Daniel Aweke(ዮዳA)

Description
?ዳኒ ነኝ! Follow አታድርጉ Fan ብቻ ሁኑ።

?ምክንያት ካላችሁኝ "Only God wanna Followers not Fans! "

?እናም ይኸ ገጽ የኔን ስራዎች የሚያገኙበት ቻናል ነው። "✍️ዮዳA "

Facebook:https://www.facebook.com/daniyeuodit.lij
Tiktok:@daniel_aweke

https://vm.tiktok.com/ZMM7JCXbQ/
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 4 weeks, 1 day ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months, 3 weeks ago

5 months, 2 weeks ago

እንትን ፊልም እንትን ሙዚቃ እኮ ከውጭ ሀገር የተቀዳ ኮፒ ፔስት ነው የሚሉትን አጥብቄ አወግዛለሁ። USA ወይም UK የተሰራ ፊልም ወይም የተዜመ ዜማ አልያም መጽሐፍ የተፃፈው በነጭነት ሊሆን ይችላል። ሀገራችን ሲመጣ ግን ግራጫ ወይምጰ ጥቁር ሆኖ ነው የሚሰራው። USA በሆሊውድ በቪላ ቤት የተሰራ ፊልም እዚህ መጥቶ በጓጆ ቤትና ኩሽና መሰራቱ ያን ህይወት ማስመልከት አንድ ልዩነት ነው፣ የኔና የኦባማ አልያም ፑቲን ህይወት መመሳሰል ሊኖረው ይችላል። ግን በፍፁም የኔን ኑሮ አልኖረውም አይኖረውምም

5 months, 2 weeks ago

ቁስ ወይስ...
✍️ጉርድወግ Gurdog

"መቼ ነው የምታገባው? መቼ ነው ወግ መአረጌን ምታሳየኝ የኔ ልጅ? " ዘወትር ያለመታከት የምትጠይቀኝ ጥያቄ ነው። እናቴ ምንትዋብ።

የኔ መልስ እንደ ፈጣሪ ቃል ሳይለወጥ አንድ ብቻ ቢሆንም፤ ምንቱ ግን ያለ መሰልቸት ትነዘንዘኛለች።ሁልጊዜ ትጠይቀኛለች።

'ምንቱ...ማግባቱን 'ኮ ጠልቼው አይደልም። ጋብቻ ሲባል ቤት፣ የቤት እቃ አለፍ ሲልም ደግሞ አዲስ ለምናመጣው ነፍስ የራሱ የሆነ ነገር ማዘጋጀት ግዴታዬ ነው እማ።' በተማፅኖ አይነት ለስለስ አድርጌ እንድትረዳኝ መልስላታለሁ።

"ኤጭ የዘንድሮ ወጣት ደግሞ፣ አጉል አስተዋይ ነኝ ትላላችሁ።
ቤት ገዝቼ፣ የቤት እቃ አሟልቼ፣ መኪናና ንብረት አከማችቼ፤ ነው ምናምን የምትሉት ጉዳጉድ አላችሁ። አረ እንዲያው ለመሆኑ ግርም የምትሉኝ ሚስት ቁስ ናት እንዴ ሁሉንም ካሟላችሁ በኋላ የጎደለች ሚስት ናት በሚል እንደ ቁስ ሴትን ለማሟላት ከጎዳና ገበያ የምትወጡት? እኔና አባትህ በዚህ አናምንም።

ቤቱን ሙሉ የምታደርገውን ዘውዴን አንቺን በቅድሚያ አግኝቼ ከሷ በኋላ ቁሳቁስ ይከተላል ብሎ ነው ከአንዲት ክፍል ቤቱ ከውስጧ አንዲት ፍራሽ ብቻ ያላትን፣ ሚስት ያለችበት ሙሉ ቤት ነው ብሎ አሳምኖ ያገባኝ።

ባይገርምህ ልጄ....ምግብ ማብሰያ፣ ወንበርና ሶፋ፣ ቲቪ ገለመሌ የሚባሉ ቁሶች ከቤታችን ባይኖርም፤ ከቁርስ እስከ 'ራት ውጭ እየተመገብን በጊዜ ሂደት ቁሱ እየተሟላ ሄደ። እንደምታየው አሁን ቤቱ ሙሉ፤ ሲታይ የሚያስቀና ቤተሰብ መሠረትን።"

'እሱ በናንተ ጊዜ ነዋ! ልጅ ወደምድር አምጥቶ በእድሉና እጣፈንታው ያድጋል የሚባልበት ዘመን አክትሟል! አሁን ላይ ልጁ ከመምጣቱና ከትዳር በፊት ከኔ በኋላ ለማምጣት ሚስትና ልጅ ምቹ አለም መፍጠር አለብኝ እማ።

ልጁ መጥቶ እኔ የኖርኩትን ኑሮ መድገም የለበትም! ተዋናይ ለመሆን ፈልጎ ገንዘብ ስለሌለ ብቻ ያለፍላጎቱ ኢንጂነር ወይም ዶክተር አልያም ሌላ ሌላ ገንዘብ ለመልቀሚያ አእምሮን ጨምቀው ኦና ለሚያደርግ ግዳጅ አልከውም። ገንዘብ እንዲያመጣ ብቻ ፍላጎቱን ገድቤ የዘፈቀደ ኑሮ አላኖረውም። ተዋናይ፣ ሙዚቀኛ፣ ኳስ ተጫዋች ...የፈለገውን እንዲሆን ቅድሚያ ተዘጋጅቼ እሱ ሲደርስ የፈለገውን እንዲማር፣ የፈለገውን እንዲያደርግ ካሁኑ ጥሪት አስቀምጬ ነው ትዳር ማሰብ።' ብዬ ከመጨረሴ

"ከባለቤቱ ያወቀ ባዳ ነው። በል ቀጥልበት፤ እኔ የአቅሜን ነግሬካለሁ። ትሰማኝ እንደሁ ስማ፤ ካልሰማህ ግን እድሜ ሲሄድና ጌዜህ እንደ እሳት ነድዶ አመድ ሲሆን አሁን ያልካቸውን አንዱንም ሳታሟላ ባክነህ እንዳትቀር። እኔ እንደሁ የሁለቱ ወንድሞችህን ወግ መአረግ አይቼ ተደስቻለሁ። ድግስ ወይም አሸወይና አምሮኝ እንዳይመስልህ በእየለቱ አግባ የምልህ። ለራስህ አስብ።" ጨረሰች። ግልግል።

ከንግግሯ ሁሉ ግን አንድ ስንኝ ጎልታ ተሰማችኝ። ሰአት ደርሶ የእማን እጆቿን ስሜ ወደስራ ቦታዬ እየሄድኩ ደግሜ አነበነብኩት ...

' "ለመሆኑ ሚስት ቁስ ናት እንዴ? ሁሉንም ካሟላችሁ በኋላ የጎደለች ሚስት ናት በሚል እንደ ቁስ ሴትን ለማሟላት ከጎዳና ገበያ የምትወጡት?" ' ትልቅ ርእሰ ነው ያነሳችው።

'ለምን ለከሰዓት የሬድዮ ፕሮግራሜ መወያያ አላድርገውም? አድማጮች በዚህ ጉዳይ ምን ይሉ ይሆን? ቤት ይሟላ? ወይስ ሚስት ትቅደም?' አልኩኝ ለራሴ-ሴባስቶፖልን አልፌ ወደ ሬድዮ ጣቢያው ዘልቄ እየገባሁ።

✍️ዮዳA
6:03ሌ (18/9/2015ዓ.ም )

5 months, 3 weeks ago

ከኢ-ትዮጵያ ልደበቅ
ከባዕዳን ምድር ልወሸቅ
ልሂድ፣ ልጓዘው
እግሬ ወደመራው
ኢያሪኮ ሆና ሀገሬ ፈርሳለች
ቅድስት ናት ያልኳት በደም በክያለች
ኢ- ያሪኮ...
የሞት ምርኮ
ኢ-ትዮጵያ...
የደም ቃርሚያ ።
እንበተን፣ እንዘራ
እንለያይ፣ ሳንፈራ
በክፋቶች ጩኸት የፈረሰችው ሀገሬ
ሁሉ የሆነባት ሽፍታ ቂም ያጎፈረ ጎፈሬ
እስክትገነባ
መጥታ እምዬ ሳባ
አልያም ፀሀይቱ
በአለም ያበራችቱ
አልያ ደግሞ እሌኒ
ጽድቅ ፍትህ ወጣኒ
የተቀበረ፣ ያልበሰበሰ ህልቁ መሳፍርት ቆፋሪ
ቆፍረሽ አውጭን ከተቀበርንበት ጽልመት እዳሪ
ብካይ ድምፅ ያፈረሳት ኢያሪኮ ትገንባ
እንደ እየሩሳሌም በዝጉ በር እንግባ
እንበተን፥ እንደፍርስ
እንለያይ፥ እንፈርከስ!
ዳግም ነጽተን እን'ገንባ
ሳይደፈርስ መቸ ይጠራል
ያልፈረሰስ መቼ ይገነባል
ኢ- አፍራሽ አሉታ ናት
ጦቢያ አዎንታ ጽኑ ጽናት
ተነሱ እንሰደድ አንፈርከስ
ኢ ጠፍታ ጦቢያ እስክትነግስ።

እንፈርከስ፥ እንገንደስ
እንፈራርስ፥ እንደፍርስ!!!
ውሃም ደፍርሶ ነው የሚጠራ
ግድየለም ሀገር ትፍረስ ሳንፈራ።

ዮዳA
5:31 ቀ
8/9/15

5 months, 3 weeks ago

#እግረመንገድ_2
☘️ ሔምሎክ

በዓለም ላይ በይፋ በገለጸው ሃሳብ የተነሳ፣ ቅጣት ይሆነው ዘንድ የሞትን ጽዋ እንዲጎነጭ የተፈረደበት ቀዳሚው ሰው ግሪካዊው ፈላስፋ ሶቅራጥስ ነው።
የታሪክ መዛግብት እንደሚገልጡልን የኖረበት ዘመን ከ470 - 399 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ነው ።

ሶቅራጥስ ሞቱን እንዲሞታት የተገደደው፣ ' በወጣቶች አእምሮ ላይ ያልተገባ ሃሳብ አሰራጭተሃል፤ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ፈጽመሃል' ተብሎ ነው። ሶቅራጥስ ከፍርድ ሂደቱ ቀደም ብሎ በገሃድ የተናገራቸው ፍልስፍናዊ ሃሳቦቹን እንዲያስተባብል ተጠይቆ ነበር። ደቀመዝሙሩ ክሪቶ ገንዘብ ሰብስቦ ለጠባቂዎቹ ሰጥቷቸው መምህሩን ከእስር ሊያስፈታ እላይ ታች እያለ መሆኑን ቢነግረውም ሶቅራጥስ ግን እንዲህ አለው "ዘመኔን ሁሉ ለሕግ እንደኖርኩ አሁንም ለእርሷ(ለህግ) ለመሞት እንደተዘጋጀሁ ታውቃለህ? ሕግን ገድዬ እኔ ነፃ ከምወጣ እኔ ሞቼ ሕግ ነፃ ትውጣ።" በማለቱ ወዳጆቹ በውሳኔው ተደናግጠው አበክረው መከሩት፤ ሆኖም ግን እሱ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ።

ከሳሾቹም በስተመጨረሻ
ሔምሎክ ከሚባለው ዛፍ የተቀመመ ሻይ በስኒ አመጡለት። ሶቅራጥስም የእስርቤት ጠባቂውን አንተ ብዙ ልምድ ስላለህ እንዴት መርዙን መውሰድ እንዳለብኝ እና እንዴት እንደምሞት ንገረኝ ብሎ በትህትና ጠባቂውን ጠየቀው።

