የሚገባውን አገልግሎት ለማግኘት ገንዘብ ለምን ይከፍላል? በመንግስት ሚድያዎች ስለ ሙስና ተደጋግሞ ቢዘገብ እና ውይይት ቢካሄድ መፍትሄ አይሆንም። እነዚህ ህዝብን አንቀው ያሉ አካላትን አንቆ በህግ መጠየቅ የግድ ይላል።

@EliasMeseret

2 months ago

እስቲ ደግሞ ለተወሰነ ግዜ ከማህበራዊ ሚድያ እረፍት!

ከማህበራዊ ሚድያ አልፎ አልፎ ራቅ ማለት (social media detox) ለጤናችን እና ለማህበራዊ ግንኙነታችን መልካም ነው። ከዚያም አልፎ አካባቢያችንን እንድንቃኝ እና ትርፍ ግዜ አግኝተን አንዳንድ ስራዎችን እንድንሰራ እድል ይፈጥራል። አእምሮን ከመረጃ ጋጋታ ነፃ ማድረግ በራሱ ቀላል አይደለም።

ለተጨማሪ ንባብ: https://www.lifehack.org/483829/9-positive-benefits-of-a-social-media-detox

እኔም detox ላድርግ መሰለኝ፣ ቸር ሰንብቱ 👋

@EliasMeseret

We recommend to visit

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

-የዝዉዉር ዜና
-የአሰልጣኞች አስተያየት
-ጎሎች እና አዝናኝ ቪዲዮዎች
-የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
-ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

አስተያየት ካሎት @ZENA_ARSENAL_BOT

ለማስታወቂያ ስራ +251911052777

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @MKHI7

Last updated 2 days, 13 hours ago