The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week, 4 days ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month, 1 week ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months, 1 week ago
"ቲቢ በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚገኝበትን ሁኔታ ለማወቅ ያስችላል የተባለ ጥናት በሚቀጥሉት 3 ዓመታት ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው" ጤና ሚኒስቴር
የቲቢ በሽታ በተመለከተ ግምታዊ ቁጥሮችን ከማስቀመጥ በዘለለ የሽታውን ተጠቂዎች ቁጥር በትክክል የሚያሳይ ሃገራዊ ጥናት ባይኖርም በሃገር አቀፍ ደረጃ 156 ሺ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ 8-10 ሺ የሚገመቱ ሰዎች በህመሙ ተይዘው እንዳሉ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተማ አካባቢዎች ለሚታየው የስርጭቱ መጨመር ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት እና የሰራተኞች ምልልስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ይታመናል።
እ.እ.እ በ 2020 ቲቢ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኝበት የስርጭት መጠን በ 20 በመቶ ለመቀነስ ታቅዶ እቅዱን ማሳካት ተችሎ የነበረ ቢሆንም ይሁን እንጂ በ Covid እና ልዩ ልዩ ምክንያቶች በተፈጠረ ጫና ወደነበረበት የስርጭት መጠን የመመለስ አዝማሚያ እያሳየ መሆኑ ይነገራል።
በጤና ሚኒስቴር የቲቢ፣ስጋ ደዌና ሌሎች የሳንባ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ዴስክ ሃላፊ የሆኑት አቶ ታዬ ለታ ለቲክቫህ እንደገለጹት ከፍተኛ የቲቢ ስርጭት ባለባቸው የተለዩ ክልሎች፣ ዞኖችና ወረዳዎች የቲቢ ጫናን ለመቀነስ እና መቆጣጠር የሚያስችል አዲስ ፕሮጀክት መጀመሩን ተናግረዋል።
እንደ ሀገር በቲቢ በሽታ ከፍተኛ ስርጭት ባለባቸው አራት ክልሎች ማለትም ሲዳማ፤ ኦሮሚያ፤ ደቡብ አትዮጲያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የበሽታዉን ጫና እና ስርጭት ለመቀነስ ያተኮረ ፕሮጀክት የጤና ሚኒስትር ከUSAID ግብረ ስናይ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት ተስማምቶ ወደ ተግባር መገባቱን ሃላፊው ተናግረዋል።
ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተሟሉ መሆኑን የተናገሩት ሃላፊው ለአራት አመት በሚኖረው የፕሮጀክቱ ቆይታ በክልሎቹ የሚታየውን የቲቢ በሽታ ስርጭት በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ መታቀዱን ጠቁመዋል።
ፕሮጀክቱ በጤና ሚኒስቴር እና በUSAID በጋራ በሚመደብ በጀት የሚደገፍ ሲሆን በየዓመቱ 12 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተመደበለት መሆኑን ተነግሯል።
በተጨማሪም በተጠቀሱት አካባቢዎች የቲቢ በሽታ ስርጭቱ ለምን ከፍተኛ ሆነ የሚለው ጉዳይ የፕሮጀክቱ አንድ አካል መሆኑን ገልጸዋል።
ቲቢ በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚገኝበትን ሁኔታ የሚያሳይ የተደራጀ ሃገራዊ ቁጥር ለጊዜው ባይኖርም በትክክል ምን ላይ ይገኛል የሚለውን ለማወቅ በሚቀጥሉት 3 ዓመታት ጥናቶችን ለመስራት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን አቶ ታዬ ተናግረዋል።
???????
⭕የሙስሊም ወንድሙ ጭንቀት ለሚያሳስበው ሁሉ የእርዳታ ጥሪ?
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
ውድ ሙስሊም ወንድምና እህቶች እነሆ "በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም(በአኺራ) የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ ﷺ ነግረውናል።
?በመሆኑም ተማሪ አህመድ እስሌማን በባህር_ዳር ዩኒቨርሲቲ የኬሚካል ምህንድስና 5ኛ አመት ተማሪ (የዘንድሮ ተመራቂ፦ ማለትም የ2016 E.C) ሲሆን ባደረበት ህመም በባህር_ዳር ጥበበ ጊዮን ሆስፒታል ሲረዳ ቢቆይም ህመሙ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ወደ አዲስ አበባ ሄዶ እንዲታከም ሪፍር ተፅፎለት ምርመራውን አድርጎ በደም ካንሰር (Leukemia) መያዙ ስለታወቀ
ካንሰሩ በፍጥነት ካልታከመ ባጭር ግዜ የሚያድግ እና ህይወቱን አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ ባስቸኳይ ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ መታከም እንዳለበት በሀኪሞቹ ተወስኗል በመሆኑም ለህክምናው ከ 2 ሚልዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ተብሉዋል ።
ይህንን የተጠየቀውን ገንዘብ ወጪ በቤተሰቦቹ አቅም የሚሸፈን ስላልሆነ በቤተሰቦች ላይ አስቸጋሪ ሁኖ ተገኝቱዋል ። በመሆኑም ውድ ወንድምና እህቶች ፣ ለዚህ ለተጨነቀ ወንድማችን ትንሽ ትልቅ ሳንል የህክምና ወጪውን በመሸፈን ካለበት ጭንቀት ወጥቶ ለቤተሰቡም ለዲኑም የሚያገለግል ወንድማችን እንዲሆን የአቅማቹህን እንድታበረክቱ ስንል ለሁሉም ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች የእርዳታ ጥሪያችንን በአላህ ስም እናስተላልፋለን።
ወንድማችን አህመድን ለመርዳት
?የባንክ አካውንት ስም ?
➕TAJU ESILEMAN MUHAMMED
1⃣የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር :- 1000455535647 (CBE)
2⃣የአቢሲኒያ ባንክ አካውንት ቁጥር፦
43148117 (ABSINIYA)
3⃣የአዋሽ ባንክአካውንት ቁጥር ፦ 01425778677200
?በገንዘብ መርዳት ባትችሉ #share በማድረግ እንተባበረው ።
"በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም(በአኺራ) የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ ﷺ ነግረውናል ።
ይሄንን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሁሉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ በተለያዩ ቻናሎች እና ግሩፖች ሼር እንድታደርጉልን በአላህ ስም እንጠይቃለን ።
✅ ግሳፄ በሞት በቃ
እጅግ አስተማሪ የሆ ታሪክ ነው።ሼር አድርጉት
ምን በምድር ላይ ቢደላን የአጭር ህይወታችን የመጀመሪያው ማሳረጊያ ሞት ነው። የሚቀጥለው ዘላቂ ማረፊያ ገነት (መንግሥተ ሰማያት) አሊያም ሲዖል (ገሀነም) መሆኑ ለአማኞች ቅርብ ነው።
የዓለማችን ታዋቂ የፋሺን ዲዛይነር እና ፀሐፊ የነበረቺው ኪርዛይዳ ሮድሪጉዌዝ ከዚህ ዓለም በደረጃ 4 የሆድ ካንሰር በ2018 ከመሰናበቷ በፊት የሚከተለውን መልእክት አስተላልፋ ነበር።
በዓለማችን ውዱ አውቶሞቢል በጋራዤ ውስጥ ነበረኝ፤ አሁን የምንቀሳቀሰው ግን በዊልቼር ነው።
መኖሪያዬ በሁሉም አይነት ዲዛይነሮች በተሰሩ አልባሳት መጫሚያዎች እና ውድ ዕቃዎች የተሞላ ነበር፤ ዛሬ ግን ከሆስፒታል በተሰጠኝ እራፊ ጨርቅ ተጠቅልያለሁ።
በቂ ገንዘብ ባንክ ውስጥ አለኝ፤ አሁን ግን ልጠቀምበት አልችልም።
ቤቴ ልክ እንደ ቤተመንግሥት ነው፤ አሁን ግን በሆስፒታል ውስጥ በታጣፊ አልጋ/ በድንክ አልጋ ላይ ቀርቻለሁ።
ከባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ወደ ሌላ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል መሄድ እችል ነበር፤ አሁን ግን ጊዜዬን የማሳልፈው ከአንድ የሆስፒታል ላብራቶሪ _ ወደ ሌላው የሆስፒታል ላቦራቶሪ በመንከላወስ ነው።
መቶዎች ፈርሚልኝ ይሉኝ ነበር (ከመቶዎች ጋር ስምምነት እፈርም ነበር)፤ ዛሬ ፊርማዬ የዶክተሮች ማስታወሻ ሆኗል።
ፀጉሬን ለማስዋብ ዘጠኝ ጌጣጌጦች ነበሩኝ። አሁን ግን አናቴ ፀጉር አልባ ሆኗል።
በግል አውሮፕላን (ጀት) ወዳሻኝ ስፍራ እበር ነበር። አሁን ግን ወደ ሆስፒታል ለመሄድ እንኳ ሁለት የሚሸከሙኝ/ የሚደግፉኝ ሰዎች ያስፈልጉኛል።
የተትረፈረፈ ምግብ ቢኖርም፤ የምመገበው በቀን ሁለት የመድኃኒት እንክብሎች እና ሲመሽ ጥቂት የጨው ጠብታ ብቻ ነው።
ይህ ቤት፣ ይህ አውቶሞቢል ይህ ጀት ይህ ዕቃ በርካታ የባንክ አካውንቶች የበዛ ክብርና ዝና፣ ሁሉም ዛሬ ለእኔ እርባና ቢስ ናቸው። የትኞቹም የከበረ ዋጋ ያላቸው ቁሶች ለህመሜ ማስታገሻ አይሆኑም።
እውነተኛ ህይወት ማለት ለበርካታ ሰዎች እንዲደሰቱ እና በፈገግታ እንዲሞሉ ማድረግ _ ከሞት በስተቀር ምንም እውነት የለም። ህይወት እንደ ጤዛ (አጭር) ናት።
? ማስታወሻ ፦
የእንግሊዝኛ በኩረ ፅሑፉን ከታች ያገኙታል ።
WORLD FAMOUS FASHION DESIGNER AND WRITER KYRZAYDA RODRIGUEZ, WROTE THIS ARTICLE BEFORE SHE PASSED AWAY FROM STAGE 4 STOMACH CANCER IN 2018
I had the world's most expensive car brand in my garage but now I'm traveling in a wheelchair.
My house is full of all kinds of designers clothing, shoes and valuables. But my body is wrapped in a small sheet of cloth provided by the hospital.
There is enough money in the bank. But now I'm not benefiting from that money.
My house is like a palace but I'm laying in a double size bed in a hospital.
I can go from five star hotel to another five star hotel. But now I'm spending time moving from lab to lab in hospital.
I signed hundreds of people. Doctor's note today is my signature.
I had seven jewelry to decorate my hair - now I don't have hair on my head.
With a private jet, I can fly wherever I want. But now I need two people's help to get to the hospital patio.
Although there are many foods, but my diet has two tablets a day and a few drops of salt at night.
This house, this car, this jet, this furniture, so many bank accounts, so much reputation and fame, none of them are useful.
None of all valuables could give me relief.
The real life is about entertaining many people and making them smile ′′ nothing is real but death ′′ Life is so short.
አንድ ወንድማችን ካነበበው ያካፈለን ፁሑፍ ነው ።
? አቡ ሁረይራ ባወሩትና ኢብኑ ሒባን ሶሒሕ ባሉት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ
" ግሳፄ በሞት በቃ " ብለዋል ።
የሕፃናት የክትባት ፕሮግራም
በአገራችን ለህጻናት የሚሰጡ ክትባት የሚከተሉትን ይመስላሉ፡
1) እንደተወለዱ የሚወሰዱ፡ የፖሊዮ ክትባት, የቲቢ መከላከያ ክትባት(ቢሲጂ)
2) በ6ኛ ሳምንት የሚወሰዱ፡የፖሊዮ ክትባት ጸረ 6 ክትባት(DPT, Hep B, HIB, PCV) የሮታ ቫይረስ ክትባት(ህጻናት ላይ በ ቫይረስ ምክንያት ከሚከሰት ተቅማጥ የሚከላከል)
3) በ10ኛ ሳምንት የሚወሰዱ፡በ 6ኛ ሳምንት የሚወሰዱትን አይነት ክትባቶች ሁለተኛ ዶዝ ይወስዳሉ።
4) በ14ኛ ሳምንት የሚወሰዱ፡ጸረ 6 ክትባት(DPT, Hep B, HIB, PCV) ሶስተኛ ዶዝ ይወስዳሉ . IPV(ክንድ ላይ የሚወጋ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት)
5) 9ኛ ወር ላይ እና አመት ከ ሶስት ወር የሚወሰድ፡ የኩፍኝ ክትባት
ከዚህም በተጨማሪ ቫይታሚን A ከ 6ኛ ወር ጀምሮ እስከ 5 አመት ድረስ የሚሰጥ ይሆናል።እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ ሌላ ተጨማሪ ክትባቶችን ሊወስዱ ይችላሉ።
ራሃ መካከለኛ ክሊኒክ... ?? በቂ ልምድና ችሎታ ባሉዋቸዉ ዶክተሮች እና ሌሎች ጤና ባለሙያዎች፣ ? ? ከተሟላ ላብራቶሪ ምርመራ ጋር፣ ??? የህክምና አገልግሎት ሊንሰጣችሁ ስራ ጀምረናል። ራሃ መካከለኛ ክሊኒክ - እንደ ስሙ ከህመማችሁ ራሃ የሚታገኙበት ክሊኒክ እንዲሆንላችሁ እየተመኘን፣ አይታመሙ፣ ከታመሙ ግን ወደራሃ መካከለኛ ክሊኒክ እንድትመጡ እንጋብዛችኃለን!!! አድራሻችን:- ሸገር ሲቲ ፣…
ከፖላንድ ነፃ ህክምና ለመስጠት 30 የህክምና ባለሞያዎች ወደ ኢትዮጵያ ገቡ
____
ከፖላንድ የመጡት የህክምና ባለሞያዎች የማህፀን እና ፅንስ፣ ኒውሮሎጂ፣ ኒውሮሰርጀሪ እና የሰመመን ህክምና ባለሞያ ናቸው።
የህክምና ባለሞያዎቹ ለአስር ቀናት በኢትዮጵያ የሚቆዩ ሲሆን ከዛሬ ከየካቲት 17 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በጦር ሀይሎች ሆስፒታል እና ሌሎች ተቋማት አገልግሎቱን ይሰጣሉ። በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሆስፒታሎች በተጨማሪም ወደ አርባ ምንጭም የሚጓዙ ይሆናል።
የህክምና ባለሞያዎቹ በተከታታይ ሶስት አመት ለሶስተኛ ዙር የመጡ ሲሆን ቁጥራቸው በየአመቱ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል።
@ healthinovation
የደም ግፊት?
የደም ግፊት ከልብ ምት የሚመነጭ እና ደም በሰውነት እንዲዘዋወር የሚረዳ የግፊት ሀይል ነው። የደም ግፊት ከሚገባው በላይ ሲጨምር የደም ቧምቧዎችን እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ሊጎዳ ይችላል። ይህም የደም ብዛት ወይም ከፍተኛ የደም ግፊት (hypertension ወይም high blood pressure) ይባላል።
ከፍተኛ የደም ግፊት ሊያመጡ የሚችሉ በሽታዎች በጥቂቱ
• የኩላሊት በሽታ
• የታይሮይድ ህመሞች
• የደም ስር ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ህመሞች
• ኩሺንግ ሲንድሮም (Cushing syndrome)
ከፍተኛ የደም ግፊት ሊያመጡ የሚችሉ መድሀኒቶች በጥቂቱ
• አድቪል(Advil/Ibuprofen)
• አንዳንድ የባህል መድሀኒቶች ለምሳሌ ኢፊድራ(Ephedra) ጅንሲንግ (ginseng) ማ-ሁዋንግ (ma huang)
• አደንዛዥ እጾች ለምሳሌ ኮኬን (cocaine) አምፍታማይን (Amphetamines)
• የወሊድ መቆጣጠርያ መድሀሂቶች (በአፍ የሚወሰዱ ኤስትሮጅን (Estrogen) ፕሮጅስትሮን (progesterone) እና አንድሮጅን (androgens))
• ስቴሮይድ ለምሳሌ ፕሪድኒሶን (prednisone)
• የጉንፋን እና የአለርጂ መድሃኒቶች ዲኮጀንስታንት (Decongestants)
• ክብደት ለመቀነስ የሚረዱ መድሀኒቶች
2. መሰረታዊ ከፍተኛ የደም ግፊት (ኢሰንሽያል (essential) ወይም ፕራይመሪ የደም ግፊት (Primary Hypertension))
አብዛኛዎቹ (ከዘጠና እስከ ዘጠና አምስት በመቶ) የሚሆኑ የከፍተኛ ይደም ግፊት ህመምተኞች በዚህ አይነት ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም ይጠቃለላሉ ። የደም ግፊታቸው ከሌላ ህመም ጋር ሳይያያዝ ወይም ይህ ነው በማይባል ምክንያት ከፍ ይላል። እንዲህ አይነት የደም ግፊት መሰረታዊ ወይም ፕራይመሪ ሀይፐርቴንሽን ይባላል።
የመሰረታዊ ከፍተኛ የደም ግፊት ትክክለኛ መንስኤ አይታወቅም። ነገር ግን አንዳንድ ነገሮች በዚህ ህመም የመያዝ እድልን ሊጨምሩ ይችላሉ።
• በዘር ከፍተኛ ደም ግፊት መኖር
• ከፍተኛ የጨው መጠን በምግብ ላይ መጠቀም
• ትንባሆ
• አልኮል
• በእድሜ መግፋት
• የኩላሊት በሽታ
• ከልክ ያለፈ ውፍረት
• የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ
የከፍተኛ የደም ግፊት (Hypertension) ህመም ምልክቶች
የደም ግፊት በአብዛኛው ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳያሳይ ሊቆይ ይችላል። ሆኖም አንዳንድ ሰዎች የሚከተሉት ምልክቶች ሊሰማቸው ይችላል
• የራስ ምታት
• የአይን ብዥታ
• ራስ ማዞር
• ደረት ላይ የሚሰማ ህመም
የደም ብዛት ለብዙ አመታት ምንም ምልክት ሳያሳይ ህመምተኛውን ሊጎዳ ይችላል። በዚህ ምክንያት አንዳንዴ የደም ብዛት ዝምተኛው ገዳይ በሚል ስም ይጠራል። የደም ግፊት ያለበት ሰው ምልክት ባያሳይም ሰውነቱ እየተጎዳ አይደለም ማለት አይደለም። እንዲያውም ህክምና ያልተደረገለት የደም ግፊት ለተለያዩ የጤና እክሎች ሊዳርግ ይችላል። ከነዚህም መካከል የኩላሊት በሽታ፣ የአይን ህመም እና የልብ እና የደምስር በሽታዎች (Cardio vascular diseases – CVD) ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
የደም ግፊት በሽታን ለመቀነስ
• ምግብ ውስጥ የሚጨምሩትን የጨው መጠን መቀነስ
• ጤናማ የሆነ አመጋገብ መመገብ
• የአካል እንቅስቃሴ ማዘውተር
• ውፍረት መቀነስ
• አልኮል መቀነስ
• ሲጃራ አለማጨስ (ትንባሆ በምንም አይነት መልኩ ቢሆን አይጠቀሙ)
• የሀኪም ቤት ቀጠሮ እና ሀኪምዎ የሚያዝልዎትን መድሃኒት ይከታተሉ
The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 week, 4 days ago
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month, 1 week ago
◉ Welcome to the 433 Films
Best Place To Find All Movies..
🤞For Promo - @Abusheymc
☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433
Last updated 9 months, 1 week ago