BikuZega - ብቁ ዜጋ

Description
ልጆች በአካል፣ በአእምሮ፣ በስነ-ልቦና እንዲሁም በማህበራዊ ህይወታችው ብቁ ና ተወዳዳሪ ትውልድን ሆነው እንዲያድጉ ማስቻል።

Follow us on:
www.facebook.com/ethiobikuzega
www.twitter.com/BikuZega
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago

3 weeks, 1 day ago
3 weeks, 1 day ago

እንደምን አረፈዳቹ? በእናትነትና ህልምን መኖር በሚል ያዘጋጀነው ውይይት ተጀምሯል፡፡ ተቀላቀሉን፡፡

1 month ago

ስለፆታ ጥቃት እንዴት ልጆችን እናስተምር?

2 months, 3 weeks ago

እጅግ በጣም ገንቢ እና አስተማሪ ውይይት ነበረን ፣ ሁላችሁንም ላመሰግን እወዳለው ። መልካም አዳር

2 months, 3 weeks ago
2 months, 3 weeks ago

ሰላም በADHD ላይ የምናደርገው ውይይት ተጀምራል ።

5 months ago
**በ በድንችና በአበባ ጎመን የሚዘጋጅ በርገር …

በ በድንችና በአበባ ጎመን የሚዘጋጅ በርገር ለልጀች ምሳ

ግብዓቶች ለ2 ልጆች

▪️ግማሽ አነስ ያለ ግንድ አበባ ጎመን
▪️4 ተለቅ ያለ ድንች
▪️1 ተለቅ ያለ ካሮት
▪️1 አነስተኛ ቀይ ሽንኩርት
▪️2 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ዳቦ
▪️3 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት (እንደአስፈላጊነቱ )
▪️1 የሻይ ማንኪያ የተከተፈ ሮዘማሪ ቅጠል
▪️ቁንጥር ጨው
▪️ቁንጥር ቁንዶ በርበሬ
▪️ዘይት ለ መጥበሻ

አዘገጃጀት

▪️ድንቹን፣ አበባ ጎመኑንና ካሮቱን አጥቦና ልጦ መፈቅፈቅ
▪️ሽንኩርቱንና ነጭ ሽንኩርቱን ልጦ መክተፍ
▪️መጥበሻ ምድጃ ላይ ጥዶ ዘይቱን ማድረግና እንዲግል ማድረግ
▪️ሽንኩርቱንና ነጭ ሽንኩርቱን ጨምሮ መጥበስ በመቀጠል ፈቅፍቀን ያዘጋጀነውን
አትክልቶች ጨምሮ ለ 10 ደቂቃ እንዲበስል ማድረግና ማቀዝቀዝ
▪️የተፈጨ ዳቦውን ጨምሮ በጨው፣በቁንዶ በርበሬና በሮዘማሪ ቅጠል ማጣፈጥና ትንንሽ የበርገር ጥፍትፍ ማዘጋጀት
▪️ለበርገሩ መጥበሻ ምድጃ ላይ ጥዶ ዘይት ማድረግና እንዲግል ማድረግ
▪️በርገሩን እያገላበጡ ቡናማ ቀለም እስከሚሆን ማብሰል

በዚህ መልክ የተዘጋጀውን በርገር በዳቦ፣በበሰለ አትክልት መመገብ ወይም ምግብ ለት/ቤት መቋጠር ይቻላል

ማሳሰቢያ ፡
- ምግብ ከማዘጋጀታችን በፊት እጃችንን በደንብ መታጠብ ይኖርብናል፣
- የምንሰራበት ቦታና የምንጠቀምባቸው እቃዎች ንጹህ መሆን አለባቸው።

@BikuZega #HealthyCooking

5 months, 1 week ago
**በዝኩኒና በካካዎ የሚዘጋጅ ኬክ

በዝኩኒና በካካዎ የሚዘጋጅ ኬክ
ለልጆች መክሰስ

ግብዓቶች

▪️5 የቡና ሲኒ ዱቄት
▪️2 የቡና ሲኒ ተቆልቶ የተከካ ለውዝ
▪️1 ከፍ ያለ የተፈቀፈቀ ዝኩኒ
▪️2 የቡና ሲኒ ዘይት
▪️2 የቡና ሲኒ ማር / ስኳር
▪️3 እንቁላል
▪️1 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ/የተፈጨ ቀረፋ
▪️2 የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር

አዘገጃጀት

▪️ኦቭን ወይም የዳቦ መጋገሪያ በ 170 ዲግሪ ሴንቲ ግራድ ሙቀት ለኩሶ እንዲሞቅ ማድረግ
▪️ዝኩኒውን አጥቦና ፈቅፍቆ ማዘጋጀት
▪️ሰፋ ያለ ጎርጓዳ ሰሀን ውስጥ እንቁላሉንና ማሩን/ ስኳሩን ጨምሮ በሚክሰር በደንብ እስኪዋሀድና ክሬም እስኪመስል
መምታት በመቀጠልም ዘይቱን እና የተቀሩትን ግብአቶች በየተራ ጨምሮ ማደባለቅ
▪️የመጋገሪያ እቃውን አዘጋጅቶ የገበታ ቅቤ (ዘይት) መቀባት
▪️በመጨረሻ የተዘጋጀውን ሊጥ እቃው ላይ ገልብጦ በጋለው ኦቭን(የዳቦ መጋገሪያ)ው ለ 50-60 ደቂቃ ማብሰል
▪️በመጨረሻም ከኦቨን ማውጣትና አቀዝቅዞ ማቅረብ።

ማሳሰቢያ ፡
- ምግብ ከማዘጋጀታችን በፊት እጃችንን በደንብ መታጠብ ይኖርብናል፣
- የምንሰራበት ቦታና የምንጠቀምባቸው እቃዎች ንጹህ መሆን አለባቸው።

@BikuZega #HealthyCooking

5 months, 2 weeks ago
**ሾተላይ ምንድን ነው?**

ሾተላይ ምንድን ነው?

(በዶ/ር ቱሚም ጌታቸው)

አንዲት እናት ከገጠር አካባቢ እንደመጣችና ካገባች 8 አመት እንደሆናት ለመውለድ ሞክራ 4 ጊዜ የጽን መቋረጥ እንደገጠማት በዚህም ምክንያ ትዳሯን እንዳታጣ ፍርሀት ላይ እነደሆነችና ሾተላይ ሊሆን ይችላል ብላ መገመቷን ነገረችኝ።

ሾተላይ እንዴት ይከሰታል?

በተለምዶ ሾተላይ በመባል የሚታወቀው ክስተት ብዙ ጊዜ አንዲት እናት ከመጀመሪያ እርግዝናዋ በኃላ በተደጋጋሚ የሚከሰት የጽንሱ መቋረጥ (በማህፀን ዉስጥ መሞት) ነው።

በምን ምክንያት ይከሰታል?

የሰዋች የደም አይነት A+, A-, B+B-, O+, O-, AB+, AB- ነው።

ሾተላይ የሚከሰተው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ  ኔጋቲቭ (ለምሳሌA-, B-, AB-,  O-)ሆኖ የባሏ ፖዘቲቭ ከሆነ  ልጇ  ፖዘቲቭ የመሆን እድሉ ከፍተኛ በመሆኑ ፖዘቲቭ ከሆነ (ለምሳሌ A+, B+, AB+, O+) ከሆነ እና የ ልጁ ደም ህዋስ ወደ ሰውነቷ ሲገባ ፖዘቲቭ የሆኑ የደም ህዋሶችን በሙሉ የሚያጠፋ ተዋጊ ንጥረ-ነገር (Antibodies) በደሟ ውስጥ ይመረታል። 

ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ህይወቷ ፍጻሜ ድረስ ይኖራል።

የተመረተው ንጥረ-ነገር (Antibodies) ጽንሱን እንደ ባእድ አካል ስለሚቆጥረው ያጠቃዋል። በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ የምትይዘው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ አስፈላጊውን ህክምና ካልተደረገላት ይሞትባታል።

የደም ዓይነቱ  አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ከሆነ ግን አንድ አይነት ስለሆነ እንደ ባእድ አይቆጠርም ስለዚህ ልጁም በጤና ይወለዳል።

ህክምናው ምንድን ነው?

- የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) የሆነች እናት የ እርግዝና ክትትሏ እና ሕክምናዋ በሆስፒታል ውስጥ መሆን አለበት።

- በደሟ ውስጥ ያለውን የንጥረ-ነገር መጠን መለካትና የጽነሷን የጉዳት መጠን በማየት ብዙ ሳይጎዳ እንዲወለድ ማድረግ።

- በሀገራችን በቅርቡ  የተጀመረው ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እያለ ደም በመለገስ እንዲያድግና እንዲወለድ ማስቻል።

እንዴት እንከላከለው?

- ማንኛዋም ሴት ከማርገዟ ወይም ማንኛውንም ደም ከመውሰዷ በፊት የደም ዓይነቷን ማወቅ አለባት።

- የወንድ አጋሯን የደም ዓይነት ማወቅ አለባት።

- እርግዝና አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ አጋሯ ከተፈጠረ መጀመሪያ በሚደረግላት ምርመራ  (Indirect coomb’s test) ተዋጊ ንጥረ-ነገሩ መመረቱ እና አለመመረቱን ይረጋገጣል።

- እዳይመረት የሚከላከል የሾተላይ መከላከያ(Anti-D)መድኃኒት በእርግዝና 7ተኛ ወሯ ላይ ይሰጣታል። ከወለደች በኃላ የልጇ የደም ዓይነት አር ኤች ፖዘቲቭ (Rh +) ከሆነ በድጋሚ መድኃኒቱ ይሰጣታል።

- እርግዝናው ከማህጸን ውጭ ወይም በውርጃ ቢያበቃም የሾተላይ መከላከያውን መድኃኒት መውሰድ አለባት።

@BikuZega

5 months, 3 weeks ago
**በደበርጃንና በሽንብራ ዱቤ የሚዘጋጅ ለልጆች ምሳ …

በደበርጃንና በሽንብራ ዱቤ  የሚዘጋጅ  ለልጆች ምሳ (ለት/ቤት የሚቋጠር)

ግብዓቶች  ለ 2  ልጆች

▪️ግማሽ ደበርጃን
▪️ግማሽ ኩባያ ተዘፍዝፎ አድሮ የተቀቀቀለ የሽንብራ ዱቤ
▪️1 ተለቅ ያለ ቲማቲም(1/2  ቀይ የፈረንጅ ቃሪያ)
▪️ግማሽ አነስተኛ ዝኩኒ
▪️አነስተኛ ቀይ ሽንኩርት
▪️3 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
▪️1 የሾርባ ማንኪያ የቲማቲም ድልህ
▪️ቁንጥር ጨው
▪️ቁንጥር ቁንደ በርበሬ
▪️2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
▪️ለጣዕም የተከተፈ ፐርስሊን (ሮዘማሪ)

አዘገጃጀት

▪️ደበርጃኑን፣ ቲማቲሙን( ቃሪያውን)፣ዝኩኒውን አጥቦና ከትፎ ማዘጋጅት
▪️ሽንኩርትና ነጭ ሽንኩርቱን ልጦ መክተፍ
▪️መጥበሻ በመካከለኛ ሙቀት ለኩሶ መጥበሻው ላይ ዘይት አድርጎ እንዲግል
ማድረግና ሽንኩርቱንና ነጭ ሽንኩርቱን ጠበስ ማድረግ
▪️ደበርጃኑን  ጋል ያለው መጥበሻ ላይ ለ3 ደቂቃ መጥበስ
▪️ዝኩኒውን ጨምሮ ለ5 ደቂቃ እንዲበስል ማድረግና  ቃሪያውን (ቲማቲሙን) አከታትሎ በመጨመር ለቀጣይ ለ3 ደቂቃ ማብሰል
▪️የሽንብራ ዱቤውንና የቲማቲም ድልህውን ጨምሮ ትንሽ ውሃ በመከለስ በቁንዶ በርበሬና በጨው ቀምሞ እንዲሁም ፐርስሊን( ሮዘማሪ) ጨምሮ በተከደነ ሙቀት ለ5 ደቂቃ ማብሰልና ከምድጃው ማውረድ
▪️የተዘጋጀውን ምግብ በዳቦ፣በሩዝ ፣በመኮረኒና በፓስታ መመገብ ወይም ለት/ም ቤት መቋጠር ይቻላል

ጥቆማ፡
በዚህ መልክ የተዘጋጀውን  ሶስ በተለያዩ አትክልቶች ማዘጋጀት ይቻላል

ማሳሰቢያ ፡
- ምግብ ከማዘጋጀታችን በፊት እጃችንን በደንብ መታጠብ ይኖርብናል፣
- የምንሰራበት ቦታና የምንጠቀምባቸው እቃዎች ንጹህ መሆን አለባቸው።

@BikuZega #HealthyCooking

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago