FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

Description
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 weeks, 5 days ago
የኢትዮጵያና የናይጀሪያ መከላከያ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ …

የኢትዮጵያና የናይጀሪያ መከላከያ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ለመሥራት በሚያሥችሉ ጉዳዮች በናይጀሪያ እየመከሩ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንዳንት ብርጋዲየር ጀኔራል ከበደ ረጋሳ የተመራ ልዑክ በናይጀሪያ ፌደራል ሪፖፕሊክ ዋና መስሪያ ቤት ተገኝቶ በሁለትዮሽ ወታደራዊ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እያደረገ ነው።

ውይይቱ የኢትዮጵያን እና የናይጀሪያን የመከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ ፕሮፌሽናሊዝም በትምህርትና ስልጠና ዙሪያ ለማሳደግ ተግባር ላይ ማዋል በሚችሉ የጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን በሁለቱም ሀገራት በኩል ሠፊ ወይይት በማድረግ ጠንካራ ስምምነት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

በብርጋዲየር ጀኔራል ከበደ ረጋሳ የተመራው ወታደራዊ ልዑክ በቀጣይ የሁለቱን ሃገራት የመከላከያ ሠራዊት መጥቀም በሚያስችሉ የትምህርት ፣ የስልጠና ፣ የልምድ እና መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሃገሪቱን የመከላከያ ተቋማት ተዘዋውሮ ይጎበኛል። መረጃውን ያደረሰን የልዑካን ቡድኑ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

3 weeks, 5 days ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
3 weeks, 5 days ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
1 month ago
የመቻል ከ20 ዓመት በታች እግር ኳስ …

የመቻል ከ20 ዓመት በታች እግር ኳስ ቡድን የሲዳማ ቡና አቻውን 2ለ1  በሆነ ውጤት አሸነፈ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ታህሳስ  04 ቀን 2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድር በምድብ ለ በአሰላ ስታዲየም መቻል ሲዳማ ቡናን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ለመቻል ሁለቱን የማሸነፊያ ጎሎች  ቢኒያም ተክሉ አስቆጥሯል።

በጨዋታው ላይ ለመቻል ባለድል እንዲሆን ሁለት ጎሎችን ከመረብ ያሳረፈው ቢኒያም ተክሉ የጨዋታው ኮከብ ተብሏል።

ጥሩ የጨዋታ ፉክክር እና በርካታ የጎል እድሎች በታዩበት በሁለቱ ጨዋታ የመቻል ከ20 ዓመት በታች እግር ኳስ ቡድን አሸናፊ መሆን ችሏል።

በሁለት ምድብ ተከፍሎ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ምድብ ሀ ቡራዩ ከተማ ምድብ ለ ደግሞ በአሰላ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ ታህሳስ 07 ቀን መቻል ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ዘጋቢ ገረመው ጨሬ
ፎቶግራፍ ገረመው ጨሬ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

1 month ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
1 month ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
1 month, 1 week ago
ፅንፈኛው ቡድን ይጠቀምባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎች …

ፅንፈኛው ቡድን ይጠቀምባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎች እና ተሸከርካሪዎች ተይዘዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

በሰሜን ሸዋ ዞን በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ የኮማንዶና አየር ወለድ እዝ ክፍለ ጦር ከወረዳው የፀጥታ ሀይሎች ጋር በቅንጅት ባደረጉት ኦፕሬሽን ልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎች እና ተሸከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በክፍለ ጦሩ የሻለቃ አዛዥ ሻለቃ ተስፋዬ በላይነህ፤ የክፍለ ጦሩ ሠራዊት በትላንትናው እለት በወረዳው የታጣቂ ሀይሉን ካምፕ በመክበብ ባደረጉት ኦፕሬሽን ታጣቂ ሀይሉ ይጠቀምባቸው የነበሩትን ባጃጅ ፣ሞተር ሳይክሎች መሣሪያዎች እና ተተኳሾች በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል፡፡

አሁን በጫካ የሚገኙ ሀይሎች አላስፈላጊ መስዋዕትነት ከመክፈል ይልቅ እጃቸውን በሰላም ለመከላከያ ሠራዊቱ መስጠት እንዳለባቸው አመላክተዋል ዘገባው የክፍለጦሩ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

1 month, 1 week ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
1 month, 1 week ago
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ …
1 month, 2 weeks ago
በኢፌዴሪ አየር ኃይል "ዛሬን ለነገ ሲሰራ" …

በኢፌዴሪ አየር ኃይል "ዛሬን ለነገ ሲሰራ" ፊልም ተመርቆ ለእይታ በቅቷል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በኩራት ፒክቸርስ ፊልም ፕሮዳክሽን ተሰርቶ ለእይታ የቀረበው ዛሬን ለነገ ሲሰራ ፊልም የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በክብር እንግድነት በተገኙበት በአየር ኃይል ሲኒማ አዳራሽ  ለእይታ በቅቷል፡፡ 

በፊልም ምርቃት ስነስርዓቱ ላይ በአየር ኃይል ምክትሎች እና ምድቦች የተሰሩ የፈጠራ ስራዎችን በማወዳደር ለተቋም ብሎም ለሀገር ከሚሰጡት ፋይዳ አንፃር ተገምግመው ከአንድ እስከ ሦስት ለወጡ ተወዳዳሪዎች የእውቅና እና የሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቷል፡፡

ሽልምቱ የተበረከተለት እና በአንደኝነት የተመረጠው  ምክትል መቶ አለቃ መሃመድ ተማም የሰራው የፈጠራ ስራ የአገልግሎት ጊዜው ያለፈበት እና መወገድ የነበረበትን የቮልጋ ሚሳኤል ኬሚካል ተጠቅሞ የአፈር መዳበሪያ የሰራ ሲሆን ምክትለሰ መቶ አለቃ ቢኒያም ስዩም እና ሃምሳ አለቃ ፍቅረ መለስ በጋራ ዲጂታላይዝድ የሆነ የሱ-27 እና ሱ-30 ሀይድሮሊክ ዘይት መሙያ ማሽን የሰሩ እንዲሁም ምክትል መቶ አለቃ ይበልጣል መንደፍሮ ለተለያየ ግልጋሎቶች የሚያገለግል ተንቀሳቃሽ  ሮቦት በመስራት ነው፡፡ ዘገባው የአየር ሃይል ሚዲያ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana