Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

Raha M/Clinic Channel

Description
Raha Medium Clinic//ራሃ መካከለኛ ክሊኒክ
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago

1 Monat, 3 Wochen her

ግሳፄ በሞት በቃ

እጅግ አስተማሪ የሆ ታሪክ ነው።ሼር አድርጉት

ምን በምድር ላይ ቢደላን የአጭር ህይወታችን የመጀመሪያው ማሳረጊያ ሞት ነው። የሚቀጥለው  ዘላቂ ማረፊያ ገነት (መንግሥተ ሰማያት) አሊያም ሲዖል (ገሀነም) መሆኑ ለአማኞች ቅርብ ነው።

የዓለማችን ታዋቂ የፋሺን ዲዛይነር እና ፀሐፊ የነበረቺው ኪርዛይዳ ሮድሪጉዌዝ ከዚህ ዓለም በደረጃ 4 የሆድ ካንሰር በ2018 ከመሰናበቷ በፊት የሚከተለውን መልእክት አስተላልፋ ነበር።

  1. በዓለማችን ውዱ አውቶሞቢል በጋራዤ ውስጥ ነበረኝ፤ አሁን የምንቀሳቀሰው ግን በዊልቼር ነው።

  2. መኖሪያዬ በሁሉም አይነት ዲዛይነሮች በተሰሩ አልባሳት መጫሚያዎች እና ውድ ዕቃዎች የተሞላ ነበር፤ ዛሬ ግን ከሆስፒታል በተሰጠኝ እራፊ ጨርቅ ተጠቅልያለሁ።

  3. በቂ ገንዘብ ባንክ ውስጥ አለኝ፤ አሁን ግን ልጠቀምበት አልችልም።

  4. ቤቴ ልክ እንደ ቤተመንግሥት ነው፤ አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ በታጣፊ አልጋ/ በድንክ አልጋ ላይ ቀርቻለሁ።

  5. ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ሌላ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል መሄድ እችል ነበር፤ አሁን ግን ጊዜዬን የማሳልፈው ከአንድ የሆስፒታል ላብራቶሪ _ ወደ ሌላው የሆስፒታል ላቦራቶሪ በመንከላወስ ነው።

  6. መቶዎች ፈርሚልኝ ይሉኝ ነበር (ከመቶዎች ጋር ስምምነት እፈርም ነበር)፤ ዛሬ ፊርማዬ የዶክተሮች ማስታወሻ ሆኗል።

  7. ፀጉሬን ለማስዋብ ዘጠኝ ጌጣጌጦች ነበሩኝ። አሁን ግን አናቴ ፀጉር አልባ ሆኗል።

  8. በግል አውሮፕላን (ጀት) ወዳሻኝ ስፍራ እበር ነበር። አሁን ግን ወደ ሆስፒታል ለመሄድ እንኳ ሁለት የሚሸከሙኝ/ የሚደግፉኝ ሰዎች ያስፈልጉኛል።

  9. የተትረፈረፈ ምግብ ቢኖርም፤ የምመገበው በቀን ሁለት የመድኃኒት እንክብሎች እና ሲመሽ ጥቂት የጨው ጠብታ ብቻ ነው።

ይህ ቤት፣ ይህ አውቶሞቢል ይህ ጀት ይህ ዕቃ በርካታ የባንክ አካውንቶች የበዛ ክብርና ዝና፣ ሁሉም ዛሬ ለእኔ እርባና ቢስ ናቸው። የትኞቹም የከበረ ዋጋ ያላቸው ቁሶች ለህመሜ ማስታገሻ አይሆኑም።

እውነተኛ ህይወት ማለት ለበርካታ ሰዎች እንዲደሰቱ እና በፈገግታ እንዲሞሉ ማድረግ _ ከሞት በስተቀር ምንም እውነት የለም። ህይወት እንደ ጤዛ (አጭር) ናት።

🔹 ማስታወሻ ፦
የእንግሊዝኛ በኩረ ፅሑፉን  ከታች ያገኙታል ።

WORLD FAMOUS FASHION DESIGNER AND WRITER KYRZAYDA RODRIGUEZ, WROTE THIS ARTICLE BEFORE SHE PASSED AWAY FROM STAGE 4 STOMACH CANCER IN 2018

  1. I had the world's most expensive car brand in my garage but now I'm traveling in a wheelchair.

  2. My house is full of all kinds of designers clothing, shoes and valuables. But my body is wrapped in a small sheet of cloth provided by the hospital.

  3. There is enough money in the bank. But now I'm not benefiting from that money.

  4. My house is like a palace but I'm laying in a double size bed in a hospital.

  5. I can go from five star hotel to another five star hotel. But now I'm spending time moving from lab to lab in hospital.

  6. I signed hundreds of people. Doctor's note today is my signature.

  7. I had seven jewelry to decorate my hair - now I don't have hair on my head.

  8. With a private jet, I can fly wherever I want. But now I need two people's help to get to the hospital patio.

  9. Although there are many foods, but my diet has two tablets a day and a few drops of salt at night.
    This house, this car, this jet, this furniture, so many bank accounts, so much reputation and fame, none of them are useful.

None of all valuables could give me relief.

The real life is about entertaining many people and making them smile ′′ nothing is real but death ′′ Life is so short.

አንድ ወንድማችን ካነበበው ያካፈለን ፁሑፍ ነው ።

🔹 አቡ ሁረይራ ባወሩትና ኢብኑ ሒባን ሶሒሕ ባሉት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ

" ግሳፄ በሞት በቃ " ብለዋል ።

https://t.me/bahruteka

1 Monat, 4 Wochen her

የሕፃናት የክትባት ፕሮግራም

በአገራችን ለህጻናት የሚሰጡ ክትባት የሚከተሉትን ይመስላሉ፡

1) እንደተወለዱ የሚወሰዱ፡ የፖሊዮ ክትባት, የቲቢ መከላከያ ክትባት(ቢሲጂ)

2) በ6ኛ ሳምንት የሚወሰዱ፡የፖሊዮ ክትባት ጸረ 6 ክትባት(DPT, Hep B, HIB, PCV) የሮታ ቫይረስ ክትባት(ህጻናት ላይ በ ቫይረስ ምክንያት ከሚከሰት ተቅማጥ የሚከላከል)

3) በ10ኛ ሳምንት የሚወሰዱ፡በ 6ኛ ሳምንት የሚወሰዱትን አይነት ክትባቶች ሁለተኛ ዶዝ ይወስዳሉ።

4) በ14ኛ ሳምንት የሚወሰዱ፡ጸረ 6 ክትባት(DPT, Hep B, HIB, PCV) ሶስተኛ ዶዝ ይወስዳሉ . IPV(ክንድ ላይ የሚወጋ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት)

5) 9ኛ ወር ላይ እና አመት ከ ሶስት ወር የሚወሰድ፡ የኩፍኝ ክትባት
ከዚህም በተጨማሪ ቫይታሚን A ከ 6ኛ ወር ጀምሮ እስከ 5 አመት ድረስ የሚሰጥ ይሆናል።እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ ሌላ ተጨማሪ ክትባቶችን ሊወስዱ ይችላሉ።

@healthinovation

1 Monat, 4 Wochen her

ፈጣን ክፍት የስራ ቦታ

የስራው መደብ :- ፋርማሲ
የትምህርት ደረጃ :- ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ
ደሞዝ :- በስምምነት

0919247587 /
@Huwafishen

2 Monate, 3 Wochen her

ከፖላንድ ነፃ ህክምና ለመስጠት 30 የህክምና ባለሞያዎች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ
____

ከፖላንድ የመጡት የህክምና ባለሞያዎች የማህፀን እና ፅንስ፣ ኒውሮሎጂ፣ ኒውሮሰርጀሪ እና የሰመመን ህክምና ባለሞያ ናቸው።

የህክምና ባለሞያዎቹ ለአስር ቀናት በኢትዮጵያ የሚቆዩ ሲሆን ከዛሬ ከየካቲት 17 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በጦር ሀይሎች ሆስፒታል እና ሌሎች ተቋማት አገልግሎቱን ይሰጣሉ። በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሆስፒታሎች በተጨማሪም ወደ አርባ ምንጭም የሚጓዙ ይሆናል።

የህክምና ባለሞያዎቹ በተከታታይ ሶስት አመት ለሶስተኛ ዙር የመጡ ሲሆን ቁጥራቸው በየአመቱ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል።

@ healthinovation

3 Monate her

የደም ግፊት?

የደም ግፊት ከልብ ምት የሚመነጭ እና ደም በሰውነት እንዲዘዋወር የሚረዳ የግፊት ሀይል ነው። የደም ግፊት ከሚገባው በላይ ሲጨምር የደም ቧምቧዎችን እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ሊጎዳ ይችላል። ይህም የደም ብዛት ወይም ከፍተኛ  የደም ግፊት (hypertension ወይም high blood pressure) ይባላል።

ከፍተኛ የደም ግፊት ሊያመጡ የሚችሉ በሽታዎች በጥቂቱ

• የኩላሊት በሽታ
• የታይሮይድ ህመሞች
• የደም ስር ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ህመሞች
• ኩሺንግ ሲንድሮም (Cushing syndrome)

ከፍተኛ የደም ግፊት ሊያመጡ የሚችሉ መድሀኒቶች በጥቂቱ

• አድቪል(Advil/Ibuprofen)
• አንዳንድ የባህል መድሀኒቶች ለምሳሌ ኢፊድራ(Ephedra) ጅንሲንግ (ginseng) ማ-ሁዋንግ (ma huang)
• አደንዛዥ እጾች ለምሳሌ ኮኬን (cocaine) አምፍታማይን (Amphetamines)

• የወሊድ መቆጣጠርያ መድሀሂቶች (በአፍ የሚወሰዱ ኤስትሮጅን (Estrogen) ፕሮጅስትሮን (progesterone) እና አንድሮጅን (androgens))
• ስቴሮይድ ለምሳሌ ፕሪድኒሶን (prednisone)
• የጉንፋን እና የአለርጂ መድሃኒቶች ዲኮጀንስታንት (Decongestants)
• ክብደት ለመቀነስ የሚረዱ መድሀኒቶች

2. መሰረታዊ ከፍተኛ የደም ግፊት (ኢሰንሽያል (essential) ወይም ፕራይመሪ የደም ግፊት (Primary Hypertension))

አብዛኛዎቹ (ከዘጠና እስከ ዘጠና አምስት በመቶ) የሚሆኑ የከፍተኛ ይደም ግፊት ህመምተኞች በዚህ አይነት ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም ይጠቃለላሉ ። የደም ግፊታቸው ከሌላ ህመም ጋር ሳይያያዝ ወይም ይህ ነው በማይባል ምክንያት ከፍ ይላል። እንዲህ አይነት የደም ግፊት መሰረታዊ ወይም ፕራይመሪ ሀይፐርቴንሽን ይባላል።

የመሰረታዊ ከፍተኛ የደም ግፊት ትክክለኛ መንስኤ አይታወቅም። ነገር ግን አንዳንድ ነገሮች በዚህ ህመም የመያዝ እድልን ሊጨምሩ ይችላሉ።

• በዘር ከፍተኛ ደም ግፊት መኖር
• ከፍተኛ የጨው መጠን በምግብ ላይ መጠቀም
• ትንባሆ
• አልኮል
• በእድሜ መግፋት
• የኩላሊት በሽታ
• ከልክ ያለፈ ውፍረት
• የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ

የከፍተኛ የደም ግፊት (Hypertension) ህመም ምልክቶች

የደም ግፊት በአብዛኛው ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳያሳይ ሊቆይ ይችላል። ሆኖም አንዳንድ ሰዎች የሚከተሉት ምልክቶች ሊሰማቸው ይችላል

• የራስ ምታት
• የአይን ብዥታ
• ራስ ማዞር
• ደረት ላይ የሚሰማ ህመም

የደም ብዛት ለብዙ አመታት ምንም ምልክት ሳያሳይ ህመምተኛውን ሊጎዳ ይችላል። በዚህ ምክንያት አንዳንዴ የደም ብዛት ዝምተኛው ገዳይ በሚል ስም ይጠራል። የደም ግፊት ያለበት ሰው ምልክት ባያሳይም ሰውነቱ እየተጎዳ አይደለም ማለት አይደለም። እንዲያውም ህክምና ያልተደረገለት የደም ግፊት ለተለያዩ የጤና እክሎች ሊዳርግ ይችላል። ከነዚህም መካከል የኩላሊት በሽታ፣ የአይን ህመም እና የልብ እና የደምስር በሽታዎች (Cardio vascular diseases – CVD) ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

የደም ግፊት በሽታን ለመቀነስ

• ምግብ ውስጥ የሚጨምሩትን የጨው መጠን መቀነስ
• ጤናማ የሆነ አመጋገብ መመገብ
• የአካል እንቅስቃሴ ማዘውተር
• ውፍረት መቀነስ
• አልኮል መቀነስ
• ሲጃራ አለማጨስ (ትንባሆ በምንም አይነት መልኩ ቢሆን አይጠቀሙ)
• የሀኪም ቤት ቀጠሮ እና ሀኪምዎ የሚያዝልዎትን መድሃኒት ይከታተሉ

@healthinovation

3 Monate her

𝗨𝗿𝗴𝗲𝗻𝘁 𝘃𝗮𝗰𝗮𝗻𝗰𝘆 𝗮𝗻𝗻𝗼𝘂𝗻𝗰𝗲𝗺𝗲𝗻𝘁

𝗥𝗲𝗾𝘂𝗶𝗿𝗲𝗱 𝗽𝗿𝗼𝗳𝗳𝗲𝘀𝗶𝗼𝗻𝗮𝗹:-
1. 𝗣𝗵𝗮𝗿𝗺𝗮𝗰𝗶𝘀𝘁

𝗤𝘂𝗮𝗹𝗶𝗳𝗶𝗰𝗮𝘁𝗶𝗼𝗻: Degree in pharmacy ,with COC and minimum work experience of 3 years and above, Who can present clearance

𝗝𝗼𝗯 𝘁𝘆𝗽𝗲: Full time with his/her license
Salary: Negotiation

𝗪𝗼𝗿𝗸 𝗽𝗹𝗮𝗰𝗲: Asco, Adiss Ababa(A new pharmacy going to be opened)
NB!!!!

Female applicants, a person living around Asco will get priority.

𝗛𝗼𝘄 𝘁𝗼 𝗔𝗽𝗽𝗹𝘆:-
send your CV and necessary information on telegram by using 0911726349

@healthinovation

4 Monate, 3 Wochen her

የእግር ፈንገስ (Tinea Pedis)

የእግር ፈንገስ ማለት የቆዳ በሽታ በሚያመጡ ፈንገስ (Dermatophytic infection) የሚመጣ በሽታ ነዉ ።  አብዛኛዉን ጊዜም የእግርን የጫማ ክፋልንና የእግር ጣት መሃል የሚያጠቃ ሲሆን አንዳዴም የእግርን ጥፍር ና እጅ ላይም ሊከሰት ይችላል ።

አጋላጭ ምክንያቶች
  1. በባዶ እግር ብዙ ህዝብ ወደ ሚገኝበት መሄድ
  2. ካልሲን ፣ ጫማን ፣ የእግር ማድረቂያ ፎጣን በሽታዉ ካለባቸዉ ሰዉ ጋር በጋራ መጠቀም
  3. የሚያጣብቅ ሽፍን ጫማ ብዙን ጊዜ መልበስ
  4. እግርን ለረጅም ጊዜ እርጥብ ማድረግ
  5. እግርዎ በጣም ሚያልብዎ ከሆነ
  6. ሙቀታማ ቦታ መኖር
  7. እግርዎ ሳይደርቅ ሽፍን ጫማ መልበስ

ምልክቶቹ
- በእግር ጣት መሃል ወይም የእግር ጫማዎት ክፍል አካባቢ  ፦ ማሳከክ ፣ የማቃጣል ስሜት ፣ መሰነጣጠቅ ፣ ከቆዳዉ ላይ ነጭ ነገር መፋፋቅ ፣ መድረቅ ፣ ዉሃ የቋጠረ ቁስለት

ህክምናዉ
ሊቀቡ የሚችሉ አንቲፈንገስ
   -ክሎትሪማዞል (clotrimazole) ክሬም 1% በቀን ሁለት ጊዜ ለ 2- 4 ሳምንት መቀባት
  -ተርቢናፊን (terbinafine) ክሬም 1% ወይም ጀል 1% በቀን አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ለ 2-4 ሳምንት መቀባት
  -ሚኮናዞል (miconazole) ክሬም 2% በቀን ሁለት ጊዜ ለ 2-4 ሳምንት መቀባት
  -ኬቶኮናዞል (ketoconazole) ክሬም 2% በቀን አንዴ ለ 2-4 ሳምንት
ሊዋጡ የሚችሉ አንቲፈንገስ ለአዋቂዎች
-አይትራኮናዞል (itraconazole) 200 ሚግ በቀን ሁለት ጊዜ ለአንድ ሳምንት
-ተርቢናፊን (terbinafine) 250 ሚግ በቀን አንድ ጊዜ ለሁለት ሳምንት
-ፍሉኮናዞል (fluconazole) 150 ሚግ በሳምንት አንድ ጊዜ ለ 2-6 ሳምንት

እንዴት መከላከል ይቻላል ?
-እግርን በየቀኑ በሳሞና መታጠብ ና ማድረቅ
-የጫማ ካልሲን ማጠብ ፣ የእግር ማድረቂያ ፎጣን ማጠብ ከሰዉ ጋር በጋራ አለመጠቀም
-እግርዎት ከረጠበ ካልሲዎን መቀየር
-ሁለት ጥንድ ጫማ ካለን በቀን በቀን እየቀያየሩ መልበስ እዲደርቅ
-ህዝብ ለመዝናናት በሚበዛበት ቦት የራስዎን ነጠላ ጫማ መልበስ
-ሙቀት ማይጨምሩ ጫማዎችን መልበስ

4 Monate, 3 Wochen her

Druggist or Pharmacist Needed!

- Druggist or Pharmacist With License
- Sex :- Either
- Site :- West Arsi/Negelle
(On the way to from Addis to Shashemene - High Way)
- Salary:- Negotiable

Call:- 0922651918
Or Contact me Inbox
http://t.me/DrKhedirMA
-----------------
#Share
Add & Join this Group to get Same info and services 👉 http://t.me/FuriMed

5 Monate, 1 Woche her

የጡት ካንሰር 💥

(ክፍል 2)

ⓡⓜⓒበጡት ካንሰር የመያዝ እድልን የሚጨምሩ ነገራቶች

- ከማንኛዉም ስምንት ሴቶች አንዳቸዉ (ወይም 12 ከመቶ) በጡት ካንሰር የመያዝ እድል አላት። ግን አንዳንድ ሴቶች በካንሰሩ የመያዝ እድላቸዉ ከፍ ይላል። ዋና ዋና ከሚባሉ መንስኤዎች:-

ጡት ላይ የሚሰራዉ “እስትሮጂን ሆርሞን" የሚባለዉ ለረጅም ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እንድመነጭ የሚያደርጊ ሁኔታዎች:-
- የወር አበባ በትንሽ እድሜዋ የሚመጣባት፣ በኋላም ወር አበባ በሚጠፋበት እድሜ የሚቆይባት፣

- ልጅ ያልወለደች፣ ወይም ዉስን ልጆችን በቻ የዉለደች ከሆነች፣

- ዉፍረትና ቅባት የበዛበት ምግብ ማዘዉተር (የሆርሞኑ መጠን እንዲጨምር ስለሚያደርግ)

አልኮል መጠጥን የሚያዘወትር

ጨረር (ለምርመራም ሆነ ለህክምና ጨረር ያገኛት ሴት)

ከቅርብ ቤተሰቦች በጡት ካንሰር ተይዞ የነበረ ካለ

እነዚህ ሁኔታዎች ባሉበት በጡት ካንሰር የመያዝ እድል ይጨምራ!!!

ⓡⓜⓒየጡት ካንሰር የተገኘባት ሴት ምን አይነት የህክምና አማራጮች አሏት? ከበሽትዉ ደረጃ ከሚደረግላት የህክምና ምርጫዎች ከካንሰሩ የመዳን ወይም ባይድንም ከካንሰሩ ጋር የመቆየት እድሉ ምን ይመስላል?!

ይቀጥላል...

© [Raha Medium Clinic

ራሃ መካከለኛ ክሊኒክ](https://t.me/RahaMediumClinic/37)

ራሃ መካከለኛ ክሊኒክ ፣ እንደስሙ ራሃ የሚያገኙበ ክሊኒክ!!!

አድራሻችን ፉሪ ክፍለ ከተማ ጀሞ ሶስት በሃጫሉ መንገድ ወደ ሎጂ በሚወስደዉ ዋና ኮቢል መንገድ 200ሜ ገባ ብሎ።

ስልክ ቁጥር:

0933818926
0994321555

#ሼር #ጆይን
👇👇👇

https://t.me/RahaMediumClinic/37

6 Monate, 2 Wochen her
***💙******💙***Kiliinika***↘️******🤍***

💙💙Kiliinika↘️🤍
💙💙💙💙 G/G↘️🤍
💙💙💙💙💙 Raahaa🤍

💙💙💙💙💙💙💙ራሃ↙️🤍
💙💙💙💙መካከለኛ↙️ 🤍
💙💙💙💙ክሊኒክ🤍

Raha🔁Medium🔁Clinic

https://t.me/RahaMediumClinic/18

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago