ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile

Description
Henok Haile
Author
https://instagram.com/henok.haile?igshid=MzRlODBiNWFlZA==
Advertising
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week, 2 days ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months ago

1 month, 1 week ago
1 month, 3 weeks ago

አህያና ግርዛት

አሁን ሐዲስ ኪዳን ነው:: መገረዝ ግዴታ አይደለም:: ዋናው ጥምቀት ነው:: ባንገረዝ ምንም አይጎድልብንም:: በዚህ ጉዳይ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ ተነሣ:: አሕዛብ ሳይገረዙ ኖረዋልና ጸረ ግዝረት ሆኑ:: አይሁድ ደግሞ እንዴት ግዝረት እንተዋለን አሉ::

ወደ ክርስትና የተጠሩት እነዚህ ሁለት ወገኖች ሁለቱም ከራሳቸው አመጣጥ አንጻር እውነት አላቸው:: አሕዛብ የማያውቁትን ነገር መቀበል ሊገደዱ አይችሉም:: ክርስትናም አላስገደዳቸውም:: አይሁድ ደግሞ የኖሩበትን መተው አይችሉም:: ክርስትናም ግዝረትን ባይጠይቅም አልከለከለም::

በመጨረሻ በብዙ ምክር የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አሕዛብንም ያላገለለ እስራኤልንም ያላቃለለ ውሳኔ ወሰነች:: ውሳኔውን በጥሩ ቃል በመልእክቱ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ገልጾታል::

“ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ፡፡ ... እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር" 1 ቆሮንቶስ 7:18፣ 20

በዚህ መሠረት ኦሪትን ተቀብለው ተገርዘው ወደ ክርስትና የተጠሩት እስራኤል በመገረዛቸው ይቀጥሉ እንጂ ወደ አለመገረዝ አይመለሱ ተባለላቸው:: ሳይገረዙ የተጠሩት አሕዛብ ግን መገረዝ የእነርሱ ልማድ አልነበረምና አይገረዙ ተባለ:: ይህ ለእስራኤል የተወሰነ ውሳኔም እንደ ኢትዮጵያ ኦሪትን ተቀብላ ለኖረችና ተገርዛ ሳለ የተጠራች (ሐውልቶችዋ ሳይቀር የተገረዘ ወንድን የሚያሳዩባት) ሀገርም ላይ ይጸናል::

ይህ ውሳኔ ለሁሉም እንደ ግዝረት ያሉ ሕግጋት ይሠራል::

“ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ”

"ማንም አህያ እየበላ ተጠርቶ እንደ ሆነ አህያ ወዳለመብላት አይመለስ ፤ ማንም አህያ ሳይበላ ተጠርቶ እንደሆነም አህያ አይብላ"

እስራኤል በግዝረት ቀጥሉ ሲባሉ ደስ አላቸው አሕዛብም አትገረዙ ሲባል ደስ አላቸው:: ለእስራኤል ሔደህ የአሕዛብን ዜና ብትነግራቸው ምንም እንኩዋን ግዝረት ግድ ባይሆንም ቅር ይላቸዋል:: የአህያ መበላት ዜናም የሚያስደስተው አህያን እንዴት ልንተው እንችላለን ብለው ለተጨነቁ አሕዛብ ብቻ እንጂ ለእኛ ሆድ የሚበጠብጥ ዜና ነው::

ከዚያ ውጪ እንደ ክርስቲያን ብሉ ብለን ልንሰብከው የሚገባን የሕይወት እንጀራ ሥጋ ወደሙ ብቻ ነው::

እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት ይኑር!

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ቄራ(የበሬ)

#share

▫️ @diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile

1 month, 4 weeks ago
  • ለእንቅልፋሞች መልካም ዜና +

እንቅልፍ ሲበዛ የስንፍና ምልክት መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው:: "ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ፤ ዓይንህን ክፈት፥ እንጀራም ትጠግባለህ” ፤ “የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳል" የሚሉት ጥቅሶች ለዚህ ምስክር ናቸው:: (ምሳሌ 20:13 ፣ 23:21)

ሆኖም በእንቅልፋቸው የተጠቀሙ ብዙ ሰዎችም አሉ:: አንቀላፍቶ ሚስቱን ያገኘው አዳም እንዴት ይረሳል? ከኤሳው ጋር ሲታገል የኖረው ያዕቆብ ሲባረክ ያደረውስ በእንቅልፉ አልነበር? ያዕቆብማ ምነው ባልነቃ ያሰኛል:: ሰማይ ድረስ መሰላል ወጥቶ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ያየው በእንቅልፉ ምክንያት ነበር:: በባቢሎን ምርኮ ዘመን የነበረው አቤሜሌክ ደግሞ የእንቅልፋሞች ንጉሥ ቢባል አያንስበትም:: የኢየሩሳሌምን ጥፋት አታሳየኝ ብሎ ሲጸልይ የነበረው ይህ ሰው በፈጣሪ ፈቃድ ለስድሳ ስድስት ዓመታት ያህል ተኝቶ ነበር:: ከእንቅልፉ ሲነሣም እንቅልፍ ሳይጠግብ እየተበሳጨ ነበር:: ማንቀላፋቱ ግን ብዙ ጉድ ከማየት አዳነው:: (ተረፈ ኤርምያስን ይመልከቱ)

ዛሬ ግን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የአቤሜሌክን የእንቅልፍ ክብረ ወሰን የሰበሩ ሰባቱ እንቅልፋሞች (The Seven Sleepers) የተሰኙ ቅዱሳንን እንተዋወቅ:: ወቅቱ የሮም ነገሥታት አላውያን የነበሩበት ክርስቲያኖች በግፍ እየተገደሉ የነበረበት ዘመነ ሰማዕታት ነው:: ክርስቲያን መሆን ወንጀል በነበረበት በዚያ ወቅት ክርስቲያኖች ከአንበሳ ጋር እየታገሉ በመስቀል እየተሰቀሉ በሰይፍ እየተቀሉ እየሞቱ የነበረበት ዘመን ነው::

በንጉሥ ዳክዮስ ዘመነ መንግሥት (249-251) ታዲያ በንጉሣዊ ምክር ቤቱ ውስጥ አባል የነበሩ ሰባት ወጣት ልዑላን ድንገት ክርስትናን ተቀብለው "ለጣዖት መሥዋዕት አንሠዋም" ብለው አሻፈረኝ አሉ፡፡ ወጣቶቹ ይህን በማድረጋቸው የሚከተለውን ጽኑ ቅጣት ያውቁ ነበረና ፈርተውም በቅርብ ወዳለ አንድ ተራራ ሸሽተው በዋሻ ውስጥ ተደበቁ።
@diyakonhenokhaile

በዚያ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው እያሉ ታዲያ ሰባቱንም እንቅልፍ ይጥላቸዋል፡፡ ንጉሥ ዳክዮስ አሳድዶአቸው ሲመጣ ተኝተው እንዳሉ ያያል:: አውሬው ንጉሥ ሁኔታውን ሲያውቅ እዚያው ዋሻ ውስጥ ይሙቱ ብሎ የዋሻውን መግቢያ በር በግንብ አስደፍኖት ሔደ፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን ወጣቶቹ እንቅልፍ ላይ ናቸው::

ከመቶ ሃምሳ እስከ ሁለት መቶ ዓመታት ገደማ ከሆነ በኋላ እነዚህ ወጣቶች ከእንቅልፋቸው ይነቁና የረሃብ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ከእነርሱ አንዱን ወደ ከተማ ሔዶ ምግብ እንዲገዛላቸው ይልኩታል፡፡

ዋሻው የተዘጋበት በር ከዘመን ብዛት ፈርሶ ነበርና የተላከው ወጣት ከዋሻው በቀላሉ ወጥቶ ወደ ከተማ አቀና፡፡ ወደ ከተማ ገብቶ ለሰባቱም የሚበቃቸውን ምግብ አገኘና ሂሳብ ሊከፍል ከኮሮጆው ሳንቲም አወጣ፡፡ ያወጣው ገንዘብ ግን ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት መገበያያ የነበረውን 'የጣዖት አምላኪዎቹን' ነገሥታት የወርቅ ሳንቲም ነበር። ሰባቱ ያንቀላፉ ቅዱሳን ከእንቅልፍ የነቁበት ያ ዘመን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ የኤፌሶን ከተማ ሙሉ በሙሉ ክርስቲያናዊት ከተማ በሆነችበት ደግ ዘመን ነበር፡፡
@diyakonhenokhaile

የሰባቱ ወጣቶች ዝና ወዲያው በወቅቱ የነበሩት ክርስቲያን ነገሥታትና ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ ደረሰ፡፡ ወጣቱ ወደ ዋሻው ከተመለሰ በኋላ ግን ሰባቱም ቅዱሳን ድጋሚ እንቅልፍ ጣላቸው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ሲተኙ ግን እስከወዲያኛው በክብር አሸለቡ፡፡ ለእነዚህ ሰባት ሰማዕታት በሥፍራው ትልቅ ቤተ መቅደስ ተሠርቶላቸዋል፡፡

"እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም ደግፎኛልና ነቃሁ" መዝ.3:5

“የኤፌሶን ወንዝ” ገፅ 64 የግርጌ ማስታወሻ ላይ የተወሰደ

ሙሉ ገቢው ለግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እድሳት የሚውለው የኤፌሶን ወንዝ መጽሐፍ የመጀመሪያ እትም እያለቀ ነው:: እርስዎ እጅ ገብቶ ይሆን?

አርጋኖን መጻሕፍት መደብር Areganon Book Store

#share

▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile

4 months, 2 weeks ago

...ሁለቱ ጸሐፍያን በደብረ ታቦር ...
ክፍል ሁለት

ቅዱስ ኤፍሬም " የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን አዩ " በማለት በደብረ ታቦር ተራራ ከኤልያስ ውጪ ዐራት ግሩማን ጸሐፊያን እንደነበሩ መረዳት እንችላለን ፡፡ ከእነዚህ ጸሐፊያን መካከል ግን የሙሴንና የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስን ነገር ግን ለማንጻጸር የተመቸ ነው ፡፡ ለምን? ብለን መጻሕፍትን ስንመረምር

° የተሸፈነውን ሐዲስ ኪዳን የጻፈልን ሙሴ ፥ የተገለጠውን ብሉይ ኪዳን ከጻፈልን ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ተገናኝተዋልና ፡፡

° " ዓለሙም በእርሱ ሆነ " ብሎ የተናገረው የሐዲስ ኪዳኑ ዘፍጥረት(የዮሐንስ ወንጌል) ጸሐፊ ከብሉይ ኪዳኑ የኦሪቱ ዘፍጥረት ጸሐፊ ጋር ተገናኝቷልና ፡፡

° " በመጀመርያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ " ብሎ የሥነ ፍጥረትን መነሻ የጻፈው ቅዱስ ሙሴ " በመጀመርያ ቃል ነበር ብሎ " ብሎ ፍጥረት የተፈጠረበት የቃልን ነገር ከተናገረው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ተገናኝቷልና ፡፡

° ስለ መላእክት መፈጠር ያልተናገረው ሙሴ " ሁሉ በእርሱ ሆነ " ብሎ ነገረ ፍጥረትን ጠቅልሎ ከጻፈው ዮሐንስ ጋር ተገናኝቷልና ፡፡

° " ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም፦ ብርሃን ይሁን አለ ፤ ብርሃንም ሆነ ( Darkness, Light, and Life) " ብሎ የጻፈው ሙሴ " በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች፡፡ ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም ::(Life, Light, and Darkness)" ብሎ ከጻፈው ወንጌላዊው ጋር ተገናኝቷልና ፡፡

° " ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት በበደል መሥዋዕት በግ ያስተሰርይለታል የሠራውም ኃጢአት ይቀርለታል፡፡" ብሎ የእስራኤል ዘሥጋን ኃጢአት ስለሚያስተሰርየው በግ የጻፈው ሙሴ " እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፡፡ " ብሎ የእስራኤል ዘነፍስን ኃጢአት ስለሚያስተሰርየው የእግዚአብሔር በግ ከጻፈው ወንጌላዊ ጋር ተገናኝቷልና ፡፡

" ጀርባዬንም ታያለህ፤ ፊቴ ግን አይታይም፡፡ " ተብሎ ምስጢር የተሰወረው ሙሴ " ኢየሱስም ይወደው የነበረ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በኢየሱስ ደረት ላይ ተጠጋ፤ "ተብሎ ብዝኃ ምስጢር ከተገለጠለት ዮሐንስ ተገናኝቷልና ፡፡

° የኤደን ገነቱ የሰርግ ታሪክ ጸሐፊ ከቃናው የሰርግ ታሪክ ጸሐፊ ተገናኝቷልና።

° የብሉይ ኪዳኑ ወንጌል(ዘፍጥረት ) ጸሐፊ ሙሴ " አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ " አየም ደስም አለው፡፡" ብሎ ኦሪት ሳትሰራ ወንጌል እንደነበረች ከመሰከረለት ወንጌላዊ ዮሐንስ ጋር ተገናኝቷልና ፡፡

ስለዚህም በታቦር ተራራ የብሉይ ኪዳን ጸሐፊ የሐዲስ ኪዳኑን ጸሐፊ አየ ፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ልቡናችንን የታቦር ተራራ አድርጎ በመለኮታዊ ብርሃኑ እንደ ሊቀ ነቢያት ሙሴ አእምሮአችንንና ማደሪያ ቤተመቅደሱ የሆነውን ሰወነታችንን ያብራ፡፡ መለኮታዊው ብርሃኑም ለአእምሮአችን ማስተዋልን በመጨመር በጽድቅ እንድንመላለስ ያብቃን ለዘለዓለሙ አሜን!!!

henok.haile
#share

▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile

4 months, 2 weeks ago

...ሁለቱ ጸሐፍያን በደብረ ታቦር ...
ክፍል አንድ

በሕይወት ታሪካችን ብዙ የቅርብ ፣ የሩቅም ወዳጆች አሉን ፡፡ እጅግ ቅርብ በሆኑን ወዳጆቻችን በኩል ለእነርሱ ቅርብ ፥ ለእኛ ደግም በጣም ሩቅ ስለሆኑ ሰዎች ሰምተናል ። ስለ ማንነታቸው ፣ አስተሳሰባቸው ፣ ፍልስፍናቸው ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው ፣ ዝናቸው ባጠቃላይ ስለ ነገረ ሥራቸው ሁሉ የተደነቅን ከመስማታችን የተነሳ በአካል ሳናውቃቸው የልብ ወዳጆቻችን የሆኑ ብዙዎች አሉ ። ታዲያ! እነዚህን ሰዎች በአጋጣሚ በአካል ብናገኛቸው ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል ? ስለምን እናወራቸው? ምንስ እንጠይቃቸው ይሆን? ይህን ጥያቄ እንድንጠይቅ ከሚያጓጉን ታሪኮች አንዱ በደብረ ታቦር የተፈጸመው ነው ፡፡

እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው ሦስቱ ወንጌላውያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን ምስጢር አዘል ታሪክ በተመሳሳይ ሁኔታ መዝግበዋል ፡፡ ምንም እንኳን ሶስቱ ወንጌላውያን በደብረ ታቦር ተራራ የተከናወነውን ድንቅ ክስተት ቢመዘግቡም የተለያየ የታሪክ አጻጻፍ ተክትለዋል ፡፡ አንዱ ያጎደለውን አንዱ አንዱ እየጨመረ ፣ አንዱ የረሳውን አንዱ እያስታወሰ ጽፈዋል። ማቴ 17÷ 1-9 , ማር 9÷ 2-10 ,ሉቃ 9÷ 28-36

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እስከገለጠበት እስከዚያች ቀን ድረስ ለሐዋርያት ፥ እስራኤላውያን አብልጠው ስለሚወዱት ሙሴ እንዲሁም “ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናል " ተብሎ ስለ ተነገረለት ኤልያስ ፥ ብዙ ጊዜ ስማቸውን እያነሳ ብዙ አስተምሯቸዋል ፡፡ ታዲያ! በክርስቶስ አንደበት ስለ እነዚህ ታላላቅ አባቶች ታሪክና ድንቅ ሥራ የተገረሙ ሲሰሙ የነበሩ ሐዋርያት እነዚህን አባቶች ምን ያህል ማየትና መነጋገር ሽተው ይሆን? የሐዋርያትና የእነዚህ አባቶች መገናኘት አስደናቂ ገጠመኝ ነው ፡፡

ይህን የደብረ ታቦር ታሪክ በተመለከተ የሶርያውያን ፀሐይ ፣ የኤዴሳው ዲያቆን ቅዱስ ኤፍሬም የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮት የተገለጠበት ተራራ ላይ የተፈጸመውን

"There the authors of the old covenant saw the authors of the new. Holy Moses saw Simon Peter the sanctified; the steward of the Father saw the administrator of the Son... The virgin of the old covenant (Elijah) saw the Virgin of the new (John); the one who mounted on the chariot of fire and the one who leaned on the breast of the Flame. And the mountain became a type of the Church, and on it Jesus united the two covenants :...

'የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን አዩ ፤ ቅዱሱ ሙሴ ቅዱስ ጴጥሮስን አየው የአብ እንደራሴ የወልድን አገልጋይ ተመለከተው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ድንግል ኤልያስ የሐዲስ ኪዳኑን ድንግል ዮሐንስን አየው፡፡ በእሳት ሰረገላ ላይ የተሳፈረው ኤልያስ ወደ እሳታዊው ክርስቶስ ደረት የተጠጋውን ዮሐንስን አየው፡፡ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ሆነ ፤ ክርስቶስም ሁለቱን ኪዳናት አዋሐዳቸው!' " በማለት በንጽጽር ድንቅ ምስጢር ይነግረናል ።
#share

▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile

4 months, 4 weeks ago
5 months, 2 weeks ago

ሐምሌ 15 የትሕትና ባሕር ፣ የቅኔ ዋናተኛ ፣ የኤፍራጥስ ወንዝ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ያረፈበት ዕለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ጸጋን በሚሸከም ትሕትና የተሞላ አባት ነበር::

ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያን ለማግኘት ባደረገው ጉዞ ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ ባስልዮስ እየሰበከ ነበር፡፡ ስብከቱን ሲፈጽም በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት አንድ ቋንቋ ከመናገራቸው በፊት በአስተርጓሚ እርዳታ

'ኤፍሬም ነህ ወይ?' አስብሎ ቅዱስ ባስልዮስ አስጠየቀው፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም በባስልዮስ አንደበት ስሙ ሲጠራ ሲሰማ “ከመንግሥተ ሰማያት መንገድ СФ የተጣልሁ ኤፍሬም እኔ ነኝ" ካለ በኋላ በዕንባ እየታጠበ 'አባቴ ሆይ ኃጢአተኛው ክፉ ሰው ራርተህ በጠባቡ መንገድ ምራኝ” አለ፡፡

አንድ ሶርያዊ መነኩሴ አግኝቼ የቅዱስ ኤፍሬምን መቃብር መሳለም እንደምፈልግ ጠይቄያቸው ነበር:: ፈገግ አሉና እንዲህ አሉ :‐ "ቅዱስ ኤፍሬም እኮ መቃብሩ እንዳይታወቅ ታናዝዞ ስለሞተ የት እንደተቀበረ የሶርያ ቤተ ክርስቲያንም አታውቅም"

ቅዱስ አባታችን ሆይ በመንፈሳዊው ብዕርህ ትዕቢተኛ ልባችንን ፈውስልን::
#share

▫️@diyakonhenokhaile
https://t.me/diyakonhenokhaile

We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 week, 2 days ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months ago