ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated hace 1 semana, 1 día
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated hace 1 semana
BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot
Last updated hace 2 meses
ረሱል (▫️) እንዲህ ብለዋል፦
﴿شيبتني هودٌ وأخواتُها قبل المشيبِ﴾
“የሁድ ምዕራፍና እህቶቿ (አምሳያዎቿ) ከመሸበቴ በፊት አሸበቱኝ።”
📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 3721
📌ጥቂት ማብራሪያ፦ በቁርዓን ውስጥ የሁድ ምዕራፍና እህቶቿ (አምሳያዎቹ) ወልዋቂያ፣ ወልሙርሰላት፣ አማ የተሳዓሉን፣ ወኢዘሸምሱ ኩዊረት የያዙት መልዕክት በቀጣዩ አለም (የቂያማ እለት) በሰዎች ላይ ስለሚከሰቱ አሳዛኝ፣ አስደንጋጭ፣ አስፈሪ ነገሮች በውስጣቸው መልዕክት ያለባቸው ምዕራፎች ናቸው። እነዛ መልዕክቶች ናቸው ከመሸበታቸው በፊት ያሸበታቸው።
ከአቡ ሁረይራ (▫️) ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦
﴿سُئِلَ النبيُّ ▫️ أيُّ الأعْمالِ أفْضَلُ؟ قالَ: إيمانٌ باللَّهِ ورَسولِهِ قيلَ: ثُمَّ ماذا؟ قالَ: جِهادٌ في سَبيلِ اللَّهِ قيلَ: ثُمَّ ماذا؟ قالَ: حَجٌّ مَبْرُورٌ.﴾
“ነቢዩ (▫️) እንዲህ በማለት ተጠየቁ፦ ከስራዎች ብልጫ ያለው የቱ ነው? በአላህና በረሱል ማመን ነው አሉ። ከዛ ቀጥሎ ሲባሉ? በአላህ መንገድ ላይ መታገል (ጂሃድ) ነው አሉ። ከዛስ ቀጥሎ ሲባሉ? ሐጀል መብሩር ነው አሉ።”
📚 ቡኻሪ (1519) ሙስሊም (83) ዘግበውታል
@muhamedunresulullah
የአረፋ ቀን ፆም መፆም እንዳትረሳ!
ከአቢ ቀታዳ ተይዞ፡ ነቢዩ ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦
“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”
ሙስሊም ዘግበውታል: 1162
ማስታወሻ፦ የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ቅዳሜ ሰኔ 8 ነው።
ስታርድ እዝነት ይኑርህ!
ረሱል እንዲህ ብለዋል፦
“አላህ ኢኽሳንን (ማሳመርን) በሁሉም ነገሮች ላይ ፅፏል። የገደላችሁ እንደሆነ አገዳደልን አሳምሩ። አንዳችሁ ባረደ ግዜ አስተራረዱን ያሳምር ማረጃውን ይሳል። የሚታረደውንም እንስሳም ያሳርፍ።”
ሙስሊም ዘግበውታል: 1955
በሌላ ሀዲስ፦
“አንድ ሰው ወደ አላህ መልዕክተኛ በመምጣት እንዲህ አላቸው፦ ‘እኔ በጌን አርጄ ለሷም እዝነትን አድርጌ ነበር’ ረሱል አሉት፦ ‘ለሷ ለበግህ እዝነትን እንዳደረክ አላህ ለአንተም ይዘንልህ።’”
ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 1081
ቁርኣንን የማስተማር ትሩፋት!
ረሱል እንዲህ ብለዋል፦
“ከአላህ መፅሀፍ (ቁርኣን) አንዲትም አንቀፅ ያስተማረ፤ ለሱ በሚቀራው (በሚነበበው) አጅር (ምንዳ) ይኖረዋል።”
ሲልሲለቱ አሶሂሃ፡ 1335
ተፈጥሯዊ ፅዳቶች!
ረሱል እንዲህ ብለዋል፦
“አምስት ነገሮች ተፈጥሯዊ ፅዳቶች ናቸው። መገረዝ፣ የብልትን ፀጉር መላጨት፣ ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፣ ጥፍርን መቁረጥና የብብትን ፀጉር መንጨት፡፡”
ቡኻሪ (5891) ሙስሊም (257) ዘግበውታል
ማስታወሻ!
ረሱል እንዲህ ብለዋል፦
“የዙልሂጃ ወርን ጨረቃ ካያችሁና ከናንተ መካከል አንዱ ኡድሂያን ለማረድ ካቀደ ፀጉሩንና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ።”
ሙስሊም ዘግበውታል: 1977
ደጃልም ወረርሽኝም አይገባም!
ከአቡ ሁረይራ ተይዞ፡ ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፦
“በመዲና መግቢያዎች መንገዶች ላይ በጥበቃ ላይ የተሰማሩ መላእክት አሉ። ተላላፊ ወረርሽኝና ደጃል አይገባበትም።”
ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 7133
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated hace 1 semana, 1 día
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated hace 1 semana
BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot
Last updated hace 2 meses