የእስርቤት ጠባቂውም ሶቅራጥስን እንዲህ አለው "አወሳሰዱ በጣም ቀላል ነው።አንድ ግዜ ከተጎነጨኸው በኋላ በሰውነትህ እስኪሰራጭ በደንብ ተንቀሳቀስ እና ሰውነትህን ዘርግተህ ተኛ " አለው። ሶቅራጥስም ሻዩን ጠጥቶ ሰውነቱ እስኪዝል ድረስ ከተንቀሳቀሰ በኋላ በሰውነቱ ሙሉ መርዙ ሲሰራጭ አ
እንደተባለው መሬት ላይ እግሩን ዘርግቶ ላይመለስ አንቀላፋ።

ሀሳብ እና ማሰብ በተለይም ደግሞ ምክንያታዊ አስተሳሰብና አመለካከቶች ልክ እንደመርዝ ናቸው። ይፈውሳሉ ወይም ይገድላሉ። ወይ እራስንና ትውልድን ያስመልጣሉ ወይም ያጠፋሉ። በመሆኑም እንደ ግለሰብ፣ እንደ ቤተሰብ፣ እነደ ሀገር በአጠቃላይ እነደ ሰው በጎ በጎውን እናስብ።

እንደመነሻና ማጣቀሻነት:-
-<የጋዜጠኛና መምህር አብረሃም ፀሀዬ መጣጥፍ
-<የዮናስ ዘውዴ ከበደ "ሔምሎክ" (ሰኔ 2010 እትም)መጽሐፍ

ዮዳA

5 months, 4 weeks ago

#እግረመንገድ
#የቲቪ_ላይ_ትያትሮች (ሲትኮም ድራማ!)

አሁን ላይ በቴሌቪዥን መስኮት ላይ የሚታዩ የሲትኮም ወይንም አስቂኝ ድራማዎች እንደ ምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ክዋክብት በዝተዋል ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከዚህም በላይ ደግሞ ከቴሌቪዥን መስኮት ባለፈ በየዩቲዩብ ገጽ ላይ የሚሰሩ ሲትኮሞችም እንዲሁ በዝተዋል። እነዚህ ሲትኮም ድራማዎችን እኔ በግሌ የትያትር አምሮቴ ጥም መቁረጫ ሌላ የቴያትር መድረክ ስለሆኑ እግር በእግር እከታተላለሁ።

በቴሌቪዥን መስኮት ከሚታዩት ውስጥ:-
->ዘጠነኛው ሺህ (ቀድሞ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት-FBC፤ አሁን ደግሞ በኢቲቪ-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መታየቱን የቀጠለው---[ግን ለምን በፋና ቲቪ እስካሁን ድረስ ተቋርጦ ቆየ?]
->በስንቱ (በኢቢኤስ )
->የከርሞ ሰው (ቀድሞ በLtv ፤በቅርቡ ደሞ በdstv)
-አስኳላ(በdstv-አቦል)
->የያዕቆብ ልጆች (100ሚሊዮን በዩቲዩብ )

አይኔን ገልጬ፣ ጆሮዬን ሰጥቼ ከምከታተላቸው ውስጥ ናቸው፤ በርግጥ ከነዚህም በላይ ያልጠከስኳቸው ሌሎች ሲትኮም ድራማዎች መኖራቸውን ልብ ይሏል።

እንደተመልካችነቴ ግን ከጥቂቶቹ በቀር አብዛኞቹ ችግሮቻችን ላይ ስቀውና ለማሳቅ(ለማሳቀቅ ) ሞክረው ከማለፍ ባሻገር ይኸ ነው የተባለ የመፍትሔ ሃሳብ አሊያም ደግሞ ጭብጣቸውን ይሄ ነው ብዬ ለመወሰን እቸገራለሁ።በተለይ ደግሞ "ትወና ጥርሳቸውን የነቀሉበት ነው" ከተባሉት አንዳንድ ተዋናዮች ስብስብ የማይጠበቅ የፌዝ "ሰራሁ" ለማለት ብቻ ተመልካቹን ንቀው የሚሰሩት የጓዳ ውስጥ ሸንጎና ሰጥአገባ ትዝብት ውስጥ ይከታል። በተቃራኒው ደግሞ ጀማሪ (Amateur ) ከተባሉት ደግሞ የማይጠበቅ ትልቅ አቅም ሲታይ ግርምት፣ አልፎም ደግሞ መወደድና ለቀጣዩ እርምጃቸው መሠረት ይጥሉበታል።

ለምሳሌነት ብናነሳ "የከርሞ ሰው" ሲትኮም በጊዜው በጣም ተወዳጅ የነበረ ነው።

ከከርሞ ሰው አንዱ ነበራቸውንና አሁናቸውን እንዲህ ሲል በውስጥ መስመር ገልፆልኛል፦
<<
"የከርሞ ሰው" በኤል ቲቪ ሲታይ የነበረነቱ እርግጥ ቢሆንም ከመዘጋቱ አንድ ዓመት ቀድሞ ነው በአቅም እጥረት የቆመው እንጂ ከጣብያው መዘጋት ጋ አይደለም። በነገራችን ላይ በዓመቱ አሐዱ ቲቪ ላይ (ኤል ቲቪ እያለ) በነሱ የቀረጻ ቁሳቁስ ድጋፍ ልዩ የገና በዓል ክፍል ሰርተን እንደነበር ልብ ይሏል።

ሌላው የምዕራፍ አንድ ቀረጻው እየተገባደደ ያለው ስራችን አሁን በዲኤስ ቲቪ እየታየ አይደለም። ጨርሰን መጀመር ስለፈለግን ገና ለመተላለፍ መቆየቱ አይቀሬ ነው።

ሲጀመር "ከከርሞ ሰው" ጋር አይገናኝም። ዘመኑን ሰባ ሁለት ላይ ያደረገ ሌላ ሀዘን ከፍስሃ (ትራጃይ ኮሜዲ) ስራ ነው እየቀረጽን ያለነው እንጂ ሲትኮምም አይደለም። ሁለቱን ስራዎች ዘመን ብቻ ነው የሚያመሳስላቸው እንጂ ዘውጋቸው ይለያያል።

እኒህ ዘመን ያፈራቸው ድንቃዮች በድራማቸው ለመንካት የማይደፈረውን ትላንታችንን ወደ ኋላ መለስ ብለው በደም የጨቀየ የተባለለትን የ"ደርግ"ን ዘመን ሳቅ ጨዋታና ፍቅርም እንደነበረ ሰርተው አሳይተዉናል። ለዚህም ብሩክ ሚፍታህ ጉምቱውን ቦታ ይይዛልና ባለህበት ምስጋናዬ ከልብ ነው።

በዩቱብ ገጽ ካገኘኋቸው መካከል ደግሞ የ "ፍቃዱ ከበደ" ስራ የሆነውን "100 ሚሊዮን " ፍቄና ጥቂት ሲነየሮችን እና ከሌሎች ጀማሪ ከሚባሉት ጋር የተሰራው ጥሩ ሳቅ plus ደግሞ ብዙ ቁምነገር የሚያጋራ ሆኖ አይቸዋለሁ (ታላላቅ ተዋናዮች ግን እንደዚህ ዝቅ ብለው ከሚመጣው ከአዲሱ ትውልድ ጋር የመስራት ልምድ ቢደልብ ባይ ነኝ።)

ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስና ሳቅ መፍጠሩ ሸጋ ሆኖ፥ ከሳቁ ጀርባ ደግሞ ተመልካቹ የሆነ ስንቅ ነገር በልቦናው መቋጠር አለበት በዚያ መልኩ የታሰበበትና የተደከመበት "ቀራጺ" የሆነ "ፍሬከርስኪ" ያልበዛው ስራ ተመልካቹንና ተደራሲውን አክብሮ ማቅረብ አለባቸው።

ለዚህም ከ "በስንቱ" ሲትኮም ድራማ ልምድ መወሰድ አለበት። በስንቱ ከካሜራ ጥራት ጀምሮ ሁሉም ነገር ጥንቅቅ ብሎ የቀረበ "ምርጥ!!!" ቃሉ የማይገለጸው ሲትኮምም፣ ትያትርም፣ፊልምም፣ ኑሮ፣ ህይወትም፣ ጋዜጠኝነትም(ለህዝቡ የመኖርን አቅጣጫ የሚዘግብ) ነው። (ማስታወቂያ እየሰራሁ እንዳልሆነ፣ ድንቡሎ ሰባራ ዶላር እንዳልተከፈለኝ አለማየሁ ታደሰ ምስክሬ ነው?)

ደራሲያኑ "አብረሃም ዘበነ፣ አብረሃም ገዛኸኝ እና ቢንያም ገብሩ" ሲሆኑ
አዘጋጁ አብረሃም ገዛኸኝ እንዲሁም ደግሞ
ፕሮዲዩስ በማድረግ ግሩም በላይ ናቸው።
ድርሰቱን ደግሞ ነፍስ የዘሩበት ተወዳጅና ልምድ ያላቸው ተዋናዮች እነ አለማየሁ ታደሰ፣መስከረም አበራ ፣ዮሐንስ ተፈራ፣ ስዩም ተፈራ፣ ፍቅርተ ጌታሁን ናቸው።የዚህ ሲትኮም ልዩነቱ ምንድነው? በቀልድ አድርገው መጨረሻውን በትልቅ ቁምነገር ሲያስሩትና የማህበረሰብን ንቃተህሊና ከፍ ለማድረግ ሲታገሉ ልዩነታቸው ከፍያለ ነው (ከአክቲቪስት አንቂዎቻችን ይሻለናል)።ሌላኛው ልዩነቱ ደግሞ አቀራረቡ፣ ያለተጠበቁ ክስተቶችን አዘጋገቡ፣ ጥያቄና መልሳዊ ንግግሮችን በጣልቃ ገብነት ማስገባቱ "ግሩም ነው" ያስብለዋል።
በጽናት እስከ43 ክፍል( 43ሳምንት ወይም 11ወር) መዝለቁም ከሃሳብ ውስጥ መግባት አለበት።

በጥቅሉ የዘመናችን ትልቁ ጥያቄ ላይ #ሳቃችን ላይና ደስታ መከሰትን የሚለው ድምድማት ላይ ይወስደናል። ("ሳቅዎን እንመልሳለን" ከሚል የ dental ዶክተሮች ማስታወቂያ ራስን ማዳንና ኪስንም ለመጠበቅ መፍትሔውን ማየት ጥሩ ነው?)

(ከላይ ባቀረብኩት ግላዊ ምልከታ ወለምታ ሊኖረው ይችላልና በሎሚ ይታሽልኝ ስል በትህትና እጠይቃችኋለሁ?)

✍️ዮዳA

6 months ago

ኢያሪኮ በድምፅ ማዕበል ፈረሰ
ዮርዳኖስም በክብር ደፈረሰ
ልብ በይ እዚ ጋር
ነገር አለሙ ሲቃቃር
ኢያሪኮም ፈርሶ ኢየሩሳሌም ስትገነባ
በዝግ ከተማ ተገብቶ በክፍት ከተማ ሲወጣ
እንደዛ ነበረ ልብሽ የተዘጋ
እንዲያ ነበርሽ ማንም ወዳንቺ ያልተጠጋ
ብመጣ ባንድ ቀን ድምፄን አሰምቼ
ኢያሪኮውን ልብሽ ሳላንኳኳ አስከፍቼ

4:7ጧ
4/9/2015

6 months ago

አንቺ ስትሄጂ !.!.!..
ጨረቃ ረግፋለች፥ ጸሀይ ተቆጥታለች
ከዋክብትም ረግፈው፥ አለም ተክዛለች
አለም ተከተተች፥አረጀች አፈጀች ምፅአቷ ሆነ
አራዊት ረገፉ እጽዋት ደረቁ፥ምድር ባንቺ ተኮነነ
እለቱ ሳይቀርብ፥ ወቅትና ሰአቱ ሳይደርስ
አምላክ ሊፍርድ መጣ፥ ከአንቺን ሊካሰስ

(ጠበቃሽ እኔ ነኝ
የምሟገትልሽ )
ምን አጠፋች ጌታ? ለምን እሷን ከሰስክ
እኔን ነው የተወች፥ከላይ ለምን ወረድክ?
ብዬ ብጠይቀው
አምላክ ክሱን ተወው
ግን ለኔ እንዲህ አለኝ
መስቀለኛ ጥያቄ አለኝ!
ዳኛው ፈቀዱለት ጠይቅ ያንተን መስቀለኛ
ፈራጅ በዳኛ ፊት መቆሙ በራሱ 1 መስቀለኛ።
መስቀለኛ ጥያቄ...
(መስቀለኛ መስቀል መሰቀል ማይሰለቸው አምላክ
ተቀብሮ ቢነሳም ደጋግመን ምንሰቅለው በእልክ!)
ፍቅርን ያስተማርኳት በሞቴ ልክ ነው
ያላስተማርኩትን መክዳቷ ምንድነው?

አረ ተው ኢየሱስ አረ ተው አረ ተው
መስቀለኛ ጥያቄህ በራሱ መልስ ነው
ሰነፍ ተማሪ አታውቅም?
የጎበዘ መስሎት ስህተት የሚቅም?
እንደ ይሁዳ ያለ!
ያታለለ መስሎት ራሱ የታለለ
አታውቅም?
አልደረሰብህም?

ዳኛው....
አነሱ መዶሻ
ስላላመራቸው የኛ መጨረሻ
ድው..ድም..ቷ..ቷ
ወትሮም ለአምላኳ ነው የአለም ሙቀቷ።
ስርዓት ተከሳሽ
አምላክን አታንቋሽ
በትህትና መልስ
ከቻልክም ተቅለስለስ
(እርሶን ብሎ ዳኛ
ቲሽ! ጉቦኛ )

ብለው መሃል ገቡ
ሳይከርብን ጸቡ
አምላክም ቀጠለ
በስጭቶ እንዲህ አለ
አንተን ጥላህ ስትሄድ፥ እኔ እንደደበረኝ፣ ሆድ እንደሚብሰኝ ማን አየልኝ
አንዷ እሷ ብትጠፋ 99 ትቼ 1ዷን ለመፈለግ ማሰቤን ማን አወቀልኝ
ቢለኝ ጊዜ አምላኬ
ታየኝ ጥፉ መልኬ።

11:24ቀ
4/9/15

6 months, 1 week ago

አምላክ ሆይ አመሠግንሃለሁ! ጫማ የለኝም ብዬ በተማረርኩ ሰአት አይን የሌለው ለመራመድ የሚጓጓ እንዳለ እያሳየህ እኔን በማጽናናትህ አመሠግንሃለሁ!

"የአይን አምላክ አይኑን ለጥቂት አተረፈው" ሲሉ እሰማለሁ የሃገራችን ብሂለኞች፤ ዛሬ ግን ሆኖ አየሁት። አይን የራሱ የሆነ ፈጣሪ፣ የራሱ የሆነ አምላክ አለው። እሱ እየተኛ የሚጠብቀው ግን አይተኛም፤ አይደንቅም?

ጌታዬ ሆይ አመሠግንህ ዘንድ ምክንያቴ ብዙ ነው። አማኑኤል ሆይ እኔን እንደ ጥላዬ እየተከተልክ ከገደል አፍ ነጥቀህ ስለምታወጣኝ ስምህ ለአፌ ባይመጥንም ባነጻሃት፤ ባነጽሃት ነፍስያዬ አወድስሃለሁ።

ክበርልኝ የኔ ጌታ?

6:26ሌ
4/9/2015 ዓ.ም

We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 4 weeks, 1 day ago

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 9 months, 3 weeks ago