ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Description
Journalist-at-large
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 23 hours ago

Last updated 4 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 2 days ago

2 months, 3 weeks ago

የሰሞኑን የብር መዳከምን (የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን) ተከትሎ ገበያ ላይ ያልጨመረ ነገር የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም

ይህ አልበቃ ብሎ የመንግስት ተቋማት ህዝብ ላይ እልህ እየተወጡ ይመስል ተራ በተራ እስከ 700 ፐርሰንት ጭማሪ ያረጉ አሉ።

ኢሚግሬሽን፣ ንግድ ባንክ፣ ኤሌክትሪክ፣ ውሀ፣ ቴሌ፣ አየር መንገድ፣ የመኪና ቦሎ እና መንጃ ፈቃድ፣ የትራፊክ ቅጣት... ከሰሞኑ ደግሞ የዳኝነት ክፍያ እንኳን ጭማሪ ይደረግበታል። የኔ ጥያቄ:

አንደኛ፣ ጭማሪ ሲደረግ ነባራዊ የህዝብን አቅም እና ችግር ማገናዘብ የለበትም ወይ?

ሁለተኛ፣ በሌላው አለም እንደምናየው progressive የሆነ የ10%፣ የ20%... ወዘተ እያለ ጭማሪ ይደረጋል እንጂ ሲፈልግ የ150%፣ ሲያሻው የ700% ጭማሪ ማድረግ ማለት ነው?

ሶስተኛ ደግሞ አንድ ሰሞን ሲወራ የነበረውን ጥቂት የሆነ የደሞዝ ጭማሪ እንኳን ተግባራዊ ሳያደርጉ ህዝብ ላይ ሸክም መጫን ለምን ተፈልጎ ይሆን?

እውነት ይሄ ነገር አንድ ወዳጄ እንዳለኝ "መንግስት ከህዝብ ጋር እልህ ተጋብቶ እየቀጣው ነው" ያለው እውነት ይሆን እንዴ?

ዝመት ሲባል ዘምቶ ለሚቆም፣ ደግፍ ሲባል በሚሊዮኖች ወጥቶ ለሚሰለፍ፣ ሀገርህ ተደፈረ ሲባል "ኢትዮጵያን!" ብሎ ለሚዘምት ግን ይህ አይገባውም።

@EliasMeseret

2 months, 3 weeks ago
[#ለግልፅነት](?q=%23%E1%88%88%E1%8C%8D%E1%88%8D%E1%8D%85%E1%8A%90%E1%89%B5) በትናንትናው እለት ለእታገኝ አየናቸው ያጋራሁትን …

#ለግልፅነት በትናንትናው እለት ለእታገኝ አየናቸው ያጋራሁትን የድጋፍ ጥሪ ተከትሎ ከ 375,000 ብር በላይ በቀጥታ በንግድ ባንክ አካውንቷ ተሰብስቧል። አንድ ዶክተርም ለታማሚው ልጅ ህክምና ለመስጠት ፈቃደኛ ሆነዋል።

ድጋፍ በማድረግ ለተካፈላችሁ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ።

2 months, 3 weeks ago
ይቺ እህታችን እታገኝ አየናቸው ትባላለች፣

ይቺ እህታችን እታገኝ አየናቸው ትባላለች፣

የዛሬ ሰባት አመት የተወለደው አንድ ልጇ የእድገት ውስንበት ያለበት ሲሆን መናገር እና መራመድ አይችልም። በስልክ እንደነገረችኝ የልጁ አባት ገና ውልደቱን ሳያይ ተለይቷታል፣ ስለዚህ ልጇን እያዘለች አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ቤተክርስቲያን በር ላይ ጧፍ እና ሻማ በመሸጥ ትተዳደር ነበር።

"አሁን ግን ልጄ 7 አመት ስለሞላው ተሸክሞ መዞሩ ከበደኝ፣ የተከራየሁበት አንድ ክፍል ቤት ገደል ስር ያለ ስለሆነ ይዞ መውጣቱ እና መውረዱ አቃተኝ" ያለችው እታገኝ አሁን አሁን የሚያመውን ልጇን ይዛ ምንም ማድረግ ስለማትችል 4 ሺህ ብር የቤት ኪራይ መክፈል እና ምግብ መግዛት እያቃታት እንደሆነ ትናገራለች።

ኪራይ እንዲቀንስላት ደባል ለመሆን ሞክራ ልጇ ማታ ማታ ስለሚጮህ ማንም ሊያስጠጋት እንዳልቻለም ታስረዳለች።

እታገኝን አቅም በፈቀደ እንደግፋት፣ ለማስጀመርያ እንዲሆን በአቅሜ ድጋፍ አደርጋለሁ።

በስልክ ለማግኘት የምትፈልጉ: +251923166298

Etagegn Ayenachew Kabte
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000536867817

*ፎቶው በፍቃድ የተለጠፈ ነው።

5 months, 3 weeks ago
5 months, 4 weeks ago

ሀይ ባይ ያጡት የኢትዮጵያ ባንክ ሹመኞች እና የምዝበራ ስራዎቻቸው

(በግል ከደረሰኝ ጥቆማ የተወሰደ ነው)

ዱሮ ዱሮ አይደለም የባንክ ባለስልጣን መሆን ተራ የባንክ ሰራተኛ መሆን እንደ ትልቅ ማዕረግ ይቆጠር ነበር። ለዛም ነበር ባንከሮች "Trust me, I am a banker" የሚሉት።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከወትሮ በተለየ አብዛኛው በተለይ የኢትዮጵያ የግል ባንኮች መደበኛ የባንክ ስራ መስራትን ወደ ጎን ትተው የወንበዴዎች እና ወንጀለኞች መፈንጫ ከመሆንም አልፎ በህዝብ ገንዘብ የተመሰረቱት እና ከድሃ ማህበረሰብ በተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ የሚንቀሳቀሱት እነዚህ ባንኮች ምዝበራዎቻቸው ልክ ከማጣቱ የተነሳ ህልዉናቸውን አደጋ ላይ እስከመጣል ደረጃ ላይ ደርሰዋል።

ይሄ ብቻ ሳይሆን በነዚህ ባንኮች ዉስጥ በሚደረገው ምዝበራ እና ጤናማ የንግድ ሂደትን ባልተከተለው የንግድ ሰንሰለት የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብን እያማረረ ከሚገኘው የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ዉደነት አስተዋፅኦአቸው ይህ ነው የማይባል ከፍ ያለ ነው። ለዚህ ህገወጥ እና ልክ ያጣ ድርጊታቸው ምክንያት የሆናቸው ደግሞ እጅግ ክፍት የሆነ የህግ ማዕቀፍ መኖሩ እና ባለፉት አመታት ከተቆጣጣሪ አካል (ብሔራዊ ባንክ, Finacial intelligence እና ሌሎች የመንግስት አካላት) ተገቢ ትኩረት ባለማግኘቱ ነው።

ሰሞኑን የበዛው የብሔራዊ ባንክ የመመሪያ ጋጋታም ይሄንኑ ክፍተት የተገነዘበ ይመስላል፣ ብቻ ያለፈው አልፎ የሚመጣውን ችግር ቢያስቀርልን የሚናቅ አይደለም።

ለማንኛዉም በነዚህ የግል ባንኮች ከፍተኛ ኃላፊዎች ከሚሰሩት ምዝበራዎች ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል:

  1. ለብዙ ሰው ለማመን በሚከብድ ደረጃ በዋናነት የ black ማርኬት ዋነኛ አዋዋዮች ወይም አገናኞች ሆነው የሚሰሩት እነዚህ ሹመኞች ተብለው የተሰየሙት የባንክ ባለስልጣናት ናቸው። ይሄም አሰራሩ እንዲህ ነው: መንግስት ኤክስፖርትን ለማበረታታት ለኤክስፖርተሮች ወደ ዉጭ ሀገር ልከው ከሚያስገኙት የዶላር መጠን ዉስጥ 30% እና በቅርብ ጊዜ ደግሞ 50% ለራሳቸው ለዕቃ አስመጭነት እንዲጠቀሙ መፍቀዱ ይታወሳል። ነገር ግን ሁሉም ላኪዎች አስመጪ ባለመሆናቸው ከሚደርሳቸው ዶላር ላይ ለተለያዩ አስመጪዎች በነዚህ የባንክ ሹመኞች አስተባባሪነት ከ black market ዋጋ ላይ በተሻለ መልኩ ያሻሽጣሉ፣ ይሄን በማድረግ ለነዚህ ሹመኞች በመልሱ ዳጎስ ያለ commission ይከፈላቸዋል። ከዚም አልፎ እንደምንሰማው ከሆነ ለአንዳንዶቹ ከዱባይ እስከ አሜሪካ ድረስ በቱጃር አስመጪዎች የመኖርያ ቤት በስጦታ መልክ ይገዛላቸዋል።

  2. በብዛት በዚህ ድርጊት ዉስጥ የሚሳተፉት ፕሬዝደንቶች፣ የብድር እና የዉጭ ንግድ ምክትል ፕሬዝደንቶች እና እስከ ዳይሬክተሮች የሚገኙት ናቸው። የእነዚህ ሹመኞች ምዝበራቸው በዉጭ ምንዛሬ ብቻ ቢቆም ጥሩ ነበር፣ ነገር ግን የተለያየ የህግ ክፍተትን ተጠቅመው ከድሀ የተሰበሰበውን ብር በቢሊየኖች የሚቆጠር መጠን በብድር መልክ የአንድ ግለሰብ ሀብት እና የንግድ አቅም ከሚችለው በላይ እንደፈለጉ ከ collateral free/clean base በሆነ እና የብሔራዊ ባንክ ሕግ ከሚፈቅደው ዉጭ ሲሰጡ ይስተዋላል። ይሄን በማድረጋቸው አንድ አንድ ተበዳሪዎች የወሰዱትን ብድር ጠቅላላ የአንድን ባንክ total capital እስከመድረስ የሚሄዱም አሉ። ይሄን ሁሉ ሲያደርጉ ባንኮቹ ቦርድ ወይም ተቆጣጣሪ አካል የላቸውም ወይ ልትሉ ትችላላችሁ፣ ግን እነዚ ሹመኞች እጃቸው በጣም እረጅም ከመሆኑ የተነሳ በየእርከኑ የሚገኝ የትኛዉንም አካል በጥቅማ ጥቅም እጅ የመጠምዘዝ ስራ ይሰራሉ ምክንያቱም ብር በነሱ እጅ ስለሆነ በስጦታ መልክ እንደውም አነስ ባለ ወለድ በብድር መልክ ሰዎችን አፍ የሚያስዙበት ከመኪና እስከ ቤት ድረስ ይጨብጣሉ። በስራቸው የማይተባበሩ ወይም እንቅፋት ይሆናሉ ብለው ያሰቡትን አካል ደግሞ በፈለጉበት ጊዜ ያባርራሉ፣ ወይም ያስፈራራሉ ወይም ከፊታቸው ዘወር ያስደርጋሉ። በተጨማሪ፣ አንዱ አካል አንዱን እንዳይጠይቅ (Check and balance እንዳይኖር) ለማድገረግ ከቦርድ እስከ ክፍል መሪዎች ከ10 ሚልዮን ብር እስከ 200 ሚልዮን ብር የሚደርስ የንግድ ብድር (commercial loan) ይሰጣጣሉ። በዚህ ሁሉ ግዜ ግን ታች ላሉ ሰራተኞቻቸው በዓመት አንዴ እንኳን ስልጠና ሳያሰጡ የቦርድ እና የባንክ አመራሩ በዓመት ከ 3-4 ጊዜ ተሰብስቦ ወደ ዉጭ ሀገር ሄዶ ለሳምንታት ተዝናንቶ ይመለሳል፣ ገንዘብ አባከንክ የሚላቸው ሰው የለም።

  3. እነዚህ ሀብታሞች በዚህ መልክ በሚያፈሩት ሀብት ሀገራቸው ውስጥ ቢሰሩበት ጥሩ ነበር፣ አብዛኞቻቸው ግን ወደ ዱባይ እና ወደ ሌሎች ሀገራት ሀብታቸውን በኤክስፖርት ስም ተጠቅመው የሀገር ሃብትን በገፍ ሲያሸሹ ይስተዋላሉ። በዚህ ድርጊት ዉስጥም የነዚህ የባንክ ባለስልጣናት ሚና ከፍ ያለ ነው። በዚህ ህገወጥ ምዝበራ ዉስጥ የሚሳተፉት ሁሉም ባንኮች ላይሆኑ ቢችሉም በሚያሳዝን መልኩ ግን ከዉጭ ጤናማ እና ብዙ ስም ያተረፉት የግል ባንኮች ዉስጣቸው ቢፈተሽ ከላይ ለመጥቀስ የሞከርኩት ችግሮች በመጠኑም ቢሆን የማይመለከታቸው ምናልባት ጥቂት ሊሆኑ ይችላሉ። በተጨማሪ አሁን በምናየው ተጨባጭ ሁኔታ ሁሉም የኢትዮጵያ የግል ባንኮች ማለት በሚቻልበት ሁኔታ ጤናማ የሆነ የባንክ ስራ ይሰራሉ ማለት እጅግ ያዳግታል፣ ምክንያቱም አብዛኞቻቸው ከጤናማ ፉክክርም አልፎ ደንበኞችን ለመሳብ/ለመነጣጠቅ በሚል ጥላ ስር ሆኖ ያልተገባውን ጥቅምን ትላልቅ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ለሆኑ የድርጅቶች ስራ አስኪያጆች እና ሌሎች ሰራተኞቻቸው የመኪና እና የቤት ቁልፍ በስጦታ መልክ (ከባንክ ወጪ አድርገው) እስከ መስጠት የደረሱም አሉ። አንዳንዶች ደግሞ ለደንበኞቻቸው ከሚፈቅዱት ብድር እና ዋስትና (guaratee)፣ commision ተደራድሮ ሲወስዱም ይስተወላል። ከዚ የተነሳ የአንዳንድ ደንበኞች ብድር ተበላሽቶ ሳይከፈሉ ሲቀሩ የተበላሸ ብድር (NPL) ዉስጥ ይመደባል። ከዚ ጋር ተያይዞ አንድ የተለመደ ቀልድ አለ ይባላል፣ የብድር ባለሙያዎች ብድር መክፈያ ጊዜ ለተበዳሪዎች ብድር ክፈሉ ሲሉዋቸው "ግማሹ እናንተ አለቃ ጋር ነው የቀረው፣ ከየት አምጥቼ እከፍላለው" ይላሉ።

  4. በዚህ የህዝብ እና የሀገር ሀብት ምዝበራ ዉስጥ በቀዳሚነት የሚሳተፉት እና ሲሳተፉ የከረሙ ግለሰቦች ወይም ባንኮች ስም መጥቀስ አስፈላጊ ስላልሆነ እሱን ለሚመለከተው አካል ትቼ ለጥቆማ ያህል በቅርቡ አንዱ ባንክ በዚህ ምዝበራ ወስጥ በመሳተፍ የባንኩን ስራ በእጅጉ ጎድተውታል በሚል ከዉስጥ በበረታበት ጫና አንዱ ባንክ የንግድ አገልግሎት እና የትላልቅ ደንበኞች ክፍል ምክትል ፕሬዚደንት የነበረውን ግለሰብ ያለ ምንም የሕግ ተጠያቂነት ማሰናበቱን መጥቀስ ይቻላል።

መልካም አዳር።

@EliasMeseret

5 months, 4 weeks ago

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተጠርጣሪዎችን ፎቶ በመለጠፍ "ሌባ ያዝኩ/ያዝን" የሚሉ ዜናዎችን በብዛት እያየን ነው

ተጠርጣሪን መያዝ፣ በህግ መጠየቅ እና ፍርድ ማሰጠት ያለ እና ወደፊትም የሚኖር ነው። ይሁንና አንድ ተጠርጣሪ ምን ይሁን ምን በህግ ፊት ነፃ ሆኖ የመገመት ህገ-መንግስታዊ መብት አለው። ፍርድ ቤት ወንጀለኛ ካለው በኋላ ይህ የሚቀየር ይሆናል።

ታድያ ከሰሞኑ "መና ከበደ" በተባለች ግለሰብ ላይ እንደደረሰው አይነት በጥርጣሬ ተይዞ፣ በህዝብ ዘንድ ሌባ ተብሎ ከዛ ነፃ እንኳን ቢባል ለደረሰበት በደል፣ የስም መጥፋት እና የሞራል ስብራት ማን ነው ተጠያቂው?

እንደሌላው ሀገር የገንዘብ መካሻ (compensation) የለ፣ በይፋ ይቅርታ የሚል የለ፣ ብቻ መጥፎ ስም ይዞ መኖር።

ፖሊስ ይህን አካሄድ በትክክል ቢያስብበት ይበጃል፣ ሁላችንም ደግሞ ለሰው ስም ከመስጠት በፊት ብናስብበት፣ ነግ በእኔ ነውና።

@EliasMeseret

5 months, 4 weeks ago

የሁለት ጋዜጠኞች ወግ...!

ጋዜጠኛ 1: በሀገሪቱ በተከሰቱ ግጭቶች፣ ስደቶች እና ውዝግቦች ዙርያ ደጋግሞ ዜናዎችን ሰራ፣ ህዝብም አድናቆትን ቸረው። ይሁንና ስራው በሀላፊዎች አልተወደደለትም፣ በዚህም ደጋግሞ ታሰረ፣ ማስፈራርያ ደረሰው። ጭንቁ ሲበዛበት ቤተሰቡን እና የሚወደውን ስራውን ጥሎ ለብቻው ተሰደደ። አሁን ቤተሰቡን የሚረዳበት እና በማያውቀው ሀገር ራሱን በምግብ እንኳን የሚችልበት አቅም የለውም። ቀን ይመሻል፣ ይነጋል፣ ከተስፋ ውጭ ምንም የለውም።

ጋዜጠኛ 2: ከኢህአዴግ ግዜ ጀምሮ ለባለስልጣናት ቅርብ ነው፣ ግጭቶች፣ ሞቶች እና መፈናቀሎች ሲከሰቱ ስለማይዘግብ ተወዳጅ ነው። ባለፉት ጥቂት አመታት ምንጩ ብዙም የማይታወቅ ከፍተኛ ሀብት አፍርቷል፣ ቦሌ ላይ 'Pent House'፣ አሜሪካን ሀገር ሲያትል ከተማ ውስጥ ደግሞ 'Town House' ገዝቷል። በበርካታ መቶ ሚልዮን ብር አንድ በመንግስት የሚሸጥ የስኳር ፋብሪካ ላይ ሼር ለመግዛት ጫፍ ደርሷል፣ መንግስትም በቅርቡ መሬት ችሮታል። እሱም በሌሎች ጋዜጠኞች እስር እና እንግልት ሲያሻው ያሾፋል፣ ሲለው ይሳለቃል።

የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ለጋዜጠኞች እንዲህ ናት... የሁለት ጋዜጠኞች ወግ!

@EliasMeseret

8 months, 1 week ago

አስተያየት እና ጥቆማ ለምታደርሱኝ፣

አካውንቶቼ ለተወሰኑ ሳምንታት ዝግ ሆነው ይቆያሉ፣ ሁሉንም መልእክቶቻችሁን ላልመለከት ስለምችል አቆዩልኝ።

መልካም ግዜ ??

@EliasMeseret

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 23 hours ago

Last updated 4 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 2 days ago