Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

TIKVAH-MAGAZINE

Description
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 3 weeks, 6 days ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 3 weeks, 5 days ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 1 week ago

3 weeks, 5 days ago
TIKVAH-MAGAZINE
3 weeks, 5 days ago
TIKVAH-MAGAZINE
3 weeks, 6 days ago
1 month ago
በኢትዮጵያ ባለፈው የካቲት ወር ብቻ 705 …

በኢትዮጵያ ባለፈው የካቲት ወር ብቻ 705 ሺ ሰዎች በወባ ተይዘው 764 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ ባለፈው የካቲት ወር ውስጥ ብቻ 705 ሺ ሰዎች በወባ በሽታ ተይዘው፥ 764 ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።

በሪፖርቱ መሰረት በኢትዮጵያ በወባ በሽታ ተይዘው የተመዘገቡ ሰዎች ቁጥር ወደ 5.2 ሚሊዮን ከፍ ሲል፥ የሟቾች ቁጥርም በጥር ወር ከነበረነት 611 በየካቲት ወር ወደ 764 ጨምሯል። በዚህም የሟቾች ቁጥር በ25 በመቶ መጨመሩን ሪፖርቱ አመልክቷል።

በወባ በሽታ ​​የተያዙት ሰዎች አብዛኞቹ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ሲሆኑ የአማራ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በቅደም ተከተል ከፍተኛውን በወባ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስመዝግበዋል። የጋምቤላ ክልል ደግሞ ከ100,ሺ ሰዎች መካከል ከፍተኛውን በወባ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እንዳስመዘገበ ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine

1 month ago
ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ከውጭ ለማስገባት የኬንያን ላሙ …

ኢትዮጵያ ማዳበሪያ ከውጭ ለማስገባት የኬንያን ላሙ ወደብ ልትጠቀም ነው ተባለ

ኢትዮጵያ በኬንያ ላሙ ወደብ በኩል ከውጭ ማዳበሪያ ለማስገባት ከሳምንት በፊት ሁኔታውን እንዲገመግሙ ልዑካን ቡድኗን ወደ ኬንያ መላኳን ካፒታል ዘግቧል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ደንጌ ቦሩ “ወደቡን በቅርቡ እንጠቀማለን” ያሉ ሲሆን ልዑካን ቡድኑ ያገኘውን ውጤት ለትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እንደሚያቀርብና በእቅዱ መሰረት ከፊሉ የማዳበሪያ ጭነት በላሙ ወደብ በኩል እንደሚጓጓዝ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ከህዳር ወር ጀምሮ በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት የጅቡቲ ወደብን መጠቀም እክል እንደሆነባት ተገልጿል። ይሁን እንጂ ከጅቡቲ ወደብ ጋር ሲወዳደር ኢትዮጵያ ልትጠቀመው ያቀደችው አማራጭ የኬንያ ወደብ ከርቀቱ አኳያ የሚያስወጣው ዋጋ ውድ እንደሆነ ተነግሯል።

@TikvahethMagazine

1 month ago
የ 3 አመቷን ህጻን አስገድዶ በመድፈር …

የ 3 አመቷን ህጻን አስገድዶ በመድፈር ገድሎ ተሰውሮ የነበረው ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ

ቢሊሱማ መሃመድ የተባለችውን የሶስት አመት ህጻን የእንጀራ ልጁን አስገድዶ በመድፈር ገድሎ ተሰውሮ የነበረው ተጠርጣሪ ግለሰብ በድሬዳዋ ከተማ መልካ ጀብዱ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የድሬዳዋ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የሟች እናት ከባለቤቷ ጋር በትዳር መቀጠል ባለመቻላቸው ምክንያት ከተለያዩ በኃላ ወደ ሀሮማያ ከተማ በመሄድ ሌላ ባል አግብታ ህጻኗም ከእናቷ እና እንጀራ አባቷ ጋር ትኖር ነበር፡፡ ተከሳሹ የእንጀራ አባቷ ግለሰብ ለ15 ቀን በትዳር ከቆየ በኃላ ለጋዋን ህጻን አስገድዶ ደፍሮ መግደሉ ተገልጿል።

ለአስራ አንድ ወራት ተሸሽጎ የቆየው ተጠርጣሪው መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት ከተሸሸገበት ወጥቶ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ  በቁጥጥር ስር ውሎ ለሀሮማያ ከተማ ፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine

1 month, 1 week ago
አሜሪካ ኤችአይቪ ኤድስን ለመግታት ይረዳል ያለችውን …

አሜሪካ ኤችአይቪ ኤድስን ለመግታት ይረዳል ያለችውን 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንደምትሰጥ አሳወቀች

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2030 ኤችአይቪ ኤድስን ለመግታት  የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የሚውል 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ እንደምታደርግ አሜሪካ አስታውቃለች።

የገንዘብ ድጋፉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የአስቸኳይ ጊዜ የኤድስ ድጋፍ ዕቅድ (PEPFAR) በኩል የሚሰጥ ሲሆን የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የኤድስ አስተባባሪና የዓለም ጤና ጥበቃ እና የጤና ደህንነትና ዲፕሎማሲ ከፍተኛ ባለስልጣን አምባሳደር ዶ/ር ጆን ንኬንጋሶንግ ድጋፉ መፅደቁን ይፋ አድርገዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የአስቸኳይ ጊዜ የኤድስ ድጋፍ ዕቅድ ኮፕ 23 የተሰኘ ኤችአይቪ ኤድስን ለመከላከል የሚረዳ መርሃ ግብር ይፋ ያደረገ ሲሆን በዋነኛነት ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የኤችአይቪ አገልግሎትን ማሻሻል፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ እንደ ህጻናት፣ ታዳጊዎች እና ጾታን መሰረት ካደረገ ጥቃት የተረፉ ሰዎችን መደገፍ  ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆኑም ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine

1 month, 1 week ago
በዳዉሮ ዞን ከፓርክ የወጡ 12 ዝሆኖች …

በዳዉሮ ዞን ከፓርክ የወጡ 12 ዝሆኖች በሰዉ እና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሱ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዳዉሮ ዞን ከጪ ወረዳ ኦዳ ጎፋ ቀበሌ ዝግና ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከፓርክ የወጡ 12 ዝሆኖች በሰዉ እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የዳዉሮ ዞን ፖሊስ አስታውቋል።

እንደ ፖሊስ ሪፖርት የዱር እንስሳቱ መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ከጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፖርክ የወጡ ሲሆኑ በሃያዎች ዕድሜ ክልል የምትገኝ ወጣት ከትምህርት ቤት ወደ መኖሪያ ቤቷ በመሄድ ላይ የነበረች የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ በዝሆኑ መንጋ ሆዷ ላይ ተረግጣ ጉዳት እንደደረሰባት ተነግሯል።

ወጣቷ ታርጫ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላት እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን የዝሆን መንጋዉ በንብረት ላይ የደረሰዉን የጉዳት መጠን እየተጣራ እንደሚገኝና ዝሆኑ ወደፖርኩ አለመመለሳቸዉን ፖሊስ ገልጾ ህ/ሰቡ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስበት ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቱን አስተላልፏል ሲል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት አስታውቋል።

@TikvahethMagazine

1 month, 1 week ago
TIKVAH-MAGAZINE
1 month, 2 weeks ago
በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ …

በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 31 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ

በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ 38 የትራፊክ አደጋዎች መድረሱንና በነዚህ አደጋዎች የ31 ሰዎች ህይወት ማለፉን የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል መግለፁን ብስራት ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።

አደጋዎች የተከሰቱት ከየካቲት 25 እስከ መጋቢት 2 ፥ 2016 ዓ/ም ባሉት ቀናቶች ሲሆን በተከሰቱት 38 አደጋዎች የ31 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፥ 17 ከባድ የአካል ጉዳት እና በ18 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ዘገባው ጠቁሟል።

የአደጋዎቹ መንስኤ  ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት ፣ ያለመንጃ ፍቃድ ማሽከርከር፣ በፍጥነት ማሽከርከር ፣ ላልተፈቀደ አገልግሎት ጨለማን ተገን አድርጎ ማሽከርከር መሆናቸውም ተጠቅሷል።

አደጋዎቹ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች እና ዞኖች ላይ የተከሰቱ ሲሆን በአጠቃላይ በደረሱት አደጋዎች ምክንያት በ 8 ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት  መድረሱም ነው የተገለፀው።

ፎቶ፦ ፋይል

@TikvahethMagazine

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 3 weeks, 6 days ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 3 weeks, 5 days ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 1 week ago