Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

Description
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago

1 month, 3 weeks ago

ሙያው በለገሰን ችሎታ የደረስንበት ከፍታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ሙያው ታሪክ ሠሪ ትንታጎች ፈጣሪ የዛሬውንም ሆነ የነገውን ትውልድ አኩሪ ዘመን ተሻጋሪ የመሆን ማንነትን ያጎናፅፋል፡፡

የኛ ትልቅ ጉልበት ሙያው የለገሰን እልፍ በረከት ነው፡፡የኢትዮጵያ ወታደሮች የድል አድራጊነት ምስጢራቶች በርካቶች ናቸው፡፡ህዝባዊ ፍቅራችን የአስተማማኝና ፅኑ አጋር የሆነ ህዝብ ባለቤቶች መሆናችን እንደ ተጠበቀ ሆኖ ከሙያው ያገኘነው ማንነት በሂደት የተቃኘነው ቅኝት ድርሻ መለኪያ የለውም፡፡

የመጀመሪው አንድ ዓይነትነት ነው፡፡ማሰልጠኛ ስንገባ ፀጉራችንን ፣ተላጭተን ፣አንድ አይነት አልባሳት ለብሰን ፣በኘሮግራሞች ተመርተን፣ ወጥ የሆነ የምግብ ዓይነቶች ተመግበን፣ የአመጋገብ ሥርዓት ይዘን፣ ዲሲኘሊንና ሥነ-ምግባር ተላብሰን መጀመራችን፣ መቀጠላችን፣ እናም ተመርቀን መውጣታች አሁን ለያዝነው መልክ ለምንገኝበት ልክ አብቅቶናል፡፡

በተልዕኮ አፈፃፀም ብቃት፣ በመሥክ፣ በቢሮ በተለያዩ ግዳጆች በአህጉርና ዓለም ዓቀፍ ተልዕኮዎች በምናስመዘግባቸው ውጤት ልንለያይ እንችል ይሆናል፡፡በሀገራዊ ፍቅር፣ በሙያዊ ክብር በፅናት፣ ጀግንነት ግን ፈፅም የተለያየን ልንሆን አንችልም ብቻ ሳይሆን አይቻልምም፡፡ ምክንያቱም ከነዚህ መጉደል ሀገር መበደል ታሪክን ማቃለል ነው፡፡

"ጀግና ይሠራል እንጂ አይወለድም"ለሚለው ወታደራዊ አባባል ከኛ የታላቋ ሀገር የኢትዮጵያ ወታደሮች በላይ አብነት አይገኝም፡፡ የውትድርና ሙያ የሠጠን ማንነት ፣ለሀገር አንድነት ፣ለህዝቦች ሠላምና ደህንነት እኩል ለግላችንም ህይወት ዜጋዊ ማንነት የሠጠንም ትልቅ ነው፡፡ ወታደር የተሟሸ ምጣድ ነው ሲባል ያለምክንያት አይደለም፡፡

የአሉባልታና ወሬ ጋጋታ አልፈን የውጭና ውስጥ ጠላቶቻችን እንቅፋቶች ተሻግረን በፅናት የቆምነው፤ የተስፋዋ ብርሃን ነፃብራቅ ምክንያት የሆነው ፤ከሙያው ባገኘነው ዕውቀት ክህሎት ችሎታ አስተሳሰብና ባህሪይ ነው፡፡ወታደርነት የተለየ ማንነት ከግል የሚያልፍ የሚሊዮኖች ስኬት ደህንነት ኩራት መሆን የሚያስችል ማንነት ማግኘት  ነው፡፡

በከርስ የተገዙ፣ ከጥንት ጀምሮ የጠላትነት መንፈስ የያዙ እንዴትም ከማንም ጋር ቢሠሩ እኛ ከአባቶቻችን ወኔና ጀግንነት የአሸናፊነት ውርስ የፅናት መንፈስ የያዝን የቁርጥ ቀን ልጆችን አልፈው ሀገራችንን አያፈርሱም፡፡ይጀምሩ ይሆናል እንጂ አይጨርሱም፡፡ቢጓዙ ቢኖጡ ካሰቡበት አይደርሱም፡፡

በሠንደቅ ዓላማው ፊት የገባ ቃልኪዳን ፤በወል የተቃኘበት እሴቶች፤ ዘመኑ የሚጠይቀው ወታደራዊ ብቃት የማይላላ እምነት የማይፈተን ፅናት፣ የአገልጋይነትና የመስዋዕትነት ፍላጎትና ዝግጁነት ያለው ሠራዊት መቼም የትም እንዴትም አይሸነፍም፡፡ ያ ሠራዊት ማለት የኢትዮጵያ አስተማማኝ ዘቦች መከታና ጠባቂዎች እኛ ነን፡፡

ምንም ቢወሳ ፣ከየትም ቢነሳ እኛ አሸናፊዎች ነን፡፡ድል አድራጊዎች ነበርን ድል በማድረግ ላይ ነን፡፡ድል አድራጊዎችም ሁነን እንቀጥላለን፡፡ ዘመን ተሻጋሪ  ትንታጎች ፈጣሪ ዛሬ ህዝባችንን ነገ ትውልዱን አኩሪ ሆነን እንቀጥላለን፡፡ ሙያው የሠጠን ችሎታ ውትድርና የለገሰን ከፍታ ይሄው ነውና ።

በፈይሳ ናኔቻ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Telegram

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

# ቁልፍ እሴቶች 1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣ 2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣ 3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።

ሙያው በለገሰን ችሎታ የደረስንበት ከፍታ
1 month, 3 weeks ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
1 month, 3 weeks ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
2 months ago

የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ ብሎም የአለም ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፦

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

ሠላም ከምንም በላይ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሠጠው የሁሉም ነገር መሠረት ነው። ለዚህም ነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለተሠለፈበት ዓላማ ፅኑ አቋም በመያዝ በየትኛውም የሀገራችን መልክዓ ምድር ማንኛውንም ምድራዊ ፈተና አልፎ ሠላም የሚያረጋግጠው ።

የኢትዮጵያ ሠራዊት ከሀገሩ አልፎ ለአፍሪካ ብሎም ለአለም ሠላም ዕውን መሆን በተለያዩ የአለም ሀገራት ለሠላም ማሥከበር ተልዕኮ በመሠማራትና በርካታ ፈተናዎችን አልፎ ተልዕኮውን በውጤት በማጠናቀቅ ከአለማችን ተመራጭ ሠራዊት በመሆን የሠላም አምባሳደርነቱን በተደጋጋሚ ያረጋገጠ ጠንካራ ሠራዊት ነው።

ኢትዮጵያን በየትኛውም አጋጣሚ ሠላሟን ለማሣጣት ዕድገቷን ለማደናቀፍ ከውስጥም ከውጪም ትንኮሳዎች ሲሠነዘሩም የዜጎችን ሰላም እና የሃገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ለሠንደቅ ዓላማው ክብር የትኛውንም አይነት ምድራዊ ፈተና አልፎ ግዳጁን በድል የሚፈፅም የህዝብና የሀገራት ኩራት የሆነ ሠራዊት መሆኑ ተመሥክሮለታል።

ከጦርነት እንጅ ከሰላም ማትረፍ አይቻልም የሚል እሳቤ ያላቸው ፣ ያልተገባ ለህዝብም ለሀገርም የማይጠቅም ይልቁንም የዕድገት ማነቆ የሆነ ዘመኑን የማይመጥን ተግባር ላይ የሚጣዱ ሃይሎች ያሰቡትን ያህል ርቀት መሄድ እንዳይችሉ ሠራዊቱ ከህዝብ ጋር ሆኖ በተሳሳተ ስሌት የሚያደርጉትን ሴራ እያከሸፈም ይገኛል።

ሀገራችን ሠላሟ ተረጋግጦ ዕድገቷ እውን እንዳይሆን ካለፈው ዘመን ጀምሮ ያለእንቅልፍ የሚሠሩ ሴራ ሸራቢዎች የጥፋት እጃቸውን ለመዘርጋት ቢጥሩም፣ የተንኮል እጣታቸውን ቢቀሥሩም፣ እኛ ብቻ እንደግ የሚል አባዜ በተጠናወታቸው ሀገሮች የሚዘወሩ መሆናቸውን በውል መገንዘብ የግድ ይላል።

እነኝህ የአጭርና የረጅም ጊዜ የጥፋት አጀንዳ ቀርፀው የሚንቀሳቀሱ ሀገራት ኢትዮጵያን የጦርነት ቀጠና በማድረግ ህዝቦቿ ከመተማመን ይልቅ መጠራጠር ከመግባባት ይልቅ መቃረን ከአንድነት ይልቅ ልዩነት ውስጥ ገብተው ለዕድገት መሠረት የሆነው ልማት ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ አሁንም ድረስ እንቅፋት መፍጠራቸውን ቀጥለውበታል።

የእነኝህን ፀረ ኢትዮጵያዊ አመለካከት እና ድርጊት የሚደገፉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ከቶውንም ቢሆን የማያስቡ ፣ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ፊት የተሠለፉ ፣ በውጪ ጣልቃ ገብ ሀገራት የሚዘወሩ ራስ ወዳዶች በማንኛውም ጊዜ የጥፋት አጀንዳ ማራገብ የተሠለፉበት ዓላማ ነው።

ሥለሆነም ሁኔታዎችን በስክነት በመገንዘብ ፍላጎታቸው እንዳይሳካ የሀገር አፍራሽነታቸው ጉዞ እንዳይሠምር ማድረግ ከሁሉም ሠላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚጠበቅ አሁናዊ ሥራ ሊሆን ይገባል ። በአለማችን በጦርነት ያደገ ከጦርነት ያተረፈ ሀገርም ህዝብም የለምና ለሀገራችን ሠላም በህብረት መቆም ያሥፈልጋል።

በውብሸት ቸኮል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Telegram

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

# ቁልፍ እሴቶች 1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣ 2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣ 3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።

የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ ብሎም የአለም ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፦
2 months ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
2 months ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
2 months, 1 week ago

በሶማሊያ በለደወይኒ ፣ መሃስና ሃልገን የሚገኙት የሴክተር 4 የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ አባላት አለም አቀፉ የሴቶች ቀንን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አከበሩ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

በበአሉ ላይ  ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሴክተሩ ምክትል አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ሹመት ጠለለው ሴቶች በአመራርም ሆነ በተዋጊነት በሚሰጣቸው ተልዕኮና ሃላፊነት ውጤታማ መሆናቸውን እና በተለይም ሃገራችን ኢትዮጵያ በየዘመናቱ ጀግና ሴት መሪዎች ያሏት መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገራችን በየዘመናቱ ጀግና ሴቶች ያፈራችና ዛሬም አህጉር አቀፍ ተልዕኮን ተቀብለው  ግዳጃቸውን በላቀ ብቃት የሚወጡ ጀግና ሴት የሰላም አስከባሪ አባላቶች መኖራቸውን በተለይም በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ግዳጅ የመልክዓ ምድሩ ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ሳያግዳቸው ተልዕኳቸውን በአኩሪ የግዳጅ አፈፃፀም እየተወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በግዳጅ ቀጠና የሚታየው የሴት ሰራዊት አባላት  ቁርጠኝነትና የሞራል ጥንካሬም  ከእለት ወደ እለት የሴቶችን የእችላለሁ መንፈስ በተግባር የሚያሳይና የውሳኔ ሰጭነት ሚናቸውን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡

የUNSOS ፖሊስ ሴቶች ጉዳይ ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ኒና ጃምኖንግ እና የሴክተር 4 ሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ሻለቃ ዶክተር ለምለም ሃይሌ በበኩላቸው አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ስናከብር እኛ ሴቶች በአለም መድረክ ያለንን ተሳትፎ በማሳደግና እምቅ አቅማችንን አውጥተን በመጠቀም፣ ሙያዊ እውቀትና ችሎታችንን ዘመኑ ከሚጠይቀው አቅም ጋር በማስተሳሰር ተወዳዳሪ ለመሆን  በመዘጋጀት መሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡

በዕለቱ  ሴት የሠላም አስከባሪ አባላቱ በቀጠናው ካሉ የ UNSOS አባላት  ጋር የወዳጅነት እግር ኳስ ጨዋታ ውድድር ያካሄዱ  ሲሆን የየሃገራቸውን በዓል በማስተዋወቅና የተሞክሮ ልውውጥ በማድረግ፣ አብሮነትን እና አለም አቀፋዊነትን አሳይተዋል፡፡

ዘጋቢ መንበረ መለሰ
ፎቶግራፍ ከክፍሎች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Telegram

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

# ቁልፍ እሴቶች 1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣ 2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣ 3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።

በሶማሊያ በለደወይኒ ፣ መሃስና ሃልገን የሚገኙት የሴክተር 4 የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ አባላት አለም አቀፉ የሴቶች ቀንን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አከበሩ።
2 months, 1 week ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
2 months, 1 week ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
2 months, 1 week ago

የሀገርን አንድነት ለማስቀጠል ሰራዊቱ የማይተካ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ውይይት የተደረገ ሲሆን የሀገርን አንድነት ለማስቀጠል ሰራዊቱ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

ውይይቱን የመሩት የሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል ሀይሌ ብሩ  ሀገር እንደ ሀገር ልትቀጥል የምትችለው ባላት የሰራዊት አቅም እና ሰራዊቱ ባለው የሀገር ፍቅር ነው ብለዋል።

ሠራዊቱ ለቆመለት ዓላማ መሳካት መኮንኑ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀው አመራሩ የሚመራውን ሰራዊት በቅርበት መከታተል እና ያለውን አቅም በየጊዜው እያሳደገ የመፈፀም አቅሙን እንዲያጎለብት ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉም ገልፀዋል።

የሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ድጋፍ  ኮሎኔል አስፋው አርጎ በበኩላቸው አሁን ላይ እየታዩ ያሉ ፅንፈኞች ሀገራችን የበለፀገች እና የጎለበተች እንዳትሆን የሚፈልጉ የሀገር ውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን የሚልኳቸው ሀገር አፍራሾች መሆናቸውን በማወቅ ሀገር የማስቀጠል አላማችንን በትጋት ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

ዘጋቢ ይልቃል አዲስ
ፎቶግራፍ ይልቃል አዲስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Telegram

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

# ቁልፍ እሴቶች 1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣ 2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣ 3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።

የሀገርን አንድነት ለማስቀጠል ሰራዊቱ የማይተካ ሚና እንዳለው ተገለፀ።
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago